እውነታዊ ታሪኮች ✌ (@yenebiyat_tarik) Kanalının Son Gönderileri

እውነታዊ ታሪኮች Telegram Gönderileri

እውነታዊ ታሪኮች ✌
ይህ ግሩፕ የተከፈተበት ዋነኛው አላማ
😯 አጓጊ ታሪኮችን
😯 የነቢያቶችን ታሪኮች
😯 የነቢያት አስተምህሮቶች
😯 ሀዲሶችን
የምንለቅበት የምንማማርበት channel
9,452 Abone
683 Fotoğraf
204 Video
Son Güncelleme 01.03.2025 03:05

እውነታዊ ታሪኮች tarafından Telegram'da paylaşılan en son içerikler


ያሸህረል ቁርአን  አህለን 🕋
ያ ሸህረል ወህዳ አህለን🕌
ያ ሸህረል ተውባ አህለን🌙💚

የአንድነት የህብር ቀለም፣❤️
የከፍታ የፍካት ዓለም፣😍
አዲስ ንጋት የሩህ መስከረም፣🥳
ረመዳን አገናኘን በፍቅር ዳግም፤ 🥰

#ረመዳን_12_ቀናቶች_ይቀሩታል

اللهم بلغنا رمضان

@yenebiyat_tarik
@yenebiyat_tarik

የእስራኤል ወታደሮች በናቡለስ የሚገኝ ትምህርት ቤት በ West bank  ቶክስ በፍተው ብዙ ተማሪዎቸረን ክፉኛ አቁሱለዎል
@yenebiyat_tarik

ትላንት የተለቀቀው የወራሪዋ እስረኛ አሌክሳንደር ትሮባኖቭ ለሙጃሂዶቹ የፃፈው መልዕክት

ደግነታችሁ በህሊናዬ ውስጥ ተቀርጿል። በእናንተ መካከል በኖርኩባቸው 498 ቀናት  ከደረሰባችሁ ከዚያ ሁሉ ግፍና መከራ መሐል እውነተኛ ወንድነትን፣ ንፁህ ጀግንነትንና የመከባበር ባህልን ተምሬባችኋለው።

እናንተ የተከበባችሁ ነፃ ሰዎች ናችሁ። እኔ እስረኛ እናንተም ስለ ህይወቴ ጠባቂዎች ነበራችሁ። ለልጁ እንደሚያዝን አባት ተንከባከቧችሁኛል። ጤንነቴን፣ ክብሬንና ውበቴን ጠብቃችሁልኛል። ምንም እንኳ የሀገሬ መንግስት ከባድ እልቂት በሚፈፅምባቸው፣ ለምድራቸውና በግፍ ለተነጠቀው ሐቃቸው በሚፋለሙ ወንዶች እጅ ውስጥ ብሆንም ርሃብም ሆነ ውርደት እንዲነካኝ አልፈቀዳችሁልኝም።

በዓይናችሁ መሐል እስካየሁት ድረስ የወንድነት ትርጉሙ ከቶ አልገባኝም። የመሥዋዕትን ዋጋም በመካከላችሁ ኖሬ እንጂ ፈፅሞ አልተገነዘብኩትም። ሞትን በፈገግታ ፊት ለፊት ስትጋፈጡ፣ መግደያና ማጥፊያ መሣሪያዎችን ሁሉ የታጠቀውን ወታደር በራቁት ሰውነታችሁ ስትቃወሙ ከማየቴ በፊት የመሥዋዕትነት ዋጋ አይገባኝም ነበር። የቱንም ያህል አንደበተ ርቱዕና አስተዋይ ብሆን እንኳ የእናንተን ደረጃ የሚገልፁ ቃላት አላገኘሁም። በታላቁ ሥነ ምግባራችሁ መደነቄንና መደንገጤንም መግለጽ አይችሉም።

እስረኞቻችሁን እንድትይዙ ሃይማኖታችሁ የሚያስተምራችሁ እንዲህ ነው?
ወንዶችን በዚህ ከፍታ የሰራ ምን ያማረ ታላቅ ኃይማኖት ነው። ሁሉም ሰው ሰራሽ የሰብአዊ መብት ህጎችና ከጠላት ጋር የመኗኗር ፕሮቶኮሎች ሁሉ ከፊትለፊቱ ይወድቃሉ።
ፍትህን እና ምህረትን በጣም አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ያደረጋችሁት በውሸት መፈክሮች ላይ የተገነባ ሳይሆን በኖርንበት ተጨባጭ እውነታ ላይ ያየነው ነው። በከባባድ ሁኔታዎች ውስጥም ቢሆን መሰረታዊ መርሆችዎን አክብራችኋል።

እመኑኝ አንድ ቀን ወደ ጋዛ ዳግም ብመለስ ከእናንተ ሰልፍ መሐል ተዋጊ እሆናለሁ። እውነቱን ከነዋሪዋ አውቄያለሁ። የመሬቱ ባለቤቶች ብቻ ሳትሆኑ የመርህና የፍትህ አገልጋዮች ጭምር መሆናችሁን አይቻለሁ።

