ብሩህ እናት !
ሴቶችን እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚያሸልም “ ብሩህ እናት ” የተሰኘ የፈጠራ ውድድር መዘጋጀቱ ተገለጸ።
የሴቶችን ድካም የሚያቀሉ ቴክኖሎጂ ተኮር የፈጠራ ሀሳቦችን በማቅረብ ለሚያሸንፉ ሴቶች ቋሚ ችግር ፈቺ ተቋም የሚሆኑበትና ከ100 ሺሕ እስከ 500 ሺሕ ብር የሚያሸልም ውድድር ለሴቶች ብቻ ማዘጋጀቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገልጿል።
የፈጠራ ውድድሩ የተዘጋጀው ከኢንተርፕርነሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት፣ ከእናት ባንክ፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሴቶች ጉዳይ ጋር በጋራ በመሆን መሆኑን መስሪያ ቤቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
በዚህም “ ማሰልጠን፣ መሸለም፣ ማብቃት ” በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢ ላሉ ሴቶች እድሉ እንጀተመቻቸ፣ ከተመዘገቡት 5ዐ የተሻለ ሀሳብ ላቀረቡ ተወዳዳሪዎች ስልጠና እንደሚሰጥ አመልክቷል።
“ ፕሮግራሙ ላይ የላቀ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ሴቶች ተወዳዳሪዎች መከካልም 10 ለሚሆኑት አሸናፊ የቢዝነስ ሀሳብ ፈጣሪዎች እውቅናና የገንዘብ ሽልማት እንዲያገኙ ይደረጋል ” ሲል መስሪያ ቤቱ ጠቁሟል።
ለውድድሩ አሸናፊዎች ሽልማቱ ምንድን ነው ?
ከተመዝጋቢዎቹ የተሻለ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሀሳብ ያቀረቡ 1ዐ ተወዳዳሪዎች እንደየደረጃቸው ከ100 ሺሕ እስከ 500 ሺሕ ሽልማት መዘጋጀቱ ተገልጿል።
በገለጻው መሠረት፣ ለ1ኛ አሸናፊ 500 ሺሕ፣ ለ2ኛ አሸናፊ 400 ሺሕ፣ ለ3ኛ አሸናፊ 300 ሺሕ፣ ለ4ኛ አሸናፊ 200 ሺሕ፣ ለ5ኛ አሸናፊ 150 ሺሕ እንዲሁም ከ6 እስከ 10ኛ ላሉ አሸናፊዎች 100 ሺሕ ብር ይሸለማሉ።
በመግጫው የተገኘው እናት ባንክ በበኩሉ፣ ለአሸነፉበት ሴቶች ቴክኖሎጂ ተግባራዊነት የሚያስፈልገውን የገንዘብ ብድር እንደሚያመቻች ገልጿል።
ምዝገባው መቼ ተጀምሮ ? መቼ ይጠናቀቃል ?
ምዝገባው ከዛሬ (ሰኞ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ/ም ጅምሮ እስከ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ/ም ደረስ እንደሚከናወን ተነግሯል።
ለተወዳዳሪዎች የቡት ካምፕ ስልጠና ከመጋቢት 8 እስከ መጋቢት 19/2017 ዓ/ም እንደሚሰጥ እና የውድድሩ ማጠቃለያና ሽልማት መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ/ም እንደሚሆን የተመላከተ ሲሆን፣ ለተጨማሪ መረጃ 0948874085፣ 0913154944 መደወል ይቻላል ተብሏል።
#ThikvahEthiopiaFamilyAA
@thikvahethiopia