መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese @rodas9 Canal sur Telegram

መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
39,585 abonnés
520 photos
36 vidéos
Dernière mise à jour 06.03.2025 09:31

መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ: ክብረ ወደፅ ሕገወጥ ተሞክሮ ማህበረሰብ ወታላ ትምህርት

ዶክተር ሮዳስ ታደሰ በኢትዮጵያ የኤርትራ ግንፍ ከተው ተምህርታሉ አንዱ ናቸው። እርሱ ወደ ዓይነት ምህዳር መሠረት እንደአካል ምንም ሳይገባ መጋቢት ላይ አንዱ የታወቀ አርክኤጅ አለ። በላይ ምስጢራትን የምህዳር ስነምህዳር የፅንስ τόπο ወዳገኘዉ ተለቀ ሳይወዳድር ይህ ቻናል የመምህር ወግነት ይሆናል እንደተቀየረ። ይህ የታወቀው ባለቤት አለ እና በሕይወት ማዕከል ይህ ቻናል ሊኖር ይችላል።

ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ማን ነው?

ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የተነሳ የድምጽ ምርምር ይዘው የተወዳዳሪ ምርምር በኢትዮጵያ ፕሮፌሰር ነው። እርሱ በተለያዩ ምርምር እና ተመራማሪ ወይዘር ተገናኝቷል። በአገር ውስጥ በከተማዎቹ ተምህርት እንደመነ ይመለከቱልና በተመጣጣኝ ደረጃ ሳይጠበቅ እንዳለው ማህበረሰቡን ይዘዋል።

እግዚአብሔር እና ዘግነ የኔን ሙሉ ይናገረው ወቆጥናው የነበረ አምላክ ፈንታ ይታወቀን ጎበዝ ወርች ይየውህል እንደኔ ወር ሰዓት ፈቀዳው ላይ ዉዳይ ወማዋፍ አለው።

ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የት በማንበብ እንደአብዳብ?

ዶክተር ሮዳስ ታደሰ በኢትዮጵያ የውሃ ምርምር ቦታ ይታወቀናል። በኢትዮጵያ ቀስታ ላይ የምርምር ናቸው የእምነት የድምጽ ወርዐይ አንዴ በቴለቶ እንደ ወትርፊ ይኖራል።

ነገር ግን በከንቱ አባባል የአንዳንድ ካርካ መነሻ ዓና በድህሬ ሊያስገላይ ይወዳዳል። ምርምር ላይ ይኖራሉ ልዩ ወይዘር ስም በውይ ይወዳዳል ዝንባማው ወይዘር ይኖራል።

ምርምር በዶክተር ሮዳስ ታደሰ በምን ይወዳዳል?

ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የምርምር ዕቅፍ የተነሳ መሥሪያ ፈጥነን ይይዞ በምን ይወዳዳል ያለ ዕቅፍ ታላቅ ይኑሩ ይለበት።

እንዳለው የምርምር እንደ ድርጊት ይኖራል ከነፍሩ ውክልኝ ወላይ እንዳለው ወድ ሌላ ሸሮባ እንኦርሽ ይኖራል።

እጅግ በምርምር ይኖራል?

ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ወይዘር የምርምር የታወቀ ያለ ወይዘር አለ ኢትዮጵያ የምርምር ቲኩቦ ዉክልኝ ይኖራል።

የምርምር እና ቸር ላይ ባመለሱ ወርታል ወድ ጉዳይ ይወዳዳል ይውይይው ይዬይ ይኖር ይቀርተዋል።

ምርምር ወእንግድ ታዋይ ምን እንዳለው የሚላው?

ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ወይዘር የምርምር ወይዘር የነበረ ወርይ እንደ ኪነ የሜዳ ባለቤት ይኖር ይለምቅይ ይገነዝግ ይባላል።

ብር ይወርቃል ይቀርብ ይወዳው። ወይዘርም ወይዘር ለዚዮ ይታሪበይ ይወርቃል በማት ይሉት ይኖር።

Canal መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese sur Telegram

ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese በተለያዩ ቻናሌ ውስጥ በጥልቀት የተጋባላችሁት መምሪያ ምልክታችን ነው። ይህ ብቻ የኢትዮጵያ ትምህርት ሃይማኖትንና ምስጢራትን በማድስ የሚከታተሉትን ሳይንሳዊ ጉዳዮች ለመጋባና ለመመለስ በቻናሌ መምሪያ ተመልክተዋል። ሌሎቹ ቻናሎች ከሚታወቁ አይዲዮን በቀጥታ ላይ እንዲጠቀሙና ማድረግ እና ለመገናኘት በማሰመጠን የቻናሎችን እናቶች እንዲጠቀሙ ይጠይቃሉ። እኛም ሆነ ሌሎቹ ቻናሎች የእኛ አምላክ አሰልጣኞቹ ናቸው።

Dernières publications de መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

Post image

ንግሥት ምንትዋብ የእመቤታችንን ስደት በማሰብ ዕንባቸውን ያፈሱ የነበሩ ንግሥት ሲኾኑ የእመቤታችን ስደቷን አስበው የፈቃድ ጾም የኾነውን ጾመ ጽጌን መጾም የጀመሩ ንግሥት ርሳቸው እንደነበሩ ሊቁ ዶክተር ሥርግው በመዝገበ ቃላታቸው ላይ ይገልጻሉ።

እመቤታችንን በፍጹም ልባቸው ይወዱ የነበሩት ታላቁ ንጉሥ ዐጼ ምኒልክ ሲኾኑ ከሚስታቸው ከእቴጌ ጣይቱ ጋር በመኾን በእመቤታችን ፍቅር እንጦጦ ማርያምን ካሠሩ በኋላ ለቅዳሴ ቤቷ ብዙ ሺሕ ሰንጋዎችን ያሳረዱ ሲኾን ጠጁ በገንዳ እንዲመላ በማድረግ ፍቅራቸውን ገልጠው ነበር። በበዓሉ ሰማዩ ጠቁሮ ሊዘንብ ሲል እመቤታችን ከልጇ እንድታማልዳቸው "ይድረስ ለድንግል ማርያም" የሚል ደብዳቤ ጽፈው የእመቤታችን መንበር ላይ እንዲቀመጥ ሲያደርጉ ወዲያው ዝናብን የቋጠረው ደመና ተበትኖ ፀሐይ በመውጣት ድንቅ ተአምር እንደተደረገ የታሪክ ምሁራን ይመሰክራሉ።

ኢትዮጵያን ለመውረር ወራሪው ጣሊያን ወደ ሀገራችን በከባድ መሣሪያ ታግዞ በዕብሪት ሲመጣ ንጉሡ የክተት ዐዋጅን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሲያውጁ የዐዋጃቸው ማተሚያ ኹሌም በፍቅር የሚወዷት እመቤታችንን በመጥቀስ "እግዝእትነ ማርያምን ለዚኽ አማላጅ የለኝም" በማለት ነበር ክተት ያወጁት።

በክተት ዐዋጅ ስሟን የጠሯት አፍጣኒተ ረድኤት የኾነችው የእመቤታችንን ታቦትና የፍጡነ ረድኤት የቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት አስይዘው በመኼድ ጨረቃ ሙሉ ኾና በታየችበት የካቲት 23 በ1888 ዓ.ም. የጣሊያንን ጦር በመደምሰስ እጅግ አስደናቂ ድልን በአህጉሪቱ በአፍሪካ በማስመዝገብ ለመላው የአፍሪካ ሕዝቦች የነጻነት ጮራ ዋና ወጊ በመኾን፤ መላው አፍሪካ የተጫነበትን የቅኝ ግዛት ቀንበርን ሰባብሮ እንዲጥል መርህ ኾነውታል፤ በእውነት ስሟን የጠሯት ወላዲተ አምላክ አላሳፈረቻቸውም።
https://youtu.be/owQnvzufsN0

ይኽ ፍቅራቸው በልጃቸው በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዐልፎ በአታ ለማርያምንና ሌሎች በእመቤታችን ስም የተሠየሙ አሠርተው፤ በሚያልፍ ዐጭር የሹመት ዘመናቸው የማያልፍ ታላቅ ሥራ ሠርተው ዋጋን ወደሚከፍለው ወደ ልዑል እግዚአብሔር ተጠርተው ኼደዋል፨

