በአላህ ፍቅር ጥላ ስር..... @waseta1 Channel on Telegram

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

@waseta1


«ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት ከዚያም ወደርሱ ተመለሱ ጌታዬ አዛኝ ወዳድ ነውና ፡፡(ሁድ:90)



« إنما غايتنا أن نَدُل الناس علىٰ اللّٰه وليس علينا »

ተጓዥ ብእረኛ (Amharic)

እያንዳንዱ ሰው እንደተወሰዱ መጠን እስር ቤት አሁኑን እየታከለ የሚመለሱ ሰዎች ስልካቸን ከሆነ ስክራይን ቤት ተጓዥ ብእረኛ ድምፅ እንዲያግዝ እንዲሞላ ስክራይንና የተማ ቤት ገንዘብ ስለሚባል አሁን አይረሳም ። በአሁኑ ቤት በማንኛውም አንድ ተጓዥ ብእረኛ ውስጥ የሚገነኙ የለውጥ ብምኖች ስራ አንዱ ሲሆን ነው ። መናገር በማግኘት በእነዚህ ቤቶች የሚተላለፍ ችግሮችም እንደ እውነቱ ይታየጋል ። የተጓዥ ብእረኛ ውስጥ የሚገነኙ ሌላ ተጓዥ ህጻን ውስጥ ሁለት አፓላር ከሚበላ ጃንኒካ፣ ቄሮውተይንድ ተሲፋኪካ ማርቲኒካና የሚዲበሪ ኮርፖሬሽን ከመዋቅር የሚገነኑ እና የሚጎዱ ሌላ ጃንኒ ውስጥ ።

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

08 Jan, 03:58


ለጌታው ልክ እንደሚያየው ሆኖ በልቡ ያለውን ሁሉ ስሞታ ያቀርባል ይህች ነፍስ ከአላህ ሌላ መጠጊያ አለመኖሩን ጠንቅቃ ሳትረዳ አትቀርም

ይሄ ሰውዬ ምናልባት ተበድሎ ከሆነ ግን በዳዩ ጉዱ ፈላ

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

07 Jan, 14:23


رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَاعْبُدْهُ وَاصْطَبِرْ لِعِبَادَتِهِ ۚ هَلْ تَعْلَمُ لَهُ سَمِيًّا

(እርሱ) የሰማያትና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው፡፡ እርሱን በመገዛትም ላይ ታገስ፡፡ ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን

وَيَقُولُ الْإِنسَانُ أَإِذَا مَا مِتُّ لَسَوْفَ أُخْرَجُ حَيًّا

ሰውም «በሞትኩ ጊዜ ወደፊት ሕያው ኾኜ (ከመቃብር) እወጣለሁን» ይላል፡፡

أَوَلَا يَذْكُرُ الْإِنسَانُ أَنَّا خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ وَلَمْ يَكُ شَيْئًا

ሰው ከአሁን በፊት ምንም ነገር ያልነበረ ሲኾን እኛ የፈጠርነው መኾኑን አያስታውስምን
(መርየም 65-67)

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

07 Jan, 11:49


ከበኒ ኢስራኢሎች አንድ ሰው አላህን ጠየቀ “ጌታዬ ስንቴ አመፅኩህ ግን አልቀጣኸኝም ስንቴ ነው ማምፅህ አንተ ግን አትቀጣኝም አለ”

አላህም ወደ ሙሳ ወህይ አወረደ ለባሪያዬ ለእከሌ እንዴ በለው “ባሪያዬ ስንቴ ቀጣሁክ አንተ ግን አታስተውልም ከኔ ጋር የማውራትን ጥፍጥና አልከለከልኩህምን የኢባዳን ጣእም አላሳጣሁክምን” አለው

መንገዳችንን እንድንስትና እንድንጠፋ መደረግ እጅግ ትልቅ ቅጣት ነው ዱንያ አልተነካችብንም ማለት አልተቀጣንም ማለት አይደለም ዋናውን ነገር አኼራን የአላህን ፍቅር ተቅዋን ተነጥቀን ሊሆን ይችላልና እናስተውል
ያለንበትን ሁኔታ መርምረን አላህን ይቅርታውን እንጠይቅ
ወላሂ ከአላህ ጋር ብንታረቅ ይሻለናል

#አስተግፊሩላህ_ወአቱቡ_ኢለይህ

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

06 Jan, 16:47


«እፅፋለው ፅፈት እስታለሁ ስተት
ቢሞላልኝ ከጌታዬ ባጎድል ከኔ ድክመት»

ለሚያውቀኝ ሁሉ የምለው ዑመር ኢብኑ ዐብዲልዓዚዝ ለጓደኛው እንዳለው ነው።👇

"መንገድ ስቼ ካገኘኸኝ። ልብሴን ሰብስበህ አንገቴ ስር ቀፍድደህ ያዘኝና በደንብ አድርገህ አንቀህ ነቅንቀኝ። ከዛም ዑመር ሆይ! አላህን ፍራ! ነገ ሟች ነህ! በለኝ።"

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

06 Jan, 16:39


25 (ሙሳም አለ) ጌታዬ ሆይ ልቤን አስፋልኝ

26 ነገሬንም ለኔ አግራልኝ

27ከምላሴም መኮላተፍን ፍታልኝ

28 ንግግሬን ያውቃሉና

29 ከቤተሰቦቼም ለኔ ረዳትን አድርግልኝ

30 ሀሩንን ወንድሜን

31 ሀይሌን በእርሱ አበርታልኝ

32 በነገሬም አጋራው

33 በብዙ እናጠራህ ዘንድ

34 በብዙም እናወድስህ

35 አንተ በእኛ ነገር አዋቂ ነህና (ጧሀ 25–35)

#ልብህን_በጌታህ_ቃል_ህያው_አድርጋት

ልብህን ከቁርአን አርቀሀት በጭራሽ ህይወት አይኖራትም

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

06 Jan, 04:50


ብዙዎቻችን የማናውቀው የዱንያ መልክ አለ

አንዳንዴ ከአላህ እጅግ የራቀ ሰው ታገኛለህ እና በቃ ዱኒያ እንዲህ ብቻ ትመስለዋለች ዱንያ ማለት ጭንቀት ድብርት ሰቀቀን ትመስለዋለች

ይህ ሰው ለአላሁ ሱብሀነሁ ወተአላ እጅግ የገዘፈ ጨለማውን ሚገፍለት ብርሀን እንዳለው አይገምትም ወደርሱ ቢዞር ኖሮ ወንጀልን ቢተውና በትእዛዙ ላይ ቢፀና አላህ ይህን ግዙፍና ፍፁም ብርሀን ልቡ ውስጥ ባስቀመጠለት ነበር ይህ ብርሀንም ዱንያ ላይ እያለ ጀነትን ያኖረው ነበር

የአላህ ቅርብ ሰዎች የሚኖሩበት ሰኪናና ሰላም ዱንያ ላይ መኖሩን የማያውቅ ብዙ ሰው አለ እንዲያ አይደለም ወላሂ ወደ አላህ ብትቀርብ የከለከለህን ብትተውና ያዘዘህ ላይ ብትፀና እስከዛሬ የኖርክባት ዱንያ ላይ ይህን የመሰለ ስሜት አለ ብለህ ያልገመትከውን ህይወት ያሳይሀል

በአንዴ እስከ ጥግ ሷሊህ ሁን አልልህም ነገር ግን አትሰግድ ከነበር ዛሬ ሰላት ጀምር ትሰግድም ከሆንክ አሳምረህ ልትፈፅማት ጣር አንዲት ሱናን ጨምር ቁርአን አትቀራ ከነበር አንዲትን ገፅ በራስህ ላይ ግዴታ አድርገህ ያዝ አላህ አንድ እርምጃ ሲጠጉት አንድ ክንድ ሚቀርብ ነውና በክንድ ሲቀርቡት በእርምጃ ሚጠጋ ነውና ወደሱ በእርምጃ ሚጠጉን እርሱ በእሩጫ ይመጣ ጌታ ነውና ከፀናህ ብዙ ሳትቆይ ጌታህን ብርሀኑንም ታገኛለህ ግን ፅና ወደሱ ያለህን ጉዞ አታቁም ወደ ኋላም አትመለስ አለሁ ብሏልና አለ  ታገኘዋለህ

#በመንገዱ_ላይ_ፅና

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

04 Jan, 16:31


قل رسول الله - إنَّ للَّهِ أَهْلينَ منَ النَّاسِ قالوا: يا رسولَ اللَّهِ ، من هُم ؟ قالَ: هم أَهْلُ القرآنِ ، أَهْلُ اللَّهِ وخاصَّتُهُ ; الراوي : أنس بن مالك

የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል
ለአላህ ከሰዎች ውስጥ ቤተሰብ አለው፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ እነማን ናቸው? ተባሉ እርሳቸውም፡- የቁርኣን ሰዎች፣ የአላህ ቤተሰቦችና ከህዝቦች መሀል የመረጣቸው ሰዎች ናቸው። አሉ አነስ ቢን ማሊክ
ዘግበውታል

የቁርአን ሰው መሆን መመረጥ ነው ወላህ
አላህ ሁላችንንም ይወፍቀን

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

03 Jan, 17:37


አንተ ፍፁም ጥበበኛና ጥልቅ አዋቂ ነህ አምላኬ 🍃
ለኔ የተሻለው ወደ ሆነው እየመራኸኝ በመሆኑ ላይ ጥርጥር የለኝም

ጥራት ይገባው የሰጠ ,ጥራት ይገባው የከለከለ
እሱ አዋቂ ነው ባስከፋኝ ነገር ውስጥ ምን ኸይር እንዳከለ

አልሀምዱሊላህ ስለሰጠኸኝ አልሀምዱሊላህ ስላልሰጠኸኝም 🍃

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

03 Jan, 14:07


ዱአቹን አትርሱ ይህ ሰአት እጅግ ዱአ ሚከጀልበት ነው አደራቹን ተጠቀሙት እኛንም በመልካም ዱአቹ አስታውሱን

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

03 Jan, 08:44


አብሽር የምትለዋ ቃል ምንኛ ያማረች ናት!  ደግሞ ከአላህ ዘንድ ስትሆንስ:-

إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَبْشِرُوا بِالْجَنَّةِ الَّتِي كُنتُمْ تُوعَدُونَ

እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት (አብሽሩ)ተበሰሩ» በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡
አልፉሰሊት 40


اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين
በእዝነቱ ከእርሱ ዘንድ በጀነት አብሽሩ(ተበሰሩ)  የምንባልበት ፣ በሩቋ ሀገር ያሉትም በድል እና በጀነት የሚበሸሩበት፣ ከሀዘን የምንላቀቅበት በሰለዋት የደመቀ በካህፍ የተዋበና በዱዓ የታጀበ ጁምዓ ይሁንልን!!!

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

02 Jan, 17:41


አያመሰግኑህም

ቁርአን ላይ በተደጋጋሚ የሰፈረ አንድ በጣም ልቤን የሚነካኝ ጉዳይ አለ
አላህ ሸይጣንን ከጀነት ሲያባረው ሸይጣን እስከመቀስቀሻው እለት አቆየኝ በማለት ተማፀነ አላህም ያንን ፈቀደለት አንተ ከሚቆዩት ነህ አለው

ይሄኔ ሸይጣን ዛቻዎቹን ይደረድር ጀመር አጠማቸዋለሁ በቀጥተኛው መንገድ ላይ እቆምባቸዋለሁ ከፊትም ከኋላም ከቀኝም ከግራም እመጣባቸዋለሁ በጣም ብዙ ዛተ ከሁሉም በላይ ግን ልቤን የሚነካኝ አያመሰግኑህም ብሎ መዛቱ ነው

ثُمَّ لَآتِيَنَّهُم مِّن بَيْنِ أَيْدِيهِمْ وَمِنْ خَلْفِهِمْ وَعَنْ أَيْمَانِهِمْ وَعَن شَمَائِلِهِمْ ۖ وَلَا تَجِدُ أَكْثَرَهُمْ شَاكِرِينَ
«ከዚያም ከስተፊቶቻቸው ከኋላቸውም ከቀኞቻቸውም ከግራዎቻቸውም በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ፡፡ አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ኾነው አታገኛቸውም» (አለ)፡፡ (አእራፍ 17)

እኛ አላህን ከማመስገን በተሳነፍን እና በተዳከምን ጊዜ የሸይጣን መሳለቂያ ነው ምንሆነው
ብዬ ነበር አይነት ፌዝ ነው የሚያፌዝብን

አስባቹታል እኛ አላህን ባመሰገንን ቁጥር ሸይጣን በንዴት ይከስማል ይሸማቀቃልም ምክኒያቱም አያመሰግኑህም ብሎ በድፍረት የዛተው ዛቻ ተራ ወሬ ብቻ ይሆንበታል

ሲጀምር ለምን አናመሰግንም አላህ በፀጋዎቹ አላካበበንምን? ከትቢያ አንስቶ አላላቀንምን? መመልከቻ መስሚያ መንቀሳቀሻ አካላትን አሟልቶ አልሰጠንምን? ከሁሉም በላይ እስልምናን ሰቶ ከፍ አላደረገንምን?

