ርዕስ - ደካማ እና የማይደክም (weak and miserable)
↪️ ገላትያ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን?
ገላትያ 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ አሁን ግን እግዚአብሔርን ዐውቃችሁታል፤ ይልቁን ደግሞ በእግዚአብሔር ታውቃችኋል። ታዲያ እንደ ገና ወደ ደካማና ወደማይጠቅም ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? ዳግም በእርሱ በባርነት ለመጠመድ ትፈልጋላችሁን?
↪️ ህግ እና ጸጋ ፈፅሞ አይቀላቀልም የትኛውም ትምህርት ጸጋን ከህግ ጋር ከቀላቀለ ደካማና የማይጠቅም ትምህርት ነው አጋር ከሳራ ህግም ከጸጋ ተቀላቅለው ሊኖሩ አይችሉም።
↪️ ዘሌዋውያን 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ሥርዓቴን ጠብቁ። እንስሳህ ከሌላ ዓይነት ጋር አይደባለቅ፤ በእርሻህም ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ፤ ከሁለት ዓይነት ነገር የተሠራ ልብስ አትልበስ።
↪️አማኞች በተለያየ ተፅእኖ ስር የሚኖሩት ህግን ከጸጋ ቀላቅለው ሲረዱ ነው የሰሙት ስለማይጠቅማቸው በህይወት ተጨባጭ ነገር መስራት አይችሉም።
🔑 ሰዋዊ ዘዴ ወይም ለአይምሮ የሚመች ትምህርት ሳይሆን እግዚአብሔር ያለው ቃል ነው ነጻ የሚያወጣው።
↪️ሮሜ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ አንድ ሰውም ኃጢአትን በማድረጉ እንደ ሆነው መጠን እንደዚያው ስጦታው አይደለም፤ ፍርድ ከአንድ ሰው ለኵነኔ መጥቶአልና፥ ስጦታው ግን በብዙ በደል ለማጽደቅ መጣ።
¹⁷ በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ።
↪️ ጸጋ እየሠራ መሆኑ አንዱ መገለጫ ሰዋዊ ብልሀትን እና አቋራጭ መጠቀም አቁመን ጌታ ላይ ብቻ ተመርኩዘን ተረጋግተን ሰው በሚዳክርበት ጉዳይ ላይ በፍፁም እረፍት ሆነን ስንነግስበት ነው።
2ኛ ቆሮ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ፥
↪️ ህጉ ለአመዛዛኝ አይምሮ ምቹ ነው አድርግ አታድርግ ስለሚል ከተደነገገው አንዷን የፈፀሙ የመሠላቸው ቀን እርካታን ስለሚያገኙ ነው ነገር ግን የሞት አገልግሎት ነው ፊደል ይገድላል መንፈስ ግን ጸጋ እና ህይወትን ይሠጣል።
↪️ዮሐንስ 1 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ።
↪️ ህግ ማድረግ የማይቻል ተፈፅመህ የማይጨረስ መሆኑን አውቆ ሠው አዳኝ እንዲፈልግ ነው የተሠጠው
↪️ኤፌሶን 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፥
↪️ህግ ከውጪ የሚሰጥ ይህን አድርግ ይህን አታድርግ የሚል ከልካይ እና ኮናኝ አገልግሎት ሲሆን ጸጋ ግን ከውስጥ ሆኖ የሚያበረታ ውጤቱ ከውጪ ለሁሉ የሚታይ እና ግልፅ ነው።
↪️ 1ኛ ቆሮንቶስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵⁶ የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው፤
↪️ ሮሜ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና።
↪️ ህጉ የኀጢአት ኀይል እና ጉልበት ነው ኃጢአት እንኳን የሚታወቀው በሕግ በኩል ነው።
↪️ በእኛ አንድ መልካም ነገር ከተገኘ ያንን ያደረገው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው የሰው ጀግና የለውም ድል የሚሠጥ በነገሮች ላይ ተዘልለህ እንድትኖር የሚያደርግ ጸጋ ነው።
↪️ ገላትያ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?
↪️ገላትያ 3 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እናንተ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ! ለመሆኑ ማን መተት አደረገባችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ በፊት ለፊታችሁ በግልጥ ተሥሎ ነበር።
↪️ሕጉ የክርስቶስን የመስቀል ስራ የሚሸፍን መጋረጃ ነው የስህተት ትምህርት ማለት ህግ እና ጸጋን መቀላቀል እና ኩነኔ እና ሞትን ደባልቆ ማስተማር ነው።
↪️ ገላትያ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤
⁷ እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።
↪️ገላትያ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ነገር ግን ባሪያዎች ሊያደርጉን በክርስቶስ ኢየሱስ ያለንን አርነታችንን ይሰልሉ ዘንድ ሾልከው በስውር ስለ ገቡ ስለ ሐሰተኞች ወንድሞች ነበረ።
🔑 መፅሀፍ ሀሰተኛ የሚላቸው በክርስቶስ ያገኘነውን አርነት አስትተው በህግ ባርያ የሚያደርጉትን አስተማሪዎች ነው።
↪️1ኛ ጢሞቴዎስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶-⁷ ከእነዚህም አንዳንዶች ስተው፥ የሚሉትን ወይም ስለ እነርሱ አስረግጠው የሚናገሩትን ሳያስተውሉ፥ የሕግ አስተማሪዎች ሊሆኑ እየወደዱ፥ ወደ ከንቱ ንግግር ፈቀቅ ብለዋል።
↪️ስድብ እና ከንቱ ንግግር ጸጋን የማጣት እና የመሳት ዋንኛ ምልክቶች ናቸው
➩ የስህተት ድብልቅ አዚም ያለበት ትምህርት ምን ያደርገል?
የክርስቶስን መስቀሉን ስራ ይከልላል ምትካችን ሆኖ እኛን ወክሎ ኢየሱስ መሠቀሉን እንዳናስተውል ይሸፍናል።
↪️ በእንጨት ላይ የተሠቀለ የተረገመ ነው እየሱስ ስለኛ እርግማን ሆኖ ከህግ እርግማን ዋጅቶናል ባለጠጋ እንድንሆን ደህይቷል ድህነት በኛ ላይ አይሰራም
➸ እኔ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ነኝ ❗️❗️❗️
Not Me But Christ