Últimas publicaciones de ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ (@yaregalabegaz) en Telegram

Publicaciones de Telegram de ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
This channel is not operated by Deacon Yaregal Abegaz- ይህ ገጽ የሚንቀሳቀሰው በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ አይደለም

https://youtube.com/@yaregalabegaz?si=1f5NHTaQ2l2LbxWQ

“ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 11፥28
30,806 Suscriptores
426 Fotos
107 Videos
Última Actualización 01.03.2025 00:50

El contenido más reciente compartido por ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ en Telegram


ኪዳነ ምሕረት

በድንቅ ጥበቡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ያደነው እጅጉን መሐሪ ስለሆነ ነው፡፡ የቀደሙት የብሉይ ኪዳን ኪዳናት ሕዝቡን ከሲኦል መታደግ አልቻሉም ነበር፡፡ ፍጹም የሆነው ኪዳን የተደረገው በሰባተኛው ኪዳን ይህም ለሰው ዘር ምሕረትን ባስገኝች በንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡  
 
የምሕረት ቃል ኪዳን የተሰጠችውን እናታችንንም ‹‹ኪዳነ ምሕረት›› እያልን የምንማጸናት ለዚህ ነው፡፡ ለአዳም የተገባለት የምሕረት ቃል በእርሷ ተፈጽሟልና፡፡ እመቤታችን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ወልዳዋለችና፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራን ተቀብሎ እንዲሁም በመስቀል ተሰቅሎ ዓለምን ያዳነው ከእርሷ በነሣው ሥጋና ነፍስ ነውና፡፡  
 
በነገረ ማርያም ተጽፎ እንደምናገኘው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት በኋላ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ልጇ መቃብር ቦታ ጎልጎታ እየሄደች ትጸልይ ስለ ነበር  በየካቲት ፲፮ ቀን በጸለየችው ጸሎት ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ ጸሎቷም እንዲህ የሚል ነበር፤ ‹‹ልጄ ወዳጄ ሆይ፥ ከሥጋዬ ሥጋ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በቻለችህ ማኅፀኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡››
 
ጌታችንም ምን ሊያደርግላት እንደምትሻ ሲጠይቃት በስሟ ለሚማጸኑ፣ መታሰቢያዋን ለሚያደርጉ፣ ለችግረኛ ለሚራሩ፣ በስሟ ቤተ ክርስቲያን ለሚያንጹ፣ ዕጣን፣ ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን ለሚሰጡ ምሕረትን እንዲያደርግላቸው ጨምራ ጠየቀችው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በየካቲት ፲፮ ዕለት የገባላትን ቃል ኪዳን እንዲህ በማለት በመሐላ አጽንቶታል፡፡  ‹‹መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበአቡየ ወበመንፈስ ቅዱስ ሕያው፤ በራሴ፣ በአባቴ እና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ፡፡›› 
የምሕረት ቃል ኪዳን የተሰጠበት ይህ ዕለት ታላቅ ነውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቅት ታከብረዋለች፡፡ ቀድሞ ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነውና፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡
 
በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ የሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና ችግረኛ መርዳት ይገባናል፡፡  

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎት፣ አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን! 

"የመናፍቃንን ጥንካሬያቸው በራሳቸው አስተምህሮ ላይ ሳይሆን እንደ ዝንቦች የእኛን ቁስሎችና ደካማ ጎኖች በመፈለግና እነዚያ ላይ በመረባረብ ነው።... ዝንቦች 'ህር' እያሉ ከቁስል ወደ ቁስል እንደሚዘዋወሩ ሁሉ እነርሱም በእኛ ላይ ይዘምታሉ። ስለዚህ ስለራሳችን የማናውቅ፣ በእነዚህ ነገሮች ላይም ሊደረግ ስለሚገባው ነገር ጠንቅቀን የማንገነዘብና ግድ የለሾች አንሁን።"

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘእንዚናዙ
#መድሎተ_ጽድቅ ፩፣ ገጽ 16-17