እልፎች ሚመኙትን ህይወት እየኖርን ነው

ወላሂ ላለማመስገን ኡዝር የለንም ሸይጣንን ለማስደሰት ካልሆነ

እየከፋህ ሊሆን ይችላል ውስጥህ ተሰብሮ ሊሆን ይችላል አንዳንድ ምቶዳቸውን ነገሮች አተህ ሊሆን ይችላል ቢሆንም ግን አመስግን

የሰጠህ ከወሰደብህ በጣም ይበልጣልና አመስግን

ባለህበት ጉዳት ውስጥም የተደበቀ መልካም ነገር አለና አመስግን

ግዴታህ ነው ማመስገን አመስግን

አላህዬ ከዘልአለም ሚበልጥ ተመስገን አልሀምዱሊላህ

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

02 Jan, 15:17


ልቤ እዚ ማማ ጫፉ ላይ ተቀምጧል አምላኬ እባክህ ፍቃድህ ይሁንና ሄጄ ላምጣው እዚ ቤት ውሰደኝ ያ አላህ

ቁርአንን የወረደበት ቦታ ላይ ሄጄ ሳላነበው ቀልቤ አልረጋም የኔ ጌታ በቂብላዬና በኔ መሀል ያለው ርቀት ትንሽዬ ብቻ ሆኖ መስገድን ናፈቅኩ ያ ረብ የውዴን የረሱሌን ሰለላሁ አይሂ ወሰለም ቤት በአይኖቼ መመልከትን ሲበዛ ከጀልኩ ያ አላህዬ

ይህን የከበደኝን ጉዳይ “ሁን” በለው ያ ጀባር

አህ ያ መካ አህ ያ ጦይባ ልቤማ እዚህ የለም ዱአ አድርጉልኝ ውዶቼ 🍃

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

02 Jan, 10:21


የመዝሪያ ወቅት

ይኸው ገርሞ ገርሞ እንዲገርመን የረጀብ ወር ገባ  ከአምናው ረጀብ አመት ማለፉ አጂብ ነው የሆነብኝ

አምና አስታውሳለሁ በረጀብ ያልዘራ በሻእባን ኮትኩቶ ያላጠጣ ረመዳን ላይ ምርት ለመሰብሰብ አይታደልም ሚለው አባባል ተደጋግሞ ሲነገር ነበር የተወሰነ ብንሞካክርም ግን ችላ አልነው በዛ ሁኔታችንም እንዳለን ረመዳን ገባ ከዚያም ያልተዘራ ለመሰብሰብ ብዙ ለፋን እንዳዲስ ለመዝራትም ብዙ ባከን ወቅቱ ግን ውጤት መሰብሰቢያ እንጂ አዲስ መዝሪያ አልነበረም

ይኸው እጅግ ቸር የሆነው ጌታችን ሌላ እድል ሰጠን ዛሬም በድጋሚ ረጀብ ላይ ነን

አንደበታችንን ዛሬ ከሀሜትና ከውሸት ካላፀዳነው ነገ እንዴት መጥራት ይችላል ቁርአንን ዛሬ ካልተዋወቅን ነገ እንዴት ነው ምንወዳጀው ዛሬ ዚክርን ካላስለመድን ነገ እንዴት ነው ከባድ ማይሆንብን

ሁለት ወር ረጀብና ሻእባን ከአላህ ጋር መጥፎ ልማዶችን ለመላቀቅ በቂ ጊዜያት ናቸው ረመዳን መልካም የሆነውን ሁሉ ለመሰብሰብ እንጠቀምበት አላህ ይርዳን

#ረጀብ_2

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

31 Dec, 18:10


🍃

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

31 Dec, 04:32


وَتَظُنُّ أنَّكَ هَالِكٌ ثُمَّ يَأتِي لُطْفُ الله .!

ልትጠፋ የደረስክ ይመስልሀል ከዚያ ግን የአላህ ቸርነት ይመጣል🍃

በአላህ ፍቅር ጥላ ስር.....

31 Dec, 04:20


ከለታት በአንዱ ቀን አዛኙ ጌታህን አንድን ነገር
ጠይቀኸው ነበር፤ነገር ግን ያንን ነገር አሁን
አግኝተሀዋል...ጠየከው ሰጠህ
#እንዳትረሳው_አደራህን_እንዳትረሳው
                               "Dr ሙሀመድ ራቲብ "

ስንትና ስንት ኒእማ ነው የሆነ ጊዜ አላህን ስንለምነው የነበረና አሁን እጃችን ላይ የሚገኝ

ስንቱን ዘነጋን አዳዲሶቹ ምኞቶቻችን የቀደሙትን ፍላጎቶቻችንን ማግኘታችንን አላስረሱንም አላሁል ሙስተአን

አምላኬ ሆይ ለፊትህ ልቅና ለስልጣንህ ግዝፈት የሚመጥን ምስጋና በለይሉም በቀኑም ይድረስህ

አንተ እንደ ሰው አይደለህም #እወድሀለሁ ጌታዬ

ተጓዥ ብእረኛ

30 Dec, 04:32


“ዛሬ እጥበቱ ካለፈኝ እሞታለሁ"

ጠና ያሉ ሰውዬ ናቸው - በግምት 54 አመት ገደማ

"ልጄ እባክህን እርዳኝ: የኩላሊት እጥበት አለብኝ" አሉኝ

ስልክ ላይ ነበርኩኝ: አንገቴን ጎንበስ አድርጌ "ፈጣሪ ይርዳዎች" ብዬ ወደ ስልኬ ተመለስኩኝ

"እባክህን ልጄ ዛሬ እጥበቱ ካለፈኝ እሞታለሁ" ሲሉኝ የማወራው ስልኬን ዘጋሁኝ

👇🏾

ሰውዬው በተለያዩ የውጭ ድርጅቶች ውስጥ ለ17 አመታቶች በተለያዩ ሀላፊነቶች ሰርተዋል - ከ7 አመት በፊት ግን የስኳር ህመም ተጠቂ ሆኑ: ኩላሊቶቻቸው ስራ መስራት አቆሙ: የመተንፈሻ ችግር ገጠማቸው

ቤታቸውን እስከ መሸጥ ድረስ ገንዘባቸውን አንጠፍጥፈው ተጠቀሙት

ኩላሊቶቻቸው በየሳምንቱ ይታጠባሉ

በስኳር ህመም የተነሳ የሚበሉት ውስን ምግቦችን ነው

የመተንፈሻ መሳርያ ይጠቀማሉ

👇🏾

ኩላሊቶቼ በየሳምንቱ የማይታጠብ: ያገኘሁትን ምግብ ሳላማርጥ የምበላ: አየሩን እንደፈለግኩኝ የምምግ እኔም አማርራሉሁኝ

ኩላሊትህ በየሳምንቱ የማይታጠብ: እንደፈለግክ እየበላህ: አየር ያለምንም ከልካይ እየሳብክ ታማርራለህ
👇🏾
ወላሂ የተሰጠን ይበልጣል !!
ሁሌምና ለዘልአለም ምስጋናዎች ሁሉ ለአላህ የተገቡ ናቸው አልሀምዱሊላህ

ተጓዥ ብእረኛ

29 Dec, 04:46


ወንጀልን መተው ቢያቅትህ እስቲግፋርን አትተው ይላሉ ሷሊሆች
አስተግፊሩላህ ወአቱቡ ኢለይህ

ሰባኸል ኸይር

ተጓዥ ብእረኛ

28 Dec, 17:01


አውቃሁ ላትሰጠኝ አላስከጀልከኝም አላህዬ አንተ እጅግ ቸርና አዛኝ ጌታ ነህ አምነዋለሁ ቃልህን

ሱረቱ ዱሀ አምስተኛውን አንቀፅ ስሰማ ውስጤ ሚሆነውን መሆን ታውቅ የለ የኔ ጥልቅ አዋቂ ጌታ

ሱረቱል ዩኑስን እየቀራሁ አያ 89 ላይ በደረስኩ ቁጥር በልቤ አደራ ምልህን ትሰማ የለ የኔ ሚስጥረኛ አምላክ

ካንተ ውጪ ለማንም ያልነገርኩትን ጉዳይ አደራህን ወዱዴ 🍃

ተጓዥ ብእረኛ

28 Dec, 05:34


ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«ያልተጨነቀ አይደሰትም፣ ያልታገሰ አይጣፍጠውም፣ ያልተቸገረ አይደላውም፣ ያልለፋ አያርፍም። ይልቁንስ ባሪያ ትንሽ ከለፋ ረጂም ጊዜ ያርፋል፣ የሰአታት ትዕግስት ለዘላለማዊ ህይወት ትመራዋለች። የዘውታሪ ፀጋ ባለቤቶች ያሉበት ሁሉ የጥቂት ሰአት ትዕግስት ውጤት እንጅ ሌላ አይደለም።»

ጌታችን ሆይ በመንገድህ ላይ እንድንፀና ሰብር ስጠን

ተጓዥ ብእረኛ

27 Dec, 15:13


ጌታችሁ መለመን ይወዳል ሲለመን መስጠት ደግሞ ባህሪው ነው ባሪያው እጁን አንስቶ ለምኖት በባዶ ከመመለስ ሀያእ የሚያደርግ ነው ጌታችን

አትለምኑትም ወይ ሀጃ የለባችሁም ወይ

ተጓዥ ብእረኛ

27 Dec, 08:13


በቃሪእ ኑረይን መሀመድ ሲዲቅ ( ረሂመሁላህ)🌹🍃

🎙 ሱረቱ አል ካህፍ

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
 
ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
↩️‏ سنن_يوم_الجمعة
➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት

اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد
      
الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ 
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ

ተጓዥ ብእረኛ

27 Dec, 03:39


ቸጓዥ ብእረኛ የዛሬ የቁርአን ዊርድ

ጁምአ ጁማደል ኡኽራ/26/1446

አስራ ስድስተኛ ቀን ዊርዳችን

              👉 ደረጃ 1 ገፅ 31 እና 32

👉 ደረጃ 2 ከገፅ 75-80

             👉 ደረጃ 3 ከገፅ 150-160

👉 ደረጃ 4 አስራ ስድስተኛ ጁዝ

በዚህ ሁሉ ነገር በፍጥነት በሚለዋወጥበት ዘመን ትልቁ ፅናት በዲን ላይ መጽናት ነው።
አላህ ጽናቱን ይስጠን።

ዊርዳቹን አጥብቃቹ ያዙ አህባቢ

ተጓዥ ብእረኛ

25 Dec, 08:35


የቢቢሲው ጋዜጠኛ አስገራሚ ጥያቄ


የሶሪያ ሙጃሂዶች ደማስቆን ከተቆጣጠሩ ቡሀላ ቢቢሲ ከአህመድ አሽ-ሸርዕ ጋር ቃለ ምልልስ አደረገ። አስገራሚ ጥያቄዎችን ይዞ ብቅ አለ። አህመድ በሚሰጠው መልሶቹ ይህ አለም ምን መስማት እንደሚፈልግ ያወቀ ይመስላል። ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ መልስ ለመስጠት እንዳሰበ ያሳብቃል። ሁለት ጥያቄዎች ግን አስገረሙኝ፡-
"ሴቶች እንዲማሩ፣ ሰዎች አልኮል እንዲጠጡ ትፈቅዳላችሁ?" ሲል የቢቢሲው ጋዜጠኛ ጠየቀ።

ስለሶሪያ ሴቶች በህይወት የመኖር መብት ደንታም የሌለው የምዕራቡ ዓለም ስለሶሪያ ሴቶች የመማር መብት ተጨነቀ። አስራ ሶስት አመታት በፈንጂ በርሜል በኬሚካልና በድሮን ሲጨፈጨፉ ድምፁ ያልተሰማው፣ አሥራ ሦስት ዓመታት ልጆቻቸው ታስረው ሲደፈሩ ዝም ጭጭ ያለው፣ አንድም ጉባኤ ያላደረጉት ፌሚኒስቶች ዛሬ ከየተደበቁበት ወጡ። አሳቢ መስለው ብቅ አሉ። የሶሪያ ሴቶች የመማር መብት ይኖራቸው ይሆን?! ሲሉ ጠየቁ።
ውሸታም! ቀጣፊ!

የአፍጋኒስታን ሴቶችን ገድለው ደፍረው ጨፍጭፈው ሲያበቁ ሀገሩን ለቀው ሲወጡ ሴቶች እዚያ ምድር ይበደላሉ የመማር መብታቸው ይከበር ሲሉ በሚዲያቸው የጮኹት ማን ሆኑና?!

440 ቀናት የጋዛ ሴቶች ሲያለቅሱ የተደበቁ፣ እንደ ሰወኛ አዝነው ዱቄት እንኳ ያልላኩ፣ ጦርነቱ ሲያበቃ የጋዛ ሴቶች ሊጠየቅላቸው የሚገቡ መብቶች አሏቸው ሊሉን ይመጣሉ።

"ሰዎች አልኮል እንዲጠጡ ትፈቅዳላችሁ?!"
ገዳያቸው አይኖቻችሁ እያየ ደማቸውን ሲጠጡ የት ነበራችሁ?! ወንዶቻቸው እስር ቤት ውስጥ ሲዋረዱ፣ ሴቶቻቸው ግፍን ከመራራው ሲጎነጩ፣ ልጆች በእንባቸው ሲታነቁ፣ ልጃገረዶች ሲደፈሩ ሰቆቃቸው እንዲሰማ በመስጂድ ድምፅ ማጉያ እያስተጋቡ በስቃያቸው ሲረኩ ከቶ የት ነበራችሁ?!

