በ2017 ዓ.ም ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዳል ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፡፡
በ 2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ በሪሚዳል ፕሮግራም (Remedial Program) ትምህርታችሁ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ወደ ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ህዳር 26 እና 27፤ 2017 ዓ.ም (December 05- 06, 2024 G.C.) መሆኑን በአክብሮት እየገለፅን፤በተጠቀሱት ቀናት በዩኒቨርሲቲዉ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናስታዉቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
የ8ተኛ ክፍል ዉጤት ካርድ ዋናዉና ፎቶ ኮፒዉ፤
ከ9-12ተኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናዉና ፎቶ ኮፒዉ፤
12ተኛ ክፍል ዉጤት ሰርተፍኬት ዋናዉና ፎቶ ኮፒዉ
የቅርብ ጊዜ የሆነ 6 (3*4) ጉርድ ፎቶ ግራፍ እንዲሁም
የግል አልባሳት ማለትም አንሶላና ትራስ ጨርቅ ይዛችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን፤
ከላይ ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲዉ የማያስተናግድ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ከአክብሮታዊ ሰላምታ ጋር!
ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
*********************************
To stay up to date on this and other university-related topics, please follow our Facebook page: https://www.facebook.com/share/p/ycv74NJS69XKtvbn/?mibextid=WC7FNe