ራስህን መለወጥ @rasehnmelewet33 Channel on Telegram

ራስህን መለወጥ

@rasehnmelewet33


"እንኳን ደህና መጣችሁ"Welcome!
ለማንበብ ራሳችንን እናስለምድ!
፨ተራ ነገር በመስራት የሚባክነውን ጊዜያችንን በንባብ ላይ ስናውለው ከራሳችን አልፈን ለብዙዎች የመለወጥ ምክንያት እንሆናለን፡የንባብ ባህላችንን እናዳብር! ባለንበት ራሳችንን በእውቀት እንገንባ!
፨በዚህ ቻናል የተለያዩ፣ጠቃሚ ሀሳቦች፣አነቃቂ ሀሳቦች ይቀርባል ይቀላቀሉ: ማወቅ መልካም ነዉ ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው።

ራስህን መለወጥ (Amharic)

ራስህን መለወጥ ትላንት ይሁን! እንኳን ደህና መጣችሁ ለማንበብ ራሳችንን እናስለምድ፡ተራ ነገር የሚባክነውን ጊዜያችንን በንባብ ላይ ስናውለው ከራሳችን አልፈን ለብዙዎች የመለወጥ ምክንያት እንሆናለን፡የንባብ ባህላችንን እናዳብር፡ ባለንበት ራሳችንን በእውቀት እንገንባ፡ በዚህ ቻናል የተለያዩ፣ ጠቃሚ ሀሳቦች፣ አነቃቂ ሀሳቦች ይቀርባል ይቀላቀሉ: ማወቅ መልካም ነዉ ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው።

ራስህን መለወጥ

21 Nov, 03:43


ሰላም ለሁላችሁ!

ከማንም ሰው ጋር ለመኖር ከመሞከራችሁ በፊት ከራሳችሁ ጋር መኖርን ልመዱ፡፡ ያን ጊዜ ሰዎች ትተዋችሁ ሄዱም፣ አልሄዱም ከራሳችሁ ጋር በሰላም ትኖራላችሁ፡፡

ማንንም ሰው ለማሸነፍ ከመሞከራችሁ በፊት ራሳችሁን የማሸነፍ አቅም አዳብሩ፡፡ ያን ጊዜ ሰዎችን ብታሸንፉም፣ ባታሸንፉም ከራሳችሁ ጋር በሰላም ትኖራላችሁ፡፡ 

ማንም ሰው ይቅር እንዲላችሁ ከመታገላችሁ በፊት ራሳችሁን ይቅር በሉ፡፡ ያን ጊዜ ሰዎች አኮረፏችሁም፣ አላኮረፏችሁም ከራሳችሁ ጋር በሰላም ትኖራላችሁ፡፡

ማንም ሰው እንዲቀበላችሁ ከመታገላችሁ በፊት ራሳችሁን ተቀበሉ፡፡ ያን ጊዜ ሰው ተቀበላችሁም፣ አልተቀበላችሁም ከራሳችሁ ጋር በሰላም ትኖራላችሁ፡፡

ሰላማዊ ቀን ይሁንላችሁ

Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

19 Nov, 14:11


24ቱ የምንጊዜም የህይወት ህጎቼ

ከመናገርህ በፊት→አስብ፣

_ከመፈረምህ በፊት→አንብብ፣

ከማስተማርህ በፊት→ተማር፣

_ከመምከርህ በፊት→ተግብር፣

ከመቁረጥህ በፊት→ለካ፣

ከማጉደልህ በፊት→ተካ፣

_ከመዋጥህ በፊት→አላምጥ፣

ከመገንዘብህ በፊት→አድምጥ፣

ከማመንህ በፊት→አረጋግጥ፣

ከመረከብህ በፊት→ቁጠር፣

_ከመወሰንህ በፊት→መርምር፣

_ከመስራትህ በፊት→አቅድ፣

_ በትጋት ሳይሆን በብልሃት ስራ፣

_ከመተኮስህ በፊት→አልም፣

_ከመተቸትህ በፊት→አጣራ፣

_ከመብላትህ በፊት→ስራ፣

_ከመሞትህ በፊት→ነሰሃ ግባ፣

_ከመሄድህ በፊት→ተስፋ ሰንቅ፣

_ስትወያይ→ሁን አስተዋይ፣

_ስትናደድ→ቶሎ ብረድ፣

_ስትናገር→በቁምነገር፣

__ ስትቸገር→መላ ፍጠር፣

--ስትቀመጥ ➞ቦታ ምረጥ

_ስትወስን→ቆራጥ ሁን!!

መልካም ምሽት
Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

18 Nov, 16:05


ወደራሳችን መለስ እንበል!

•  ስለሰዎች የግል ጉዳይና ሁኔታ ለማወቅ በሞከርን ቁጥር ራሳችንን የማወቅና የማሻሻል ብቃታችን እየቀነሰ ይሄዳል፡፡

•  ስለሰዎች ጉዳይና ሁኔታ የመስማት ጥማታችን በጨመረ ቁጥር ራሳችንን የማድመጥና ከራሳችን ጋር የመግባባት ብቃታችን እየወረደ ይሄዳል፡፡

•  ስለሰዎች ስኬትና ውድቀት የማውጣትና የማውረድ ፍላጎታችን በበዛ ቁጥር የራሳችንን የስኬት ደረጃ የማወቅና ከዚያ አንጻር የመስራት ምልከታችን ይጠፋብናል፡፡    

•  ስለሰዎች ማሰብንና ማውራትን በለመድን ቁጥር ሰዎች ስለ እኛ ስለሚያስቡትና ስለሚያወሩት ነገር መጨነቅና መናወጥ እንጀምራለን፡፡

•  ሰዎች ያደረጉብንና ያላደረጉልንን እየቆጠርን መራራ በሆንን ቁጥር፣ ራሳችንን የምናደርጋቸው መልካም ነገሮች ላይ የማተኮር አቅማችንን እናስወስዳለን፡፡

ወደ ራሳችን መለስ እንበል! 

ስለጠፋን ይቅርታ እንጠየቃለን
Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

30 Oct, 09:09


PAWS #AIRDROP BIG #AIRDOP 

በጣም  ትልቅ  #AIDROP ነው
በጣም
#በቅርቡ ላይ List ይደረጋል
ያልጀመራችሁ #አሁኑኑ ጀምሩሩ.......

አጨዋወት በጣም ቀላል ነዉ
እንደ doge ነው ።

                       ⤵️⤵️⤵️⤵️
          START #ብለው  ይጀምሩ
      
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=nkFckMMy


JOIN & #SHARE ማድረግ አይርሱ
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
   Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

28 Oct, 08:00


እ-ረ-ስ-ቼ-ዋ-ለ-ሁ!

አንድ ሴት ወደ አንድ መንፈሳዊ አባት ዘንድ ቀርባ "እግዚአብሔር ሁሌም ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትዮዋ ሁኔታ ግራ የተጋቡት እኚህ አባትም በሁኔታው ተበሳጭተው ጥለዋት ይሄዳሉ።

ከዚያን ቀን በኋላ እቺ ሴት እየደጋገመች በመምጣት "እግዚአብሔር ማታ ማታ እየመጣ ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ጭቅጭቅ የተሰላቹት እኚህ አባትም እንደለመደችው አንድ ቀን መጥታ ስታናግራቸው እንዲህ አሏት ....

