Latest Posts from ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል (@mkpublicrelation) on Telegram

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል Telegram Posts

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
46,849 Subscribers
6,907 Photos
80 Videos
Last Updated 06.03.2025 03:40

The latest content shared by ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል on Telegram

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

04 Mar, 16:17

4,681

Ready for an Epic Gathering, yet again?

Calling all incoming freshmen, college students, and recent grads! Join us for our 7th in-person General Assembly this July in Atlanta! Don’t miss out – register now to secure your spot using the link below. Let’s embark on this spiritual journey of connection and enlightenment together.
We can’t wait to see you!

Registration form:
https://forms.gle/cqgiQz4tcv8SwNhU6
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

04 Mar, 10:47

5,861

“ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ” በሚል መሪ ቃል የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር መካሄዱን የአቡዳቢ የግንኙነት ጣቢያ  ገለጸ

የካቲት ፳፭/፳፻፲፯ ዓ.ም 

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአቡዳቢ ልዩ ግንኙነት ጣቢያ 5ተኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር “ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ” (ኤፌ ፭፥፲፮) በሚል መሪ ቃል ቅዳሜ የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም በአቡዳቢ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም መከናወኑ ተገልጿል።

ጸባቴ አባ ፍ/ማርያም ተከስተ (ቆሞስ) የአቡዳቢ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አስተዳዳሪ፣ መላከ ፀሐይ ቀሲስ ኪሩቤል ይገዙ የራስ አልኬማ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ የገዳሙ ቀሳውስት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የተስፋ ስዱዳን ሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ምእመናን በተገኙበት ዝግጅቱ ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ መዝሙር በማኅበሩ፣ በተስፋ ስዱዳን ሰንበት ትምህርት ቤትና በግቢ ጉባኤ አባላት የቀረበ ሲሆን መምህር እስጢፋኖስ “ከእርሱም በተደረገው ድንቅ ነገር ሕዝቡ ሁሉ ደስ አላቸው” በሚል የዕለቱን ወንጌል ሰጥተዋል።

የዋናው ማእከል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዲ/ን ሲሳይ ብርሃኑ የማኅበሩ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በማስከተልም ስለ ግንኙነት ጣቢያው አጠር ያለ የስራ ሂደት በግንኙነት ጣቢያው የሕዝብ ግንኙነት ተወካይ መቅረቡ ተገልጿል።

በመጨረሻም በአባቶች ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ተሰጥቷል።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

03 Mar, 10:12

7,443

በቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ በሀገሪቱ ሰፊውን ቁጥር ይዞ የሚገኘው ወጣቱ ክፍል በሱስ ተይዞ መገኘቱ የማኅበረሰብ ክፍል ቤተክርስቲያንንም ሆነ ሀገርን በማገልገል ሂደት ውስጥ ያለው ሚና ቀላል የማይባል ሆኖ ሳለ ከሱስ ጋር በተያያዘ ግን እንደ ቤተክርስቲያንም እንደ ሀገርም አስጊ ሁኔታ በመድረሱ ትውልድን ለመታደግ ቤተክርስቲያን የሱስ ማገገሚያ ተቋማትን በማዘጋጀትና በማከም ሂደት ውስጥ ተሳትፎ በማድረግ የራሷን በጎ አሻራ ማሳረፍ ግድ እንደሚላት ተመላክቷል።

አገልግሎቱ እስካሁን እየሰጣቸው ባሉ የአማካሪዎች ሥልጠና የችግሩን አሳሳቢነት መነሻ በማድረግ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን ለካህናትና በምክክር አገልግሎት ለሚሰማሩ ባለሙያዎችም በሥልጠና መልክ እያስገነዘበ  እንዳለም ማወቅ ተችሏል።

ለዚህም ጥናት መፍትሔ ተግበራዊነት ማኅበረ ቅዱሳን ከባላድርሻ አካላት ማለትም ከጠቅላይ ቤተክህነት፣ ከሀገረ ስብከት፣ከወረዳ ቤተክህነት፣ ከሰንበት ትምህርት ቤት፣ከተለያዩ ማኅበራት፣ ከባለሀብቶች ጋር በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል። በቀጣይነትም የተጠናው ጥናት ውጤትና ወደ ተግባራዊ ተቋምነት በሚቀየርበት ሁኔታ ላይ አጋርና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ መታቀዱን የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

