ቀን 7/03/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ
በውይይቱ የባንኩ አመራሮች የተግባር አፈፃፀም ሚናቸውን በአግባቡ በመወጣት የባንኩን እንቅስቃሴ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
የባንኩን የሥራ አፈፃፀም ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም ዲስትሪክቶች ዕቅድ በመንደፍ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊገቡ እንደሚገባ ተገልፆል።
በሌላ በኩል ደግሞ ኦሞ ባንክ የቢዝነስ ተቋም መሆኑን በመገንዘብ ለሁለንተናዊ ዕድገትና ትርፋማ ለመሆን ግብ ተይዞ መስራት ያስፈልጋልም ተብሏል።
በቁጠባ የሚሰበሰበዉን ሀብት በአግባቡ በመምራትና መልሶ ለብድር ስርጭት አገልግሎት እንዲውል በማድረግ ትርፍን ማዕከል ያደረገ እንቅስቃሴ ላይ ውጤታማ ሥራ መስራት አስፈላጊ እንደሆነም የባንኩ ኘሬዝዳንት አቶ አብርሃም አላሮ ለስብሰባው ተሳታፊዎች አስገንዝበዋል።
የመረጃ ማጥራት ሥራን በሚመለከት የሁሉም ዲስትሪክት ማናጀሮች ኃላፊነት በመሆኑ በጥንቃቄና በትጋት መስራት እንደሚያስፈልግም አሰተያየት ተሰጥቷል።
ባንኩን ውጤታማ ለማድረግ ማንኛውም ውጣ ውረዶች ወደኋላ እንዳይጎትቱን በቁርጠኝነት ወደ ተሻለ ውጤት ላይ ለመድረስ ተግቶ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ የዕለቱን መድረኩ የመሩት የባንኩ ኘሬዝዳንት ተናግረዋል።
አላስፈላጊ ወጪዎችን በመቀነስ ጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ሥርዓትን ወጥ በሆነ መንገድ በመምራትና ማዕከላዊነትን መጠበቅ ከሁሉም ስራ መሪዎች እንደሚጠበቅ ኘሬዝዳንቱ አሳስበዋል።
አሁን የሚስተዋለውን አንዳንድ የኦፕሬሽን፣ የፋይናንስ አስተዳደር ስርአት፣ ወጪና ገቢን አመጣጥኖ ያለማስኬድ ችግሮችን በአጭር ጊዜ ወደ ውጤታማነት መቀየር ከምንጊዜም በላይ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር እንደሆነ ያሳሰቡት የባንኩ ፕሬዝዳንት ይህንኑ ተግባር አፈፃፀም የሚገመግም የማናኔጅመንት አካላት በተደራጀ መልኩ ወደ ስራ መግባቱና ሁሉም የአመራር አካል በላቀ ትጋትና ቅንጅት ለላቀ ምርታማነትና ለትርፋማነት በህብረት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ኦሞ ባንክ የሁላችንም ባንክ!
Our Addresses
Website:- www.omobanksc.com
Email: - [email protected]
Facebook: - https://www.facebook.com/OMFIHQ
Instagram: - https://www.instagram.com/omobankofficial
linkedin:- https://www.linkedin.com/in/omobankofficial
Twitter: - https://x.com/omobankofficial
Youtube: - https://www.youtube.com/@omobankofficial