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

ጸሎተ ፍትሐት የሚደረግባቸው መሠረታዊ ምክንያቶች

👉እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ስለ ሆነ

👉የቤተ ክርስቲያን ባሕርይዋና ማንነቷ የሚገለጥበት ስለሆነ

👉ከዕረፍታቸው በኋላም ሕያዋንና አዋቂዎች ስለ ሆኑ

👉አስተምህሯችን፣ እምነታችን፣ ተስፋችን፣ ... የሚገለጥበት ስለ ሆነ

በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

# ከ መምህረ ቤተክርስትያን ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ የተገኙ እንቁ መጻሕፍት
©አነዚኽን ጣፋጭ ምግቦች  ተመግበዋቸው ይኾን...?

📚
#ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
ሕይወቱ እና ትምህርቱ
እና
# ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕይወቱ እና ትምህርቱ

#ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
ሕይወቱ እና ትምህርቱ


ከሕይወቱ ቅምሻ
[....አባ እለእስክንድሮስም አትናቴዎስን በመንበረ ፓትርያርኩ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና ሥርዓት እያስተማረ አሳደገው፤ እርሱም ተወዳጅ ልጅ ሆነው፡፡ ከዚሁም ጋር ሰዋስው፣ ፍልስፍና፣ ክሂሎተ ነቢብና ሌሎች በዘመኑ የነበሩ ትምህርቶችንም በሚገባ ተማረ፡፡ ቆይቶም ለመዓርገ ምንኵስና በቃ᎓᎓ በቅድስናው፣ በሞያውና በግብረ ገብነቱ እንከን የሌለው ወጣቱ አትናቴዎስ በ23 ዓመቱ ....]

#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ሕይወቱ እና ትምህርቱ


ከሕይወቱ ቅምሻ
[....ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ራሱን ከዚህ ዓለም የበለጠ ለመሰወርና ብቻውን ዘግቶ ለመኖር በመፈለጉ ወደ ዋሻ ውስጥ ገብቶ በብሕትውናና በጽኑ ትኅርምት ለሁለት ዓመት ሲጋደል ኖረ። በዚያም በትጋሃ ሌሊት፣ ለራሱ ዕንቅልፍ በመከልከል፣ በቀዊም፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን በቃል በማጥናት፣ በጸሎትና በተዘክሮ ኖረ በመቀጠልም ....]

#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከውስጥ ገጽ የተቆረሰ
[..ሁሉም የሌሊት ቅዠቶች ኖረዋል፡፡ ሌሊቱ አልፎ ቀኑ በመምጣቱ ከጨለማው ጋር አብረው የጠፉ ህልሞች ብቻ ነበሩ፡፡ ያለ መስሎ ታይቶ እንደጠፋ ጥላ፣ ወደ አየር ተኖ እንደጠፋ ጢስ፣ ሟሙቶ እንዳለቀ አረፋ፣ እንደተበጣጠሰ የሸረሪት ድር ነበሩ፡፡ ስለዚህ ሁል ጊዜ ይህንን መንፈሳዊ መዝሙር እንዘምራለን፡- “ሁሉ ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ ነው” የሚለውን፡፡]››

👉መጻሕፍቱን በግዮን መጻሕፍት ያገኙታል !

ይደውሉልን !📞፦0913083816 https://t.me/GhionBookStore1623

በቤተክርስቲያን አስተምሮ በመዳን ዙሪያ ለመዳን እምነት እና ስራ አስተባብሮ መያዝ እንደሚገባን ያስተምረናል ነገር ግን በእምነት ብቻ የዳኑ እንዳሉ ቅዱስ መፅሀፍ ይነግረናል። ለምሳሌ ፈያታዊ ዘይማን በተመሳሳይ 12 ዐመት ደም ሲፈሳት የነበረችውንም እምነትሽ አድኖሻል ብሏታል። ይሄንን እንዴት እንመለከተዋለን?

ለጥያቄው ምላሽ በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

      📖“ቃልኪዳን በነገረ ድኅነት”

(በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ)