"እውነት አንቺን እለት እለት እየመጣ ፈጣሪ የሚያናግርሽ ከሆነ አምንሽ ዘንድ ሁለት የቤት ሥራ ልስጥሽ" አሏት ትኩር ብለው እየተመለከቷት!

ሴትዮዋም የሚሏትን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገባች! ፡

እኚህ አባትም ከዚች ሴት ጭቅጭቅ ይገላግለኛል ያሉትን ጥያቄ አቀረቡላት እንዲህ በማለት "እውነት አንቺን እግዚአብሔር የሚያናግርሽ ከሆነ እስቲ ዛሬ ማታ ሁለት ጥያቄ ጠይቂልኝ" አሏት።

ሴትየዋም በእርጋታ "ምን ልጠይቅልዎ አባቴ?" አለቻቸው።

አባትም ጥያቄያቸውን እንዲህ ሲሉ ቀጠሉ አንደኛው የቤት ስራሽ "አንዲት ሴት ከእኔ ዘንድ በተደጋጋሚ እየመጣች አንድ በጣም ህመም የሆነባትን ችግሯን እያነባች እየነገረቺኝ ትሄዳለች። እኔም ይሄ ችግሯ ይወገድላት ዘንድ እየጸለይሁላት ነው፡፡ እስቲ እውነት ፈጣሪ ካንቺ ጋር የሚያወራ ከሆነ ይህቺ ሴት ለኔ አንብታ የነገረቺኝ ችግሯ ምን እንደሆነ ጠይቂልኝ አሏት፡፡

ሁለተኛው የቤት ስራሽ "ለረጅም አመት ልተወው ያልቻልኩት የዛሬ ወር ገደማ ግን ንስሀ ገብቼ የተውኩት አንድ ከኃጢያት እሰራ ነበር። ያ በፊት እሰራው የነበረ አሁን ግን ንሰሀ ገብቼ የተውኩት ኃጢያት ምን እንደነበረ ጠይቀሽ ንገሪኝ። እነዚህ ሁለቱን ጥያቄዎች በትክክል ከነገርሺኝ እውነትም ላንቺ እግዚአብሔር እንደሚናገር አምናለሁ" አሏት።

ሴትዬይቱም ወደ ቤቷ ሄደች።

አባት ተመልሳ እንደማትመጣ ገምተው ነበር። ዳሩ ግን በንጋታው ያቺ ሴት መጥታ አባን አስጠራቻቸው።

አባም ሴቲዮይቱን ሲያዩ በጣም ተገርመው ወደ እርሷ በመሄድ በፌዝ መልክ "እህስ ልጄ! ... እግዚአብሔርን የሴትቷን ችግር ምን እንደ ሆነና እኔም እግዚአብሔርን ንስሀ ገብቼ ያቆምኩት ኃጢያት ምን እንደነበር ጠየቅሺው?" አሏት ሳቅ እያሉ፤

"አዎን አባ" አለቻቸው ሴትየዋ አንገቷን እንዳቀረቀረች ...

"እህሳ ምን አለሽ?" አሏት አባ በመጓጓት ...

"የሴቷ ችግርና ጭንቀት ልጅ መውለድ አለመቻሏ ሲሆን የእርስዎን ግን እረስቼዋለሁ አለኝ" አለቻቸው፡፡

እኚህ መንፈሳዊ አባት ባልገመቱት ሁኔታ እውነተኛውን የልጅቷን ጭንቀት ሲሰሙ እጅግ ደነገጡና ለእርሳቸው ኃጥያት የእግዚአብሔር ምላሽ ልባቸው ተነክቶ ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ወደ ደረታቸው አስጠግተው አቀፏት!

እ.. ረ .. ስ .. ቼ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!!

ሰው እንጂ እግዚአብሔር ያለፈ ስህተትህን አያስብም ወይም እንደ ፍርድ ቤት የሰራሃውን ነገር ፋይል አድርጎ መዝገብ ቤት አያስቀምጠውም.... በቃ ወደ እርሱ በንስሃ ስትቀርብ ጥፋትህን ሙሉ ለሙሉ ይረሳዋል። ይቅርታዉ ትላንትን አያስብም። የሰው ልጅ ግን ሙሉ ይቅርታ የለውም። ዛሬ ምን ፍሪዳ አርዶ ቢታረቅህ፣ ምን በልቅሶ ታጅበህ እየተንፈራፈርክ ይቅር በለኝ ብትለው "ይቅር ብዬሀለሁ" ይልህና የሆነ ቀን ስታስቀይመው ይቅር ያለውን በደልህን እየቆጠረ ሲወቅስህ ይውላል! በአንድ ወቅት ያደረግከኝን የረሳሁት እንዳይመስልህ ይልሃል።

እግዚአብሔር ግን ይቅር ካለህ በቃ ረሳው! ፍቅር ነዋ!

ታዲያ ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሄርን በኛ መጠን መትረን ንስሀ በገባንበት ኃጢያት ዘወትር የምናለቅስ? ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሔር እንደኛ ቂመኛ መስሎን በፍቅር ያጠበውን ኃጢያታችንን እያስታወስን ዘወትር በፀፀት አለንጋ ራሳችንን የምንገርፍ? ... ይቅርታ ከመለመን እኮ ይቅር ማለት ይከብዳል! ምሬሀለሁ ከማለት ማረኝ እያሉ እግር ስር መደፋት አቤት በቀለለ!

በህይወታችን የገፋንና ያቆሰለንን ሰው በደል ከመርሳት እኮ ሺህ ጊዜ ፍሪዳ እያረዱ "እንታረቅ" ማለቱ እጅግ ቀላል ነው...! ለዚያም ነው መሰል ኢየሱስ ክርስቶስ ፀሎት አስተምረን ባሉት ጊዜ "እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አንተም ይቅር በለን" ብላችሁ ፀልዩ ያለን ...

"እግዚአብሔር ይቅርታን የሚጠይቅ አንደበት እና ይቅርታን የሚያደርግ ልብ ይስጠን!"
አሜን!

ሚክያስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።
¹⁹ ተመልሶ ይምረናል፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል።

Telegram ይቀላቀሉ
👇👇👇
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

25 Oct, 10:56


ቁምነገርን በፈገግታ

ዳመና የውሃን ክብደት መሸከም ሲያቅተው ዝናብ ይጥላል።ልብም የውስጡን ህመም መሸከም ሲሳነው አይን እንባ ያፈሳል።ስሜትህ ሲጎዳ፣ልብህ ሲሰበርና ሲጨንቅህ እጅህን ወደላይ ከፍፍ አድርግና ጌታህን ለምነው፡፡እርሱ የለመኑትን አያሳፍርምና!በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ ሰው ሁሉ ክርስቲያን አይደለም፡፡በእስር ላይ ያለ ሰው ሁሉ ወንጀለኛ አይደለም፡፡የቀረበህ ሁሉ እውነተኛ ጓደኛህ አይደለም፡፡ የተጋቡ ሁሉ ጥሩ ባለትዳሮች ይሆናሉ ማለት አይደለም፡፡የተማረ ሁሉ አዋቂ ነው ማለት አይደለም፡፡ በማስተዋል ውደዱ በማስተዋል ኑሩ። ቸኩላችሁ አታድንቁ ቸኩላችሁም አትውቀሱ፡፡ እውነት ከመልክ በላይ ትናገራለች፡፡

እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን__ እግዚአብሔር ብርሃኔና-መድሃኒቴ ነው፡፡

Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

21 Oct, 04:57


ለመለወጥ ስታስብ ዛሬህን መቀበል አትርሳ!