03 Mar, 10:12

6,355

ለወጣቶች የሱስ ማገገሚያ ተቋም ለማቋቋም ጥናት ማካሄዱን የማኅበረ ቅዱሳን ሙያዊ፣ማኅበራዊና ኢኮኖያዊ አገልግሎት አስታወቀ

የካቲት ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን ሰ/ት/ማ/መ/የማኅበረ ቅዱሳን ሙያዊ፣ማኅበራዊና ኢኮኖያዊ አገልግሎት በሱስ ለተጠቁ ምእመናን ከበሽታቸው መላቀቅ የሚያስችላቸውን የሱስ ማገገሚያ ተቋም ለማቋቋም የሚያስችል ጥናት ማካሄዱን አስታውቋል።

በአገርም ሆነ በዓለም-አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ ሁኔታ ከደረሱ ችግሮች አንዱና ዋነኛው ሱስ ሲሆን በተለይ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሱሶች የተጠቁ ልጆቿን ከህመማቸው የሚያገግሙበት ስፍራ   በገዳማት፣ በአጥቢያ ቤተክርስቲያናት፣በጸበል ቦታዎች ፣ በሌላም አከባቢዎች በሚገነባ ተቋም ውስጥ ልጆቿን የምታክምበትን መንገድ ለመጠቆም የሚያስችል ጥናት መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።                                                       

ጥናቱ በችግሩ ዙሪያ ዝርዝር መረጃዎችና ማስረጃዎችን በስፋት አካቶ የተዘጋጀ መሆኑንም ከተዘጋጀው ሰነድ መረዳት ተችሏል።

ቤተክርስቲያን ካለባት ኃላፊነት አንጻር ትውልዱን ከሱስ ተጠቂነት ማውጣትና እንደ ምዕመን ለቤተክርስቲያን የሚያገለግል፣ የእግዚአብሔርን ሕግ የሚጠብቅ፣ ሰውን የሚያከብር፣ ለእናት ለአባቱ የሚታዘዝ፣ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ሕገ እግዚአብሔር፣ ትውፊት፣ ቀኖና፣ ካህናትና እና የሥነ ልቦና ባለሙያ ምክር፣ በተዋሕዶ ከብሮ ለቅዱስ ሥጋና ለክቡር ደሙ የሚበቃ ምዕመን ለማፍራት የሚያስችሉ የሱስ ማገገሚያ ተቋማት መቋቋም እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

03 Mar, 07:42

7,503

የብፁዕ  ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  ፲፪ኛ ዓመት  በዓለ ሢመት እየተከበረ ይገኛል

የካቲት ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፲፪ኛ በዓለ ሢመት  በዛሬው ዕለት  የካቲት ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከናወነ ነው።

ምንጭ :- Eotc broadcast
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

02 Mar, 10:20

2,196

ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤ መምህራን ማሰልጠኛ ማእከል ፕሮጀክት ይፋ አደረገ።

የካቲት ፳፫/፳፻፲፯ዓ.ም

በዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር “የግቢ ጉባኤ መምህራን ማፍሪያ” የሚል ፕሮጀክት እንደተቀረጸ የጥናቱ አቅራቢ አቶ ዳንኤል ተስፋዬ አስታውቀዋል።

ፕሮጀክቱ የግቢ ጉባኤ መምህራን ማሰልጠኛ ማእከል በማዘጋጀት መምህራንን በሥርዐተ ትምህርቱ በበቂ ሁኔታ ለማፍራት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ማኅበረ ቅዱሳን በሀገር ውሰጥ በ467 እና በውጭ ሀገራት በ18 ግቢ ጉባኤያት ከ160 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ሥርዓተ ትምህርት ቀርጾና መጽሐፍትን አሳትሞ እያስተማረ ይገኛል።

መምህራንንም ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 3 በመለየትም አሰልጥኖ ለአገልግሎት እያሰማራ ነው።

ነገር ግን በበቂ ሁኔታ ለማስተማርና የበለጠ ተደራሽነቱን ለመጨመር የመምህራን እጥረት ትልቅ ፈተና እንደሆነበት ገልጿል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም በ4 ዓመት ተፈጻሚ የሚሆን ፕሮጀክት ቀርጿል።

በ13ኛው የግቢ ጉባኤያት ሴሚናርም ፕሮጀክቱ ቀርቦ ተፈጻሚነቱ ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

02 Mar, 08:53

2,704

“ማኅበረ ቅዱሳን ዓላማው ታማኝ የሥራ ሰው እና በቅንነት የሚያገለግል የሰው ኃይል ለሀገርና ለቤ/ክ ማፍራት ነው”

