ሁሉም ካልተፈቱ የገሀነም እሳት በጋዛ ላይ ይዘንባል የተባለለት ዛቻና መግለጫ የቀሳሞችን ውሳኔ አልቀለበሰም። ሁሉንም እስረኞች ሊፈቱ ይቅርና አሜሪካ እንዲፈቱላት የጠየቀችው ስድስት ዜጎቿም አይለቀቁም። ትራምፕም ሆነ ኔታንያሁ ከሙጃሂዶቹ ፍላጎት ውጪ መራመድ አልቻሉም።
ከመረካከቢያ መድረኩ ጀርባ የጀግንነት ጥቅሶች በደማቁ ተፅፈዋል። እንዲህ የሚሉ መፈክሮች ከባነሩ ሰፍረዋል:-
"ወደ ቁድስ እንጂ ስደት የለም"
"ኢየሩሳሌም ሆይ! ወታደሮችሽ መሆናችንን መስክሪ"
"እንደ ፀሐይ ክር ይህን ሁሉ ተሻገርን"
እነርሱ ቀሳሞች ናቸው ትራምፕን ሳይቀር ያስገረሙ
"የተለዩ ግትሮች ሲበዛ ከባድ ከሆኑ ሰዎች ጋር ነው እየተደራደርን ያለነው" ብሎ ነበር ድርድሩ ገና ከመጀመሩ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
Mahi Mahisho
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
@yenebiyat_tarik