Последние посты አንዳንዴ (@rremedan) в Telegram

Посты канала አንዳንዴ

አንዳንዴ
አንዳንዴ የባጢል ሰዎች ወይም ቡድኖች የምናጋልጥበትና የተለያዩ ሙሀደራዎች፣ ደርሶች፣ አስተማሪ ጹሁፎች የሚተላለፍበት ቻናል
1,772 подписчиков
734 фото
94 видео
Последнее обновление 01.03.2025 11:37

Последний контент, опубликованный в አንዳንዴ на Telegram


ፆም የሚያበላሹ ነገሮች
~
1- የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም፣
2- የዘር ፈሳሽን ሆን ብሎ ማውጣት፣
3- መብላትና መጠጣት፣
4- በአፍ መድሃኒት መዋጥ፣
5- ሲጋራና መሰል ነገሮችን ማጨስ፣
6- የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም መምጣት፣
7- ፆምን የማቋረጥ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ መድረስ (ባይበላም ባይጠጣም)

እነዚህ ነገሮችን ፆምን የሚያበላሹት የሚያፈርሱ እንደሆነ እያወቀ፣ አስታውሶ እና በምርጫው በቀኑ ክፍለ ጊዜ ከፈፀማቸው ነው።
* የሚያፈርሱ መሆናቸውን ሳያውቅ ቢፈፅም ፆሙ አይበላሽም። ልክ እንደዚሁ ያልነጋ መስሎት ወይም ፀሐይ የገባ መስሎት ቢፈፅምም ፆሙ አይበላሻም።
* የሚያፈርሱ መሆናቸውን እያወቀ ነገር ግን ረስቶ ቢፈፅም ፆሙ አይበላሽም።
* የሚያፈርሱ መሆናቸውን እየወቀ ግን ተገዶ ቢፈፅም ፆሙ አይበላሽም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

አልሐምዱ ሊላህ! ሸዕባን አጠናቀናል። ቅዳሜ ረመዷን 1 ነው። ምሽቱን ተራዊሕ እንጀምራለን።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

*️⃣*️⃣*️⃣ኢንሻ አላህ *️⃣*️⃣*️⃣

እሁድ ከጠዋቱ 3 ሰኣት ጀምሮ እስከ ዙሁር በሑዘይፋ መስጂድ የዳእዋ ፕሮግራም ይኖራል።

ፕሮግራም አቅራቢዎች

1️⃣🔁ኢብኑ ሙነወር፣

2️⃣🔁አቡ ኡስዋ፣

3️⃣🔁ሳዳት ከማል፣

4️⃣🔁አብዱ ሰኢድ፣

5️⃣🔁አማር በህረዲን።

ፕሮግራሙ ከሚያካትታቸው ትምህርቶች ውስጥ

1️⃣🔤ቁርኣንን በጥሞና ማዳመጥ፣

2️⃣🔤አቀራራችን ማስተካከል፣

3️⃣🔤የተመረጡ ምእራፎች የቁርአን ትርጉም፣

4️⃣🔤ዳእዋ እና ሌሎችም

ለሴቶች በቂ ቦታ አለ።
🚘🚘🚘🚘🚘🚘🚘🚘
አድራሻ ሸገር ሲቲ ከየሺ ደበሌ ከፍ ብሎ።
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem

በያካባቢያችሁ ያሉ አቅመ ደካማ መሻይኾችን፣ ዱዓቶችን፣ የቁርኣን አስተማሪዎችን፣ የመስጂድ ኢማሞችን፣ ሙአዚኖችን፣ በዒልም ፍለጋ ላይ የተሰማሩ ደረሶችን፣ ... ብትችሉ አስተባብራችሁ፣ እሱ ባይሆን የአቅማችሁን በራሳችሁ ማገዝን አትርሱ። "እንዴት እየኖሩ ይሆን?" ብላችሁ አስቡ። ኑሯቸውን ደጉሙ። ኪታብ ግዙላቸው። ከጎናቸው ቁሙ። እነዚህን ማገዝ ዲንን ማገዝ ነው።