ለሃምሳ አመታት የፈለጉትን ያደርጓቸው ዘንድ ለገዳዮቻቸው አልተዋችኋቸውምን?! ህዝቡ ባመፀ ጊዜ ወታደሮቻችሁን ልካችሁ የነዳጅ ትቦውን እንዲጠብቁ ሰራዊታችሁን አላሰማራችሁምን?! አሁን ስለሴቶች የመማር መብት ልትጠይቁ እንዴት ብቅ አላችሁ?! ማፈርያ!

Mahi Mahisho

ተጓዥ ብእረኛ

24 Dec, 16:05


#ወንዶች እያስቸገሩኝ ነው ብላ ለወንድሟ ትነግራለች።.. ሸሪዐዊ ልብስ ወደ ሚሸጥበት ወስዷት ያለብሳታል።

..ከተወሰነ ጊዜ ቡኃላ "አሁንም እያስቸገሩሽ ነው ወይ?" ብሎ ይጠይቃታል።
#አረ በፍፁም! ይህን ልብስ ከለበስኩ በኋላ ሁላቸውም ያከብሩኛል አለች።.. ቀለል ባለ ንግግር #በአለባበስሽ_እያስቸገርሽ_የነበርሸው_አንቺ_እንጂ እነሱ_አይደሉም! ..እነሱ ቢሆኑ እንዲህ ተስተካክለሽም ማስቸገራቸውን በቀጠሉ ነበር አላት ይባላል።..

#እህቶቼ እናንተስ...በአለባበሳችሁ እያስቸገራቿቸው ነው ወይስ እያስቸገሯቹ?

ተጓዥ ብእረኛ

24 Dec, 16:01


👆👆👆👆👆👆 ለቻናሉ አዲስ ነኝ ስለ ቁርአን ዊርዱ አላውቅም ያላቹ ልጆች ይሄን ፁፍ አንቡብት👆👆👆 በደንብ ያብራራላቿል ከዛ ተቀላቀሉን ለአኼራችሁ

ተጓዥ ብእረኛ

24 Dec, 09:55


عن الفُضيل بن عِياض:
    "اتَّبِع طُرق الهُدىٰ، و لا يضرك قِلَّة السَّالكين
و إيَّاك و طريق الضَّلالة، و لا تغترَّ بكثرةِ الهالكين !


ፉደይል ኢብኑ ኢያድ እንዲህ ይላሉ:

የቅናቻን መንገድ ተከተል የተጓዦቹ ትንሽነት አያዘናጋህ
አደራህን ደግሞ ከጥመት መንገድ ራቅ በጠፊዎች ብዛት አትታል🍃

የቁርአን ዊርዱን ስንጀምር 37 ሰው ነበር አብሮ የጀመረው እስከዛሬ መፅናት የቻለው ሰው ቁጥር ግን---

ብቻ የቀጠላቹ አላህ ፅናትን ይጨምርላችሁ
ይህ ቀናት እጥፍ ድርብ እያደረገ የሚያነባብረው ተግባር ነውና ወደ ኋላ አትበሉ የቂያም ቀን ሚዛናችሁ ላይ ትልቅ ክምር ሀሰና ታገኙ ዘንድ አላህ ይወፍቃችሁ

