አንዳንዴ (@rremedan) के नवीनतम पोस्ट टेलीग्राम पर

አንዳንዴ टेलीग्राम पोस्ट

አንዳንዴ
አንዳንዴ የባጢል ሰዎች ወይም ቡድኖች የምናጋልጥበትና የተለያዩ ሙሀደራዎች፣ ደርሶች፣ አስተማሪ ጹሁፎች የሚተላለፍበት ቻናል
1,772 सदस्य
734 तस्वीरें
94 वीडियो
अंतिम अपडेट 01.03.2025 11:37

አንዳንዴ द्वारा टेलीग्राम पर साझा की गई नवीनतम सामग्री


ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡
https://t.me/husu_Neg

አንድ ክርስቲያን ልጅ እስልምናን ተቀብሏል
ከብዙ ጥያቄ እና ከብዙ መማማር በኋላ እስልምናን ሳይቀበል በፊት ቁርአንን አሳምሮ የሚቀራዉ ዳጊ የነበረዉ ኻሊድ እስልምናን ተቀብሏል። ለአለማቱ ጌታ ምስጋና ይገባዉ
!!

አዲስ ወሳኝ ሙሀዶራ‼️
---------------------

«የአክፍሮት ሐይሎች ዘመቻ»
---------------------------

👉አደራ በደንብ ይደመጥና ሸር ይደረግ ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

👉ብዙወችቻችን እንደ ቀላል እያየነው ህዝባችን በጠላት እየተበላ ነው በተለይ የቀድሞው ደቡብ ክልል አብዛኛው ቦታ በሚሽነሪወችና በመንግስት ድጋፍም ጭምር ታግዞ እስልምናን ለማጥፋት ሰፊ በጀት ተመድቦ እየተሰራበት ነው እንንቃ!!

⭕️በሸዕባን 22 /1446 ھ በወንድም ኑረዲን ቻናል የተደረገ ወሳኝ ማስታወሻ ይደመጥና ይሰራጭ ሐያ....!!

🎙ዑስታዝ አብደ-ናስር መኑር ሀፊዞሁሏህ

http://t.me/+eWy4dgKs3GZkODA0

ኒቃብ (አይነ ርግብ) መልበስ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነው
~
ብዙ ክርስቲያኖች የሙስሊም ሴቶችን አለባበስ (በተለይም ኒቃብን) የዐረብ ባህል እያሉ ሲተቹ ይሰማሉ። በመሰረቱ የፈረንጅ ባህል ተከትለው ሴቶች ከሚራቆቱበት ባህል የዐረብ ባህል ቢሆን እንኳ ግብረ ገብነትን የሚጠቁመው አለባበስ የተሻለ ስርአት ያለው እንደሆነ ግልፅ ነው። ዛሬ የማርያም ምስል ነው ብለው ክርስቲያኖች በሚገልፁት ምስል ላይ ያለው አለባበስ ሙስሊሞች ዘንድ እንጂ ክርስቲያኖች ዘንድ የለም። ለምን የሚለውን ክርስቲያኖች ራሳቸውን ቢጠይቁ መልካም ነው።
ከአለባበስ ጋር ተያይዞ ሙስሊሞች የሚያራምዷቸው መርሆዎች - ፊት መሸፈንን ጨምሮ - በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ እንደሆኑ ክርስቲያኖች ሊያውቁ ይገባል። ብዙ ክርስቲያኖች ለመፅሀፋቸው ባይተዋር ስለሆኑ ጥቂት ምሳሌዎችን እጠቅሳለሁ፦

1- በኢስላም በሴት የሚመሳሰል ወንድ እና በወንድ የምትመሳሰል ሴት የተረገሙ ናቸው። መፅሀፍ ቅዱስስ ምን ይላል?
"ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፥ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ። ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።" [ኦሪት ዘዳግም 22፥5]

2- ሴት ፀጉሯን እንድትሸፍን ኢስላም በጥብቅ ያዛል። መፅሀፍ ቅዱስስ ምን ይላል? ይሄውና :- "ሴትም ራስዋን ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።" [1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 6]