በተለይ በተለይ የመስጂድ ኮሚቴዎች በዚህ ረገድ ሃላፊነታችሁን ተወጡ። ነጋዴዎች ጓደኞቻችሁን አስተባብሩ። ሌሎችም እንዲሁ አላህ የገራላችሁን ያህል ሳትሰስቱ በየ ሰፈሩ ላሉ አቅመ ደካሞች አድርጉ። ነብዩ ﷺ “ከሰው ሁሉ በላጩ ለሰዎች ይበልጥ ጠቃሚ የሆነው ነው” ይላሉ። [አሶሒሐህ፡ 426] በደዕዋ ላይ የተሰማሩ አካላትን ማገዝ ሲሆን ደግሞ ዋጋው ይለያል።

"ሼር" አድርጉ፣ ባረከላሁ ፊኩም። ምናልባት ለሆነ አካል መታገዝ ሰበብ ትሆኑ ይሆናል።
الدَّالُّ عَلَى الْخَيْرِ كَفَاعِلِه
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

🔖 አዲስ ሙሓደራ

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
🔗የካቲት 17/2017 ዓ.ል
🔗 شعبان ١٤٤٦/٢٥ه‍
https://t.me/IbnuMunewor

መኖርህ እዳ አይሁን!
ላንተ ነው! “ቀለም ለገባህ”!
~
1. አንተ ልዩ አይደለህም!

ሙስሊሙ፤ እንደ ማህበረሰብ ሰቅዘው የያዙት ብዙ አይይነት ችግሮች እንዳሉበት ግልፅ ነው። በኛ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አለማት ኢኮኖሚው የደቀቀ፣ ማህበራዊ ህይወቱ የተናጋ፣ ፖለቲካዊ ስርኣቱና ሚናው የወረደ፣... ብዙ ሙስሊም ማህበረሰብ አለ። ችግሩን ‘ፍሬም’ በማድረግና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ላይ ሃሳቦች ሊለያዩ ቢችሉም ይህን እውነታ በመረዳት አንተ ብቸኛ አይደለህም። እራስህን ከማህበረሰቡ አንዱ እንጂ ልዩ አድርገህ አትሳል። ሙስሊሙ ኡማ ውስጥ የተማረው የቀለለ ከመሆኑ ጋር የተማርከውን የተማሩ፣ የምትረዳውን የሚረዱ ብዙ እንዳሉ አትዘንጋ። ይህንን እውነት ለነፍስህ ሹክ በላት። “ብርቅየ አይደለሽም” በላት። ያኔ እብጠቷ ይተነፍሳል። መንጠራራቷ ይቀንሳል።

2. የደዕዋው ዘርፍ የመፍትሄዎቻችን ሁሉ እናት ነው!

ቀዳዳዎቻችን ብዙ ናቸው። በዚያው መጠን ዘርፈ ብዙ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ያስፈልጉናል። በሆነች ዘርፍ ላይ ትንሽ አስተዋፅኦ ስለኖረችህ ለሌሎች በተለይም ለደዕዋው ዘርፍ ያለህ እይታ አይንሸዋረር። ለደዕዋው ዘርፍ ያለህ አክብሮት ለኢስላምህ ያለህ አክብሮት ነው። የደዕዋውን ዘርፍ ሳታከብር ለኢስላም አክብሮት ሊኖርህ አይቻልም። ኢስላም ያለ ደዕዋ ምንም ነው። አዎ በደዕዋው ዘርፍ ላይ ብዙ ችግሮች አሉ። ግና “ችግሩ የሚፈታው በማነው?” ብለህ እራስህን ጠይቅ። አንተ ለዚህ ብቃቱ አለህ? የተማርከው ትምህርት ለዚህ የሚያበቃህ ነው? የእውነት አካደሚ ስለተማርክ ብቻ ያለውን መሰረታዊ ችግር የምታውቀው ይመስልሃል? እንዴት ሆኖ?!

3. አንጃዎችን መኮነን ከአንጃ ውጭ አያደርግህም!