ታሪክ የምትሰራ በሰጡህ ጠመንጃ የአላህን ጠላቶች የምታጠቃ ያድርግህ።
 
                 Mahi Mahisho

@yenebiyat_tarik
@yenebiyat_tarik

ሐማስና በጋዛ የሚገኙ ሌሎች የትጥቅ ቡድኖች ትጥቃቸውን ይፈታሉ እንዲሁም ጋዛን ይለቃሉ የሚል መረጃ ሰሞኑን በበርካታ የዐረብ ሚዲያዎች ሲሰራጭ ነበር።ይህን አስመልክቶ የሐማስ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ኡሳማህ ሐምዳን የሚከተለውን ብለዋል:-

"የእስራኤል ምትክ ሆኖ ለመስራት የሚመጣን ማንኛውም አካል እንደ እስራኤል ነው የምናስተናግደው።በግልፅ ለመናገር..የእስራኤል ወኪል ሆኖ መስራት የሚፈልግ ማንኛውም አካል ይህ ድርጊቱ የሚያስከትልበትን መዘዝ ለመቀበል መዘጋጀት አለበት።ስለ ትጥቅ ቡድኑ መሳሪያዎች፤አመራሮች፤የቡድኑ ደጋፊ ህዝቦች እንዲሁም ከደጋፊ አጋሮቻችን ጋር ስላለን ግንኙነት...እነዚህ ጉዳዮች በሙሉ በየትኛውም የውይይት ጠረጴዛ የምንደራደርባቸው ጉዳዮች አይደሉም። በዚህ ጉዳይ ማንም ሰው መጥቶ ጫና እንዲፈጥርብንም አንፈቅድም።"

account

የክፍያ ዘዴዎች
1) commercial bank (CBE)
1000674564078
2) zamzam Bank
0028509020101
Telebirr merchant
ID 901777

በዚህ#ረመዳንአላህ🥰 ያላሰባችሁትንሪዝቅይስጣችሁ

በቻላቹት አቅም እየሰደቃቹ ኢንሻ አላህ

#ረመዳን_13_ቀናቶች_ይቀሩታል። 9/6/2017

@yenebiyat_tarik

«ከሰደቃዎች ሁሉ #በላጩ የረመዳን ሰደቃ ነው።» (ቲርሚዚይ) ስለሆነም #በረመዳን ሰደቃ ላይ መሳተፍ #በላጭ ዒባዳ ላይ የመሳተፍን አጅር ያስገኛል!

ረመዳንን ከመሳኪኖች ጋር ስንል እኮ እንደነዚህ አይነት አባቶች ወሩን እንዳይቸገሩ በማሰብ ነው ! እነዚህ አባቶች የኛ አባት ናቸው ሁላችንም እንሳተፍ

#ረመዷንን_ከሚስኪኖች_ጋር_#ሰደቃ

ከእለታት አንድ ቀን የአላህ መላክተኛ (ሰ ዐ ወ) መንገድ ላይ ሳሉ አንዲት በእድሜ የገፉ ሴት እቃ ተሸከመው ይመልከቱና፤ወደሴትዬዋ ጠጋ በማለት እናቴ እቃውን ላግዞት በማለት ይጠይቃሉ?!

ሴትዮዋም የአላህ መላክተኛ ስለመሆናቸው የሚያቁት ነገር አልነበረም፤እቃው ከራሳቸው ላይ አውርደው ሰጧቸው፤የ አላህ መላክተኛም
(ሰ ዐ ወ) እቃውንም ተሸክመው እስከ በር ድረስም አደረሱላቸው።

ሴትዮዋ ትንሽ ጠብቀኝ ብላቸው ወደቤት ገቡ፤
የአላህ መላክተኛ (ሰ ዐ ወ) ሴትዮዋ እስኪመጡም ጠበቁ፤ ሴትዮዋም ከቤት በመውጣት እንዲህም አሉ፦
ሊጄ ምክር ብሰጥህ ትቀበለኛለህ አሉ?የአላህ መላክተኛም (ሰ ዐ ወ) እንዴት አልቀበልም ሲሉ መለሱ፤ሴትዮዋም ልጄ እኔ አደራ የምልህ
የሙሀመድን እምነት እንዳትከተል ነው አሉ፤
የአላህ መላክተኛም(ሰ ዐ ወ) እንዲህም አሉ እኔ ሙሀመድ ከሆንኩኝስ አሉ?!ሲሉ ጠየቋቸው!

ሴትዮዋም አንተ ሙሀመድ ከሆንክማ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም ሙሐመድም የአላህ መላክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለው አሉ፤

እንዲህ ነበር የአላህ መላክተኛ (ሰ ዐ ወ)አለምን በፀባያቸው የገዙት!!!

