✅ከቤት እንስሳቶች ሁሉ ከውሻ ቀጥሎ አስተዋይ ጭንቅላት ያላት እንስሳ አህያ ናት፡፡
✅ ከእንስሳቶች ሁሉ አቅጣጫን እና መንገድን በመለየት እና ፈጥኖ በመረዳት የምትበልጠው አህያ እንደሆነች ያውቃሉን?
🔇 ከቤት እንስሳቶች ሁሉ ራስዋን በራስዋ በመምራት እና በማስተዳደር የምትበልጠው አህያ እንደሆነች ያውቃሉን?
✅ አህያ አንድ ጊዜ ያየችውን ወይም የሄደችበትን መንገድ በጭራሽ አትረሳም፡፡
✅ አህያ ወደ ፊት እያነጣጠረች የኋላዋን ኮቴ ጥርት አድርጋ ማየት ትችላለች፡፡
✅ አህያ በአመድ ላይ የምትንከባለለው በተፈጥሮ የሰርከስ አይነት ስፖርት ስለምትወድ ነው፡፡
✅ አህያ የመሬት መንቀትቀጥ አደጋ ከመድረሱ በፊት በትክክል ምልክት መስጠት እና ቅድመ ጥንቃቄ ጩኸት በማሰማት የሰው ልጆችን ታገለግላለች ወይንም ትታደጋለች፡፡
✅ከቤት እንስሳት ሁሉ አህያ የምትጠላው ቢኖር ውሻን ነው፡፡ ይህ የአህያ እና ውሻ ጥል የተጀመረው ግን ሁለቱም የቤት እንስሳ ከመሆናቸው በፊት በጫካ እያሉ ነው፡፡
🔇በጫካ ውስጥ ልክ እንደ ጅብ አህያን ሲያስቸግራት የነበረው ውሻ ነበር፡፡ ዱር በቃን ብለው ሁለቱን የቤት እንስሳ ከሆኑ በኋላ አህያ ቂምን ለልጅ ልጆችዋ ስታስተላልፍ ውሻ ግን ይህንን መረጃ ለትውልዱ አላስተላለፈም፡፡ ስለዚህ አሁንም ድረስ አህያ ቢቸግራት እና አማራጭ ቢጠፋ እንጂ ውሻ በሌለበት መንደር ብትኖር ደስ ይላታል፡፡
✅ በጣም ጨዋ ከሚባሉ ፍትረታት ውስጥ ዶልፊን፣ ጋ'ንዳ፣ ፈረስ፣ እርግብ እና አህያ ዋንኞቹ ናቸው፡፡
✅አህያ በተፈጥሮ እርጋታን እንጂ ሩጫ አትወድም፡፡ አንዲት አህያ ድንገት መሮጥ ከጀመረች አንዳች ትልቅ ችግር በአካባቢው ውስጥ አለ ማለት ነው፡፡
''ልናከብራት የሚገባ የቤት እንስሳ አህያ❗️''
ካነበብነው🙏