ብዙ የተማሩ ወንድሞች አንጃዎችን ስላወገዙ ብቻ ገለልተኛ የሚሆኑ ይመስላቸዋል። ነገሮችን በዚህ መጠን መረዳት ሲበዛ ግልብነት ነው። በቅድሚያ ገለልተኝነትህ ከሐቅም ሊሆን ስለሚችል ጉዳዩን ከልብ መርምር። ጉዳዩን ቀርበው ሳይመረምሩ ሁሉንም በጭፍንና በጅምላ ማውገዝ በስንፍና ውስጥ ማድፈጥ እንጂ ልዩነትን መፀየፍ አይደለም። ይህንን ለማድረግ አቅምና ፍላጎቱ ከሌለህ ዝምታን ማን ያዘብህ? ምላስህንም ብእርህንም ከንዲህ አይነቱ ጉዳይ ሰብስበህ በምትችለው ሙያ ወገንህን አገልግል። በአደብህ ተከበር። የማትችለውን ገብቼ አቦካለሁ ስትል፣ በምትችለው ዘርፍ ልታበረክተው የምትችለውን አስተዋፅኦ ታመነምነዋለህ።
ልንገርህ ወዳጄ! የሆኑ የሚፋጩ አካላትን ስላየህ፣ የሚወረወሯቸውን ቃላት ስለሰማህ ብቻ ስለጉዳዩ ያለህን መረዳት በዚያ መጠን አቅልለህ አትመልከት። እንዲህ አይነቱ ጥራዝ ነጠቅ ድምዳሜ ነው አንዳንዶችን በመሰረታዊ የኢስላም ክፍል ላይ እንዲሳለቁ እየገፋቸው ያለው። ሳይረዱ እንደተረዱ ማሰብ።
እንዲያውም የአንዳንዶቹ ገለልተኝነት ከማስመሰል የዘለለ አይደለም። ክስተቶችን እየጠበቁ ለይተው ሲያጠቁ፣ ለይተው ደግሞ ሲያደንቁ ታገኛቸዋለህ። “የአይነላህ ተቆርቋሪዎች” እያለ በነብዩ ﷺ ሐዲሥ ላይ የሚያሾፍ ሰው፣ “ተው” እና “ሂድ” እያለ በተውሒድ ላይ የሚሳለቅ ሰው በየትኛው ሞራሉ ነው ስለ ገለልተኝነት የሚያደነቁረን? ለኡማው መትረፉ ቀርቶ እራሱን ባዳነ!

4. ይልቅ ለኡማው ሸክም አትሁን!

እራስህን ብቻ ሁን! ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም። ማኔጅመንት ወይም ፖለቲካ ተምረህ የደዕዋ ስልጠና ካልሰጠሁ አትበል። በዱዓት ላይ መዘባነንህን አቁም። ፖለቲካ ብትደሰኩርም፣ ታሪክ ብትተርክም፣ መድረክ ብታደምቅም ዋጋ የሚኖረው ለተውሒድ በሚኖርህ ክብር ነው። አክብሮቱ ቀርቶ ሸክም የምትሆን ከሆነ የትኛውም ያንተ አበርክቶ ገለባ ነው። ተውሒድና ሺርክን የማትለይ፣ በተውሒድ ላይ እየተሳለቅክ ለቀብር አምልኮ የምትወግን ከሆነ፣ ወይም ደግሞ በገለልተኝነት ስም ተውሒድንም ሺርክንም እኩል የምታወግዝ ከሆነ እውነቴን ነው የምልህ ከመኖርህ አለመኖርህ የሚሻል ለመባል እንኳን አትመጥንም። እንዲያውም ለሙስሊሙ ኡማ ከጠላት የከፋ እዳ ነህ።

5. ከ“ንቃትህ” ንቃ!

