Последние посты ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል (@mkpublicrelation) в Telegram

Посты канала ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
46,863 подписчиков
6,912 фото
81 видео
Последнее обновление 09.03.2025 00:17

Последний контент, опубликованный в ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል на Telegram

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

08 Feb, 09:53

4,487

አቶ አበበ አክለውም ከዚህ ቀደም የሙከራ ትግበራ ሥልጠና በበይነ መረብ (በቨርቹዋል) ሲሰጥ እንደነበር በመግለጽ በመስፈርት የተመረጡ ደረጃ አንድ ግቢ ጉባኤያት ያሉባቸው ማእከላት ተወካዮቻቸውን በመላክ መምህራንና አስተባባሪዎች በአካል ለሁለት ቀናት እየሠለጠኑ እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።

ሠልጣኞቹ ከዚህ እንደተመለሱ በተመረጡት ግቢ ጉባኤያት ላይ ሥርዓተ ትምህርቱን እንዲተገብሩ፣ በየማእከላቱ እንዲያሠለጥኑና እንዲያስተምሩ ለማድረግ እንደሆነም በመግለጽ የሙከራ ትግበራውን ውጤት በመገምገም በሚቀጥለው ዓመት ለሁሉም ማእከላት ተግባራዊ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

08 Feb, 09:53

4,348

ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት ሥርዓተ ትምህርት የአሠልጣኞች ሥልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ተገለጸ

የካቲት ፩/፳፻፲፯ ዓ.ም 

ማኅበረ ቅዱሳን በአዲሱ ግቢ ጉባኤያት ሥርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራና ለማእከላት የአሠልጣኞች ሥልጠና በዛሬው ዕለት በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል እየሠጠ እንደሚገኝ የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማሥተባበሪያ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አበበ በዳዳ ገልጸዋል።

ለሥልጠናው ከ12 ማእከላት ማለትም (ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን፣ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ሐረር፣ ሚዛን፣ አርባ ምንጭ፣ አምቦ፣ ወልቂጤ፣ ሐዋሳና ባሌ ሮቤ) የተወጣጡ ሠልጣኞችን አያሠለጠነ ሲሆን ሥልጠናውን የሚሠጡት በሥርዓተ ትምህርት ዝግጅቱ ላይ በከፍተኛ ኃላፊነት ሲሰሩ የነበሩ ባለሙያዎች ናቸው ተብሏል።

የሥልጠናው ዋና ዓላማም አዲሱ ሥርዓተ ት/ት  ሙሉ ትግበራ ከመከናወኑ በፊት ከ 2013-2015 ዓ.ም ግምገማ በማድረግ ሥርዓተ ትምህርቱን ለመከለስ የተዘጋጀ ሲሆን ይህም ነባሩ ሥርዓተ ት/ት ላይ የነበሩ ጉድለቶችን ለማተካከል ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ተቋማዊ ለውጥ በግቢ ጉባኤያት ላይ በተጨማሪነት እንዲሠሩ ያሰባቸውን ተግባራዊ ለማድረግ፣ የሰንበት ት/ቤት ሥርዓተ ት/ት ከግቢ ጉባኤያት ጋር በት/ትና በይዘት የሚመሳሰለውን ለማስተካከል እንዲሁም ትምህርት ሚንስቴር የቀየረው  የት/ርትና የሥልጠና ፍኖተ ካርታ በግቢ ጉባኤያት ት/ት  ላይ ያለውን ተጽዕኖ ከግምት ያስገባ እና መፍትሔ የሚሰጥ ሥርዓተ ት/ት ለማዘጋጀት እንደሆነ ሥራ አሥፈጻሚው ተናግረዋል ።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

07 Feb, 16:56

5,724

  .#ዐውደ ስብከት  ሥር” # “በእንተ ጾም ”  በሚል ርእስ  ጾም ማለት ምን ማለት እንደሆነ ፣ጾም በብሉይ ኪዳን ፣ጾም በሐዲስ ኪዳን ፣የጾም አይነቶች ፣የጾም መሠረታዊ ጥቅሞች ፣ዐቢይ ጾምን የምንጾምበት ምክንያት  በስፋት  ታስነብባለች።
  #በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “# “መኑ ይእቲ ዛቲ   ክፍል አንድ " በሚል ዐቢይ ርእስ  እመቤታችን ማን  እንደሆነች፣ የእመቤታችን ከሴቶች መለየት እንዴት እንደሆነ ፤በነገረ ድኅነት የእመቤታችን ድርሻ  የሊቃውንት መጽሐፍ በማጣቀስ ትምህርት ይሰጣል ።