ቢከብድ ቢከብድ እንኳን በሁለት ገፅም ቢሆን ፅኑ ግን አትተዉት

ተጓዥ ብእረኛ

23 Dec, 04:17


°•°•°• የማስተዋል ግብዣ •°•°•°
~~~~
ዶክተር ገርቢያ አልገርቢ ትባላለች። በሙያዋ ዶክተር ናት። እንዲህ ስትል አስተዋዮችን ታናግራለች:–

"እጅግ አደገኛና ውስብስብ የሆኑ ቀዶ ጥገናዎች በሰው ልጅ ወሳኝ ክፍሎች ላይ ይካሄዳሉ። በአእምሮውና በልቡ ላይ። ህይወቱ ባጠቃላይ በነዚህ ክፍሎቹ ላይ የተንጠለጠለ ነው።
°
ይህን ቀዶ ጥገና የሚያካሂደው ሰፋፊ አልባሳት የለበሱ፣ እራሳቸውን የሸፈኑ፣ የፊት መሸፈኛ የለበሱ፣ የእጅ ጓንቶችን ያጠለቁ ሰዎች ያሉበት የህክምና ቡድን ነው።
ይህ አለባበሳቸው ግን ለዚህ ውስብስብና አደገኛ ስራ እንቅፋት አልሆናቸውም።

ከዚያ ግን ‘ሒጃብና ኒቃብ ስራን፣ እድገትንና ስልጣኔን ከሚያደናቅፉ እንቅፋቶች ውስጥ ናቸው’ የሚል ሰው ታያለህ!!"

✍️IbnuMunewor

ተጓዥ ብእረኛ

23 Dec, 03:48


ቸጓዥ ብእረኛ የዛሬ የቁርአን ዊርድ

ሰኞ ጁማደል ኡኽራ/22/1446

አስራ ሁለተኛ ቀን ዊርዳችን

              👉 ደረጃ 1 ገፅ 23 እና 24

👉 ደረጃ 2 ከገፅ 55-60

             👉 ደረጃ 3 ከገፅ 110-120

👉 ደረጃ 4 አስራ ሁለተኛ ጁዝ

በዚህ ሁሉ ነገር በፍጥነት በሚለዋወጥበት ዘመን ትልቁ ፅናት በዲን ላይ መጽናት ነው።
አላህ ጽናቱን ይስጠን።

ዊርዳቹን አጥብቃቹ ያዙ አህባቢ

ተጓዥ ብእረኛ

22 Dec, 07:47


እንደ መድከም..
.........እንደ መዛል..
..................እንደ መከፋት..

አላህዬ ይጠቅሙኛል ያበረቱኛል እነሱ እያሉ አልወድቅም ይደግፉኛል ብዬ አስባቸው የነበሩ ነገሮች ሁሉ ምንም መሆናቸው ተመለከትኩ አንተና መፅሀፍህ ብቻ ስትቀሩ

አሁን ካንቸ ውጭ ባሉ ላይ ሁሉ የቀረኝ እንጥፍጣፊ ተስፋ እንኳ የለም

ቀድሞውንም በእነዛ ነገራቶች መተመተማመኔ ከባድ ስህተት ነበር ይቅር በለኝ ያ አላህ
ይህ መሰበርም ካንተ ውጭ ባለ ነገር ላይ ለተማመኑ ሁሉ ተገቢ ቅጣት ነው

አላህዬ አሁን እጅግ በተዋረደና በተናነሰ ስሜት ውስጥ ሆኜ ነብይህ ኑህ አለይሂ ሰላም ያለህን ብቻ ነው ምለው

فَدَعَا رَبَّهُ أَنِّي مَغْلُوبٌ فَانتَصِرْ
ጌታውንም «እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ» ሲል ጠራ፡፡ (ቀመር 10)

ተጓዥ ብእረኛ

20 Dec, 14:48


በአላህ ካዝና ውስጥ ብዙ ኸይሮች፣ ብዙ በረከቶች ፣ ብዙ ሰርፕራይዞች አሉ።
ቀጣዩ ሰርፕራይዝህ/ሽ

ዑምራ ሊሆን ይችላል፣
ኒካሕ ሊሆን ይችላል፣
እርግዝና ሊሆን ይችላል ፣
ልጅ ሊሆን ይችላል ፣
ሀብት ሊሆን ይችላል ፣
ሐጅ ሊሆን ይችላል ፣
መኪና/ ቤት ሊሆን ይችላል ፣
ዓፊያ ሊሆን ይችላል ፣
ምርቃት ሊሆን ይችላል ፣
ተውባ ሊሆን ይችላል ...

ማን ያውቃል ። እስቲ ተመኙ። በአላህ ላይ መልካም አስቡ። ዱዓ አድርጉ፣ ኢስቲግፋር አብዙ። ተማምናችሁ ጠብቁ።
አላህ ብዙ አለው።


Abx

، استغفروا 🌼..

ተጓዥ ብእረኛ

20 Dec, 09:39


ይህ የጌታዬ መፅሀፍማ ባልኖረ ኖሮ ነፍሶቻችን በጭንቀት በሞተች ነበር 🍃🍃🍃

አልሀምዱሊላህ አለ

ተጓዥ ብእረኛ

20 Dec, 03:33


ተጓዥ ብእረኛ የዛሬ የቁርአን ዊርድ

ጁምአ ጁማደል ኡኽራ/19/1446

የዘጠነኛ ቀን ዊርዳችን

              👉 ደረጃ 1 ገፅ 17 እና 18

👉 ደረጃ 2 ከገፅ 40-45

             👉 ደረጃ 3 ከገፅ 80-90

👉 ደረጃ 4 ዘጠነኛ ጁዝ

በዚህ ሁሉ ነገር በፍጥነት በሚለዋወጥበት ዘመን ትልቁ ፅናት በዲን ላይ መጽናት ነው።
አላህ ጽናቱን ይስጠን።

ዊርዳቹን አጥብቃቹ ያዙ አህባቢ

ተጓዥ ብእረኛ

03 Dec, 16:28


ℹ️ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄℹ️

💎በእስልምና 『በሂጅራ』 አቆጣጠር 9️⃣ኛው ወር ምን ይባላል⁉️

⚡️ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና⚡️

🔥Add🎁የሱና ቻናሎች📥 የሚለውን በመንካት ውሰዱ🌹

ሀ}  ረጀብ 『 رجب 』

ለ}  ረመዷን 『رمضان 』

ሐ}  ሸዕባን  『 شعبان 』

መ}   ሸዋል   『شوال 』

መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ ትክክል አይደላችሁም ማለት ነው

🔘መልካም እድል🔘

ተጓዥ ብእረኛ

02 Dec, 16:18


ነቢዮ ዮሱፍ ከሁለት ወጣቶች ጋር እስር ቤት ገቡ።
ግና ሁለቱም ቀድመዋቸው ወጡ።
ሲወጡ የሱን ነገር ለአለቃቸው እንዲነግሩለት አደራ አላቸው።
እነርሱ ግን አደራዉንም እሱንም ረሱ።

ሓጃቸዉን ከነርሱ ይልቅ ለአምላካቸው መናገር የነበረባቸው ዩሱፍም ለዓመታት በእስር ቤት ቆዩ።
ቀድመዋቸው ከወጡት መካከል አንደኛው አገልጋይ ሆነ።
ሁለተኛው በስቅላት ተገደለ።

ዘግይተው የወጡት ዩሱፍ ግን ከግብጽ ሚኒስቴሮች አንዱ ሆኑ።

እናሳ
እናማ ያንተ/ያንች ፋይል አልተረሳም።
ጌታህም ረሺ አይደለም።
ጉዳይህ የዘገየው ለምክንያት ሊሆን ይችላል።
በደንብ አብስሎ ሊሰጥህ ይሆናል።
እስቲ አትቸኩል ንጉሥ ትሆን ይሆናል።
ሚኒስቴር ትሆን ይሆናል።
ይቅናህ አቦ ..
ዘግይተህ መድረስህን አትጥላ ወዳጄ።


وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمْرِ رَبِّكَ ۖ لَهُ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَٰلِكَ ۚ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّا

(መለአኩም አለ) «በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም፡፡ (መርየም 64)

መሳኧል ኸይር !

ተጓዥ ብእረኛ

30 Nov, 18:38


አንድ ሰው አንድ ወዳጁ ለርሱ ካለው ፍቅር የተነሳ እጅግ ውድ ስጦታ ገዝቶ ቢሰጠውና የተሰጠው ሰው ግን ከሰጪው በላይ ስጦታው ላይ ቢመሰጥ

ውዱን ስጦታ ያመጣለትን ሰው ችላ ብሎ ሰጪውን ማመስገን ቢዘነጋ

ከሰጪው በላይ ስጦታውን ቢያከብር ነውር አይደለምን?

ነው አላቹ አይደል እሺ አንዴ ወደኛ ህይወት እንምጣ

ምትሳሳልን እናታችን መከታው አባታችን እውቀታችን ውበታችን ሀብታችን ክብራች ምኖዳቸውና ሚወዱን ሰዎች ያለን ነገር ሁሉ የማን ስጦታ ነው?

የአላህ አይደለምን? ነው እንጂ ወላህ

ይህ ከመሆኑ ጋር ታድያ ለነሱ የሰጠውን ክብር ከሱ አልነፈግንም?

ለነሱ የሰጠነውን ፍቅር የእሩብ እሩብ አልነሳነውምን?

ይባስ ብለን ራሱ በሰጠን ፀጋ እሱ ላይ አልተመፃደቅንም?

አልካድንም የሬሴ ነው በልፋቴ ያመጣሁት ነው አላልንም ?

ከማመስገን አልታጣንም ወይ?

ወላሂ አላህ ከኛ የተብቃቃ ነው እኛ ግን ነፍሳችንን እጅግ ሲበዛ በድልን

قَالَا رَبَّنَا ظَلَمْنَا أَنفُسَنَا وَإِن لَّمْ تَغْفِرْ لَنَا وَتَرْحَمْنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ

«ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን፡፡ ለእኛ ባትምር ባታዝንልንም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ፡፡(አእራፍ 23)

ተጓዥ ብእረኛ

29 Nov, 13:54


ጁምአ ከአስር ቡሀላ ዱአ ተቀባይ መሆኑ የተረጋገጠባት ጥቂት ያህል የምትቆይ ሰአት እንዳለች ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ነግረውናል ኡለማኦች ደግሞ ከአስር በኋላ እንደምትገኝ ጠቁመዋል ምናልባትም አሁን ማለት ሊሆን ይችላል በዱአ ተበራቱ ያ ጀመአ

ይህ ከላይ ያያያዝኩላቹ ኦዲዮ እንዴት ሚገርም ዱአ መሰላችሁ

ዱአ ማድረግ ሚከብዳቹ ካላቹ ቢያንስ እሱን ከፍታቹ አሚን በሉ

ዱአ ላይ መካከለኛ ከሆናችሁ ከፍታቹ እያዳመጣቹ አላህን እያወደሱ እያመሰገኑ እያላቁ ዱአ ማድረግ እንዴት እንደሆነ እዩበት

ዱአ ላይ አሪፍ ከሆናችሁ እንግዲ ክፈቱትና ከሸይኽ ተውፊቅ ጋር አብራቹ ፍሰሱ ልባቹን ያሰክንላቿል ኢንሻአላህ

ብቻ ሁሉም ከፍቶ ቢያዳምጥና አሚን ቢል ይጠቀምበታል በአላህ ፍቃድ

ረመዳን 20ኛው ለሊት ላይ የተቀዳ ነው

አሚን አሚን አሚን ያ ረብ 🍃

ተጓዥ ብእረኛ

29 Nov, 13:34


#ውረድ!

የተሳሳተ አውቶብስ ውስጥ እንደተሳፈርክ ብታውቅ ምን ታደርጋለህ?

በቀጣዩ ፌርማታ ላይ ትወርዳለህ አይደል?

በሕይወትህም ላይ በተሳሳተ አቅጣጫ ውስጥ በቆየህ መጠን ከመዳረሻህ በጣም እየራቅክ ትመጣለህ፣ _ በቶሎ ውረድ (:  

አላህ ያግዝህ ዱአ አደርግልሀለሁ አንተም ዱአ አድርግ አንቺንም እህቴ አላህ ብርታትን እንዲሰጥሽ እለምንልሻለሁ አንቺም በርቺልኝ እናቴ

ለማላውቃችሁ ካላቹበት መጥፎ ሀል ወታቹ ወደ ጌታችሁ ለመጓዝ ለምትውተረተሩ የዲን ቤተሰቦቼ ሁሉ አብሽሩ ይህ ያላችሁበት ትግል አይነቱና መጠኑ ቢለያይም ሁላችንም ያለንበት መንገድ ነውና በዱአ እየተጋገዝን እንበርታ ለኔም ዱአ አድርጉልኝ ያ አህባብ
🍃

ተጓዥ ብእረኛ

28 Nov, 19:11


ጁምአ ለሊት

እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ በውዱ ነብይ በታላቁ መልክተኝ በደጉ ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ ሰለዋት አውርዱ

አላሁመ ሰሊ ወሰሊም ወባሪክ አላ ነብይና ሙሀመድ

ተጓዥ ብእረኛ

28 Nov, 15:47


ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ

የጀነት ገበያ የምትቆመው በየትኛው ቀን ነው

🌱ትክክል መሆናቹን የምታቁት ከመልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌱

add በማለት ውሰዱ

🔘መልካም እድል🔘

ተጓዥ ብእረኛ

28 Nov, 04:03


ንግስናም ምስጋናም ለአላህ ሆኖ በሰላም አነጋን አልሀምዱሊላህ

ከአላህ በቀር በሀቅ የሚመለክ የሚመለክ አምላክ የለም ብቸኛ ነው አጋር የለውም ንግስናም ምስጋናም ለርሱ ነው እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው

ጌታዬ በዚ ቀን ውስጥ ያለውን መልካም ነገር ሁሉ ጠይቅሀለው በለሊቱም ውስጥ ያለውንም መልካም

በዚህ ቀን ውስጥ ካለው መጥፎ ነገር ሁሉ በአንተ እጠበቃለው በለሊቱም ውስጥ ካለው

ጌታዬ ከስንፍናና ከመጃጀት ባንተ እጠበቃለው

ጌታዬ ከእሳትና ከቀብር ቅጣትም ባንተ እጠበቃለው

አልሀምዱሊላህ ጌታዬ አንተ አለኸኝ ዛሬ ቀኑ ደስስ ይላል 🍃

ተጓዥ ብእረኛ

27 Nov, 03:37


ልብ ብለሃል!
➩አዛን በወጣ ቁጥር እድሜህ ጨምሯል፡፡