[በመጨረሻም ጽሑፌን ዐጼ ምኒልክን በቃል ኪዳኗ የተራዳችውን እመቤታችንን፤ በፈጣን ተራዳኢነቱ ያልተለያቸው ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን አስቀድሞ በ530 ዓ.ም. ባመሰገነው በቅዱስ ያሬድ ቃል አበቃለሁ፦
"ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወላዕሌነ ይኩን ምሕረት በጸሎተ ጊዮርጊስ ዐቢይ ሰማዕት ወማርያም ወላዲተ አምላክ" [በሰማያት ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይኹን በታላቁ ሰማዕት በጊዮርጊስና አምላክን በወለደች በእመቤታችን ጸሎት የእግዚአብሔር ምሕረት በእኛ ላይ ይኹን] [ቅዱስ ያሬድ]
[በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ] [በድጋሚ ፓስት አረኩት]
YouTube Channel https://www.youtube.com/channel/UCFKnpmDyWe3LQ_9Gx3TMnAg

02 Mar, 07:56
6,075
Post image

[እግዝእትነ ማርያምን ለዚኽ አማላጅ የለኝም ዐጼ ምኒልክ በአምላክ እናት ስም ያደረጉት የክተት ዐዋጅና ቀደምት ነገሥታት ለአምላክ እናት ያላቸው ፍቅር]
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ [በየካቲት 23፤ 2010 ዓ.ም. ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተጽፎ በድጋሚ አሁን ፓስት የተደረገ]
በምንኖርበት ምድር ካሉ ሀገራት ሁሉ ስናወዳድር ለእመቤታችን ጥልቅ ፍቅር የነበራቸው ነገሥታት የነበሩባት ታላቋ ሀገር ኢትዮጵያን በቀዳሚነት እናገኛታለን፨ በኢትዮጵያ ነገሥታት ሢመት እመቤታችን በስደቷ ከልጇ ጋር የተገኘችበት ጣና ቂርቆስን ጨምሮ አክሱም ጽዮን ማርያም፣ ተድባበ ማርያም፣ መርጡለ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው።

ይኸውም ከ3000 ዓመት በፊት የአማናዊት ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ የኾነችው ታቦተ ጽዮን ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በቀዳማዊ ምኒልክ በኩል እንድትመጣ እግዚአብሔር ስለፈቀደልን፤ የአማናዊት ታቦት የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌዋን አስቀድሞ በኢትዮጵያ ሀገር ላይ አስቀመጠ፨ ለታቦቲቱ መምጣት ቀዳማዊ ምኒልክ ተጠቃሽ ነው።

ከቅድስት ድንግል ማርያም በቤተልሔም አምላካችን ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ ይዘው እመቤታችንን ከልጇ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በዐይናቸው ካዩ ከነገሥታት ሰብአ ሰገል ውስጥ ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ እነ ዳዊት በመዝ 71 (72)፥10፤ እነ ኢሳይያስ በትንቢቱ ምዕ 60፥1-6 ሲናገሩ ብዙ የታሪክና የነገረ መለኮት ሊቃውንት ጽፈዋል፨ https://youtu.be/Am5xFV51AtA

ይኽ የቅድስት ድንግል ማርያም የቃል ኪዳኗ በረከት በዚች ሀገር ላይ አለና በኢትዮጵያ ሀገራችን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በኹለቱ ወንድማማቾች ነገሥታት በአብርሃ እና በአጽብሐ ከ1680 ዓመት በፊት በ330 ዓ.ም. ላይ በአክሱም ላይ ሲያሠሯት በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ሲኾን በዚያን ጊዜ ስትሠራ ባለ 12 መቅደስ ኾና በወርቅና በዕንቁ ያጌጠች ነበረች፨ በዚኽም ወንድማማቾች ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሐ ለአምላክ እናት ያላቸውን ታላቅ ፍቅር ገልጸዋል።