    #ዐቢይ ጉዳይ  ዐምድ  ሥር  ደግሞ “# መከራው እንጂ ፣ለሞት ጣር እንዳይሆን እንሥራ" በሚል ርእስ  የመከራው ዶፍ መገለጫዎችና ማድረግ ያለብን ጉዳዮች በዝርዝር ያሳያል
   •  #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር  ደግሞ  "#የኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ ትምህርት "በሚል ርእስ   ዐቢይ ርእስ  በመልአከ ሰላም  ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው  ስለ ምሥጢረ ተክሊል፣ጋብቻ እንዴት እንደተጀመረ፣የጋብቻ ዓላማው ፣ከመጀመሪያው ጋብቻ ምን እንማራለን? ጋብቻ ብዙኃኑ የሚመኘው ሲሆን እንደምኞቱ ጸሎቱ የደረሰለት ስእለቱ የሰመረለት ስንቱ ይሆን? በሚል ሰፊት ትምህርት  ታሰተምራለች።
   • #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#ቅዱስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ፣ወላዴ አእላፍ አበ ብዙኃን" በሚል ርእስ  ስለ ቅዱሱ መጠራት፣ አገልግሎት በስፋትታስቃኛለች ።
   •  #በነገዋ  ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ  ሥር “ መንፈሳውያን ማኅበራት ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን " በመ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል ክፍል ፫   በሚል ርእስ በ፭ መቶ ክፍለ ዘመን፤በዘመነ ላስታና ድኅረ ላስታ ፣ መንፈሳውያን ማኅበራት ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን በ21ኛው ክ/ዘመን ፣መንፈሳውያን ማኅበራት በአሁኑ ዘመን የሚሉ ርእሶች ይዛለች ።
  #በኪነ ጥበብ ዐምድ "#ጥሪ_ክፍል _፪ "በሚል  ታስነብባለች ።
•  #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “የማዕረግ ስም አሰጣጥ # ክፍል ፩ " በሚል ርእስ #በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን የአንድምታ ትርጓሜ መምህር የሆኑትን #መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ አዳምጤን ጋር የተደረገ  ጥያቄና መልስ ይዛለች።  ።
   ሐመር መጽሔት #፴፩ ኛ ዓመት   ቁጥር ፲፪ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !

magazine @eotcmk.org  #ሐመር #መጽሔት  ዝግጅት  ክፍል
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

07 Feb, 16:56

5,007

✍️✍️ሐመር መጽሔት በየካቲት ወር እትሟ!  
  ".. እጅግ ብዙ የመከራ ማዕበል ቢጎርፍም ሁልጊዜም አምላኳ ከእርሷ ጋር ስለሆነ ይገፏት ይሆናል እንጂ አትወድቅም "  የካቲት ዕትም በ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዐምድ
 #የኅትመት ዘመን ፦#የካቲት ፳፻፲፯  ዓ.ም
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
•  ገጽ ብዛት፦፳፰
   ዋጋ ፦፵ ብር 
•  ሐመር  መጽሔት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት  ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል  በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
•  ሐመር መጽሔት ፴፪ኛ ዓመት  ቁጥር ፪  # የካቲት ፳፻፲፯  ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን " # ‹‹  #የአሕዛብን ስድብ አትሸከሚም ››  በሚል ጠንንካራ መልእክት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ምእመናን የክፋት ጠማቂዎችን ሤራ በመታገስና በታላቅ ንቃት በመመልከት ትኩረታቸውን በበዓላቸው ላይ፣ ልባቸውንም ከአምላካቸው ጋር በማድረግ በዓሉን በሰላም እንዳሰለፋና ትንኮሳዎቹ ትዕግሥትን የሚፈታተኑ ቢሆንም ‹‹ራሳቸው አምጥተው፣ ራሳቸው በሚያሮጡ›› ተንኮለኞች ሤራ ላለመጠለፍ ያደረጉት ጥንቃቄ የሚያስመሰግን እንደነበረ ።
       በአጠቃላይ ሲታይ ግን እንዲህ ዓይነቱ የክፉዎች መዳፈር ለሀገርም፣ ለመንግሥትም፣ ለቤተ እምነቶች ግንኙነትም አይጠቅምም፡፡ ድፍረቱ ደግሞ በሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን ሁሉን በሚችል አምላክ ላይ የተፈጸመ ደፍረት በመሆኑ ሀገርና ወገንን የሚያስከፍለው  ዋጋ አሁን እየተቀበልን ካለው በላይ እንዳይሆን መጠንቀቅ  እንደሚገባ ሐመር በመልእክት ዐምድ ታስነብባለች።
   