➩ ቀን በተለወጠ ቁጥር ቆይታህ ቀንሷል፡፡
➩ ጀንበር በጠለቀች ልክ ትንፋሽህ ተመናምኗል፡፡
➩ ፀሃይ በወጣች ቁጥር ሞትህ ታቃርቧል፡፡

🔻እናም ወዳጄ! ‹ ምድር ላይ አመታት እና ወራት ይቀሩኛል፡፡› ማለቱን ተውና ህይወትህን በሰዓታትና በደቂቃዎች እድሜ ቁጠር፡፡፡ አደራህን ማስላቱ ላይ አትሣሳት፡፡ ቀን በቀን ተተካ ማለት የእድሜህን መጨመር ሣይሆን መቀነሱን ነው የሚያመለክተው፡፡

ያ አላህ መልካም የሆነችን መመለስ ወዳንተ መልሰን

ተጓዥ ብእረኛ

26 Nov, 12:55


.......................................
The house of wisdome
🏆 ዘመኑ የቴክኖሎጂ
  የመማር ነው::
♤ ታዲያ በሰለጠነው ዘመን ምን አዲስ ነገር ቀስመዋል::
🔸️በአለም ላይ በስፋት የሚነገረውን የኢንግሊዘኛ 
ቋንቋ እና
🔸️በሀገራችን በስፋት የሚነገረውን  የኦሮምኛ  ቋንቋ በአጭር ግዜ መልመድ ይፈልጋሉ
👉እንግዲያውስ ይምጡ ይመዝገቡ
👉ትምህርቱን በየትም ቦታ ሆነው በኦንላይን መከታተል መቻሎ ለየት ያደርገዋል::

ለመመዝገብ በዚህ
👇👇👇👇👇👇
@WisdomeAcadamy
የቴሌግራም አካውንት ይመዝገቡ
'The house of wisdome'
..................................


https://t.me/wisdomehouse

ተጓዥ ብእረኛ

26 Nov, 10:13


እኔ ወንጀለኛ ነኝ እኔ ጥፋተኛ ነኝ እኔ አመፀኛ ነኝ

እሱ መሀሪ ነው እሱ አዛኝ ነው እሱ ታጋሽ ነው

ሶስቱንም ባህሪዎቹን በሶስቱ ባህሪዎቼ ተቃርኜዋለሁ ነገር ግን ወላሂ ታሸንፋለች

ታሸንፋለች የእርሱ ባህሪ የእኔን ባህሪ


وَإِنِّي لَغَفَّارٌ لِّمَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ صَالِحًا ثُمَّ اهْتَدَىٰ

እኔም ለተጸጸተ፣ ላመነም፣ መልካምንም ለሠራ፣ ከዚያም ለተመራ ሰው በእርግጥ መሓሪ ነኝ፡፡ (ጧሀ 82)

ተጓዥ ብእረኛ

24 Nov, 18:50


ልትኖረው የምትችለው እጅግ ውብ የፍቅር ህይወት የቱ እንደሆነ ታውቃለህ?

🍃 እርሱ የአላህ ፍቅር ነው ወላሂ 🥀🥀

ኢብራሂም አለይሂ ሰላም አላህን ከማመኑና ከማፍቀሩ የተነሳ ሙሉ ህዝቡን ለብቻው ተጋፈጠ እንዲህም አለ

وَقَالَ إِنِّي ذَاهِبٌ إِلَىٰ رَبِّي سَيَهْدِينِ
አለም «እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡» (ሷፋት 99)

ከዚያም ተጣርቶ ተጣርቶ በፍፁም አላህን አናመልክም ያሉትን ህዝቦቹን አባቱን ጭምር ጥሎ ወደ ሩቅ ተሰደደ በልቡ የአምላኩን ፍቅር እንደያዘ -------

ተጓዥ ብእረኛ

24 Nov, 18:29


ካላየኃቸው እና ከማላቃቸው አደጋዎች ስላዳንከኝ ፣ ያላስተዋልኳቸውን እልፍ ፀጋዎች ስሰጠኸኝ

#ተመስገን_ያ_ጀባር

ስታበይ እንደመታበዬ ፣ስበድል እንደ በደሌ ፣ ስወድቅ እንዳወዳደቄ፣ ሰጠግብ እንዳጠጋገቤ በሆንኩት ልክ ሳይሆን እንደ ቸርነትህ ስለምታኖረኝ

#ተመስገን_ያ_ከሪም

የሚያስፈልገኝን ሁሉ ስለምትሰጠኝ ፣ በመንገዴ ሞገስ ስለሆንከኝ ፣ ዙሪያዬ በመልካም ሰዎች ስላስከበብከኝ ።

#ተመስገን_ያ_ወዱድ

ፀጋህ ስለሚታየኝ ፣ጤናዬ ስለሚታወቀኝ፣
መኖርህን ተጠራጥሬ ስለማላውቅ

#ተመስገን_ያ_አላህ

الحمد لله

ተጓዥ ብእረኛ

24 Nov, 15:33


ℹ️ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄℹ️

💎በእስልምና 『በሂጅራ』 አቆጣጠር 9️⃣ኛው ወር ምን ይባላል⁉️

⚡️ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና⚡️

🔥Add🎁የሱና ቻናሎች📥 የሚለውን በመንካት ውሰዱ🌹

ሀ}  ረጀብ 『 رجب 』

ለ}  ረመዷን 『رمضان 』

ሐ}  ሸዕባን  『 شعبان 』

መ}   ሸዋል   『شوال 』

መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ ትክክል አይደላችሁም ማለት ነው

🔘መልካም እድል🔘

ተጓዥ ብእረኛ

22 Nov, 18:42


አላህን ራህማንም ረሂምም(አዛኝም ሩህሩህም) አይደለህም ያለው ሰው ታሪክ

ታሪኩን ያወራው ሸይኽ እንዲህ ይላል መስጂድ ውስጥ አንድ ሽማግሌ ሰው ነበር ሰዎች ሲውጡም አይወጣም በከባዱ ያለቅስ ነበር እኔም አጠገቡ ሄጄ አንተ ሰው ሆይ ለምንድን  እንዲ ምታለቅሰው ባንተ ላይ ምን ተፈጠረ አልኩት እሱም ተወኝ አላህ ጋር ላልቅስበት አለኝ እኔም ተውኩት

በቀጠዩም ቀን ወደ መስጂድ ገባ ሰዎች ሲወጡም አልወጣም እጅግ አምርሮ የበረታ ለቅሶንም ያለቅስ ጀመር እኔም ሄጄ ካጠገቡ ተቀመጥኩ እና ወላሂ ለምን እንደምታለቅስ ካልነገርከኝ አልነሳም አልኩት እሱም ታሪኩን እንዲህ ሲል ነገረኝ

"እኔ ለቤተሰቦቼ የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ነኝ ሚስትም አገባው ነገር ግን ልጅ መውለድ አልቻልንም ከረጅም ጊዜ ቡሀላ አላህ እጅግ ቆንጆ የሆነችን ሴት ልጅ ሰጠኝ እሷም የአይኔ ማረፊያ ነበረች ነገር ግን ልጄ አንዴ በጣም ታመመች ወደ ሆስፒታል ወሰድናት እኔም አላህን አምርሬ እለምነው ጀመር አላህ ሆይ ያ ራህማን ያረሂም(አዛኙ ሩህሩሁ ጌታ ሆይ) እያልኩ ደጋግሜ ለመንኩት ነገር ግን ዶክተሩ መቶ እኛም የአላህ ነን ወደሱም ተመላሾች ነን ካለ ቡሀላ ልጄ ሂወቷ እንዳለፈ ነገረኝ በጣም በብስጭት አላህን ራህማንም ረሂምም(አዛኝም ሩህሩህም) አይደለህም አልኩት አላህም ተአምሩን አሳየ ልጄ ከሞት ተነሳች ዶክተሩ መቶ ልጄ መንቃቷን ነገረኝ አላህን የተናገርኩትን ቃል ረስቼ ወደ ልጄ በፍጥነት ሄድኩ ሂወት ቀጠለ

እና ልጄ ዩኒቨርሲቲ ገባች እንድ ቀን ግን እንደወጣች አልተመለሰችም ጓደኛዋን ሄጄ ስጠይቃት እንዲህ አለችኝ ልጅህ አንድ ወንድ ወደደች አካሏንም ነብሷን አሳልፋ ሰጠች ከሱ ጋርም የተጠላውን ዚና ፈፀመች እናም አሁን ማርገዟን ስታውቅ ፈርታህ ኮበለለች
እናቷ ይህንን ስትሰማ በድንጋጤ የተነሳ ወድያው ሞተች እኔም እድሜዬ ገፋ የሆነ ጌዜ አንድ ሰው ወደኔ መቶ ልጅህ የት እንዳለች አውቃለው አለኝ እኔም ወደሷ ውሰደኝ ብዬ በፍጥነት ወደዛ አመራው ነገር ግን ልጄ ራቁት ሆና ስትዝናና አገኘዋት ያንን መቋቋም አልቻልኩም ነበር ያኔ አስታወስኩ አላህ ራህማንም ረሂምም(ኣዛኝም ሩህሩህም) መሆኑን ልጄ ያኔ የሞተችው አላህ ለኔ ስላዘነ ለኔ ስለራራ ነበር ይሄ ሁሉ መከራ እንዳይደርስብኝ ነበር ያኔ የተናገርኩት ሁሉ ስህተት ነበር አላህ ራህማንም ረሂምም ነው"

አላህ ሱብሀነሁ ወተአላ በቅዱስ ቃሉ እንዲህ አለ "ምናልባት አንድን ነገር ልትወዱ ትችላላቹ እሱ ለናንተ መጥፎ ሆኖ ምናልባት አንድን ነገር ልትጠሉ ትችላላቹ እሱ ለናንተ መልካም ሆኖ አላህ ያውቃል እናንተ አታውቁም (ሱረቱል በቀራ 216)

እኔም እላለው ወላሂ አላህ #ራህማንም_ረሂምም ነው
አላህ ሆይ ለኛ የወሰንከውን ነገር አስወድደን አንተ ለኛ የተሻለውን እንጂ አታደርግም እና

እስቲ አንዴ አልሀምዱሊላህ በሉ

ተጓዥ ብእረኛ

21 Nov, 15:33


ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ

አባታችን አደም 『عليه السلام』 የተፈጠሩት በየትኛው ቀን ነው

🌱ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌱

Add🎁የሱና ቻናሎች📥 የሚለውን በመንካት ውሰዱ🌹

ሀ}  እሁድ 『الأحد 』

ለ}  ሐሙስ 『الخميس 』

ሐ}  ጁሙዓህ 『 الجمعة 』

መ}   ሰኞ  『الاثنين 』

⚠️መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ ትክክል አይደላቹም ማለት ነው⚠️

🔘🩵መልካም እድል🩵🔘

ተጓዥ ብእረኛ

21 Nov, 14:40


" ለነፍሴ ፈራሁና ወደ ኸዲጃ ሮጥኩኝ።" አሉ ረሱላችን ሶልለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በሒራ ዋሻ ባጋጠማቸው እንግዳ ክስተት ተደናግጠው ሲወጡ የነበረውን ክስተት ሲተርኩ።
ወደየትኛውም ጓደኛና ወዳጅ መሄድን ትተው እሷን አሰቡ።
ባልና ሚስትነት ቀላል ጉዳይ አይደለም ።
በበኩሌ ከኢማንና ከጤና ቀጥሎ የምለምንላችሁ ነገር መልካም የትዳር አጋር ነው።
አላህ ይወፍቃችሁ።

Abx

ተጓዥ ብእረኛ

21 Nov, 14:36


عن أبي هريرة، رضي الله عنه، أن رسول الله، صلى الله عليه وسلم، قال: «من صام رمضان إيمانًا واحتسابًا غفر له ما تقدم من ذنبه، ومن قام ليلة القدر إيمانًا واحتسابًا غفر له ما تقدم من ذنبه» (رواه البخاري ومسلم)

በአቡ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ረመዳንን በእምነትና ከአላህ ዘንድ ምንዳ በመጠየቅ የጾመ ሰው የቀደመ ኃጢአቱ ይማርለታል። ለይለተል ቀድርን በእምነትና አጅርን በመሻት የሰገደ ሰው የቀደመ ኃጢአቱ ይማርለታል።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።

አዎ በትክክል ይህ የተባረከ ወር ነው ለመድረስ 100 ቀናት ብቻ የቀሩት አላህ በሰላም በኢማን በአፊያ በፍቅር ያድርሰን

🍃መታደስ ናፍቀናል ያ ረመዷን🍃🍃

ተጓዥ ብእረኛ

21 Nov, 04:53


🥀“100 ቀናት ብቻ ቀርተውታል ” 🥀🥀

          እሱ ማነው?👇 ኮመንት ላይ ገምቱ

ተጓዥ ብእረኛ

20 Nov, 14:20


እያመፅኩት ደጋግሜ እያጠፋሁ ያዘዘኝን ከመፈፀም እየተዘናጋሁም ነገር ግን አሁንም እንደሚወደኝ የምከጅለው አላህን ብቻ ነው

መቶ ጊዜ አስቆጥቼው መቶ ጊዜ ይቅር ብሎኝ በድጋሚ ለመቶ አንደኛ ጊዜ ባጠፋ አሁንም ይቅር እንደሚለኝ ተስፍ ማረገው ከሱ ሌላ ማንም የለም

ባሪያዬ ብሎ ሲጠራኝ ነፍሴ በፍቅር የምትፍነከነከውን ያህል ማንም አቆላምጦ አሰማምሮ ቢጠራኝ አልደሰትም

#እርሱ_አላህ_ነው

አላህዬ አሳምረህ ፈጠርከኝ ተንከባክበህ አሳደከኝ ያማረውን ሁሉ በገፍ ትረዝቀኛለህ ይህን ሁሉ ኸይር ወደኔ ታወርድበት እዝነትህ ይደንቀኛል

ባምፅህ ይቅር በለኝ ብዬ ከመምጣቴ ቀድመህ ነይ ይቅር ልበልሽ ትለኝ ቃልህ ይገርመኛል

እንደኔ ላለ በዳይ ያንተ ፍቅር ተአምሩ ነው አምላኬ 🥀

አሁን አንድ ነገር ብቻ ጠይቅሀለው ያ አላህ የኔንም ምስኪን ነፍስ ከሁሉ አስበልጣ ትወድህ ዘንድ አስችላት 🍃

ተጓዥ ብእረኛ

19 Nov, 09:33


🔴”አንድ ትልቅ ኮረብታ ከወጣ በኋላ አንድ ስዉ ሊያውቅ የሚችለው ብዙ ተጨማሪ ኮረብታዎች መኖራቸውን ብቻ ነው።"
ይህ የዱኒያ ተጨባጭ ነው አብሽሩ
          
وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ
በመታገስና በሶላትም ታገዙ (በቀራ 45)