ቆየት ካሉ ነገር ግን እንደ መጽሐፉ ብስለት ብዙዎች እጅ ካልገቡ፣ በጥልቅ ትንታኔ ከተዘጋጁ መጻሕፍት አንዱ የዲ/ን ያረጋል አበጋዝ “ቃል ኪዳን በነገረ ድኅነት” በሚል ርእስ የተዘጋጀው መጽሐፍ ነው፡፡  መጽሐፉን አንባቢያን ትልቅ መንፈሳዊ መረዳትን ስለሚጠይቀው ስለ ቃል ኪዳንና ነገረ ድኀነት  በቂ ግንዛቤ አግኝተን እምነታችንን በማጽናት ከክርስቶስና ከቅዱሳን ጋር ተጣብቀን በምድር ሰማያውያንን መላእክትን መስለን ተዋሕዶዊ አኗኗርን ገንዘብ እንድናደርግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብንል ማጋነን አይኾንም።
❞ ይህ መጽሐፍ ቅዱሳን ከአምላካቸው ጋር ያደረጉትን ቃልኪዳንና በተሰጣቸው ቃል ኪዳን እኛ እንዴት መጠቀም እንዳለብን የሚተነትን ብቻ ሳይሆን፣ ነገረ ድኅነትን ተተርሰው ለሚነሡ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ፣ ተግባራዊ ምልልሳችን በክርስትና ሕይወታችን ውስጥ ያለውን ፋይዳ፣ ስለንስሐና ሒደቶቹም በቂ ግንዛቤ በጥልቀት ያስገነዝበናል፡፡

መጽሐፉን በግዮን መጻሕፍት ያገኙታል


📦 ለውድ   አንባብያን ደግሞ ግዮን በአዲስ መልክ የስጦታ ፓኬጅ  ይዞ እየመጣ ነው   በቅርብ ቀን ይጠብቁ!


# ግዮን መጻሕፍት ለመላው ከሀገር ውጪ እና ሀገር ውስጥ ለምትገኙ አንባብያን  በDHL እና በEMS እንዲሁም የ Delivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

ይደውሉልን !📞፦0913083816 https://t.me/GhionBookStore1623

ጾመ ነነዌ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአጽዋማት ቀኖና መሠረት ሰባት የዐዋጅ ጾም አጽዋማት አሉ። ከሰባቱ አጽዋማት አንዷ በዕለታት ተወሳክና በዓመቱ መጥቅዕ ድምር ውጤት ወይም በመባጃ ሐመር የምትውለዋ ጾመ ነነዌ ናት።

ጾመ ሰብአ ነነዌ (የነነዌ ሰዎች ጾም) የምትጾመው ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ጾሙ የሚጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሙ የሚጀመርበት ቀን ደግሞ ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፉ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ድረስ ነው፡፡ በእነዚህ ፴፭ ቀናት/ዕለታት/ ስትመላለስ ትኖራለች፡፡ ከተጠቀሱት ዕለታት አይወርድም፤ አይወጣም ማለት ነው፡፡ በዚህም ቀመር መሠረት የ፳፻፲፯ ዓ.ም ጾመ ነነዌ የካቲት ሦስት ጀምሮ በአምስት ያበቃል፡፡

ጾመ ነነዌን የጾሙት በነነዌ የሚኖሩ ሰዎች በአምላካችን እግዚአብሔር ትእዛዝ እና በነቢዩ ዮናስ ነጋሪነት ነው፡፡ የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ በኃጢአታቸው ምክንያት ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት አምላካችም ነቢዩ ዮናስ መክሮ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ወደ ነነዌ ሕዝብ እንዲሄድ አዘዘው፡፡ (ዮናስ. ፬፥፲፩)

እግዚአብሔርም “ሄደህ በነነዌ ላይ ስበክ” ባለው ጊዜ “አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ” ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔር ግን ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩት ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ “በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ” ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነርሱም “የሰው ደም በእጃችን እንይሆንብን አይሆንም” ብለው ዕጣ ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወጣ፡፡ ነጋድያኑም ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያው የእግዚአብሔርን የማዳን መልእክት ዮናስ እንዲያደርስ፣ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ነነዌ አደረሰው፡፡

ዮናስም ከእግዚአብሔር መኮብለል አለመቻሉን ሲረዳና ነነዌ መሬት ላይ መድረሱ ሲነገረው ለነነዌ ሰዎች “ንስሐ ግቡ” ብሎ መስበክ ጀመረ፤ (ዮናስ ፩ እና ፪)፡፡ መጀመሪያ ከተልእኮው ቢያፈገፍግም “ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፦ በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ” እንደተባለው ነቢዩ ዮናስ የኋላ ኋላ ወደ ነነዌ ሄዶ የእግዚአብሔርን መልእክት ዐውጇል። (ዮናስ ፴፫፥፬) በዚያን ጊዜ የነበሩት ሰዎችም እንዲህ አደረጉ፤ “የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም ዐዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ” (ቁጥ.፭) እንዲል፡፡