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

07 Feb, 12:17

5,892

የግቢ ጉባኤያት ተቋማዊ ለውጥ ብቁ ዜጎችን በማፍራት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ።

ጥር ፴/፳፻፲፯ ዓ.ም

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎችን በግቢ ጉባኤያት ማዕቀፍ ውስጥ በማካተት ለቤተ ክርስቲያን ብሎም ለሀገር የሚጠቅሙ ዜጎችን ለማፍራት ማኀበረ ቅዱሳን ሥራዎችን እየሰራ ሲሆን አሁን ላይ ተቋማዊ ለውጥ ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በማኀበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲያቆን ጌትነት መሠረት እንደገለጹት ተቋማዊ ለውጡ ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት ግቢ ጉባኤያቱ ከደረሱበት አሁናዊ ሁኔታና ከዓለም ዓቀፍ ሁነቶች አንጻር አገልግሎታቸውን በምን መልኩ መፈጸም እንደሚገባቸው ለማሳየት ነው ብለዋል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎች ሙሉ ስብዕናቸውን የሚገነባ ትምህርቶችን በማስተማር ዘመኑን የዋጁ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊያን እንዲሆኑ : በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መዋቅር ውስጥ እንዲሳተፉ : በማኀበራዊ፣በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እንዲያገለግሉ ለማድረግ የተቋማዊ ለውጡ ዓላማ ነው ሲሉ  በማኀበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል ምክትል ሰብሳቢ አቶ በረከት መሠረት ገልጸዋል፡፡

መጋቤ ብርሃናት ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ በማኀበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል የግቢ ጉባኤያት አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ በበኩላቸው የግቢ ጉባኤያት ዓላማቸው ተተኪ ትውልድ ማፍራት ነው ያሉ ሲሆን ለውጡ እንዲሳካ ሁሉም የራሱን አስተዋፅዖ እንዲያበረክት አሳስበዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

07 Feb, 04:24

6,471

የአውስትራሊያ ማእከል  ገዳማትንና የአብነት ትምህርት ቤቶችን መደገፍ በሚቻልበት መልኩ  ውይይት ማድረጉ ተገለጸ።

ጥር ፳፱/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኀበረ ቅዱሳን በአውስትራሊያ ማእከል ከ10 የጽዋዕ ማኀበራት ጋር ገዳማትን እና የአብነት ትምህርት ቤቶችን መደገፍ በሚቻልበት መንገድ እንዲሁም የገዳማት ነባራዊ ሁኔታን አስመልክቶ በቨርችዋል(በበይነ መረብ)  የግንዛቤ ማስጨበጫ ዉይይት መካሄዱ ተገልጿል፡፡

አቶ ፍጹም መንገሻ የአውስትራሊያ ማእከል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ከማኀበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት የገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ተጨባጭ ሁኔታቸውን ለማሳወቅና ድጋፍ እንዲደረግላቸው ውይይቱ በመሠረታዊነት ተከናውኗል ብለዋል።

ኃላፊው አክለዉም በጦርነትና በድርቅ ምክንያት በከፍተኛ ችግር ያሉ በተለይም በሰሜኑና በምስራቅ የሚገኙ ገዳማትን ከጽዋዕ ማኀበራት ጋር በመሆን ድጋፉ ተደራሽ እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል፡፡

ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ እንዲያገኙ ሁሉም የቤተ ክርስቲያን ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በውይይቱ ላይ የተገኙት የማኀበራቱ ተወካዮች ለተግባሩ ቁርጠኛ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ድጋፉ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በጦርነትና በድርቅ ለተጎዱ ገዳማትንና አብነት ትምህርት ቤቶችን የሚያካትት መሆኑ ተጠቅሷል።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