ተጓዥ ብእረኛ

17 Nov, 05:03


ታጋሾች የታላችሁ ሚዛን የለ ሂሳብ

የፈተና ወቅታቸው ላይ ላሉ ወዳጆቻችሁ ላኩላቸው

@traverse1

ተጓዥ ብእረኛ

16 Nov, 04:07


🍃ወላሂ ነው ምላቹ ናፍቆኛል ንፍቅ ነው ያለኝ
አልሀምዱሊላህ ግን እሱም እየመጣ ነው
ናፍቆቴ ባይወጣልኝም ጥቂት ግን ማስታግስበት እፊያ አገኛለሁ ሲመጣ🍃🍃
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
የማወራችሁ ስለ ተከበረው ቅዱስ ወር ረመዷን ነው እድፍ ነፍሴን ላጠራበት ብኩን እኔን ሊሰበስብ ሀሰናዬን ሊያበዛ ለወንጀሌ ምህረትን ታቅፎ እየፈጠነ እየመጣ ነው አልሀምዱሊላህ ናፍቆኝ ነበር በጣም

3 ወር ከ 16 ቀን ብቻ ቀርቶታል ሊደርስ

አልሀምዱሊላህ እየመጣ ነው አላህ ሁላችንንም በኢማን በአፊያ በፍቅር ያድርሰን
ወደ አላህ እጅግ ምንቀርብበት ረመዷን ይሁን
አሚን

ተጓዥ ብእረኛ

15 Nov, 03:40


🍃የኡርወት ኢብኑ ዙበይር ሰላት አጂብ አጂብ”🍃

አረብኛ ምትችሉ ሰዎች ከፍታቹ አዳምጡት በአላህ የተወሰነም ቢሆን ቀልባቹን ያረጥብላችኋል ሀቅ

አረብኛ ለማትችሉ ሰዎች ተርጉሜ ፅፍላቿለው ኢንሻ አላህ

ተጓዥ ብእረኛ

14 Nov, 17:25


አያመል ቢድ

አቡ ዘር ረዲየላሁ አንሁ እንዲህ ሲል አስተላልፉአል "የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ  ወሰለም እንዲህ አሉኝ:– ከወሩ ውስጥ የተወሰኑ ቀናት ከፆምክ 13ኛ፣ 14ኛ አና 15ኛውን ቀን ፁም
(ቲርሚዚ 761,ነሳኢ 2424)

በሌላ ዘገባም እነዚህን የአያመል ቢድ ቀናት የፆመ ሰው ወሩን ሙሉ እንደ ፆመ ይቆጠርለታል ተብሏል

እናም አህባቢ ዛሬ በሂጅራ አቆጣጠር #ጁማደል_አወል_12 ነው ያ ማለት የዚህ ወር የአያመል ቢድ ቀናት ነገ ይገባሉ ማለት ነው የቻለ ይፁም ያልቻለም ለሌላው ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁን

#አስታውሱ ረያን የተባለችው የጀነት በር ለፆመኞች ተዘጋጅታለች!!!!!

ፆሙ የሚሆነው ነገ #ጁምአ _ቅዳሜ_እሁድ ነው 

ይያዙ ለአኼራዎት ስንቅ

#ሼር

ተጓዥ ብእረኛ

13 Nov, 17:42


እርሱ ነው ጠባቂዬ

እርሱ ነው የሪዝቄ ምንጭ🍃

እርሱ ነው ያለኝን ሁሉ የሰጠኝ 🥀

እርሱ ነው ሚኖረኝን ሁሉ ሚሰጠኝ እርሱ ነው ተስፋዬ 🤍

እርሱ ነው ስታመም ሚያድነኝ😇

እርሱ ነው ሲከብደኝ ሚያግዘኝ እርሱ ነው ረዳቴ 🌷

እርሱ ነው የፈጠረኝ

እርሱ ነው ቅኑን መንገድ የመራኝ 🕋

በእርሱ ነው ልቤ ፍቅርን የምታውቀው💚

እርሱ ነው የውስጤ ሰላም🍃

እርሱ ነው ደስታዬ🤍

አምላኬ አንተን ለመውደድ እልፍ ምክኒያት አለኝ አልሀምዱሊላህ🍃


وَاسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي رَحِيمٌ وَدُودٌ

«ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት፡፡ ከዚያም ወደርሱ ተመለሱ፡፡ ጌታዬ አዛኝ ወዳድ ነውና (አላቸው)፡፡ (ሁድ:90)

🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃

ተጓዥ ብእረኛ

13 Nov, 04:00


"ገንዘብ ከጠፋ ምንም አልጠፋም፤ ጤና ከጠፋ የሆነ ነገር ጎድሏል ፤ ዲን ከጠፋ ግን ሁሉም ነገር የለም!"

በዚህ አለም ስትኖር ምንም ያህል ብትደሰት ያ ደስታ እንደሚያልፍ አትርሳ፤ ምንም ያህል ብታዝን ያም ሀዘን እንደሚያልፍ አትርሳ።

አየህ የሚገጥሙህ መጥፎ አጋጣሚዎች ዲንህን እንዲያሳጡህ በፍፁም መፍቀድ የለብህም አይዞህ በርታ ኻሊቁ ዱንያ የፈተና መሆኗን ነግሮን አይደል

ተጓዥ ብእረኛ

12 Nov, 16:03


ከታሪክ የምንማረው ሰዎች ከሌሎች ታሪክ እንደማይማሩ ነው ይለናል አንድ አሳቢ

ይህ ነገር ግን በሙስሊሞች በጣም ባሰ ለአንድ ሺ አንድ ጊዜ ያህል ሙስሊሞች ከኢስላማቸው ሸርተት ባሉ ቁጥር ውድቀት ሲቀበላቸው ከአቂዳቸው ፈቀቅ ሲሉ ሽንፈት ሲወዳጃቸው አኺራን ትተው ዱንያን ባፈቀሩበት ልክ የበታችነት ሲዋሀዳቸው መክረሙን ታሪክ ይነግረናል

ተራ እረኞችና በዳይ ህዝቦች የነበሩትን ሶሀቦች ዘራፊና ሞራል አልባ የነበሩን ግለሰቦች የበታችና የተገፉ የነበሩን ህዝቦች ቁርአን በብርሀኑ የስልጣኔ የክብርን የንግስናን የሀብትንም በር ሲከፍትላቸው አለም ጉድ ማለቱንም መዛግብት ሰንደዋል

ሶሀቢው የሮሙ ንጉስ ዘንድ ሄዶ እኛ አላህ በቁርአን ያላቀን ህዝቦች ነን ሲል ነበር ጣፋጭ ንግግሩን የጀመረው

እኛ ግን ዛሬ እነሱ ፊት ስለ እስልምናችን ማውራት እንኳ የምናፍር ደካሞች ሆንን ቁርአንን ችላ ብለን በፍልስፍናቸው ተገረምን

አይወዷችሁም መባላችንን ችላ ብለን እነሱን ለማስደሰት ሆነ ትጋታችን

እና እንደ ሁሌው ታሪክ ሲነግረን የከረመው ደርሶ ልቅናችን መደርመስ ሲጀምር ግን ከታሪክ ተምረን ወደ ኢስላማችን ከመመለስ ይልቅ አሁንም የሞኝ ድካም መድከም ቀሎናል

ሰዎች በኛ ላይ የፈፀሙትን በደል ስናወራ ዘመናት ነጎዱ አሁንም እኛ በራሳችን ላይ የፈፀምነውን በደል ለማስተንተን ጊዜው አልደረሰምን?

ተጓዥ ብእረኛ

11 Nov, 17:55


ቀርአን ጊዜህን ሚፈልግ ሊመስልህ ይችላል ነገር ግን አትሳሳት ጊዜህ እራሱ ነው ቁርአንን ሚፈልገው 🍃

ተጓዥ ብእረኛ

11 Nov, 16:11


ከተዋደዱ ቶሎ ብለው ወደ ትዳር ይሂዱ…

ረሱል (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦


﴿لم يُرَ لِلْمُتَحابَّيْنِ مثلُ النكاحِ﴾

“➜ለሁለት ለሚዋደዱ ጥንዶች ኒካህን (ትዳርን) የመሰለ መልካም ነገር አላየሁም።”

ሶሂህ አልጃሚ፡[ 5200 ]

ያ አላህ ይሄን ነገር ለከበዳቸው ሁሉ አግራው

ተጓዥ ብእረኛ

11 Nov, 04:04


🌿🌿
በኢስቲግፋር

መጥፎ ስራዎች ወደ መልካም ይቀየራሉ

ካላሰብነው በከኩልም ሪዝቅ ይመጣል

የአላህ ውዴታም ይገኛል

ጭንቀትም ይራገፋል ብዙ ብዙ

አስተግፊሩላህ
አስተግፊሩላሀል አዚም
አስተግፊሩላህ ወአቱቡ ኢለይህ
🍃
ሰባኸል ኸይር

ተጓዥ ብእረኛ

10 Nov, 18:13


እኛ እንሄዳለን
.
.
.
.
.
«ፈለጋችን ይቀራል»

ጥሩ ፈለግን አስቀምጦ ለሄደ መልካም ይገባው⚡️
አላህ ለመልካሙ ሁሉ ይግራን ያ ረብ

ተጓዥ ብእረኛ

09 Nov, 18:27


🌟ፃፍ!
ምናልባት ያንተ መፃፍ የተሰበረን ልብ ይጠግን ይሆናል
ምናልባትም ተስፋ አጥቶ የጠወለገ ልብ ላይ ተስፋን ይጭር ይሆናል
ፅናት ያለውን ሰው ያበስር ይሆናል

🌟ፃፍ
በጌታህ ፍቃድ በብእርህ ሰበብ ልቦች ህያው ይሆኑ ዘንድ
በሌሎች መመራት የማይቋረጥ ምንዳ ትቸር ዘንድ
የፀኑትን ልታበስር እውቀትህም ሊፋፋልህ

🌟ፃፍ አስታውስ ማስታወስ ለምዕመናን ይጠቅማልና
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

👉ነገር ግን ተጠንቀቅ አላህ ፊት ሆነህ ስታየው የማያስደስትህን ነገር አትፃፍ‼️‼️

=================================
ጌታዬ ሆይ
ስለአንተ የሚያወሩ አንደበቶችን፣
አንተን ለማወቅ የሚያነቡ አይኖችን፣
የነብዩን ሱንና የሚፅፉ እጆችን በአሸናፊነትህ ከእሳት ቅጣት ጠብቃቸው። ለኛም እዘንልን
================================
ረቢ ይቅር በለን፤ ማረን፤ የተሟላ ደህንነትንም ለግሰን።

https://t.me/waseta1

ተጓዥ ብእረኛ

09 Nov, 18:17


ርዝቃቸው ከአላህ ነው!

ከኢሻ ሶላት ቡሀላ ወደ ቤቱ ተመለሰ
ልጆቹም ተኝተው አየ፣ለሚስቱም ልጆቹ ሰግደዋል? እንዴ ብሎ ጠየቃት
እሷም፦ምግብ ስላልነበረ አባብዬቸው ተኙ አልሰገዱም
እሱም፦ ቀስቅሻቸው አላት
እሷም፦ የእገሌ አባት ሆይ …!!ከቀሰቀስኳቸው ከረሀብ የተነሳ ያለቅሳሉ የሚበላ ደሞ የለም! አለቺው
እሱም፦አድምጪኝ: ከኔ የሚጠበቀው እንዲሰግዱ ማዘዝ ነው…ርዝቃቸው ከኔ አይደለም ፣ቀስቅሻቸው ርዝቃቸው ከአላህ ነው !
አላህም እንዲህ ይላል (ቤተሰቦችህንም በስግደት እዘዝ ፣በእሷም ላይ ዘውትር ፅና ፣ሲሳይን አንጠይቅህም ፣እኛ እንሰጥሀለን ፣ መልካሚቱ መጨረሻ ለጥንቅቆቹ ናት )
እናቲቱም እጅ ሰጠችና ቀሰቀሰቻቸው ፣ሰግደው እንደጨረሱም የቤታቸው በር ተንኳኳ ፣
ከዛም ሲከፍቱት ከከተማው አንድ ከበርቴ  ከማእዱ ጣፋጭ ከሆነው ግማሹን ይዞ ቆሞ ነበር ፣
ሰውየውም ፦ውሰድ ላንተ እና ለቤተሰቦችህ ነው አለው
እሱም ፦እንዴት ሲለው
ሰውየውም፦«አንድ ባለ ስልጣን እንግዳዬ ነበር ማእዱን ከመመገባችን በፊት ተጣላን እና ምግቡን ላይበላ ምሎ ሄደ »ምግቡንም ይዜ እንዲህ አልኩ "እግሬ ለቆመበት ሰው እሰጣለሁ ,በአላህ እምላለሁ አንተ ደጃፍ ስር እንጂ እግሬ አልቆመም ነበር ! በአላህ ይሁንብኝ ምን ወደዚህ ይዞኝ እንደመጣ አላውቅም "አለው !!
ሱብሀነከ ማ አክረመክ

《ጌታዬ ሆይ ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድረርገኝ ፣ከዘሮቼም አድርግ! ጌታችን ሆይ ፀሎቴንም ተቀበለኝ፤》

ተጓዥ ብእረኛ

08 Nov, 16:49


የሆነ ቀን ቁርአን እያዳመጠች የተሰማትን ስሜት መቆጣጠር አቃታትን እንዲህ አለች

አላህዬ ይህ ቃልህን የመስማት ደስታ ነው ታድያ አንተን የማየት ደስታ እንዴት ሊሆን ነው 🍃🍃

ተጓዥ ብእረኛ

08 Nov, 04:52


ወንድሜ ጭንቀት አካቦሀል?
አንችስ እህቴ ደስተኛ አይደለሽም?
ወዳጆቼ ዱንያ ጥብብ ብላባቿለች?
ማነው የከፋው ያዘነ ባዶነት ሚሰማው?

ይህንን ፋይል ፀጥ ባለ ቦታ ለብቻህ ሆነህ ክፈተው ለብቻህ ባትሆንም ችግር የለም ግን ፀጥ ያለ ቦታ ሆነህ ክፈተው!!!

ጉዳይህ ምንም ይሁን ምን አሁን ማስታገሻ ይሀውልህ አስተዋይ ከሆንክ ደግሞ መድሀኒትህንም በውስጡ ተቀምጦ ታገኘዋለህ ለጊዜው ግን ቢያንስ እንደማስታገሻ ይሆንሀልና ያዝ

ተጓዥ ብእረኛ

07 Nov, 17:12


ያ አላህ

ልቤ ለኔ እንደ ውብ ግዛት ነች
እንደ ቅዱስ ምድር
እንደ ሰላማዊ አለም

ያ አላህ አንተ ብቻ ንገስባት
ቁርአን ብቻ ያስተዳድራት
ስምህ ብቻ ይላቅባት

ያ ረብ አታበላሽብኝ ያ አላህ አታቆሽሽብኝ
ፍንደቃዬ ስምህን ስሰማ ብቻ መሆኑን ከተወ መረጋጋትን ፍለጋ ከቁርአን ውጭ ወደ ሆነ አካል ካማተርኩ ችግር አለ

አንተን በማፍቀር መልእክተኛህን በመናፈቅ ቁርአንን በመጠማት እንጂ ስጓጓ ደስ አይለኝም

እርዳኝ ያ አላህ ልቤን ጠብቅልኝ የኔ ጌታ

.اللهم... تحكم أنت بحياتي... وأحكم فيها... أعلم إنك أنت خير الحاكمين.

ተጓዥ ብእረኛ

06 Nov, 16:44


እንፈክርበት....

ነቢዩሏህ ሱለይማን(አለይሂ ሰላም)  በሁለት ጥንድ ኡስፉር ወፎች  አጠገብ እያለፉ ነው...