መንቃት ማለት እንግሊዝኛ እየቀላቀሉ ማውራት አይደለም። መንቃት ማለት በግምት የታጨቀ የሴራ ፖለቲካ መፈትፈት አይደለም። መንቃት ማለት የራስን እያናናቁ በፈረንጅ ፍልስፍና ላይ መራቀቅ አይደለም። መንቃት እራስን ማወቅ ነው። መንቃት የማህበረሰብን መሰረታዊ ችግር መለየት ነው። ተውሒድና ሺርክን የማትለይ፣ የወገንህ የሙታን አምልኮ ላይ መነከር የማይቆጠቁጥህ ከሆነ እንኳን ለሰው ልትተርፍ ለራስህ አንቂ ያስፈልግሃል።
ደግሞም እወቅ! ይሄ ሌሎችን ማናናቅና እራስን መቆለል የጀርባ መንሴው ለዘመናዊ ትምህርት ያለህን የተንሸዋረረ እይታ ነው የሚያጋልጠው። ትምህርቱ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያከራክር አይደለም። ህዝበ ሙስሊሙ ባለመማሩ የደረሰብት ውስብስብ ችግር እንዳለ የሚዘነጋ አይደለም። ቢሆንም በልክ አድርገው። የቀለም ትምህርት ከዲን ትምህርት፣ እንግሊዝኛ ከዐረብኛ፣ የነ ዑመር፣ የነ ሙዓዊያ ታሪክ፣ ከነ ሶቅራጠስ ሊነፃፀር አይችልም። በቅድሚያ እራስህን ከአስተሳሰብ ተፅእኖ ነፃ አውጣ! እነ ፍሮይድና ማስሎውን እያደነቅክ ዑለማዎችን የምትንቅ ከሆነ ብሽቅነትህን ብቻ ነው የምታሳየው። “የፋርስና የሮማ ፈላስፎች ጥበብ ላይ የሚያተኩር ለኢስላማዊ ጥበብና ስርኣት ልቡ ውስጥ ቦታ አይኖርም” ይላሉ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ። [አልኢቅቲዷእ፡ 217]

6. ሚናህን ለይ!

ዱዓት መሃል ብዙ ችግሮች እንዳሉ የሚታወቅ ነው። የምታየው ቢያምህ ሰውኛ ስሜት ነው። ሃሳብ ካለህ ዲኑ ያንተም ነውና እርምትና ሃሳብ መስጠት ያባት ነው። ችግር የሚመጣው ያልገባህን እያወራህ የእብድ ገላጋይ ስትሆን ነው። ወይ ዲንህን ተማር! ወይ ሃሳብህ የተመጠነ ይሁን። ባቅምህ ልክ ብቻ አውራ። ቀይ መስመር አትለፍ። ማኔጅመንት ተምረህ ቀዶ ጥገና ህክምና ካላደረግኩ ትላለህ እንዴ? ሳይኮሎጂ ላይ እድሜህን ፈጅተህ ተፍሲር ካላስተማርኩ ይባላል ወይ? ልክ ሃያ ሰላሳ አመት እድሜህን የቀለም ትምህርት ላይ ስለፈጀህ ብቻ ይሄ ነው የሚባል ትኩረት ባልሰጠኸው እምነት ላይ ፈራጅ ቀዳጅ ካልሆንኩ አይባልም። በቃ አቅምህንና ተሰጥኦህን ለይ! የግድ ስለ ሁሉም ማውራት አይጠበቅብህም።

7. ስለ ዲንህ ተማር

በቀለም ትምህርት ላይ መራቀቅ እንደምትሻው ሁሉ ለዲናዊ ትምህርትም ጊዜ ስጥ። ከምንም በላይ የዚያኛውን አለም ስንቅ ታዘጋጅበታለህ። በመተጓዳኝ የራስህን ጨምሮ የወገንህን ችግርና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ትለይበታለህ። በርግጠኝነት ነገሮችን የምትመለከትበት መነፅርም ይቀየራል።
በተለይም ደግሞ መሰረታዊ የእምነትህን ክፍል ተውሒድን ተማር። አካደሚ ስለተማክ ብቻ ከሺርክ የምትርቅ ከመሰለህ ሞኝ ነህ ወላህ! በአለም ላይ ቁራጥራጭ እንጨቶችን፣ ያሸበረቁ ስዕሎችን፣ ላሞችን፣ አይጦችን፣ በሰው ልጅ ብልት አምሳል የተቀረፁ ሀውልቶችን የሚያመልኩ ህልቆ መሳፍርት ዶክተሮች፣ ፕሮፌሰሮች አሉ። የተማሩት ትምህርት፣ የሚቀናጡበት ቴክኖሎጂ፣ የተቆናጠጡት ስልጣን፣ የሚያጋብሱት ሀብት ግኡዛንና እንስሳትን ከማምለክ አላወጣቸውም። ብልህ በሌሎች ይማራል። ሞኝ በራሱ ላይ በሚደርሰው ይማራል። አንተ ከሁለቱም ተራ ወጥተህ ሳይማሩ የተማሩ ከሚመስላቸው አትሁን።