06 Feb, 18:04

7,630

አበሳውና ኃጢኣቱ ሲበዛ እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ ነውና ወደ ዳኝነት ተግባሩ ይገባል፤ይህ ደግሞ በሰብአ ትካት በሰዶምና በጎሞራ ያስተላለፈውን ዳኝነት ያስታውሰናል፤ አሁን ያለንበት ዘመን ዓመተ ምሕረት በመሆኑ እግዚአብሔር ለጊዜው ቢታገሠንም በኃጢኣታችን የምንጠየቅበት ጊዜ አዘጋጅቶአል፤ ዛሬም ቢሆን የማናስተውለው ሆነን ካልሆነ በስተቀር እግዚአብሔር ተግሣጹን ማስተላለፍ አላቆምም፤ በምድራችን ላይ በምናደርሰው የተዛባ ተግባር በጐርፍ፣ በድርቅ፣ በመሬት መንቀጥቀጥና በአየር መዛባት እየገሠጸን እንደሆነ ማስተዋል አለብን፤
እግዚአብሔር ከጥንቱ ከጠዋቱ ጀምሮ ምድርን እንድንከባከባት፤ እንድናበጃት፣ እንድናጠብቃትና እንድናለማት አዞናል፤ ሆኖም ይህን ትእዛዙን ገሸሽ አድርገን በኬሜካልና በመርዛም ጋዝ ምድርን በመበከል፣ደንዋን በመመጠርና ራቁቷን በማስቀረት በምናደርገው ድርጊት አበሳ እየፈጸምን እንደሆነ ያወቅነው አይመስልም፤ በዚህም ምክንያት በጐርፍ፣ በድርቅ ለሰው ልጆች በማይመች የኣየር ፀባይ ወዘተ . . . ስጋት ውስጥ እየወደቅን ነው፤

   በሌላም በኩል በምናወሳስበው የአስተዳደር ርእዮትና መሳሳብ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲጋጭና ያላስፈላጊ አደጋ ላይ እንድወድቅ እያደረግን ነው፤ በዚህም ጠንቅ ሰላም እየደፈረሰ፣ ፍቅርና አንድነት እየላላ የሃይማኖት ክብርና ልዕልና እየተነካ ራሳችንንም እየጐዳን ነው፤በዚህ ሁሉ ተግባራችን  እግዚአብሔርን እያሳዘንን ነው፤ ይህ ሊገባንና ሊቈረቁረን ይገባል፤
  የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አላቸው፤ መፍትሔውም የሚገኘው ከእግዚአብሔርና ከእኛ ነው፤ ከእኛ በንስሓ ተመልሰን ከልብ እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅና ከክፉ ተግባራችን በእውነት መጸጸት ይጠበቃል፤ እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን ዓይነቱ ንስሓ ከኛ መኖሩ ሲመለከት ምሕረትና ይቅርታን ይለግሰናል፤በዚህም መፍትሔና ፈውስ ይገኛል፤ ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ለሀገራችንና ለዓለማችን ስጋት የሆኑ የጦርነት ክሥተቶች፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የአየር መዛባት፣የድርቅ መከሠት፣የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰላም መደፍረስ፣ የሰላማውያን ወገኖች መጎዳት፣ የፍቅርና የአንድነት መላላት ወዘተ. . . . ከምድራችን ተወግደው ፍጹም ምሕረትና ሰላም እናገኝ ዘንድ በኃጢኣታችን ተጸጽተን በምህላ ንስሓ መግባት አለብን፤ ከዚህ አኳያ ከጥንት ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት መሠረት በየዓመቱ የሚጾመው ጾመ ነነዌ ለዚህ አመቺ ጊዜ ስለሆነ ከየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ  ለሦስት ቀናት ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሁላችንም ጠዋትና ማታ በየቤተክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት እየተገኘን በንስሓ በዕንባ በጸሎት በምህላ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ እንድንጠይቅ፤ እንደዚሁም በሀገራችንና በውጭ ያላችሁ ሊቃውንተ ሕዝብ ቀኖናውን ጠብቃችሁ ይህንን በማስፈጸም ምህላውን በቀኖናው መሠረት እንድታከናውኑ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፤
እግዚአብሔር አምላካችን ምሕረቱን ይቅርታውንና ሰላሙን ለሀገራችንና ለዓለማችን ይስጠን፤ ምህላችንንም ይቀበልልን፤
   “እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ” ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ምንጭ:- EOTC Broadcasting Service Agency
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