                     ወንድየው ወፍ ሴቷን እየተለማመጣት ነበር ``ኸረ    ተይ ስሚኝ. ..እኔኮ ከፈለግሁ የነቢዩሏህ ሱለይማንን የቤተመንግስት ቁባ በመንቁሬ ይዤ  በርሬ ባህር ሥር  መወርወር የምችል ጀግና ነኝ ...
                   ነቢ ሱለይማን በወፉ ንግግር ፈገግ እያሉ  ጠጋ ብለውት ••አንተ ወፍ የምርህን እንደዚያ ማድረግ ትችላለህ ግን? •• ሲሉት  •• ኸረ  አንቱ መልዕክተኛ  ያ ው የወንድን ጸባይ ታውቁት የለ ሲወድ ያለ የሌለውን እኮ ነው ሚዘባርቅ (በዘመንኛው  እየሰከሳት ነዋ ሚባለው?)...

     ነቢ ሱለይማን  ይበልጥ ፈገግ እያሉ  ወደ ሴቲቷ ኡስፉር  ቀረቡና ``አንቺት  ለምንድነው እንዲህ እየለመነሽ የትዳር ጥያቄውን እማትቀበዪው `` አሏት

       የቋጠረችውን መለሰች •አንቱ የአሏህ መልዕክተኛ   ንግግሩን ስትሰሙ  እውነት አፍቃሪ እንዳይመስልዎት.,,ፍቅር ቢሞግትም  ሌላ (ኮረዳ) ወፎችን እንደሚወድ ደርሼበታለሁ...(ለዚያ ነው እማንገላታው)...•

      ይሄኔ  የነቢ ሱለይማን ፈገግታ ወደ መሪር ለቅሶ  ተለወጠ   ••አህ አህ አህ   እኔም አሏህን እንደምወደው እሞግታለሁ..እውነታው ግን  ለአሏህ በተጠበየች ልብ ውስጥ  ድኩም ፍጥረታትን በልቤ ጥጋጥግ  ሰግስጌ ማኖሬ ነው••....ለ40  ቀን እና ሌሊት ኸልዋ ዘግተው ነፈረቁ ይባላል።

የቂሳውን እውነተኝነት እርግጠኛ አይደለሁም
የመልእክቱን ትክክለኝነት ግን ልብ ያለው ሁሉ ያውቃል ራህማከ ያ ረብ

ተጓዥ ብእረኛ

06 Nov, 16:00


ረመዳን 3 ወር ከ 27 ቀን እንደቀረው ግን እያያቹልኝ ነዋ

አጂብ አጂብ አላህዬ በሰላም በኢማን በጤና በፍቅር አድርሰን

ወደኸንና ወደንህ ረመዳንን ምንቀበል አድርገን ያ ወዱድ

አልሀምዱሊላህ እየመጣ ነው

ተጓዥ ብእረኛ

05 Nov, 19:23


"ሲወለዱኮ የማንም ያልሆኑ ልጆች የሉም፤እመቤቴ።ልጆች ሁሉ ወላጆች
እንዳሉዋቸው መቸም ግልጽ ነው።ነገር ግን የስጋ መወለድ ብቻ ልጆችን ሙሉ በሙሉ የወላጆቻቸው ልጆች አያደርጋቸውም። ልጆች ሙሉ በሙሉ የወላጆቻቸው ልጆች እንዲሆኑ ወላጆች ለልጆች ስጋና ደማቸውን፣አጥንትና ጅማታቸውን፣ ቆዳቸውን ብቻ ማካፈላቸውሀ አይበቃም።

ልጆች ሙሉ በሙሉ የወላጆቻቸው ልጆች እንዲሆኑ ወላጆች ለልጆች ታሪካቸውን፣ ስልጣኔያቸውን፣ ህገ-ወጋቸውን፣የኑሮ ስራታቸውንና ይህ ሁሉ የሚሰጠውን የመንፈስ፣ የምነትና የስሜት ጸጋ ጭምር ማካፈል ይገባቸዋል።


...አዩ? አያችሁ? የኢትዮጵያን ልጆች ኢትዮጵያውያን ወለዱዋቸው፤በቃ። የኢትዮጵያ ልጆች ኢትዮጵያውያንነታቸው እዚያ ላይ ቆመ። ከዚያ ፈረንጅ ተቀብሎ ታሪኩን፣ስልጣኔውን፣ህገ-ወጉን፣ባህሉን፣የኑሮ ስራቱንና የዚህ ሁሉ ስሜት የሚገለጽበትን ልዩ ልዩ ዘዴ እያስተማረ አሳደጋቸው።በመንፈስ፣ በምነትና በስሜት የፈረንጅ ልጆች ሆኑ።እንግዲህ እንዲህ ያሉት ልጆች፤በሙሉ ኢትዮጵያውያን አይደሉም፤ በሙሉ ፈረንጆች አይደሉም፤ ስለዚህ ማንም አይደሉም ነው ያልሁ። ታዲያ ይህ ግልጽ አይደለም? ይህ እንቆቅልሽ ነው?

👆👆 አንብቤ ቀልቤን ያዘኝና አጋራኋችሁ የኢስላምንም ልጆች አስቧቸው ማን ወላጅ እየሆናቸው እንዳለም

ራህማከ ያ ረብ

ሁሉም እጁ ላይ ያለውን ሀላፊነት በተወጣ ህም

ተጓዥ ብእረኛ

04 Nov, 16:12


ምናለ እድሜህን በምን አሳለፍክ ለሚለው የቂያም ቀን ጥያቄ

🍃ጌታዬ ሆይ ከቁርአን ጋር ነው ያሳለፍኩት ስሀፍዘው ሳነበው ሳኸትመው ሳስተነትነው 🍃

👆ቢሆንልኝ መልሴ

ተጓዥ ብእረኛ

04 Nov, 16:00


أن يكون جوابي : "عنْ عُمُرِهِ فيما أفناهُ؟"

‏مع القرآن، مع حفظه وتلاوته وختمه وتدبّره .. ياربّ!

ተጓዥ ብእረኛ

04 Nov, 15:56


🍃ልቦቻችን በፀዳች ኖሮ የአላህን ንግግር ቁርአንን ባልጠገብን ነበር🍃🍃
(ኡስማን ኢብኑ አፋን)

ተጓዥ ብእረኛ

02 Nov, 17:24


إِنَّ وَلِيِّيَ اللَّهُ الَّذِي نَزَّلَ الْكِتَابَ ۖ وَهُوَ يَتَوَلَّى الصَّالِحِينَ

«የእኔ ረዳቴ ያ መጽሐፉን (ቁርኣንን) ያወረደልኝ አላህ ነውና፤ እርሱም መልካም ሠሪዎችን ይረዳል» (በላቸው)፡፡

ተጓዥ ብእረኛ

01 Nov, 10:11


በሀዲስ እንደመጣው እናትና አባቴ ፊዳ ይሁኑላቸውና ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም እንዲህ ይላሉ
ሀውድ ላይ እስክታገኙኝ ድረስ ታገሱ

ይኸው ዛሬ በህመማችን በቁስላችን ወዳጆቻችን በመለያትም ላይ ሆነንም እሳቸውን በማግኘት ተስፋ እራሳችንን እናስታግሳለን ነገን እናስባለን የቂያም እለት ከሀቢባችን ከነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም እጅ ጣፋጩን ሀውድ ስንጠጣ እንስለዋለን ከዚያ እንዳሉንም እንታገሳለን🍃

ምን ያማረች መገናኘት ነች ያ አላህ

አላሁመ ያ ሰሚአ ዱአእ ሸፈአቸውን ሀውዳቸውን ጉርብትናቸውን አደራ

አላሁመ ሰሊ ወሰሊም ወባሪክ አላ ሀቢቢና ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም

ተጓዥ ብእረኛ

31 Oct, 18:44


ለይሉ ጁምአ ነው ሲነጋም የሳምንቱ ኢድ ላይ ነው ሱረቱል ካህፍን በፈለጋችሁት ቃሪእ መርጣችሁ ጁምችሁን አድምቁማ👆

ሰለዋትም እንዳይረሳ በከውኑ ጌጥ ላይ
አላሁመ ሰሊ ወሰሊም ወባሪክ አላ ሰይዲና ወሀቢቢና ወቁድወተና ሙሀመድ

ተጓዥ ብእረኛ

31 Oct, 18:31


((ሱረቱል ከህፍ))🌹📖🎧

በቃሪእ  ያሲር አዱስሪይ🌹🍃🌹🍃🌹

🌹🌴🌹🌴🌹🌴🌹🌴🌹🌴🌹

ተጓዥ ብእረኛ

31 Oct, 14:41


لا احد يستطيع ان يفهم قلبك بشكل افضل من الذي صنعها.

Nobody can understand your heart better than the one who created it.

ማንም ልብህን በትክክል ሊረዳልህ አይችልም ከፈጠራት በላይ 🍃

ተጓዥ ብእረኛ

30 Oct, 12:58


የሸሪአን ትምህርት በርቀት የምታገኙበት ጥሩ እድል ነው ተፈተናችሁ ውጤት ተሰርቶ መጨረሻ ላይ የዲፕሎም ሰርተፍኬት ይሰጣቿል ወደ ኋላ አትበሉ ተመዝገቡ ዲን በእውቀት ላይ ሲመሰረት እጅግ ውብ ነው
አላህ የሱ ፊት የተፈለገበት ያድርገው አሚን

ተጓዥ ብእረኛ

30 Oct, 12:53


አፍሪካ አካዳሚ 3ኛውን ዙር የሸሪዐ ዲፕሎም ትምህርት መመዝገብ ለፈለጋችሁ ባጠቃላይ ምዝገባ መጀመሩን ያበስራችኋል።

📲 የመመዝገቢያው ኪው አር ኮድ ወይም ሊንክ
https://t.me/africaacademy_diplom3

አካዳሚውን ልዩ የሚያደርገው:
💵 በነፃ መሆኑና ለሁሉም የእድሜ ክልል ላሉ ወንዶችም ይሁን ሴቶች ምቹ መሆኑ፤
💻 በስልክ ወይም በላፕቶፕ ባሉበት ቦታና ርቀት ለመማር ምቹ መሆኑ፤
📚የትምህርት አሰጣጥ መንገዱ እጅግ ያማረና ገር መሆኑ፣ እንዲሁም በተመረጡ ዑለሞች የሚሰጥ መሆኑ፤
🗒️ለየሁሉም የትምህርት ክፍል በይሳምንቱና ትምህርቱ ሲጠናቀቅ የሚሰጡ ፈተናዎች መኖራቸው፤
🎊ላለፉ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት የሚሰጥ መሆኑና የምርቃት ፕሮግራም የሚዘጋጅ መሆኑ፤

📖በአካዳሚው የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች:
1 - ሲራ
2 - ዓቂዳ
3 - ፊቅህ
4 - ተርቢያ
5 - ተፍሲር
6 - ሐዲሥ

⏱️የትምህርት ቆይታው አንድ አመት ሲሆን በሁለት ሴሚስተሮች የተከፋፈለ ነው።

📋ትምህርቶቹ ለተማሪዎች የሚቀርቡት በነዚህ መልኩ ነው:
- በፒዲኤፍ (pdf)
- በቪዲዮ
- በድምፅ

አላህ ካለ የሶስተኛ ዙር የዲፕሎም ትምህርቱ በ10/11/2024 ይጀምራል።

(የመመዝገቢያውን ሊንክ በመጀመሪያው የኮሜንት መስጫ ሳጥንና ባዮ ላይ ያገኙታል።)

እድሉ አያምልጥዎ! በዙሪያዎም ላሉ ሁሉ ያጋሩ።

ተጓዥ ብእረኛ

29 Oct, 18:42


ከአንተ ውጪ ማን አለን ያ አላህ

አባታችንን ከአፈር አንስተህ ሰው አደረከው

እኛን ከደካማ ፈሳሽ አስገኝተህ ሰው አደረከን

ሪዝቃችንን እራሱ ማግኘት የማንችል ስኖን አስመቸህልን

ከእንስሳት የተሻልን እንድንሆን አእምሮ ለገስከን

የተፈጠርንለትን አላማ እንዳንረሳ ሙስሊም አረከን

ተቆጥሮ የማያልቅ ፀጋን ሰጠሀን

እልፍ አእላፍ ምስጋና ይገባህ

አላህ ሆይ ሩሀችን ከኝ ተለይታ ሰዎች በሚያጥቡን ቀንም እዘንልን

በጨርቅ ጠቅልለው ጉርጓድ ውስጥ ሲያስገቡንም እዘንልን

አፈሩን በላያችን ላይ ሲመልሱም እዘንል

ከዛ ቡሀላ ላለውም ከኛ ጋር ሁን

አላህ ሆይ በዚያ ቀንም ከኝ ጋር ሁን

ካንተ ውጭ ማን አለን ያ አላህ!!!!!

https://t.me/waseta1

ተጓዥ ብእረኛ

29 Oct, 04:03


#መሀበተ_ረሱል

የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ፍቅር ነው ይህ

አንዳንዴ አይኖች ትኩስ እንባዎችን ያፈሳሉ በሀዘን ሳይሆን በፍቅር

አንዳንዴም ልቦናዎች እሩቅ ይሰደዳሉ ሌላ ነገር ፍለጋ ሳይሆን በፍቅር

አንዳንዴም ጀሰዶች ይከሳሉ ተጎድተው ወይም አንዳች ነገር አተው ሳይሆን በፍቅር

አንዳንዴም ደሞ ሰዎች አቅላቸውን መቆጣጠር ያቅታቸዋል በህመም ሳይሆን በጥልቅ በፍቅር ምክኒያት

#መሀበተ_ረሱል
የመልእክተኛው ፍቅር አለይሂ አፍደሉ ሰላቲ ወሰላም

https://t.me/waseta1

ተጓዥ ብእረኛ

29 Oct, 03:57


ረመዳን 4 ወር ከ 5 ቀን ብቻ እንደቀረው ግን ልብ ብላችኋል

አላህ ሆይ በሰላም በኢማን በአፊያ የምንደርስ አድርገን አሚን ያረቢ

ተጓዥ ብእረኛ

26 Oct, 04:27


በአላህ እናምናለን በእርሱ ላይ ምንንም አናጋራም ከእርሱ ጋር ማንንም አናወዳድርም
ልባችን ሲቸግረን ወደሱ ሲሞላልንም ወደሱ ትመታለች እንወደዋለን እናምነዋለንም


ከእውነት ጋ እናብራለን ። ትጋታችንን በማንም  አናስነጥቅም ። ጉዟችን ቅርብ አይደለም  ። ከመንገድ ላይ ጥቅምን ብቻ መሰረት ያደረጉ ነጋዴዎች ፣ ወዳጅነት ላይ ብቻ የተመረኮዙ ዳኞች አይረብሹንም  ።

ህይወት ደስ ይላል እንዲህ

የምንወደው ነገር ላይ ፣ ትክክለኛ ነገር ላይ፣ አቅም ሊሆነን የሚችል ነገር ላይ ፣  positive ኢነርጂ የሚያመጣ ሁነት  ጋ እንመሰጣለን ።

የውሸት ከምንስቅ የእውነት ማኩረፍን እንመርጣለን ። ስናገኝ ትህትናችን እንዳይወሰድ ፤ ስናጣ ጥንካሬ እንዳይሄድብን የሙጥኝ እንላለን ።

የሰው ሳቅ ላለመቀማት እንሞክራለን ።
ለራስ ታማኝ ለመሆን እንለማመዳለን ። 

ህይወት ደስስ ትላለች ።

ሰማይ ነው ብለን ያሰብነውን ቁልቁል አይተነው እናውቃለን ።  በሆነልን ሁሉ አመስጋኝ ነን


አልሀምዱሊላህ ህይወት ከአላህ ጋር ደስ ትላለች

ተጓዥ ብእረኛ

23 Oct, 18:20


﴿وَاجعَلنِي منْ ورَثةِ جنَّةِ النَعيم

የፀጋዋን ጀነት የምወርስም አድርገኝ (26:85)

ተጓዥ ብእረኛ