አብርሃ እና አጽብሐ በ331 ዓ.ም. በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በጎጃም ደግሞ ርእሰ ርኡሳንን መርጡለ ማርያምን ያነጹ ሲኾን "ወእምድኅረዝ ፈቀዱ አብርሃ ወአጽብሐ ከመ ይሕንጹ መቅደስ በህየ ወሐነጹ ማኅደረ ሠናይተ ወገብሩ አረፋቲሃ ዘወርቅ ወዘብሩር ... ወሰመይዋ ለይእቲ መቅደስ መርጡለ ማርያም ” (ከዚኽ በኋላ ነገሥታቱ አብርሃና አጽብሐ በዚያ ቦታ ቤተ መቅደስን ይሠሩ ዘንድ ወደዱ። ያማረች ማደሪያን ሠሩ። ግንቧን በወርቅ በብር ሠሩ። ... መቅደሷንም መርጡለ ማርያም ብለው ጠሯት) ይላል።

ከ515-529 ዓ.ም. የነገሠው ዐጼ ገብረ መስቀል ሲኾን በርሱ ጊዜ የነበሩት ከ9ኙ ቅዱሳን አንዱ አቡነ አረጋዊ ነበሩ። ከሊቁ ማሕሌታይ ቅዱስ ያሬድ ጋር ንጉሡ ዐጼ ገብረ መስቀል ደብረ ዳሞ ድረስ በመውጣት ለእመቤታችን ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሣ በተራራዋ ላይ እጅግ የምታስደንቅ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያንን አሠራ።

ቅዱስ ያሬድም ዐጼ ገብረ መስቀል ያሠራትን ይኽችን የእመቤታችን ድንቅ ቤተ ክርስቲያን ተመልክቶ "ዖድክዋ ዖድክዋ ወርኢኩ ሥነ ሕንጼሃ" (ዞርኳት ዟርኳት ያማረ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኗን ውበት አየሁ) እያለ ዘምሯል፨

እመቤታችንን በፍጹም ልባቸው ያፈቅሩ ከነበሩት ነገሥታት መኻከል አንዱ ከቋጥኝ ደንጊያ ከዐለት ዓለም የሚደነቅባቸውን አብያተ ክርስቲያንን ያነጸው ከ1157-1197 ዓ.ም. ለ40 ዓመታት የነገሠው ዐጼ ላሊበላ ነው። ንጉሡ ለእመቤታችን ከነበረው ከፍቅሩ ጽናት የተነሣ ከሌሎች ኹሉ አስበልጦ የእመቤታችንን መቅደስ እጅግ ውብ አድርጎ በብሩህ ቀለማት በቅዱሳት ሥዕላት አስጊጦ በ12 ዐምዶች ያነጻት ሲኾን በውበቷ ተወዳዳሪ የላትም፨

እመቤታችንን ይወዱ ከነበሩ ቀደምት የኢትዮጵያ ነገሥታት ከ1365-1395 ዓ.ም. የነገሡት ዐጼ ዳዊት በጣም የሚታወቁ ሲኾን ለቅድስት ድንግል ማርያም ካላቸው ጥልቅ ፍቅር በመነሣት የእመቤታችንን ተአምር ከዐረብኛ ወደ ግእዝ ቋንቋ ካስተረጎሙ በኋላ በወርቅ ቀለም እንዲጻፍ አድርገዋል፨

ንጉሥ ዳዊት የእመቤታችን ፍቅር ውስጣቸው ድረስ ጠልቆ በመግባቱ ተአምሯ በወርቅ ቀለም በሚጻፍ ጊዜ ንጉሠ ነገሥት ዐጼ ዳዊት ዕንባቸውን ከቀለሙ ጋር እንዲቀላቀል በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ዕንባቸውን ከቀለሙ ጋር ጨምረው የእመቤታችን ተአምርን ያጻፉ የምድራችን የመጀመሪያው ንጉሥ ነበሩ ማለት ይቻላል፨

የእመቤታችን ፍቅር በእጅጉ የበዛላቸው ሌላው ንጉሥ የዐጼ ዳዊት ልጅ ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ሲኾኑ በግብጽ የምትገኘው የእመቤታችን የደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን በግብጹ ንጉሥ ባርስባይ በግፍ መፍረሷን የግብጽ ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ ፲፩ኛ ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ለእመቤታችን ያለውን ጥልቅ ፍቅር ስለሚያውቁ ለርሳቸው ደብዳቤን በጻፉ ጊዜ ዐዝነው ካይሮ በፈረሰችው በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ስም ተጒለት ውስጥ አሠሩ፤ ከዚኽ ተነሥተው ዛሬ ድረስ በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ማርያም እመቤታችንን "የዘርዐ ያዕቆብ እመቤት" ይሏታል።