ከልምዶች ሁሉ ጎጂጭንቀት

የሚያኮራ ስራሰወችን መርዳት

አስቀያሚ ባህሪራስ ወዳድነት

መጥፎ ልማድመስረቅ

ትልቅ የተፈጥሮ ሀብትወጣትነት

ትልቅ መሳሪያብርታት

መጥፎ ፀባይይሉኝታ

ቆንጆ ጌጥፈገግታ

አደገኛ ስብከትአሉባልታ

ትልቅ ስጦታምክር

የሰዉ ልጅ እንቆቅልሽ ኑሮ

አደገኛ መሳርያምላስ

ራስን የመጉዳት ዘዴማልቀስ

በሀይል የተሞላ ቃልእችላለሁ

ታላቅ ተስፋእኖራለሁ

ዉድ ሀብትእምነት

ሀይለኛ የመገናኛ መሳርያፀሎት

ልንፈታዉ የሚገባን ችግር ፍርሀት

ዉጤታማ የእንቅልፍ ክኒን የአእምሮ እረፍት

መጥፎ የዉድቀት በሽታከስህተት ይቅርታን አለመጠየቅ።

የህይወት ሀይለኛ ጉልበትአእምሮ

ከህይወት ልምዶች የምድር ታላቅ ደስታ መስጠት
የህይወት ሀይለኛ ጉልበትአእምሮ

ከህይወት ልምዶች የምድር ታላቅ ደስታመስጠት

ትላንት ታሪክ ነዉና ተርከዉ

ዛሬ ቁምነገር ነዉና ተጠቀምበት

ነገ ምስጢር ነዉና ድረስበት

ለመነሳት ከፈለክ መዉደቅህን አምነህ ተቀበል

እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን __ እግዚአብሔር ብርሃኔና-መድሃኒቴ ነው

Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

19 Oct, 12:52


አታርፍድ (Don't be late)

ፍቅርን ኑርበት እንጅ አታስመስልበት። አንድ ባል እና ሚስት አብረው ሲኖሩ አንድ ልጅ አፍርተዋል። ባል ከጊዜ ወደ ጊዜ ለሚስቴ ያለው ፍቅር እየቀነሰ ይመጣል።ለሷ ያለው ስሜት ካለቀ ቆይቷል ብዙ ጊዜ ሚስቱን ለመፍታት ያስብና ለመናገር መወሰን ያቅተዋል፡፡ነገር ግን ከሌላ ሴት ጋር በድብቅ ግንኙነት ጀምሮ ከሚስቱ ጋር ሚንም አያደርግም ነበር።በመጨረሻ ግን ይወስንና ቤት እንደገባም ወደ ሚስቱ ሄዶ እንድንፋታ እፈልጋለሁ ይላታል። ሚስትም በቀዘቀዘና ሃዘን በገባው ስሜት ውስጥ ሆና ለምን አለች። ባልም ፍቅራችን አብቅቷል በቃሽኝ አላት፡፡ ሚስት እሽ ነገር ግን ፍቹን ለመፈፀም አንድ ማድረግ ያለብህ ነገር አለ ትለዋለች፡፡ባል በመሰላቸት ስሜት ውስጥ ሆኖ እሽ ምን አላት።በየቀኑ ስራ ከመሄድህ በፊት ለአንድ ወር ከመኝታ ቤት እስከ ሳሎን አቅፈህ ትወስደኛለህ አለችው፡፡ባል የልጅ ጨዎት ቢመስለውም በዚህ ይለቅልኝ በሚል ስሜት ተስማማ።

የመጀመሪያ ቀን ከመኝታ ቤት እስከ ሳሎን እንደዚህ እረዝሞበት አያውቅም ድብር እያለው ከመኝታ ቤት ሳሎን ተሸክሞ አደረሰ።አትከብድም ግን ደስ አላለውም።ልጃቸው አባቢ ማሚን አቀፋት እያለ በደስታ ዘለለ።ሁለተኛ ቀን ጠረኗ የመጀመሪያ አፍላ ፍቅራቸውን አስታወሰውና በውስጡ ጠረኗን እጅግ እወደው ነበር አሁንም አልተለወጠም አለ። ሶስተኛ ቀን የተቀባችው ሊኘስቲክ በፊት ለደቂቃዎች ፈዞ ያየው የነበረበትን ጊዜ አስታወሰው፡፡ቅርበታቸው ከቀን ወደ ቀን እየተሻሻለ ባልም እሷን ማቀፍ ደስ እያለው ልጃቸውም እነሱን ሲያይ ደስ እያለው መጣ። የመጨረሻው ቀን ደረሰና ከእቅፉ ሊያወርዳት ሲል ሚስት በካንሰር ታማ ነገር ግን ባሏ እንዳይጨነቅ በማሰብ ህመሟን ደብቃው ትሞቻለሽ የተባለችበት ቀን እንደቀረበ ታውቅ ነበርና አንገቱን አቅፋ በጆሮው ልጅን አደራ ትለዋለች፡፡ ባልም የመጨረሻው ቀን ባልሆነ ብሎ በውስጡ ተመኘ፡፡

በሚቀጥለው ቀን አዲሱ ፍቅረኛውን ከእሷ ጋር መቀጠል እንደማይችል እና ሚስቱን መፍታት እንደማይፈልግ ነገሯት ሚስቱን ይቅርታ ሊጠይቅ አበባ ይዞ ሲገባ ሚስት በህይወት የለችም።ካጠገቧ ደብዳቤ ያገኝና እየተንቀጠቀጠ አንስቶ ሲያነበው ለኔ ያለህ ፍቅር አልቆ ከአድሷ ፍቅረኛህ ጋር ፍቅር መጀመርህን ካወኩ ቆየሁ።የካንሰር ህክምናየን ለመከታተል ወደ ሃኪም ቤት ሲሄድ ከጊባችን በር ስትሳሳሙም ተመልክቻለሁ። ያኔ ነው ሁሉን ነገር ያወኩት።30ቀን እንድታቅፈኝ ያደረኩት በልጃችን ልብ ውስጥ ሚስቱን የሚወድ መልካም አባት መሆንህን ለማሳየት ነበር።ጥረቴም ተሳክቷል አመሰግናለሁ የሚል ነበር።በዚህ ጊዜ ባል ቅስሙ ስብርብር አለ። አንዳንደየ ልናስተካክላቸው የምንችላቸው ነገሮች በጣም ከረፈዱ ዋጋቸው ይገባንና ፀፀት ይሆናል ትርፋችን። በእጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል እንድሉ፡፡አክብረውን እድል ለሰጡን ሰዎች አክብረን መያዝ እንወቅበት እላለሁ።

እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን __ እግዚአብሔር ብርሃኔና-መድሃኒቴ ነው፡፡
Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

18 Oct, 03:03


የሚቀድመውን ስናስቀድም የማይተወን ፈጣሪ ይከተለናል !!

የያዝከው ነገር በቂ መስሎ ካልታየክ፤ድፍን አለምን ብትጨብጥ እንኳን፤ ሀዘንተኛ እንጂ ደስተኛ መሆን አችልም፤እናም ባለህ ነገር ፈጣሪን አመስግነህ ኑር።የሰው ዋጋው እየቀነሰ የዶሮ እና የእህል ዋጋ እየጨመረ ሲመጣ በርትተህ ፀልይ።ሰዎች ስለ አንተ መጥፎነት ቢያወሩ አይድነቅህ ምክንያቱም ውሾች በማያውቁት ሰው ላይ ነው የሚጮሁት::ጨውን ሺ ጊዜ ስኳር ብትለው ስሙን እንጂ ጣዕሙን መቀየር አችልም፡፡

ከክፋት ስትርቅ ሰላምህን ታበዛለህ፤ቅንና መልካም ስትሆን ደሞ ከጭንቀትና ከጸጸት ትድናለህ።በህይወትህ ሰዎችን ለመረዳት እንጂ ለመጉዳት አታስብ፡፡ፍቅርና መልካምነት ከቃል ይልቅ መተግበርን ይፈልጋል።የውሸት ጎደኛ እና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸዉ ሁለቱም ፀሐይ እስካሉ ድረስ ነው፡፡ውሾች እና ድመቶች አልጋህ ላይ እንዲዘሉ እየፈቀድክ ድሆች ግን የግቢህ ድንጋይ ላይ እንዲቀመጡ ባለመፍቀድህ የፈጣሪህን ምህረት ራቀህ።ከዚህ አፍ እና ልብ ከተለያዩበት ቲያትረኛ አለም ፈጥነን እንውጣ።የሳቀልን ሁሉ ሰው እየመሰለን ጠላትን ስንጠብቅ ወዳጅ እየገደለን እንዳንኖር እንጠንቀቅ።ሰዎች ሆይ የሚቀድመውን ብናስቀድም የማይተወን ፈጣሪ ይከተለን ነበር ፡፡ መልካም ቅዳሜ !!

እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን __ እግዚአብሔር ብርሃኔና-መድሃኒቴ ነው፡፡
Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

17 Oct, 08:33


ሁሉንም ዝጋ(Ignore all)

ለስራ ስትነሳ፣ መራመድ ስትጀምር፣ ሩቅ ማሰብ፣ ትልቅ ማለም ስትጀምር ሊጠልፍህ የሚሰናዳውን፣ ከፊትህ የሚቆመውን፣ የሚያዘናጋህን፣ የሚያሸብርህን እያንዳንዱን ነገር ዝጋው፡፡ ፈተናዎችህን ቀንስ፣ ጥረትህን ጨምር፤ መሰናክሎችህን አስወግድ በምትኩ ጥሩ መሻገሪያ ድልድይ አዘጋጅ፤ ግፊቶችህን አርቅ በምትኩ ድንቅ መወጣጫ አሰናዳ። በስሜት ለመጓዝ ማወቅ የሚገባህ የሌሎችን ህልም ሳይሆን የእራስህን ህልም ነው፤ እራስህን ነው፤ ማንነትህን ነው፡፡ አንተ ባለህበት ሁሉ የሚረብሽህ ነገር ሁሌም አለ፤ ወደፊትም ይኖራል። ስራዬ ብለህ ጊዜ ከሰጠሀው፣ ከሰማሀው፣ በጥልቀት ካዳመጥከው ይጥልሃል፤ ተሻግረህ ጥለሀው ካለፍክ ግን እርምጃህን ያስተካክላል፤ መንገድህን ያቃናል።

ሁሉንም ዝጋ! ሁሉንም አስወግዳቸው፡፡ ከማይሆኑ አመለካከቶች ጀምሮ፣ የሚረብሹ እየታዎችን ጨምሮ፣ ተስፋ አስቆራጭ ሁነቶችን አካቶ፡፡ ወደፊት መጓዝ ከፈለክ ትኩረትህን መሰብሰብ፤ አንድ ነገር ላይ ብቻ ማዋል ይኖርብሃል። የተበተነ ትኩረት ለተበተነ ጥረት ይዳርጋል፤ ያልተጨበጠ፣ የማይታይ እንዲሁ ድካምና ልፋት ብቻ የሆነ አሰልቺ ጉዞ ይሆናል፡፡ አሸንፋለሁ ካልክ በዙሪያህ የሚያሰናክሉህን፣ የሚረብሹህን ነገሮች ማስወገድ ተለማመድ። በSocial Media ሱስ ተጠምደህ፣ ካንተ ከማይሻሉ ሰዎች ሃሳብ እየተቀበልክ፣ ህልምና ራዕይ በሌላቸው ሰዎች ተከበህ፣ ችሎታህን የሚያሳንስ፣ አቅምህን የሚገድል ስራ ጀምረህ ትልቁን የስኬት አለም ሳይሆን በትንሹም እራስህ ላይ ተፅዕኖ መፍጠር አትችልም፡፡
ሃሳብ ስላለህ ብቻ ሳይሆን በሃሳብህ ዙሪያ የሚያንዣብቡትን አሰናካይ ሃሳቦች ማስወገድ ስትችል ከከፍታው ትደርሳለህ፣ ለስኬቱ ትበቃለህ። በጊዜ እንዳትነሳ ስለሚያደርጉህ፣ ማንበብ እንዳትችል፣ አዳዲስ ሰዎችን እንዳትተዋወቅ፣ ህልምህን እንዳትኖር፣ እቅዶችህን እንዳታሳካ፣ ቤተሰቦችህን እንዳትረዳ፣ ለጓደኞችህ እንዳትደርስ፣ በሃሳብህ ልክ እንዳትጓዝ፣ ለራዕይህ እንዳትፋለም የሚረብሹህ፣ የሚያሰናክሉህ፣ ወደኋላ የሚጎትቱህ ነገሮች ምንድናቸው? የኋላቀርነትህ ምክንያት ችሎታህ ሳይሆን ከባቢህ ሊሆን እንደሚችል አስታውስ፤ ድክመተህ ካንተ ሳይሆን ከጫናዎች ብዛት ሊሆን እንደሚችልም አስተውል፡፡ በአለማችን ትልቁ የስኬት ጠላት ትኩረት ማጣት ወይም በብዙ ነገሮች መረበሽ (distraction) ነው:: በትልቁ ታስባለህ ነገር ግን ሃሳብህን መኖር አልቻልክም፤ በፈለከው መጠን በንቃት ልታደርገው አልተሰናዳህም፤ ትክክለኛውን ጊዜ እየጠበክ መረበሽህን ቀጥለሃል፤ የተሻለ ነገ እስኪፈጠር በሃሳብህ እየተብሰለሰልክ ነው፡፡ እያንዳንዱን የሚረብሹህን መንገዶች ዝጋ፤ ሙሉ ትኩረትህን የአምላክህ ሃይል ላይ፣ እራስህ ላይና ህልምህ ላይ ብቻ አድርግ። በቅርቡ ካንተም በላይ ከባቢህ ተቀይሮ ትመለከተዋለህ።

እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን __ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኒቴ ነው፡፡

Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

16 Oct, 13:06


የተሰጠን ጊዜ የተገደበ ስለሆነ የሌላውን ህይወት በመኖር አናባክነው

ብዙ ወንዶች በጥቂት ሴቶች ከተጎዱ በኋላ ሴቶች ሁሉ አንድ ናቸው ብለው ይደመድማሉ፡፡ በተቃራኒው ብዙ ሴቶችም በጥቂት ወንዶች ይጎዱና ሁሉም ወንዶች አንድ ናቸው ሲሉ ይደመድማሉ፡፡እንደውም ለመበቀል ይሞክራሉ ማለት እችላለሁ።

እውነታው ግን.....

#በመጀመሪያ የሰው ልጅ በሙሉ የተለያየ አስተሳሰብ እንዳለው ማመን።ስነ ስርዓት እና ጨዋነት ለራስ ነው፡፡

#ሁለተኛው እራስን ሁል ጊዜም የዋህና ብልጥ ፣ ታማኝና ግልፀኛ አድርጎ ማቅረብ፡፡የዋህነት እና የልብ ቅንነት ጥቅሙ ለራስ ነው፡፡ ለሰው ብለን አናድርገው ለሰው ብለን ያደረግነው ከሆነ ሰዎች የለሉበት አውሬ እንሆናለን።

#ሶስተኛው እኔ ሰውን አልጉዳ እንጂ ሰው እኔን ሊጎዳኝ ከመጣ ከፈጣሪ እገዛ ጋር እችለዋለሁ ማለት መቻል አለብን።መልካም መሆን ያልጠቀመ ክፋት አይጠቅምም፡፡

#አራተኛው ፍቅር ከህግ በላይ መሆኑን ማመን፣በፍቅር መሸነፍ መታደል እንጅ መረገም አይደለም፡፡ በፍቅር ላይ ብልጣብልጥ መሆን ቅሽምና እንጅ እርድና አይደለም፡፡

አዳም ያለ ሄዋን ሄዋን ያለ አዳም መኖር አይችሉም፡፡ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለምና ከኖሩም እነሱ በተቃራኒ ፆታቸው በናፍቆት የሚሰቃዩና በተፈጥሮ ለተሰጡን ፀጋዎች ተፈጥሯዊ ባልሆነ መንገድ ለመጠቀም ራስንም ለስጋ እርኩሰት ነፍስን ለሃጢያት ማጋለጥ ይሆናል ትረፉ፡፡
#ወዳጆቼ ከፈጣሪ የተሰጠን ማንኛውም ነገር ጠቃሚ ነውና ሁሉንም እንደተፈጠረበት እና እንደተሰጠን አላማ በንፅህና መጠቀም መልካም ነው፡፡ስለዚህ ነገሮችን ሳናወሳስብ ያለውሸት፣ያለክፋት፣ያለበደል፣ያለ ቂም፣ያለጥላቻ፣ያለ ክህደት፣ያለ ማስመሰል በፍቅር እንኑር።

ልባችሁን ለፍቅር

ህሊናችሁን ለእውነት

ነፍሳችሁን ለፀሎት አድርጉት

ስሜታችሁን በንፅህና ጠብቃችሁ ያዙት!!

#በእናታችሁ ማንም የማንም ልብ መሰበር ምክንያት አይሁን።በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ ወድቆ መነሳት አይችልም ቢችልም ብዙ ዋጋ ያስከፍለዋል ተው!!ሁላችንም እንደተሰጠን ማንነት እና ፀጋ የራሳችንን ህይወት በንፁህና እንኑር፡፡ እንደ እርጎ ዝንብ በሰው ህይወት ላይ ዘው እያልን እየገባን ሰውን አናቁስል።

ሸር በማድረግ በፍቅርና በነፃ እንማማር!!

እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን__እግዚአብሔር ብርሃኔና-መድሃኒቴ ነው፡፡
Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

16 Oct, 10:50


ሰይጣን ተስፋ የለውም ግን ተስፋ አይቆርጥም፡፡እኛ ግን ተስፋ አለን ነገር ግን ተስፋ እንቆርጣለን።በህይወትህ ምን ጊዜም ብሆን ተስፋ አትቁርጥ፣የነገው ፀሀይ ምን ይዛ እንደምትወጣ አታወቅምና፡፡

ወደ ስኬት ስትጓዝ ወዴ ሁዋላ አትመለከት፣

ያሰብከበት ስትደርስ ግን የነበርክበትን እንዳትረሳ።

አንተ ግን ብርሃን ብቻ አብራ ጨለማው በራሱ ጊዜ

ይጠፋል!!

መልዕክቱ አስተማሪ ሆኖ ካገኙት ለወዳጅዎ #ሼር

እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን __ እግዚአብሔር ብርሃኔና-መድሃኒቴ ነው፡፡
Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

12 Oct, 05:53


ተታላላቅ ነገሮች ጊዜ ይወስዳሉ!!

ዘሩ ብቅ አላለም ብለህ ውሃ ማጠጣቱን አታቁም!

አንዳንዴ ለፍተን ለፍተን ምንም ነገር ጠብ ሳይል ሲቀር ተስፋ መቁረጥ ከተፍ ማልቱ አይቀርም፡፡ የምንለፋው ለምንድን ነው? ያሰኘናል፡፡

የምጓዘው ጨለማ መቼ ነው የሚነጋው? የልፋቴን ዋጋ መቼ ነው የማገኘው? እያላችሁ ከሆነ፤ ምላሽ የምታገኙበትን አንድ ድንቅ ታሪክ እናካፍላችሁ። አንድ ነገር ሞክራችሁ ለማቋረጥ ስታስቡ ይህንን ታሪክ መላልሳችሁ አስታውሱት፡፡

ታሪኩ የሚከተለው ነው......

የቻይና ባምቡ ዛፍ አስተዳደጉ ከሌሎች ዛፎች በጣም ይለያል። ሌሎች ዛፎች ከተተከሉ ጀምሮ ማቆጥቆጥ ሲጀምሩ፤ ይህ የቻይና ባምቡ ዛፍ ግን፤ በቀን በቀን ውሃ ቢጠጣም እስከ አምስተኛው አመት ድረስ አፈሩን በርቅሶ አይወጣም። ያለማቋረጥ እለት ተእለት ውሃ መጠጣት አለበት፤ ነገር ግን አራት አመት ሙሉ ምንም አይነት እድገት አያሳይም፡፡

በአምስተኛው አመት ግን በአምስት ሳምንት ውስጥ በአንዴ 90 feet ወይም 27 ሜትር ያድጋል።

ታዲያ ይህ ዛፍ በአምስት ሳምንት ውስጥ ነው ያደገው? ወይስ በአምስት አመት?

መልሱ በአምስት አመት ነው፡፡
ጽናት የሌለው ሰው ግን ቶሎ ብቅ ለማይል ዘር አምስት አመት ሙሉ ውሃ ማጠጣቱ አይዋጥለትም፡፡ እናም ዛፉን በእንጭጩ ይቀጨዋል፡፡

የእኛም ነገር እንዲህ ነው፤ ሃሳባችን ግቡን ባሰብነው ሰዓት ካልመታ፤ አላማችን በአቀድነው ቀን ካልተሳካ፤ ምኞታችን በእለቱ እውን ካልሆነ፤ የማይሳካ ይመስለናል። ለዚህ ነው ብዙዎቻችን ጉዟችንን የምናቋርጠው፡፡

የእውነት አላማ በውስጥህ ካለ፤ ውሃ ማጠጣትክን እንዳትተው፡፡ ዛሬ ባይሳካ በጊዜው መሳካቱ አይቀርም፡፡ አንባቢ ባታገኝም መጻህፍህን አትተው፤ የሚጎበኝልህ ብታጣም መሳልህን አትተው፤ የሚሰማህ ብታጣም መዝፈንህን አታቋርጥ፤ አይዞህ የሚልህ ባታገኝ መማርህን አታቁም፡፡

ህልማችን ልክ እንደ ቻይናው ባምቡ ዛፍ ነው፤ ሳናቋርጥ ውሃ ካጠጣነው እና ትዕግስት ካለን፤ ማቆጥቆጡ ብሎም ማደጉ አይቀርም፡፡

ለሁሉም ጊዜ አለው ይል የለ መጽሃፉ…………...በጊዜው የተከልነው ችግኝ ሰማይ ማከሉ አይቀርም፤ እስከዛ ግን ማድረግ የሚገባህን ከማድረግ አትቆጠብ፤ ነፍስህ በቀን በቀን ውሃ አጠጣት።

ክብደት መቀነስ ይሁን፣ አዲስ ቢዝነስ መጀመር ይሁን ወይም ሌላ የሕይወት ጉዞ፣ የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች በአንድ ጀንበር የስኬት ማማ ላይ የሚደረስበት እንዳልሆነ በሚገባ ያውቃሉ፡፡ ከቀን ቀን የመትጋት፣ ከቀን ቀን የማሻሻል ቁርጠኝነት አላቸው፡፡
ስኬታማ የምትሆንባትን አንዷን አመት ለማግኘት አስር አመታትን ሊፈጅብህ ይችላል። ነገር ግን ተስፋ አትቁረጥ። ምክንያቱም ትላልቅ ነገሮች ጊዜ ይወስዳሉ፡፡

ይህን መልእክት አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ወደ Groupች #share ማድረግን #አትርሱ ። መልካም ቀን
Telegram ይቀላቀሉን
           👇👇👇
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

11 Oct, 08:48


በጎ አስብ፣በጎ ተናገር፣በጎ ስራ፣በበጎ ኑር!!

ሰው መሆን ከፈለክ ፍላጎትህን ሳይሆን ህሌናህን አዳምጥ።ለሰው ከመኖርህ በፊት አንተ ሰው ሁን ቀድመህ።በማንም አትቅና ለገንዘብ ብለህ ህሌናህን አትሽጥ።ለሆድህ ብቻ አትደር። ከጥላቻ ራቅ በስጋም በነፍስም ሰነፍ አትሁን። ከማይመስሉህ ራቅ፣ጉራን እና ጉረኞችን ሽሽ ከቸልተኝነትም ተጠበቅ። በእምነትህ አትደራደር፡፡እያየህ እየሰማህ ሳትፍጨረጨር አትሙት፡፡በጥቂትም አታጭበርብር ለቃልህ ታመን።ፈፅመህ አታስመስል በተለይ ሰውን በሚጎዳ። ጊዜህን ያላግባብ አታባክን ፈፅሞ አትዋሽ።ስለነገ አታውቅምና ዛሬን በንፀህና ኑር።

እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን __ እግዚአብሔር ብርሃኔና-መድሃኒቴ ነው፡፡

Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

09 Oct, 20:07


ይህን ታሪክ በማንበባችሁ አትቆጩም!

አንድ ቀን መምህሩ ወደ ማስተማሪያ ክፍሉ ከገባ በሁዋላ ተማሪዎቹን ለድንገተኛ ፈተና እንዲዘጋጁ ይነግራቸዋል። ተማሪዎቹ ያልጠበቁት ፈተና ስለሆነ በጭንቀት ጥያቄውን ይጠባበቁ ጀመር።

መምህሩ፣ ጥያቄ የሰፈረባቸውን ወረቀቶች ለተማሪዎቹ በጠረጴዛ በጠረጴዛቸው ላይ አስቀመጠላቸው፡፡ ከዚያ ወረቀቱን ለሁሉም ተማሪዎች ካዳረሰ በሁዋላ፤

‹‹አሁን መጀመር ትችላላችሁ›› አላቸው፡፡

ሁሉም እየተጣደፉ ወረቀቱን ገልብጠው ሲያዩት አንድም ጥያቄ የለም፡፡ ደነገጡ። ከዚያ ልብ ብለው ሲያጤኑ ወረቀቱ መሐል ላይ አንዲት ጥቁር ነጥብ አለች... ከእሷ ውጭ ሌላ ነገር የለም፡፡ ዞር ዞር እያሉ እርስ በእርስ ተያዩ፡፡ መምህሩ ይሄን ግዜ እንዲህ አላቸው፡፡

‹‹ወረቀቱን ስታዩ እንደተደነቃችሁ እያስተዋልኩ ነው፡፡ በሉ ያያችሁትን ጻፉ... ፈተናው ምን እንዳያችሁ በትክክሉ መጻፍ ነው፡፡››

ተማሪዎቹ በድጋሚ ተያዩና ወደ ወረቀቱ አቀርቅረው የመሰላቸውን መሞነጫጨር ጀመሩ።

ለፈተናው የተመደበው ጊዜ አለቀና ወረቀቱ ሁሉ ተሰበሰበ። ከዚያ መምህሩ እያንዳንዱን ወረቀት እያነሳ ተማሪዎች የሰጡትን መልስ ጮክ ብሎ ያነብላቸው ጀመር። የሚደንቀው ነገር ሁሉም ተማሪዎች ለማብራራት ሲጣጣሩ የነበረው ስለዚያች ጥቁር ነጥብ እንጂ ስለሌላ ነገር አልነበረም፡፡

ነጥቧን በተመለከተ እያንዳንዳቸው፥ ስለ ጥቁረቷ፣ ስላለችበት ቦታ፣ ስለ ግዝፈቷ፣ ስለሌላም ሌላም ጥቁሯን ነጥብ ስለተመለከቱ ጉዳዮች ትንታኔዎችን አቅርበዋል፡፡

መምህሩ አንብቦ ሲጨርስ ዐይኑን መለስ ቀለስ እያደረገ የተማሪዎቹን ፊት ሲያስተውል ቆየ፡፡ ከዚያም ‹‹ተማሪዎች አንዳችሁም ትክክለኛ መልስ አልሰጣችሁም። ስለዚህ ይሄን ፈተና ውጤት አልሰጥበትም፡፡ ነገር ግን አንድ ነገር ላስተምራችሁ እፈልጋለሁ›› አላቸው፡፡

ሁሉም ተማሪ መምህሩ የሚናገረውን ለመስማት ጓጉተው መጠበቅ ጀመሩ። መምህሩም ንግግሩ ቀጠለ።

‹‹ከመካከላችሁ አንዳችሁም ስለነጩ ወረቀት አልጻፋችሁም፡፡ ሁላችሁም ትንሽዬዋን ነጥብ ዐይታችሁ፥ ትልቁንና ሰፊውን ወረቀት እስከናካቴው ረሳችሁት፡፡

በሕይወታችሁም ላይ አንዲት እንከን ስታገኙ በዚህ መልኩ ያላችሁን ጸጋ ሁሉ ጠቅልላችሁ የምትረሱ ከሆነ በጣም ትጎዳላችሁ።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ መልካም ስጦታዎች እያላችሁ ስለ አንዲቷ እንከን አብዝታችሁ የምታስቡ ከሆነ እውነቴን ነው የትም አትደርሱም፤ ቆሻሻ ውስጥ ትቀራላችሁ።
የገንዘብ ማጣቱ አስጨንቋችሁ ታማርሩ ይሆናል፤ ነገር ግን ከገንዘብ የበለጠ ጥሩ ፍቅር፣ ጥሩ ጤና፣ ጥሩ ሰላም፣ ጥሩ ቤተሰብ ወዘተ ካላችሁ ዓለም ላይ ተዓምር መሥራት ትችላላሁ።

ስኬታማ ሕይወት ለመምራት ዋናው ነገር ያላችሁ ዐቅም ስፋት ላይ ማተኮር ስትችሉ እንጂ የጎደላችሁ ኢምንት ነገር ላይ ስታተኩሩ አይደለም፡፡

እንዲህ ማሰብ ከጀመራችሁ ያለጥርጥር እንደ እናንተ ደስተኛ ሰው አይኖርም፡፡ በተቃራኒው ጉድለት ብቻ ተመልካች ከሆናችሁ ምንም ብታገኙ እርካታ የሚባል አይኖራችሁ፡፡››

የእኛው ድንቅ ደራሲ ጋሽ ስብሐት ገብረ እግዚአብሄርም በአንድ ወቅት ‹‹ጸጋህን ቁጠር›› የምትል ምክር ነበረችው፡፡

<<... ጠዋት ከእንቅልፍ ስትነሳ ተመስገን በል! አንገትህ ተቆልምሞ ሞተህ ልታድር ትችል ነበራ! እየተንጠራራህም ተመስገን በል! መንጠራራት ደስ ይላል። ይሄን ማድረግ የማይችሉ ስንቶች አሉ መሰለህ! አንተም ሽባ ሆነህ ብታድር ኖሮ መንጠራራት ባልቻልክ ነበር።...›› እያለ ስብሃት፣ እኛ ሰዎች ያለን ጸጋ ምን ያህል ብዙ እንደሆነና በዚያም ደስተኛ መሆን እንዳለብን በሚደንቅ መልኩ ያስረዳናል።

ላወቀበት ይሄ ትልቅ ትምህርት ነው፡፡ ወዳጆቼ ባላችሁ ነገር ደስተኛ መሆን ስትጀምሩ ነው ባናቱ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገር የሚጨመርላችሁ...

(በመሳፍንት ተ.)

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን የምናጋራበትን ይህን የ #Telegram አካውንታችን #follow #share በማድረግ ቤተሰብ ሁኑ።
Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

07 Oct, 11:56


ይህን ታሪክ በማንበባችሁ አትቆጩም!

አንድ ቀን መምህሩ ወደ ማስተማሪያ ክፍሉ ከገባ በሁዋላ ተማሪዎቹን ለድንገተኛ ፈተና እንዲዘጋጁ ይነግራቸዋል። ተማሪዎቹ ያልጠበቁት ፈተና ስለሆነ በጭንቀት ጥያቄውን ይጠባበቁ ጀመር።

መምህሩ፣ ጥያቄ የሰፈረባቸውን ወረቀቶች ለተማሪዎቹ በጠረጴዛ በጠረጴዛቸው ላይ አስቀመጠላቸው፡፡ ከዚያ ወረቀቱን ለሁሉም ተማሪዎች ካዳረሰ በሁዋላ፤

‹‹አሁን መጀመር ትችላላችሁ›› አላቸው፡፡

ሁሉም እየተጣደፉ ወረቀቱን ገልብጠው ሲያዩት አንድም ጥያቄ የለም፡፡ ደነገጡ። ከዚያ ልብ ብለው ሲያጤኑ ወረቀቱ መሐል ላይ አንዲት ጥቁር ነጥብ አለች... ከእሷ ውጭ ሌላ ነገር የለም፡፡ ዞር ዞር እያሉ እርስ በእርስ ተያዩ፡፡ መምህሩ ይሄን ግዜ እንዲህ አላቸው፡፡

‹‹ወረቀቱን ስታዩ እንደተደነቃችሁ እያስተዋልኩ ነው፡፡ በሉ ያያችሁትን ጻፉ... ፈተናው ምን እንዳያችሁ በትክክሉ መጻፍ ነው፡፡››

ተማሪዎቹ በድጋሚ ተያዩና ወደ ወረቀቱ አቀርቅረው የመሰላቸውን መሞነጫጨር ጀመሩ።

ለፈተናው የተመደበው ጊዜ አለቀና ወረቀቱ ሁሉ ተሰበሰበ። ከዚያ መምህሩ እያንዳንዱን ወረቀት እያነሳ ተማሪዎች የሰጡትን መልስ ጮክ ብሎ ያነብላቸው ጀመር። የሚደንቀው ነገር ሁሉም ተማሪዎች ለማብራራት ሲጣጣሩ የነበረው ስለዚያች ጥቁር ነጥብ እንጂ ስለሌላ ነገር አልነበረም፡፡

ነጥቧን በተመለከተ እያንዳንዳቸው፥ ስለ ጥቁረቷ፣ ስላለችበት ቦታ፣ ስለ ግዝፈቷ፣ ስለሌላም ሌላም ጥቁሯን ነጥብ ስለተመለከቱ ጉዳዮች ትንታኔዎችን አቅርበዋል፡፡

መምህሩ አንብቦ ሲጨርስ ዐይኑን መለስ ቀለስ እያደረገ የተማሪዎቹን ፊት ሲያስተውል ቆየ፡፡ ከዚያም ‹‹ተማሪዎች አንዳችሁም ትክክለኛ መልስ አልሰጣችሁም። ስለዚህ ይሄን ፈተና ውጤት አልሰጥበትም፡፡ ነገር ግን አንድ ነገር ላስተምራችሁ እፈልጋለሁ›› አላቸው፡፡

ሁሉም ተማሪ መምህሩ የሚናገረውን ለመስማት ጓጉተው መጠበቅ ጀመሩ። መምህሩም ንግግሩ ቀጠለ።

‹‹ከመካከላችሁ አንዳችሁም ስለነጩ ወረቀት አልጻፋችሁም፡፡ ሁላችሁም ትንሽዬዋን ነጥብ ዐይታችሁ፥ ትልቁንና ሰፊውን ወረቀት እስከናካቴው ረሳችሁት፡፡

በሕይወታችሁም ላይ አንዲት እንከን ስታገኙ በዚህ መልኩ ያላችሁን ጸጋ ሁሉ ጠቅልላችሁ የምትረሱ ከሆነ በጣም ትጎዳላችሁ።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ መልካም ስጦታዎች እያላችሁ ስለ አንዲቷ እንከን አብዝታችሁ የምታስቡ ከሆነ እውነቴን ነው የትም አትደርሱም፤ ቆሻሻ ውስጥ ትቀራላችሁ።
የገንዘብ ማጣቱ አስጨንቋችሁ ታማርሩ ይሆናል፤ ነገር ግን ከገንዘብ የበለጠ ጥሩ ፍቅር፣ ጥሩ ጤና፣ ጥሩ ሰላም፣ ጥሩ ቤተሰብ ወዘተ ካላችሁ ዓለም ላይ ተዓምር መሥራት ትችላላሁ።

ስኬታማ ሕይወት ለመምራት ዋናው ነገር ያላችሁ ዐቅም ስፋት ላይ ማተኮር ስትችሉ እንጂ የጎደላችሁ ኢምንት ነገር ላይ ስታተኩሩ አይደለም፡፡

እንዲህ ማሰብ ከጀመራችሁ ያለጥርጥር እንደ እናንተ ደስተኛ ሰው አይኖርም፡፡ በተቃራኒው ጉድለት ብቻ ተመልካች ከሆናችሁ ምንም ብታገኙ እርካታ የሚባል አይኖራችሁ፡፡››