አቶ ካሳሁን ኃ/ማርያም የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ

የካቲት ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም

እየተካሄደ በሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን ዓለም አቀፍ 13ኛው የግቢ ጉባኤ ሴሚናር የተገኙት የማኅበሩ ሰብሳቢ አቶ ካሳሁን ኃ/ማርያም መልእክት አስተላልፈዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን ዓላማው ታማኝ የሥራ ሰው፣ በቅንነት የሚያገለግል የሰው ኃይል ለሀገርና ለቤ/ክ ማፍራት በመሆኑ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የሀገርና የቤ/ክ ኃላፊነት አጣምረው እንዲይዙ አደራ ብለዋል።

ሰብሳቢው አክለውም ሀገር፣ ቤተ ክርስቲያንና መጭው ትውልድ እኛን ተስፋ ያደርጋል በማለት እዚህ ባገኛችሁት ዕውቀት በሕይወት በመግለጥ ዓለሙን አሸንፉ ድል አድርጉ ሲል አጽዕኖት ሰጥተዋል።

ለዚህም ማኅበረ ቅዱሳን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚገኙ ተማሪዎች ሥርዓተ ትምህርት በማዘጋጀት እና መምህራንን በመመደብ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አቶ ካሳሁን ኃ/ማርያም በመጨረሻ መልእክታቸውም ተሳታፊዎቹ ወክለው ለላኳችሁ ግቢ ጉባኤያት የሰማችሁትን በጎ ተሞክሮ ማካፈል አለባችሁ ብለዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

02 Mar, 08:19

2,776

“ለሁለተናዊ የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ በኃላፊነት እማራለሁ!” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው የ13ኛው ዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር 2ኛ ቀን ውሎው እየተካሄደ ይገኛል፡

የካቲት ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም

ለሁለተናዊ የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ በኃላፊነት እማራለሁ በሚል መሪ ቃል 13ኛው ዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር በትናንትናው ዕለት የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል፡፡

በዛሬው የጠዋት መርሐ ግብሩ መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል በቅድስት ሥላሴ መምህር፣ የሊቃውንት ጉባኤ አባል እና በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጥናትና ምርምር ማእከል መምሪያ ኃላፊ ”ለራሳችሁ አይደላችሁምና ” በሚል ኃይለ ቃል ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል፡፡

የደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ስምዓ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራንም ዝማሬ አቅርበዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

15 Feb, 07:40

4,676

፲፫ተኛው የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር ከየካቲት 21 እስከ የካቲት 23 እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የካቲት ፰/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ አማካኝነት በየሁለት ዓመቱ የሚዘጋጀው ፲፫ተኛው የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር ከየካቲት 21 እስከ የካቲት 23/6/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አበበ በዳዳ ገልጸዋል።

ሥራ አስፈጻሚው እንደገለጹት የመርሐ ግብሩ ዓላማ በከፍተኛ የት/ት ተቋማት የሚማሩ  ኦርቶዶክሳዊያን ተማሪዎች በቤተ ክርስቲያን አሁናዊ ሁኔታና በማኅበረ ቅዱሳን በአጠቃላይ የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዙሪያ እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት ግንዛቤ የማስጨበጥና የበለጠ ለማገልገል እንዲተጉ ለማድረግ የተዘጋጀ እንደሆነ  አስታውቀዋል።

አክለውም ከ43 ማእከላት የተወጣጡ 450 የግቢ ጉባኤ አገልግሎት ዋና ክፍል አባላትና ተሳታፊዎች እንዲገኙ እንደ ዕቅድ የተያዘ ቢሆንም አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታና በበጀት እጥረት ምክንያት ከ300 በላይ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል ብለዋል።

ሴሚናሩ በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ የሚከናወን ሲሆን ማኅበሩ በግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ላይ እያከናወነ ያለውን ተግባር ለመገምገም እና  ለወደፊት የተሻሉ አቅጣጫዎች ለማስቀመጥ እንደሚያግዝ ሥራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን ወጣቶች መንፈሳዊ አገልግሎትን እና ቤተ ክርስቲያንን እንዲያውቁ በግቢ ጉባኤያት በኩል እያስተማረ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ አበበ አያይዘውም የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸውን ለከፍተኛ ት/ት ተቋማት ሲልኩ ወደ ግቢ ጉባኤያት መሄድና መማር እንዲችሉ በማድረግ በሁለቱም በኩል እንዲጠነክሩ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው መልእክት አስተላልፈዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

15 Feb, 04:40

4,951

https://youtu.be/PZqzTBkxDQA?feature=shared