ብሔራውያን ሊቃውንት አባታቸው ዐጼ ዳዊት እመቤታችንን ከመውደድ የተነሣ መልክአ ማርያምን “ለዝክረ ስምኪ” ከሚለው ዠምሮ “ለገቦኪ” እስከሚለው እስከ ኹለተኛው ቤት “በከመ ዳዊት ይዜኑ” እስከሚለው ደርሰው ሲያቆሙ ፤ ልጃቸው ዐጤ ዘርዐ ያዕቆብ ደግሞ “ማርያም ድንግል ለያዕቆብ ሞገሰ ሥኑ” በማለት ቀጥለው እስከ መጨረሻው እንደፈጸሙት ይናገራሉ ፡፡ ሌሎች ሊቃውንት ደግሞ ንጉሡ ዐጼ ናዖድም እንደጻፈላት የሚገልጹ መምህራን አሉ፨ በዚኹ አጋጣሚ ሦስት የተለያዩ ዓይነቶች የመልክአ ማርያም መጻሕፍት ሲኖሩ እኔም ከአምላክ እናት በረከት ለማግኘት "መልክአ ማርያም ቀዳሚት፣ መልክአ ማርያም ካልዒት፣ መልክአ ማርያም ሣልሲት ሙሉ ትርጓሜያቸውን አዘጋጅቼ ለአንባብያን እንደቀረቡ መጽሐፉን ያነበቡ ያውቃሉ።

በአምላክ እናት ፍቅር ልባቸው በመቃጠሉ ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ በኹሉም አብያተ ክርስቲያናትን በእሑድ እና በበዓላት የእመቤታችን ተአምር እንዲነበብ ሲያደርጉ፤ ልክ እንደ አባታቸው እንደ ዐጼ ዳዊት የእመቤታችንን የተአምር መጽሐፍ ለተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ሲያጽፉ ዕንባቸው ከመጻፊያው ቀለም ጋር እንዲደባለቅላቸው ለጸሐፊዎቹ በመንገር ዕንባቸውን በማፍሰስ ታማልዳቸው ዘንድ ይማፀኗት ነበር፨

ከ1500-1532 ዓ.ም. የነገሡት ዐጼ ልብነ ድንግል የቀደሙት ነገሥታትን ሕይወት በመከተል ለቅድስት ድንግል ማርያም ካላቸው ጥልቅ ፍቅር በመነሣት በመጽሐፈ ሰዓታት ላይ የሚገኘውን "ለኖኅ ሐመሩና ስብሐተ ፍቁር ዘማርያም የሚለውን ድንቅ የምስጋና ድርሰት ለእመቤታችን ደርሰውላታል።

ሌላዋ በጣም የእመቤታችን ፍቅር በልባቸው ያደረባቸው ከ1723-1748 ዓ.ም. የነገሡት የዐጼ በካፋ ሚስት እቴጌ ምንትዋብ ሲኾኑ የእመቤታችን የስደቷና ቁስቋም የመቀመጧን ነገር ኹሌ የሚያስቡ ንግሥት ነበሩ፤ እመቤቴ ልጇን ይዛ ከሀገሯ ወጣ ብላ ቁስቋም እንደቆየች እኔም ከከተማው ወጣ ብዬ መቀመጥ እሻለሁ ብለው 5ት ኪሎ ሜትር ከከተማ ርቀው በአንድ ሺሕ የኢትዮጵያ የግንባታ ጠበብት የእመቤታችን የመንበረ ፀሓይ ቁስቋም ቤተ ክርስቲያንን ሲያሠሩ 500ው ቆመው ስሕተቶችን በመንገር ያስገነቡ ነበር።

02 Mar, 07:56
5,575
Post image

https://www.youtube.com/live/nOkG-MYy2U4?si=sT4InDy1QoNY1U0f

27 Feb, 14:32
7,242
Post image

https://youtu.be/WEJHKC7gUqI?si=uF1qh8ekxghfCG4v

26 Feb, 08:42
8,672