ደግሞም ልንገርህ! አካደሚ እውቀት ቀርቶ ሌሎች የሸሪዐ ዘርፎች እንኳ ዋጋ ይኖራቸው ዘንድ ተውሒድ ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው። ሸምሰዲን አሰፋሪኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ “ሌሎች የእውቀት ዘርፎች ለተውሒድ እውቀት ቅርንጫፎች ናቸው። ምክንያቱም እሱ ከአምልኮቶች ሁሉ የላቀው፣ ከትእዛዛት ሁሉ በላጩ እንዲሁም እያንዳንዱ አምልኮትና ትእዛዝ፣ ጤናማ ይሆን ዘንድ ብሎም ዋጋ ይኖረው ዘንድ መስፈርቱ ነውና። የክብርና የልቅና ባለቤት የሆነው (ጌታ ምንነት) የሚታወቅበትም ነውና።” [ለዋሚዑል አንዋሪል በሂያ፡ 1/57]
ስለዚህ በቅድሚያ ለራስህ ሁን! ለራስህ ሳትሆን ለህዝብ አትሆንም። ያለበለዚያ አስር ገንብተህ ሺ ታፈርሳለህ። ምንም ላይ ሳትሆን ትልቅ ነገር ላይ ያለህ ይመስልሃል። በተውሒድ የምትሳለቅ፣ ለቀብር አምልኮ የምትወግን ከሆንክ የታሪክም ሆነ የፖለቲካ አስተዋፆህ የዜሮ ብዜት ነው የሚሆነው። አልዓስ ብኑ ዋኢል በጃሂሊያ መቶ ግመል ሊያርድ ስለት ተስሎ ነበር። ስለቱን ሳይፈፅም ስለሞተ ልጁ ሂሻም ሃምሳ ግመል አረደለት። ሌላኛው ልጅ ዓምር ግን የድርሻውን ከማረዱ በፊት የአላህ መልእክተኛን ﷺ ስለ ጉዳዩ ቢጠይቅ {አባትህማ ተውሒድን ቢቀበል ኖሮ ብትፆምለት ብትሰድቅለት ይጠቅመው ነበር} ነው ያሉት። [አሶሒሐህ፡ 1/180] ሰላም!

(ኢብኑ ሙነወር፣ የካቲት 19/2014)
=
https://t.me/IbnuMunewor

45 ደቂቃ ቀርተዉታል ያልገባችሁ ገብታችሁ አድ አርጉ ባረከላሁፊክ

📣📣ታላቅ  የውይይት  ፕሮግራም

አሰላሙዓለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱ!

🔊እነሁ  ዛሬ  ማክሰኞ  ከምሽቱ 🕒 3:00 ላይ  ታ'ላ'ቅ  የውይይት  ፕሮግራም አዘጋጅተን  ስንጠራዎት  በደስታ  ነው።

🟪የዉይይቱ አጀዳ የሚሆነው፦
የአክፍሮት ሀይላት  እንቅስቃሴ  ምን ይመስላል? በሚለው ይሆናል።

እነሆ ተጋባዥ  እንግዶቻችን  የሚሆኑት፦
ከኡስታዞች 
ከጂንካ ተወላጆች
ከወላይታ
ከጉራጌ  እንዲሁ  ከተለያየ ቦታ  ጥሪ የተደረገላቸው  ወንድሞች  ይታደማሉ ተብሎ  ይጠበቃል።

👈እርሶም  በዚህ  ታላቅ ታሪካዊ ቀን  ሁላቹሁም  እንድትገኝሉን ስንል ጥሪያችን  እናስተላልፍለን።

▶️አዘጋጅ፦
"እነሞር ላይ  ማክፈር ይብቃ"   አባላት።

👌ሼርር  ጆይይን  አድ አድ 
https://t.me/twhidsun
https://t.me/twhidsun

ዛሬ እሁድ ሸዕባን 25/1446 (የካቲት 16/2017)
አሸዋ ሜዳ ዘህራእ መስጂድ የቀረበ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor