ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ (@orthodoxamero)の最新投稿

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ のテレグラム投稿

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
ዲያቆን ፍፁም ከበደ

ሀሳብ ካሎዎት @Fisumkeb

+ ግሩፕ ለመቀላቀል +

https://t.me/NablisNablis

+ facebook Link...

https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede

TikTok
https://www.tiktok.com/@zdfitsumkebede1?_t=8pguEgtdsVq&_r=1
138,023 人の購読者
1,313 枚の写真
30 本の動画
最終更新日 01.03.2025 04:51

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ によってTelegramで共有された最新のコンテンツ


የጥምቀት መዝሙር ጥናት ተጀምሯል

ሊንኩን በመጫን ቮይስ ቻት ግቡ 🥰🙏

በቤተ ክርስቲያናችንም የስም ፍቅርና የሚፈጥረው ችግር ፣ የማእረግ ስሞችን የኩራታቸውና የገቢያቸው ምንጭ ለማድረግ እንጂ በሚጠሩበት ስም ልክ ሥራ ለመሥራት ዐላማ ያላቸው ሰዎች በጣም ጥቂቶች መስለው ነው የሚታዩኝ፡፡ ለዚያ ነው እኮ ያልነበረ የክህነት ደረጃ ጨምረን 'በዕደ ገብሩ ካህን' የሚለውን 'በዕደ ገብሩ ቆሞስ' ወደማለት ሁላ ያመራነው፡፡ አንድም ቀን ተጠቅሜበት አላውቅም፣ አብረውኝ የቀደሱ ቆሞሳት እንደማይደሰቱ ግን ይገባኛል፡፡


( Arega Abate )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

ዘንድሮ ከተራ ቅዳሜ ነው የሚውለው ፤ ጥምቀት ደሞ ገሀድ ጾም አለው

ጥያቄ ዘንድሮ እንዴት ነው ገሀድ ሚጾመው?

መልሳችሁን በ coment section ላይ ይላኩ ዋና ምላሹን በኋላ ይዘን እንመጣለን
@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

ማቃጠሩን ትተን...
--
ተረት እናስቀድም:-
እማሆይ የአብነት ተማሪዎች ጎጆ በእንግድነት አድረው ሌሊት መቁጠሪያቸውን እየቆጠሩ “አምላክ ሆይ እንደነዚህ ሰነፍ ተማሪዎች ስላላደረከኝ አመሰግንሀለሁ” ሲሉ አንዱ ተማሪ ተነስቶ “እማሆይ ማቃጠሩን ትተው ስለራስዎ ይጸልዩ” አላቸው፡፡
--
ጉዳያችን:-
የእግዚአብሔር መጋቢነት ኃጥእ ጻድቅ አይልም። መጋቢነቱን በዚህ ምድር በሚያጋጥሙን ፈተናዎችና ዕድሎች ለመለካት መሞከር መዳረሻው የብልፅግና ወንጌል እንዳይሆን ያሰጋል። ለቅጣት መቅሠፍት ቢያመጣ እንኳ ለየትኛው ጥፋት እንደሆነ አናውቅም። ምንና ለምን ሠራህ የሚለው የለም።
--
ደግሞስ የማያበራ ጦርነት፣ ረኀብና ርዕደ መሬት ላይ ያለ ሕዝብ የሌላውን መከራ የኃጢአት ውጤት አስመስሎ ጣት ለመቀሰር፣ የሎስ አንጀለስን በደል ለመዘርዘር ምን አንደበት አለው?!
--
ማቃጠሩን ትተን ለራሳችን እንጸልይ!


(በአማን ነጸረ )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

✞  ጥር 4 የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል
የወንጌላዊ ዮሐንስ ድንቅ ታሪክን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለዮሐንስ በደረሰለት ውዳሴ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ኮከብን ብለን ጠራንህ፤ የጽድቅ ፀሓይ ያሳደገህ ባጠገቡ (በጉያውም) ያስቀመጠህ ኮከብን ብለን ጠራንህ፤ በአፉ የሳመኽ በመታጠቂያውም ያስታጠቀኽ ኮከብን ብለን ጠራንኽ፤ የተሰወረውን ምስጢር ያሳየኽ የጸጋውን ወንጌል የሰጠኽ ኮከብን ብለን ጠራንኽ፤ ዮሐንስ እንዳንተ ያለ ማን ነው ታማልደን ዘንድ ማለድንኽ።

√ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በዚህ ክፍል ላይ ተጋድሎው ሕይወቱ እንደ ኮከብ የደመቀውን ዮሐንስን አመስግኖታል፤ ይህ ዮሐንስ ቊጥሩ ከ12ቱ ሐዋርያት መካከል ሆኖ የዘብዴዎስ እና የሰሎሜ ልጅ ሲሆን በእኛ ትውፊት እናቱን ማርያም ባውፍልያ ይላታል።

√ ጌታችን ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ ዐየ፤ ጠራቸውም እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከትለውታል። [ማቴ. 4፥21-22]

√ ጌታም ኹለቱን ወንድማማቾችን ቦአኔርጌስ ብሏቸዋል፤ ትርጓሜውም የነጐድጓድ ልጆች ማለት ነው። [ማር. 3፥17]

√ ጌታችን ምስጢረ መንግሥትን ለመግለጽ ወደ ታቦር ተራራ ይዞት ወጥቷል፤ በጌቴሴማኒም ምስጢረ ጸሎትን ሲያሳይ ከጌታ ጋር ነበርና "የምስጢር ሐዋርያ" ይባላል።

√ ጌታችን ይወድደው የነበረው ደቀ መዝሙር ርሱ ነውና "ፍቁረ እግዚእ" (የጌታ ወዳጅ) ሲባል በምሴተ ኀሙስም ምስጢረ ቊርባንን ሲመሠርት ከጐኑ የተጠቀመጠው ርሱ ዮሐንስ ነበርና ሊቁ “የጽድቅ ፀሓይ ያሳደገኽ ባጠገቡ ያስቀመጠኽ” ብሎታል፡፡

√ ጌታችን ሲጠራው የ25 ዓመት ወጣት እንደ ነበር ሄሬኔዎስ የተባለ ደቀ መዝሙሩ ጽፏል፡፡

√ ቅዱስ ጳውሎስ “Pillars of the Church- አዕማደ ቤተክርስቲያን” ብሎ ከሚጠራቸው ሐዋርያት አንዱ ዮሐንስ ነው። [ገላ. 2፥9]

[ሊቁ ዮሐንስ አፈ ወርቅና አውግስጢኖስ ስለ ዮሐንስ ሲመሰክሩ]

√ “ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን እስከ መስቀል ድረስ የተከተለ ብቸኛ ሐዋርያ ነውና ጌታም ዮሐንስ ካሳየው ፍቅር ከ100 (መቶ) ዕጥፍ በላይ እናቱን እናት አድርጎ ሰጠው፡፡ ምንኛ የታደለ ሐዋርያ ነው” ይላሉ፡፡ [ዮሐ. 19፥20-27]

√ ጌታችን በጸሎተ ኀሙስ ለደቀ መዝሙርቱ ትሕትናን ሊያስተምር ከእራት በኋላ ተነሥቶ ልብሱን አኑሮ “ወነሥአ መክፌ ዘለንጽ ወቀነተ ሐቌሁ” ይላል ዘርፍ ያላት ዝናር አንሥቶ ወገቡን ታጠቀ ሥራ የምታሠራ የምታስጌጥ ስትኾን ኢዮአብ ወደ ሰልፍ ሲገባ እየለበሳት ይገባ እንደነበረች ያለች ናት፤ ልብሰ መንድያ ይላታል በሺሕ ዘሓ (ድር) የተሠራች ናት።

√ “ወወደየ ማየ ውስተ ንብቲራ ወአኀዘ ይሕጽብ እገሪሆሙ ለአርዳኢሁ ወመዝመዘ በውእቱ መክፌ ዘቀነተ” በመታጠቢያው ውሃ ጨመረ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ ይላል።

√ ይህቺ የታጠቀበትን ለዮሐንስ ወንጌላዊ ሰጥቶት ጌታ በታጠቀበት ቢታጠቅ ሕገ ሥጋ ጠፍቶለታል ፍቁረ እግዚእ ያሰኘው ይኽ ነውና ሊቁ “በመታጠቂውም ያስታጠቀኽ” በማለት አመስግኗል፡፡

√ “በአፉ የሳመኽ” ማለቱ የሮሙ ንጉሥ ጢባርዮስ ቄሳር የጌታን ነገር አይሁድ በግፍ ጠልተው ተመቅኝተው ሰቅለውት እንደሞተ እንደተነሣ እንዳረገ ሰምቶ የጌታዬን እናት ማን ባመጣልኝ እኔ ቋሚ ለጓሚ፤ ሚስቴ ገረድ ደንገጥር በኾንላት ብሎ ተመኘ፤ ተመኝቶም አልቀረ “ወለአከ ኢየሩሳሌም ሰራዊተ ወሐራ ወአዋልደ ብዙኃተ ወኅጽዋነ” ይላል ወደ ኢየሩሳሌም ብዙ ደንገጥሮች ሰራዊትና ጭፍራ እንደዚሁም የሴት ደናግልና ባለሟሎችን በክብር አጅበው ያመጧት ዘንድ ላከ።

√ ጌታም የእናቱን ተድላ ነፍስ እንጂ ተድላ ሥጋን አይሻምና

እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም መንግሥት ክብር የሚበልጥና የሚያስደንቅ የጌትነቴን ክብር ታዪ ዘንድ በጎ ዕረፍት ወዳለበት ወደ ሰማይ አሳርግሽ ዘንድ ተነሥተሸ ቁሚ አላት፤ ከዚያም ወደ ገነት አግብቶ በገነት ላሉ ነፍሳት መድኀኒታችኊ እነኋት ርሷን አመስግኑ ብሏቸው አመስግነዋታል፡፡

በእርሱም ሐዘን እንዳይጸናበት ዮሐንስ ወንጌላዊን ላከለት ከዚያም ንጉሡን ስለ ጌታችን ሥጋዌ አስተማረው፤ ንጉሡም የሚቻልህም ከሆነ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እንዳየኸው ሥዕሉን ሥለህ አሳየኝ አለው፤ ዮሐንስም ንጉሥ ሆይ እሺ በርሱ ላይ የተፈጸመውን ሁሉ ሥዬ አሳይሆለኊ አለው፤ ከዚያም ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ጌታን እንደሰቀሉት አድርጎ ሣለው።

ብፁዕ ዮሐንስም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥዕል ሠርቶ ከፈጸመ በኋላ ራሱን ወደታች ዝቅ አድርጎ የሕያው እግዚአብሔርን ልጅ ሥዕል ተሳለመ፤ በዚችም ዕለት የዚሆ ሥዕል ከናፍር ከብፁዕ ዮሐንስ ከናፍር ጋር ለብዙ ሰዓት ተያይዞ ቆየ ይህም ጽንዐ ፍቅራቸውን ለማጠየቅ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ የመድኅን ጌታ ሥዕል ንጉሥና በዚያም የቆሙ ሁሉ እያንዳዳንዳቸው እየሰሙት ወዳጄ ዮሐንስ ዮሐንስ እያለ ድምፅ አሰምቷልና ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ይኽነን ተናገረ፡፡

[ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በዚኽ መጽሐፉ ላይ]

የተሰወረውን ምስጢር ያሳየኽ የጸጋውን ወንጌል የሰጠኽ ኮከብን ብለን ጠራንኽ በማለት ለዮሐንስ የተገለጸለትን ሰማያዊ ምስጢር ተናግሯል። ይኸውም ቅዱስ ዮሐንስ ንጽሐ ሥጋ፣ ንጽሐ ነፍስ፣ ንጽሐ ልቡና ተሰጥቶት ሰማያዊ የአንድነት የሦስትነት ምስጢር ተገልጾለት።

“በመጀመሪያው ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ” እያለ ወንጌሉን ሲጽፍ መልአኩ ከውቅያኖስ አስኳሉ በወጣለት እንቊላል እየቀዳ ውሃውን ሲያፈስስ ዐየው።

ዮሐንስም በአድናቆት ሆኖ “ምን ያደርግልኻል” ብሎ መልአኩን ጠየቀው፤ “ይህንን ውሃ በዚኽ እየቀዳኊ አፍስሼ ለማድረቅ ነው” አለው፤ ዮሐንስም “ያልቅልኻልን” አለው፤ መልአኩም “ይኽስ ፍጡር ነው ቁም ነገር የለውም ይፈጸማል፤ አንተስ የማይፈጸመውን ባሕርየ እግዚአብሔርን እፈጽማለኊ ብለኽ ጀምረህ የለም” አለው፤ ያን ጊዜ ዮሐንስ “ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ” በማለት ወንጌሉን መጻፍ ጀምሯል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ከወንጌል በተጨማሪ ሦስት መልእክታትን ሲጽፍ፤ በ98 ዓ.ም በፍጥሞ ደሴት ሳለ የዓለም ፍጻሜ ነገር ተገልጾለት ራእዩን ከጻፈ በኋላ ጥር 4 እንደተሰወረ ይነገራል፤ የቅዱስ ዮሐንስ በረከት በዝቶ ይደርብን፡፡

ማጣቀሻ
መጽሐፈ ሰዓታት ንባቡና ትርጓሜው ከመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ

◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇

ከደቂቃዎች በኋላ ምሽት 2:30 ጀምሮ ።

ማንም ሰው እንዳይቀር

( በረከት አዝመራው )

https://vm.tiktok.com/ZMkPnSjv3/

ጌታችን ያለ ወንድ ዘር ስለምን ተወለደ ?

በዘር በሩካቤ መወለድ ኃጢአት ስለሆነ ይሆን ? አይደለም ! እኮ ስለምን እንልከሆነ ፦ በሴቶች የወንዶች ብድር ነበረባቸው ። ብድሩም አዳም ብቻውን ሴትን ሲያስገኝ ፥ ሴቶች ግን ወንድን አላስገኙም ነበር ። ይህን የሴቶች ብድር ሲያጠፍላቸው ከድንግል ማርያም በድንግልና ተወለደ ። ዮሐንስ አፈ ወርቅ ይህን ሲመሰክር ወበእንተዝንቱ ወለደት ድንግል ብእሴ እንበለ ዘርዐ ብእሲ ከመትፍድዮ ለብእሲ ዕዳሃ ለሔዋን ፣ ስለዚህም እመቤታችን ብእሲ ክርስቶስን ያለ ዘር አስገኘች። የሔዋንንም ብድራት ለአዳም ትከፍለው ዘንድ ብእሲ ክርስቶስን ያለ ዘር ወለደችው በማለት ይናገራል ሃይ.አበ.ም.፳፮፥፳፱። (ኦርያሬስ ገጽ-160 መምህር ሳሙኤል ሰሎሞን) ባለጠግነቱ ይህም አይደለም ታድያ ።

ሊቁ ቅዱስ ያሬድ እመቤታችንን "አንቀጸ ብርሃን" የብርሃን ደጅ በር እያለ ያመሰግናታል ሌሎች ደጆች ካልተከፈቱ አያስገቡም ካልተዘጉም አይከለክሉም መስታወት ተዘግቶም ሳለ ብርሃን ያሳልፍል ሌሎች ግዙፍን ፍጥረታትን ግን አያሳልፍም ሌሎች አናቅጽ የሌሎች ሴቶች ምሳሌ አነርሱ በድንግልና ፀንሰው በድንግልና መውለድ አልቻሉም እርሷ ግን በድንግልና ፀንሳ በድንግና ወልዳለች ያ ብርሃንን እያስገባ ሌሎቹን እንዲከለክል እመቤታችንም ጌታን በድንግልና ስትወልድ ልማደ አንስት ዘርዐ ወራዙት አላገኛትምና ከጌታችን በቀርም ልጅን አልወለደችም በዚህም አንቀጸ ብርሃን ተብላለች ። ( አንቀጸ ብርሃን አንድምታ ትርጓሜ ገጽ-35 መ/ር ኃይለ ማርያም ዘውዱ )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

ቅዳሜ ደግሞ ሰፋ ያለ የወጥ እና ሌሎች ስራዎች ስላሉ አዲስ አበባ ላይ የምትገኙ በጎ ፈቃደኞች ከታች በተቀመጠው ዩዘር ኔም አናግሩን
@Joseph2716