06 Feb, 18:04

7,168

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ
ሙሉ መልእክት የሚከተለው ነው፡፡

ጥር ፳፱/፳፻፲፯ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተላለፈ የምህላ ሱባዔ፡-
‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምህላ አስተጋብኡ ሕዝበ ሊቃውንተ ሕዝብ፤ ጾምን ቀድሱ፣ጉባኤውንም አውጁ፤ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ኣምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ (ኢዩ ፩÷፲፬)
    ሁላችንም እንደምናውቀው ያለንበት ዓለም የመከራ ዓለም ነው፣ መከራው በኛ ስሕተትና ክፋት የመጣና እየሆነ ያለ መሆኑም ይታወቃል፤ እኛ የምንፈጽመው ጥቃቅንና ትላልቅ ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን እንደሚያስቈጣ በቅዱስ መጽሐፍ ተረጋግጦ ያደረ ነው፤ ለዚህም ከነነዌ ነዋሪ ሕዝብ የበለጠ ማስረጃ የለንም፤ የነነዌ ከተማ ነዋሪዎች በፈጸሙት ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን አስቈጥተዋል፤ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ ቢሆንም እሱ ምሕረቱን ማስቀደም ስለፈለገ በዮናስ በኩል አስጠንቅቆአቸዋል፤ የነነዌ ነዋሪዎችም በዮናስ በኩል የደረሳቸውን የንስሓ ጥሪ ወዲያውኑ ተቀብለው በምህላ፣ በጾም፣ በጸሎት ንስሓ ስለገቡ እግዚአብሔር ፍጹም ይቅርታ አድርጎላቸዋል፤
•  የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን !
እኛ ሰዎች ዛሬም በየሰዓቱ ብቻ ሳይሆን በየደቂቃው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ አበሳ እንደምንፈጽም ማወቅ ኣለብን፣
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

01 Feb, 17:35

3,764

የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መምህር ዋሲሁን በላይ ግንባታው  አሁን ያለበትን ደረጃና በዚህ ዓመት የተያዘውን እቅድ አስመልክቶ  ያቀረቡ ሲሆን በዚህ የቀጣይ የቤተክርስቲያን አገልግሎትን የሚያሳልጥ ማእከል ግንባታ የማኅበሩ አባላት እና የአገልግሎቱ ደጋፊዎች የበኩላቸውን በማድረግ የዚህ ታሪክ አካል እንዲሆኑ ጠይቀዋል ::

የአሜሪካ ማእከል አባላትም በልኀቀት ማእከሉ ግንባታ ላይ የበኩላቸውን አሻራ እንደሚያስቀምጡ በውይይቱ ላይ ቃል ገብተዋል።

ዘገባው የአሜሪካ ማእከል ሚዲያ ክፍል ነው።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

01 Feb, 17:35

3,734

ለልኀቀት ማእከሉ ግንባታ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት  ዝግጁ መሆናቸውን የአሜሪካ ማእከል አባላት አሳወቁ !!!

ማኅበሩ ባለ 14 ወለል የልኀቀት  ማእከል ግንባታ  ግንባታ መጀመሩንም ለአባላቱ አብስሯል:: በውይይቱ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የማኅበረ ቅዱሳን  ሰብሳቢ አቶ ካሳሁን ኅ/ማርያም የማኅበሩ አገልግሎት እየዘመነ እና እየሰፋ በመሄዱ ተጨማሪ ሕንጻ ግንባታ ማከናወን እንዳስፈለገው አብራርተዋል :: በተጨማሪም የሚገነባው የልኀቀት  ማእከል የማኅበሩ አገልግሎት የደረሰበትን ጥልቀት እና ስፋት ከግምት በማስገባት የተጀመረ ሥራ መሆኑን አንስተው ሲጠናቀቅ ማኅበሩ ለቅድስት ቤተክርስቲያን የሚያበረክተውን ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያግዝ ይሆናል ብለዋል::

የልኀቀት ማእከሉ ከመሬት በላይ 14 ወለል የሚኖሩት ሲሆን ከመሬት በታች ደግሞ 2 ወለሎች ይኖሩታል :: እስከ 1000 ሰው ድረስ የሚይዝ ግዙፍ መሰብሰቢያ አዳራሽ እስከ 40 ሰዎች የሚይዙ የተለያዩ መለስተኛ አዳራሾች እና ዘመናዊ የሚዲይ ስቱዲዮዎች በልኀቀት  ማእከሉ የሚካተቱ ናቸው። ለማኅበሩ አገልግሎት የሚሆኑ በርካታ ቢሮዎች እና በቂ የመኪና መቋሚያም የማእከሉ ግንባታ የሚያካትታቸው መሆኑ በውይይቱ ተገልጿል :: ይህን ማእከል ለመገንባት 4 መቶ ሚሊዮን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን እስካሁን በተከናወነው ሥራ የከርሰ ምድር ቁፋሮን ጨምሮ ከመሬት በታች ያሉት ሥራዎች ተከናውነዋል ::