አንድ ብዙ ሃብት ያለው ወዳጃችሁ ካለው ሃብት ሳይሰስት ለችግራችሁ የሚሆን በቂ ገንዘብ ሰጣችሁ፤ከዛ አንድም ቀን ውለታህ አለብኝ አመስግንሃለሁ ሳትሉት በሆነ ቀን ተጨማሪ ብዙ ችግራችሁን እየዘረዘራችሁ ብድር ወይም ስጦታ ስጠኝ ብላችሁ ልጠይቁት ብትሄዱ ምን የሚላችሁ ይመስላችኋል?! አያችሁ ፈጣሪንም መጀመሪያ ስለሰጠን ማመስገን ስንጀምር የጎደለንን መሙላ ቀላሉ ነው፡፡እግዚአብሔር ሆይእንዲህ አድርግልኝ፣እንዲህ ይሁንልኝ አትበሉ።አድርግልኝ ሳይሆን መጀመሪያ ስለተደረገልን ተመስገን እንበል። ሁሌም ተመስገን፣ስላደረክልኝ ተመስገን፣ስላላደረክልኝም ተመስገን፣ጤና ስለሰጠኸኝ፣እናት አባት ፣እህት ወንድም፣ጓደኛ፣ፍቅረኛ ፣ልጅ ፣ጎረቢት ስለሰጠኸኝ ሁሉ ተመስገን እንበል።
እስኪ እናስብ ፈጣሪ ብዙ ሚሊየን ግዙፍ ፍብሪካ መክፈት የሚያስችል አዕምሮ ሰጥቶን ለትንሿ ትርፍ ፍላጎታችን ከፊቱ ስንቆም እንደት ያፍርብን?፣አለም ላይ ብንዞር በፈለግነው የሃብት መጠን የማይለካ እና የማናገኝ ሙሉ ጤና ሰጥቶን ትርፍ ለሆነችው ትንሽየ ገንዘብ ፊቱ ስንበረከክ እንደት ያፍርብን?! ፣አለም ላይ የታወቁ ዳኞች (Lawyers) ሊያስገኙልን የማይችሉት ፍትህ የሚሰጥ ፍትሃዊ ዳኛ ህሌና በውስጣችን አስቀምጦ ፈጥሮን የውሸት ፍትህን ፍለጋ ፍርድ ቤት ስንቆም ፈጣሪ እንደት ያፍርብን? ፈጣሪ ለእኛ ለሰው ልጆች ያላደረገልን አስፈላጊ ነገር ምን አለ?! አንደበት ኖሮን መናገር ባንችል እስኪ አስቡት፣አይን ሳይኖረን አለምን ማየት ባንችል አስቡት?
፣እግራችን መራመድ ባይችል አስቡት፣ጆሯችን መስማት ቢያቆም አስቡት፣አዕምሯችን ማሰብ እና ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች መልዕክት መቀበል እና ትዕዛዝ መስጠት ባይችል አስቡት፣ሰገራና ሽንታችንን መቆጣጠር ባንችል እስኪ አስቡት፣ ደማችን መዘዋወር ቢያቆም አስቡት፣ከሰውነት ክፍሎቻችን አንዷ ብትጎድል እስኪ አስቡት ?! አያችሁ ሁልጊዜም ወደ ውጭማየት ኪሳራ እንጅ ትርፍ የለም የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ ያለንን ስናውቅ የጎደለን ምንም የለም፡፡
ምስጋና ከአንደበታችን አይጥፋ።ስለፍጥረት ሁሉ እናመስግን ዝንቦች ሳይቀር እኛን ለማገልገል እንደተፈጠሩ እንወቅ፡፡እውነት ፈጣሪ ሳንጠይቅ በራሱ አምሳል ፈጥሮናልና ያለንን መንፈሳዊ ሃይ፣ስጋዊ ሃይል፣አዕምሯዊ ሃይል ብናስተውል ህይወታችን ከመብላት ፣ከመጠጣት፣ከመልበስ ባለፈ ብዙ ተአምር መስራት ነበረብን።ያለንን ሳንጠቀም ተጨማሪ ስጠኝ እያልን ብናለቅስ ፈጣሪ ለመስጠት እንደት ይቸገር ይሆን?! ምግብ መስሪያውን ሰጥቶን ምግብ ስጠኝ ብንል፣ብዙ አሳ ማጥመጃ ተሰጥቶት አንድት አሳ ስጡኝ ብሎ እንደሚለምን ሰው ነው የሚሆነው ልመናችን፡፡ስለዚህ እናስተውል።አንድም የጎደለብን የለም፡፡ያለንን ብናመሰግን ለጎደለን ገና ሳንጠይቅ በልባችን ስናስብ ሁሉ ይሆንልናል።ህይወታችሁ፣ቤታችሁ፣ ጎጇችሁ ፍፁም ሰላም እና በበረከት የተሞላ ይሆናል። ሲጎድልብን እግዚአብሔር ተመስገን ስላልን ብቻ ይሞላልናል።
ሌሊቱን ስላነጋህ ተመስገን ፣ፀሐይዋ ስለወጣች ተመስገን ፣አይናችንን ስለገለጥን ተመስገን፣ምድርን ስላፀናህ ተመስገን፣ሰማዩን ስላፀናህ ተመስገን፣የምንበላውን፣የምንለብሰውን ስለሰጠህ ተመስገን፣ስለፍጥረትህ ተመስገን፣ስለቸርነትህ ተመስገን፣ስለይቅር ባይነትህ ተመስገን፣ልጆቼን ስለምትጠብቅልኝ ተመስገን፣ሚስቴን ከክፉ ስለምጠብቅልኝ ተመስገን፣ባሌን ስለምታግዝልኝ ተመስገን፣ጎጆዬን ስለባረክልኝ ተመስገን፣መኖር ስለፈቀድክልን ተመስገን እንበል!
በነገራችሁ ላይ እግዚአብሔር ላደረገልን ነገር ሁሉ የምንከፍለው ተመስገን በማለት ነው፡፡ ምስጋና ለእግዚብሔር ክፍያው ነው፡፡ ስለጎደለን ሳናማርር ስላለን ስለተሰጠን ነገሮች ተመስገን እንበል። የጎደለውን እሱ ይሞላዋል!ዛሬ በህይወት ከአልጋቸው በሙሉ ጤንነት ከሚነሱ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ሆነን ዛሬን ለመኖር ስለተፈቀደልን ብቻ ትልቅ ውለታ አለብንና ተመስገን እንበል ።
#ተመስገን
እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋርይስጠን አሜን _ _እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኒቴ ነው፡፡
ይህ ድንቅ ትምህርት እስቲ #ሼር እናድርገው ለብዙ ሰዎች እንዲደርስ አንድ ሰው እንኳ ከተጠቀመበት ትልቅ ነገር ነው።
➡Telegram ተቀላቀሉን
እንማማርበት ቻናሉ👇👇
@rasehnmelewet33