3- ሴት ፊቷን መሸፈኗ በኢስላም ከጥንት ጀምሮ የነበረ ሐቅ ነው። በመፅሀፍ ቅዱስስ የለም? በሚገባ አለ። ይሄውና፦

* "ርብቃም ዓይኖችዋን አቀናች፥ ይስሐቅንም አየች፥ ከግመልም ወረደች። ሎሌውንም፦ ሊገናኘን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማን ነው? አለችው። ሎሌውም፦ እርሱ ጌታዬ ነው አላት እርስዋም መሸፈኛ ወስዳ #ተከናነበች።" [ዘፍጥረት 24፣ 64- 65]

* "በአይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጭሽን እንደተከፈለ ሮማን ናቸው።" [መሀልየ ዘሰለሞን 6፡7]
ልብ በሉ! አይነ ርግብ ማለት ኒቃብ ወይም የፊት መሸፈኛ ነው።

* "ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ መቱኝ፥ አቆሰሉኝም ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት።" መሀልየ ዘሠለሞን 5፡6]

* "በአይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ አይኖችሽ እንደርግብ ናቸው።" [መሀልየ ዘሠለሞን 4፡1]

ስለዚህ ሙስሊም ሴቶች እየተገበሩት ያሉት በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝን እውነት ነው ማለት ነው። ለምንድነው ታዲያ ይሄ ጉዳይ ክርስቲያኖችን የሚያበሳጨው? ከሙስሊም ሴቶች ጎን መቆም ሲገባ ጭራሽ ማንገላታትና ከትምህርት ገበታ ማራቅ ፈፅሞ የማይገባ ነውረኛ ተግባር ነው።
ደግሞም እወቁ! ብዙ ጭቆናዎች በሂደት እንደተቀየሩት ይሄም ያለ ጥርጥር ዛሬ ወይም ነገ ይቀየራል። ለትውልድ የሚቀረው የናንተ የጭቆና ታሪክ ነው። በታሪክ ጥቁር መዝገብ ላይ ስማችሁ እንዲቀር ነው የምትፈልጉት? ቆም ብላችሁ ደጋግማችሁ አስቡበት።

* ባያያዝኩት ምስል ላይ ፊታቸውን ሸፍነው የሚታዩት ሙስሊሞች አይደሉም። ይልቁንም አይሁዶች ናቸው። የሙስሊም ሲሆን ሁሉ ነገር ለሚያስጨንቃቸው አካላት ማስታገሻ ይሆናል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

♥️السلام عليكم ورحمة الله وبركاته♥️

🌙ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም🌙

♥️የፊታችን እሁድ ሸዕባን 24 [የካቲት 16] በአሏህ ፈቃድ በዘህራ መስጂድ ውስጥ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም ይቀርባል።

💡ተጋባዥ ኡስታዞች፡

♥️ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
♥️ኡስታዝ አቡል ዐባስና ሌሎችም።

⏰️ፕሮግራሙ ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት እስከ ዙሁር ድረስ የሚቀርብ ሲሆን ለሴቶች በቂ ቦታ ተዘጋጅቷል።

📍አድራሻ፡- ሸገር ሲቲ አሸዋ ሜዳ፡ ሻቃ ሞል ጀርባ አሸዋ ሜዳ ኮንዶሚኒየም አካባቢ።

✔️በአካል መገኘት ለማይችሉ ዝግጅቱ በ https://t.me/abufurat ቻናል በቀጥታ ይተላለፋል።

✔️በተውሂድ በሱናና በሰለፎች መንገድ የታነፀ ማህበረሰብን እንፍጠር⚡️

ዘህራ መስጂድና መድረሳ

📚መልዕክቱን ሼር በማድረግ እንተባበር፡ ባረከሏሁ ፊኩም።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

አሰላሙዓለይኩም ኡስታዝ እንዴት ነህ

ከሶስት ወር በፊት ወደ ባንክ አካውንቴ በርከት ያለ ገንዘብ ስለገባ እና ባንክ ሂጄ ባናገራቸውም የግል መረጃ አንሰጥም ብለው ስለመለሱኝ የእኔ ነው የሚል አካል ካለ በዚህ ስልክ ቁጥር +251935270496 ላይ ይደውልልኝ።