እህት ወንድሞቼ እኛስ እውን ባህሪያችን ስራችን ምን ይመስላል?!!

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ ዐ ወ) ለአለም የበሩ ብርሃን ናቸዉ!!

#ረመዳን_13_ቀናቶች_ይቀሩታል

@yenebiyat_tarik
@yenebiyat_tarik

#በጣም_ልብ_የሚነካ_ታሪክ_ነው

☞በአረብ አለም የሚኖር አንድ የአሥር አመት ታዳጊ ነው

ይህ ታዳጊ የሰራው ነገር ግን ሠውን አጃኢብ አስኝቷል።

ነገሩ እንዲህ ነው: ይህ የአስር አመት ህፃን ዘውትር በሠላት ወቅቶች ከመሥጂድ ይታደማል

ሠላቱም በጀመዓ ይሠግዳል ድምፅ ከፍ ተደርጎ በሚሰገድባቸው ሦስት ሠላቶች ላይ ታዲያ ኢማሙ ፋቲሀን ቀርቶ ሲጨርስ ማለትም ወለዷ ሊን ሲል ሠጋጁ በአንድነት አሚን ሢል ይህ ልጅ ድምፁን ከፍ አድርጎ ከጀመዓው ተነጥሎ ብቻውን አሚን ይላል....

ይህ ነገር በመደጋገሙ ኢማሙን እጅግ ያበሳጨው ነበር ቢያየው ቢያየው ልጁ ሊያቆም ስላልቻለ አንድ ቀን ከመግሪብ ሠላት በኃላ ንዴቱን መቆጣጠር ያቃተው ኢማም ይህን ልጅ እንቅ አድርጎ አንጠልጥሎ ያምባርቅበታል!

ለምንድነው ምትረብሸው ከጀመዓው ጋር አብረህ ለምን አሚን አትልም እና መሰል ነገሮችን ይህን ህፃን ልጅ ተናገረው😡😡

ይህ ታዳጊ በፍርሃት በተሸበሸቡት ልብሶቹና
ቲማቲም በሚመሥሉ ጉንጮቹ እምባ ያቀረሩ አይኖቹ ያንን ኢማም በሥሥት እየተመለከቱ...

«እኔ ምጮህው አለ......
እኔ ምጮህው እቤታችን መስጂዱ አጠገብ ነው አባቴ ደሞ ሠላት አይሰግድም ምናልባት የኔን ድምፅ ሢሠማ ደስ ብሎት አልያም ተደንቆ ከመጣና ከሠገደ ብዬ ነው ያ ኢማም» ብሎ መለሰለት🥺🥺

ይህን ጊዜ ኢማሙ ሚናገረው ጠፋው ሠውነቱ ተርገፈገፈ😔😔

የአከባቢውን ሠው አፈላልጎ ይህን ለአባቱ አደረሠው አባቱም በልጁ ተግባር እጅግ ተደንቆ ወደ ጌታው እያለቀሰ ተውበት በማድረግ ሠላቱን ጀመረ።

ሰዎችን አይተን ብቻ በችኮላ አንፍረድ። ይህን ለመስራት ያበቃቸው ምን ምክንያት ሊኖር ይችላል ብለን ኡዝር እንፈልግላቸው ምናልባት መጥፎ ሥራ የሚሰሩ መስሎን ሲፈተሽ ግን በጣም የሚደንቅ ሊሆን ይችላል!!   

ሱብሃን አላህ

Darul

#ረመዳን_14_ቀናቶች_ይቀሩታል

@yenebiyat_tarik
@yenebiyat_tarik

አልሀምዱሊላህ


አምና ስዊድን ውስጥ ቁርዓንን በማቃጠል ሲሳለቅ የነበረው ኢራቃዊው ስደተኛ ሰልዋን ሞሚካ በቅርቡ እዛው ስዊድን ውስጥ ባልታወቀ ሰው በጥይት መገደሉ ይታወሳል።

  ሬሳውን የሚቀበልና የሚወስደው በመጥፋቱም አስከሬኑ ወደ ማቃጠያ ስፍራ ተወስዶ እንዲቃጠል 🔥🔥🔥 ተደርጓል።

ሱብሀነላህ!ይህ የዱንያው ነው አላህ ለዓለም ህዝብ አሰተምህሮቱን እያሳየው ነው።ለአዕምሮ ባለቤቶች እዚህ ውስጥ ትልቅ ግሳፄ አስተምህሮ አለ።

የአዕምሮ ባለቤቶች ሆይ አስተንትኑ ተገሰሱ

    ጌታችን አላህ ከፈራጆች ሁሉ በላይ ፈራጅ አይደለምን?! እንዴታ ነው እንጂ!


"አብዛኛዎቹ ሰዎቺ አያውቁም አያስተነትኑም አይማሩም።  ተዓምራቱ ሙዕጂዛው እንደቀጠለ ነው።❗️🤲

@yenebiyat_tarik
@yenebiyat_tarik