23 Oct, 06:24


እንዴት ነበሩ? (1)

ኡርወት ኢብኑ ዙበይር እጅግ ግርማ ሞገስ ነበረው በቤቱ ውስጥ ደግሞ በጣም ይከበር ነበር እና እሱ ቤት ሲገባ ሁሉም ሰው ዝም ይል ነበር ጠንቀቅ ሰብሰብ ይሉ ነበር

ነገር ግን ኡርወት ልክ ሰላት ሲጀምር እንደፈለጉ ይሆናሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ያወራሉ ሚፈልጉትንም ይሰራሉ ለምን ይመስላቿል??

ምክኒያቱም ኡርወት ሰላት ውስጥ ከገባ ምንም ነገር አይሰማም ነበር
🍃ሰላቱ ጆሮውንም አእምሮውን ሁለመናውን ይቆጣጠረው ስለነበር 🍃🍃

አጂብ አጂብ እንዲህ ነበር ሰላታቸው

ተጓዥ ብእረኛ

21 Oct, 05:46


ወላሂ ወላሂ ነው ምላችሁ አላህ የተመኛችሁትን መልካም ነገር በእውነት አምናችሁት የለመናችሁትን ጉዳይ በርግጥ ይሰጣቿል

እንደ ህፃን እየገለፈጥኩ ይሄን ፅሁፍ እንድፅፍ ያደረገኝን ጉዳይ ብነግራቹ በጣም ደስ ይለኝ ነበር ግን ለመንገር አይመችም ረጅም ነው ታሪኩ

ብቻ አላህን በእውነት አምናችሁት ጠይቁት በፍፁም አሳፍሮ አይመልሳችሁም ነው ምላችሁ

የኔ ልመናን ሰሚ ጌታ
የኔ ወዱድ የኔ ለጢፍ
ዘልአለም ሚያክል ተመስገንልኝ

ባንተ ልክ ቅርብ አላየሁም የኔ ጌታ አልሀምዱሊላህ🍃

ተጓዥ ብእረኛ

19 Oct, 18:46


فَاصْبِرْ إِنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ وَلَا يَسْتَخِفَنَّكَ الَّذِينَ لَا يُوقِنُونَ *
የአላህ ቃል ኪዳን እውነት ነውና ታገስ እነዚያም (በመጪው አለም) እርግጠኛ ያልሆኑት አያታልሏችሁ።

(suret room 60)

ተጓዥ ብእረኛ

18 Oct, 07:46


አሟሟቱ ውስጥን በጀግንነት ያንቀጠቅጣል። ሰውነትን በወኔ ንጦ በሐሳብ ከቦታው ያከትማል። ጀግኖች እንዲህ ነው ዱንያን የሚሰናበቱት። ጠመንጃቸውን አቅፈው ጠላትን እያርበደበዱ ጥለው የሚወድቁት።

አሁንም አሁንም ደግመህ ደጋግመህ በአላህ መንገድ መሰዋትን ያስናፍቁሀል። በእርሱ መንገድ መሞትን ያስወድዱሀል።
እንደገናም እንደገናም እንደገናም
ደግሞ ደጋግሞ መሞትን የሚመኝ
ከሸሂዶች በቀር ማንም የለም።

በአላህ መንገድ እየታገሉ መሰዋት የተመረጡ ሰዎች እንጂ የማያገኙት ህያውነት ነው።
አቡ ኢብራሂም ያህያ ሲንዋርም
ለመስጂደል-አቅሳ ክብር በሚገባው አይነት ሞት እየተዋጋ ጥሎ ወድቋል።

ከመሬት በታች ከምሽጉ በስተጀርባ ሲጠብቁት በጀግንነት ከፊት ሲገጥማቸው ከርሞ በፍላደልፊያ ድንበር በረፈህ አቅራቢያ ነፍሱ የምትወደውን ጌታዋን ተገናኘች።

የህያ ሲንዋር የተገደለበት ቤት ባለቤት "በቤታችን ሸሂድ መሆንህ ክብራችንን ይጨምረዋል።  ቤታችንም ነፍሳችንም ያለን ሁሉ ፊዳ ይሁኑልህ ሕያው ሆነህ ሰማዕት ሆንክ ደማ ቁስላችን" በማለት ጽፏል።

ለየህያ ሳይሆን ለነፍሳችሁ አልቅሱ ስለቀሳሞችም ስለፍልስጤሞችም አታላዝኑ። ሺህ የህያ ሺህ ጀግና የሚያፈልቁ ማህፀኖች በተከበረው የፍልስጤም ምድር ይገኛሉ። የየህያን መንገድ ተከትለው የእርሱን ሞት መሞት የሚቋምጡ ሙጃሂዶች ከየዋሻው ከየጉርጓዱ ስር ዛሬም አሉ። ድል አሊያም ሸሂድነት መርሀቸው ነው።

ወንድሞቼ! የወጋችሁ እሾህ ይውጋኝ። የመታችሁ እንቅፋት ይምታኝ። የባሩዱ ሽታ እኔንም ይሽተተኝ።

رحيمك الله يا شهيد ኢላ ረህመቲላህ ያ ሲንዋር
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

Mahi mahisho

ተጓዥ ብእረኛ

18 Oct, 04:20


حَتَّى إِذَا اسْتَيْأَسَ الرُّسُلُ وَظَنُّوا أَنَّهُمْ قَدْ كُذِبُوا جَاءَهُمْ نَصْرُنَا فَنُجِّيَ مَن نَّشَاءُ وَلَا يُرَدُّ بَأْسُنَا عَنِ الْقَوْمِ الْمُجْرِمِينَ

መልክተኞቹም ተስፋ በቆረጡና እነርሱ በእርግጥ የተዋሹ መኾናቸውን በተጠራጠሩ ጊዜ እርዳታችን መጣላቸው፡፡ (እኛ) የምንሻውም ሰው እንዲድን ተደረገ፡፡ ቅጣታችንም ከአጋሪዎቹ ሕዝቦች ላይ አይመለስም፡፡

(Suret yusuf 110)

ተጓዥ ብእረኛ

18 Oct, 03:45


አብሽሪ ኡመቲ

ተስፋ መቁረጥ ሲዳብስ፣ እግር ሲከዳ፣ ዙሪያ በሙሉ ሲጨልም አላህ ነስር እያቀረበ ነው። ግለሰቦች በተከታታይ ሊሰው ይችላሉ፣ነገርግን አላህ የገባውን ቃል ለመርህ እንጁ ለግለሰቦች አይሰጥም። ሐማስ ደግሞ የመጣሸት መንገድ ነውና የመሪ ችግር የለበትም። ከየሕያ ያበዱ መሪዎች አሉት። አላህ ቃሉን ላያጥፍ፣ ነቢ ላይዋሿት የአላህ እገዛ እዚያ ዙሪያ በመንገዱ ለሚፋለሙት ናት።

እንደሚታወቀውም

ነስር ሲመጣ እንኳን ኖርማል ሰዎች ነብያትን ተስፋ አስቆርጦ ነው። ጠፋ ሲባል ይበራል፣ ከሰመ ሲባል ይለማል። የግለሰቦች ግድያ ለጠላት ድል እንዳለሆነው ሁሉ፣ ለሙጃሂድ ደግሞ ሽንፈት አይደለም። ግን ነስር ነስር ይሸታል

ተጓዥ ብእረኛ

17 Oct, 18:06


يَيَحْيَى خُذِ الْكِتَبَ بِقُوَّةٍ

«የሕያ ሆይ! መጽሐፉን በጥብቅ ያዝ!» (አልነው)።

(ሱረት መርየም 12)

ተጓዥ ብእረኛ

17 Oct, 17:31


'
أنتَ وُجهتِي #ياالله فأبعِدني عن كلّ طريق لا يوصلني إليك
'
አንተ መድረሻዬ ነህ ያ አሏህ! ወደ አንተ ከማይመራኝ መንገድ ሁሉ አርቀኝ🤲

ተጓዥ ብእረኛ

17 Oct, 04:04


‏﴿ فَقُلْتُ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ إِنَّهُ كَانَ غَفَّارًا ﴾

ተጓዥ ብእረኛ

15 Oct, 07:53


ለእርድ የቀረበ በግ ታውቃላችሁ?

ሊያርዱት ቢላዋ እየተሳለለት፣ ሊቀቅሉት ድስት ተጥዶለት፣ ከሰከንዶች በኋላ ወደ ሞት ጉዞ መሳፈሩ ላይቀር  እሱ ዘና ብሎ ሣሩን ይግጣል።
የኛና የዱንያ ነገር እንዲህ ነው።

መለከል መውት እያሳደደን፣ መቃብር አፉን ከፍቶ እየጠበቀን፣ የምናውቃቸዉም ሆነ የማናውቃቸው ሰዎች ዐይናችን እያየ ዱንያን ጥለው እየሄዱ እኛ ምንም እዳ እንደሌለበት ሰው ዘና ብለን እንኖራለን ።
🦋የሞት ቀንህ አልተነገረህም ፤ ድንገት ደርሶ ሊይዝህ ይችላል ። ጣጣህን ጨርሰህ ዝግጁ ሆነህ መጠበቅ ነው🙌

๏ ያ ለጢፍ ፋናዬን ውብ አድርገህ
መጨረሻዬንም አሳምርልኝ 🤲🤲

ተጓዥ ብእረኛ

12 Oct, 18:48


يالله إنا نُحب كتابك حُباً جمّاً

‏ فيسِر وسهل لنا طريق إتقانه واجمعه في صدورنا وثبته ثبات الجبال الراسيات واجعلنا من العاملين بما فيه ..

ያ አላህ እኛ መፅሃፍህን እጅግ በጣም እንወዳለን እርሱን በጥልቅ የማወቅን መንገዱን አግራልን አቅልልን በልቦቻችንም ሰብስበው፣ እንደ ጽኑ ተራራዎችም አጽናው በውስጡ ያለውንም ከሚሠሩት አድርገን

አሚን

ተጓዥ ብእረኛ

12 Oct, 18:34


أَنِ اقْذِفِيهِ فِي التَّابُوتِ فَاقْذِفِيهِ فِي الْيَمِّ فَلْيُلْقِهِ الْيَمُّ بِالسَّاحِلِ يَأْخُذْهُ عَدُوٌّ لِّي وَعَدُوٌّ لَّهُ ۚ وَأَلْقَيْتُ عَلَيْكَ مَحَبَّةً مِّنِّي وَلِتُصْنَعَ عَلَىٰ عَيْنِي

«(ሕፃኑን) በሳጥኑ ውስጥ ጣይው፡፡ እርሱንም (ሳጥኑን) በባሕር ላይ ጣይው፡፡ ባሕሩም በዳርቻው ይጣለው፡፡ ለእኔ ጠላት ለእርሱም ጠላት የኾነ ሰው ይይዘዋልና በማለት (ባሳወቅን ጊዜ ለገስንልህ)፡፡ ባንተ ላይም ከእኔ የኾነን መወደድ ጣልኩብህ፡፡ (ልትወደድና) በእኔም ጥበቃ ታድግ ዘንድ፡፡

ይህን የቁርአን አያ እናስተውል እስቲ መጀመሪያው ምን ያህል አስፈሪ ነበር መጣል መገፋት አደጋ -----

መጨረሻ ላይ ያለውን ግን ተመልከቱ ይህ ሁሉ ልትወደድና በእኔም ጥበቃ ታድግ ዘንድ ነው አለ ሱብሀነላህ

አሁን ላይ ህይወትህ ውስጥ እያለፈ ያለው ከባድ ጊዜ ምን ይሆን ዘንዳ እንደታሰበለት አንተ ምን አሳወቀህ

በጌታህ ላይ እጅግ መልካምን እምነት አሳድረህ ወደ ፊት መጓዝህን ብቻ ቀጥል የዚህ ሁላ መፈጠር ምክኒያት የሆነው ድብቅ ጥበብ ራሱን ይገልጣል

እየመጣ ያለው መልካም ነገር ሁሉ በቅርቡ ይደርሳል ኢንሻአላህ

ተጓዥ ብእረኛ

10 Oct, 14:12


ጌታችን አላህ ሁሌም ከለሊቱ የመጨረሻው አንድ ሶስተኛ ሲቀር (ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ጀምሮ እስከ ሱብሂ) ወደ ቅርቢቷ ሰማይ በመውረድ ይጣራል 

ማነው ምህረትን ሚለምነኝ ምምረው
ማነው (ሚፈልገውን) ሚጠይቀኝ ምሰጠው እያለ

አሁን ይህን ሀዲሰል ቁድስ የሰማና እኛን የሚያውቀን ታዛቢ ቢኖር በምን ይገረማል ግን በጀሊል

የድሀ ድሀ የከጃይ ከጃይ ከመሆናችን ጋር ለመጠየቅ በመኩራታችን?

ወይስ

ከሪም የሆነው አላህ ይህን አስቀያሚ አህዋላችንን እያየም ሁሌም ግን በየለሊቱ ለመማርና ለመስጠት መጣራቱን በመቀጠሉ?

አጂብ ወላሂ አጂብ የአላህ ነገር

ባሪያው ባይገባውም እዝነቱ ይቀጥላል🍃

ተጓዥ ብእረኛ

10 Oct, 13:49


ለይል መነሳት ፈልገን ለሚከብደን ሰዎች አላርማችንን ይሄን እናድርግ ኢንሻአላህ ትንሽም ቢሆን ያነቃቃናል ለሱቢህም መጠቀም ትችላላችሁ።

አላህ ይጠራሀል “ተነስ ቁምና ጠይቀኝ ባሪያዬ እያለ
ጠይቀኝ የፈለከውን ሰጥሀለው
ከአላህ ውጭ ያለን ግን ፈፅሞ አትለምነው

ባሪያዬ ታመህ ከሆነ አዳኝህ ነኝ እኔ
ተሰብረህም ከሆነ ከአላህ ውጭ ሌላ ጠጋኝ የታለህ”

ተነስ ጠይቀኝ ልስጥህ ነው እንግዲ ሱብሀነህ

ይህን ግጥም በአረብኛ ነሺዳ መልክ ነው ኦዲዮው ለማነሳሳት ይጠቅመናል ኢንሻአላህ

#share

ተጓዥ ብእረኛ

09 Oct, 14:55



" ይህ ቁርዓን ለእናንተ መልካምን ነገር በሙሉ የያዘ የአላህ ግብዣ ነው። ከእርሱ የቻላችሁትን ያህል ያዙ! ከቤቶች ሁሉ የአላህን መፅሓፍ ካልያዘ ቤት የበለጠ የበታች የሆነ ቤት አላውቅም። ከአላህ መፅሓፍ ጥቂትም ቢሆን የሌለበት ልብ ባዶ ነው። ልክ ነዋሪ እንደሌለው ኦና ቤት ይመስል"

#ልብህን_በጌታህ_ቃል_ህያው_አድርጋት

https://t.me/waseta1

ተጓዥ ብእረኛ

09 Oct, 04:08


ከቢሊዮኖች መካከል ሙስሊም ሆነህ ተወልደህ ዕድለኛ አይደለሁም ብለህ ታማርራለህ።
ትገርማለህ ወላሂ ።

ተጓዥ ብእረኛ

08 Oct, 15:31


ስህተቱ ሲነገረው ያላመኻኘ ፣ያላላከከ ወደ ራሱ ለማየት የሞከረ እሱ ምስጉን ነው።

ተጓዥ ብእረኛ

06 Oct, 17:18


እራሴ እየራኩህ ለምን ተውከኝ እላለው
ጥዬህ እየጠፍው ረሳኸኝሳ እልሀለው

አምላኬ ጉዳዩ ልክ አንተ በቅዱስ ቃልህ “ሰውም በዳይና አላዋቂ ነው” እንዳልከው ነው

አምላኬ እኔ ነፍሴን በብዙ በድያለውና ይቅር በለኝ!!

4,223

subscribers

377

photos

128

videos