መጽሐፉ የነነዌ ሰዎች ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር እንደማራቸው ይገልጻል፡፡ (ዮናስ ፫) ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መሆኑን አምላካችን ቅልን ምሳሌ በማድረግ አስረዳው፡፡ (ዮናስ ፬) ነቢየ ሐሰት እንዳይባልም ለቅጣት የመጣው እሳት እንደ ደመና ሆኖ ታይቶአል፡፡ የታላላቅ ዛፎች ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ የእሳቱ ወላፈን ነክቷቸው ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ በንስሐ በጾምና ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀው ከጥፋትና መዓት ድነዋል።

እኛንም ካለንበት መከራ፣ ችግርና ሥቃይ እንዲያወጣን፣ በሰላም፣ በፍቅርና በአንድነት እንዲያኖረን እንደ ነነዌ ሰዎች ንስሐ እንግባ፤ በጸሎት፣ በጾምና በበጎ ምግባር ተወስነን በሃይማኖት እንጽና! 

አምላካችን እግዚአብሔር ቸርነቱን ያብዛልን፤ አሜን!

👉 ©የነነዌን ጾም ማሳለጫችን ይኹን!!

#የምህረት በር
  በ ቃኘው ወልዴ


ንስሐን [በአንጻረ-ሕዝበ-ነነዌ] አጥብቆ ሰባኪ ፣ መንፈሳዊነት ለሚጎረብጠው መንቻካ ልብ አለዛቢ ዘይት ፣ መንፈሳዊ ቁመናን ከራስ ጠጉር እስከ እግር ጥፍር በዓይነ ሕሊና የሚከስት መስታወት ፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እና የእኛን ምንነት መሳ ለመሳ እያሳየ ነፍስን ኧረ ንቂ እያለ ወትዋች......
መጽሐፍ #የምሕረት_በር!
የነነዌን ጾም ማሳለጫችን ይኹን!!

ከተጣልኹበት ሰማኝ!!
‹‹... ተጣልኹ ፣ እርሱም ከተጣልኹበት ከጥልቁ ሰማኝ ፣ ሞት በሲኦል መካከል አሳለፈኝ ፣ አንተ ግን ጠበቅኸኝ፡፡ ባሕር ከበበኝ አንተም ያለ መቅዘፊያ ጠበቅኸኝ፡፡ አንተ በጥልቁ ቆለፍኽብኝ ፣ ወደ ባሕሩም ጣልኸኝ፡፡ ወደ ባሕሩ ጥልቅ ወረድኹ ፤ እሞት ዘንድ ግን አልተውኸኝም፡፡ ሞት ሰለቀጠኝ ፣ አንተ ግን በአፉ ውስጥ ሕያው አድርገኽ አኖርኸኝ፡፡ ምንም እንኳን ውኃው ቢሸፍነኝም ፥ እታፈን ዘንድ ግን አልተውኸኝም፡፡ ዳሩ ግን መደነቅ ያዘኝ! ህየንተ ሞት ሕይወት ከፍ ከፍ አደረገኝ! ተስፋዬ ሙሉ ለሙሉ ሲሟጠጥ አንተ መለስኸኝ፡፡ ስለዚኽ ከጥልቁ ባሕር አንደበቴ በብዙ አመሰገነኽ ፤ ከባሕሩ ጠለልም በደስታ ለገናናው ስምኽ ዘመርኩልኽ!🙏 ጌታ ኾይ፥ በኢየሩሳሌም ባለው ታላቅ ቤተ መቅደስ በታቦቱ ተውኩኽ [ከአንተ ተለይቼ <ወደ ፍቃዴ> ወጣኹ] ፣ ነገር ግን በመሬት ሥር በጥልቁ ለእኔ መንገድን ስታዘጋጅልኝ አገኘኹኽ! አንተ ከውኆች በላይና በታች ፣ በእርሱ ውስጥና ከርሱ ወዲያም በምልዓት አለኽ፡፡ አድባራት ፣ ቀላያት ፣ አቅጣጫዎች ኹሉም ያለማቋረጥ ያለመታከት ያመሰግኑኻል!! ...»
[የምሕረት በር፣ ገጽ 261]
መጽሐፉን በ፦ግዮን መጻሕፍት ያገኙታልhttps://t.me/GhionBookStore1623

https://youtu.be/3M3vl-7fH_M?si=jaeCFRsoQwTYW5BL

https://youtu.be/-U0mcE6zEa8?si=ATO5gOSpTSoFzApf