የእኛው ድንቅ ደራሲ ጋሽ ስብሐት ገብረ እግዚአብሄርም በአንድ ወቅት ‹‹ጸጋህን ቁጠር›› የምትል ምክር ነበረችው፡፡

<<... ጠዋት ከእንቅልፍ ስትነሳ ተመስገን በል! አንገትህ ተቆልምሞ ሞተህ ልታድር ትችል ነበራ! እየተንጠራራህም ተመስገን በል! መንጠራራት ደስ ይላል። ይሄን ማድረግ የማይችሉ ስንቶች አሉ መሰለህ! አንተም ሽባ ሆነህ ብታድር ኖሮ መንጠራራት ባልቻልክ ነበር።...›› እያለ ስብሃት፣ እኛ ሰዎች ያለን ጸጋ ምን ያህል ብዙ እንደሆነና በዚያም ደስተኛ መሆን እንዳለብን በሚደንቅ መልኩ ያስረዳናል።

ላወቀበት ይሄ ትልቅ ትምህርት ነው፡፡ ወዳጆቼ ባላችሁ ነገር ደስተኛ መሆን ስትጀምሩ ነው ባናቱ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገር የሚጨመርላችሁ...

(በመሳፍንት ተ.)

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን የምናጋራበትን ይህን የ #Telegram አካውንታችን #follow #share በማድረግ ቤተሰብ ሁኑ።
Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

07 Oct, 08:59


በዚህች ምድር ያለ -የሰው ልጅ ሁሉ ለማግኘት የሚጥረው #ደስታ ነው።ደስታንም ለማግኘት ከፈለግክ፣ እርግጠኛ የምትሆንበት አንድ መንገድ አለ።እሱም ሀሳብህን መቆጣጠር ነው፡፡ደስታ ከውጭ ሁኔታ የሚታይ አይደለም፡፡የሚያምር ልብስ ብትለብስ፣ ያማረ ቤት ቢኖርህ፣አዲስ መኪና ብትገዛ፣ቆንጆ ፍቅረኛ ብትኖርህ፣ አቋምህ የተስተካከለ ቢሆን ውስጥህ ሰላም ያለው ሀሳብ ከሌለ ደስተኛ ልትሆን አትችልም፡፡

ስለዚህ ደስታ የውስጥ ስሜት እንጂ ከላይ የሚታይ አይደለም።ደስታህን የምታገኘው ሀሳብህን መቆጣጠር ስትችል ነው፡፡ለሁሉም ነገር ጊዜ እንዳለው ሲገባህ፣ትግስት መራራ፣ፍሬዋ ግን ጣፋጭ እንደሆነ ስታውቅ፣ለምትሰራው ስራ ለቤተሰብህ፣ለጓደኞችህ፣በዙሪያህ ላሉ ሰዎች ሁሉ ፍቅር ሲኖርህ፣አዎንታዊ እና አርቆ አሳቢ ስትሆን፣ከውጪህ ይልቅ ውስጥህን በአእምሮ እውቀት፣ በልብ ፍቅር ሲሞላ እና አካባቢህን ለማሳመር ስትሻ፣ውስጥህ በቅንንት ሲሞላ፣የሌሎች ህመም ሲሰማህና መራራት ማዘን እና ያለ ምክንያት ሰውን መውደድ እና ያለህን ለማካፈል ውስጥ ሲፈቅድ ያኔ አንተ ብቻ ሳትሆን ደስታም ባንተ ይደሰታል!

እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን እግዚአብሔር ብርሃኔና-መድሃኒቴ ነው፡፡
Telegram
@rasehnmelewet33

ራስህን መለወጥ

05 Oct, 17:35


ከሞት በቀር እውነተኛ ነገር የለም

በ40 ዓመቷ በዓለም ታዋቂዋ ዲዛይነር እና ደራሲ''ክሪስዳ ሮድሪጌዝ'' ከመሞቷ ፊት ስለ ህይወት የተናገረችው እውነተኛ ታሪክ ላካፍላችሁ።

#አንድ.ጋራዥ ውስጥ የአለማችን ውድ መኪና ነበረኝ፣አሁን ግን በዊልቸር መንቀሳቀስ አለብኝ፡፡

#ሁለት.ቤቴ ሁሉንም አይነት ብራንድ ያላቸው ልብሶች፣ጫማዎች እና ውድ እቃዎች ይሸጣል፣ አሁን ግን

ሰውነቴ በሆስፒታሉ በተዘጋጀ ትንሽ ጨርቅ ተጠቅልሏል። #ሶስት.በባንክ ውስጥ ብዙ ገንዘብ አለኝ።አሁን ግን ከዚህ መጠን ምንም አልጠቀመኝም፡፡

#አራት.ቤቴ እንደ ቤተ መንግስት ነበር አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ በሁለት አልጋዎች ተኝቻለሁ።

#አምስት.ከባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ወደ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ ከአንድ ላብራቶሪ ወደ ሌላ በመንቀሳቀስ ጊዜዬን አሳልፋለሁ።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ፊርማ ሰጥቻለሁ ነገርግን በዚህ ጊዜ የሕክምና መዝገቦች የእኔ ፊርማ ናቸው፡፡ፀጉሬን ለመስራት #ሰባት ፀጉር አስተካካዮች ነበሩኝ፣አሁን ግን - በራሴ ላይ አንድ ፀጉር የለኝም፡፡በግል ጄት ላይ፣የትኛውም ቦታ መብረር እችላለሁ፣አሁን ግን ወደ ሆስፒታል በር ለመራመድ ሁለት እርዳታዎች ያስፈልጉኛል።ምንም እንኳን ብዙ ምግቦች ቢኖሩም, አሁን የእኔ አመጋገብ በቀን ሁለት ጽላቶች እና ምሽት ላይ ጥቂት የጨው ውሃ ጠብታዎች ናቸው. ይህ ቤት፣ይህ መኪና፣ይህ አውሮፕላን፣ይህ የቤት ዕቃ፣ይህ ባንክ፣ ብዙ ዝናና ዝና፣አንዳቸውም አይመጥኑኝም። ከእነዚህ ውስጥ አንዳቸውም አያዝናኑኝም።'"ከሞት በስተቀር እውነተኛ ነገር የለም።በቀኑ መጨረሻ ላይ በጣም አስፈላጊው ነገር ጤና ብቻ ነው፡፡ከማንበብ ባለፈ እንማርበት እውነት በየትኛውም የእድሜ ክልል ብንሆን፣በየትኛውም ቦታ፣ሰዐት ሁሉ ሰው ሆነን ንፁህ ህሌና፣የውስጥ ሰላም፣የሰከነና የተረጋጋ ማንነት፣አመስጋኝነት እጅግ በጣም ውዱ ነገራችን እንደሆነ እንወቅ።ንፁህ እስትንፋስ ስላለን እናመስግን። ቅን እንሰብ፣ደግ እንሁን፣ሁልጊዜም መልካም እንስራ መቸ እንደምንጠራ አናውቀውምና ባለን አጋጣሚ ሁሉ በፍቅር እንኑር።ለዚች አጭር ጊዜ ለዚች ከንቱ አለም፣

እድሜያችን ተመዞ ላንኖር ዘለአለም፡፡ በድንገት ተጠርተን ላይቀር መሄዳችን፣ መልካም ጥሩ ይሁን ምንጊዜም ስራችን !!

እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን 🙏
Telegram ላይ ይቀላቀሉን
          👇👇👇
@rasehnmelewet33