ይህን አድርስልኝ፣ ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኝ ነው። ጀዛከሏሁ ኸይረን

የሙመይዕ (አቅላጭ) ትርጉም በባህሩ

ባህሩ ባሰፈረው ማብራሪያ መሰረት
- ሰለፊያ መንሓጅ ሁሉን አቀፍ ነው ካልን በዐቂዳም በመንሓጅም እንጂ የቢድዓ ሰዎችም የሚካተቱበት ነው በፍፁም አንልም!
- ሰለፎች የማያውቁት መንሓጅ (ዐቂዳ) የለንም!
- እኛ ኢኽዋኖች ጠማማ መሆናቸውን በግልፅ እንናገራለን።
- ሰዎች በኢኽዋኖች ብሎም በየትኛው ከሱና ባፈነገጠ ቡድን ጥመት እንዲጠራጠሩ አናደርግም ይልቁንም እርግጠኞች እንዲሆኑና ዐቂዳቸውን እንዲጠብቁ እናስተምራለን።
- አዎን እናንተን "አታጥብቁ" ልንል እንችላለን አታጥቡ የምንለው ዲኑ ባለጠበቀው ነገር አታጥብቁ ዲናችን በአጠበቀው ነገር ላይ እንድታጠብቁ እንመክራለን።
ለምሳሌ ኢጅቲሐድ በሚያስተናግድ ጉዳይ ላይ በፎቶም ይሁን በጀርህ ወት'ተዕዲል መጥበቅ በሌለበት ቦታ አታጥብቁ እናላለን! አስተውሉ በኢጅቲሓድ ርዕስ ነው ያልኩትኝ።

https://t.me/Menhaje_Selef/

ምስክር አይቀርብብኝም፣ ሰዎች አይነቁብኝም ብለህ የሰዎችን ሐቅ አትዳፈር። ነገ ያለ ምስክር ሁሉን ከሚያውቀው ጌታ ፊት ትቆማለህ።
=
https://t.me/IbnuMunewor

ሰሞኑ በድብቅ የተቀዳዉ ከ6 ሰአት በላይ የፈጀ ሪከርድ ማን ነዉ አቋሙ የቀየረዉ በሚል መፖሰታችን ይታወቃል ነገር ግን ከብዙ እህት ወንድሞች ይሄ ሁሉ ማን ይሰማል ዋናዉ ቁም ነገሩ ማለትም ኢብኑ መስኡዶች ሙብተዲእ ናቸዉ አይደሉም የሚለዉ ጉዳይ እኛን አያጣላም ያሉበት ቆርጠህ አስቀምጥ ባላችሁት መሰረት

https://t.me/Rremedan/3211

ሙሉዉን ለማዳመጥ

https://t.me/Rremedan/3202

ምን ያህል ወንጀል እንደሰራሁ ከአሏህ የበለጠ አታውቅም ። አንተ የምታውቀው እጅግ ትንሿን ጉድለቴን ነው አሏህ ግን ገመናዬን በሙሉ ያውቃል ። ከመሆኑም ጋር ጌታዬ እንዲህ ይለኛል ።

قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَى أَنْفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِنْ رَحْمَةِ اللَّهِ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ

በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡
( ሱረቱ ዙመር 53 )

አንተስ ?
አንተማ የሆነች ውድቀት አልያም ስህተት የመሰለችን ነገር ያየህብኝ ጊዜ ብዙ አድማጭ እንዲኖርህ የአደጋ ጊዜ ጩኸት እያሰማህ በሰዎች መሃል ነውሬን ለመበተን ትኳትናለህ ። ልትጠየፈኝና ልታንቋሽሸኝም ይዳዳሃል ። ደግነቱ ጌታዬ ፍርድን በአንተ እጅ አላደረገም ።

ጌታችን እንዴት ያለ ቸርና አዛኝ ሆነ ፥ በተቃራኒው እኛ ባሮቹ ደግሞ ክፉ ...

https://t.me/Abusalahtube1