MAGIC CARPET SCHOOL ETHIOPIA

@mgc_all


OFFICIAL PAGE

MAGIC CARPET SCHOOL ETHIOPIA

24 Oct, 13:15


#MoE

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity

MAGIC CARPET SCHOOL ETHIOPIA

23 Oct, 10:50


ቀን 13/02/2017 ዓ.ም

ለማጂክ ካርፔት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ
ጉዳዩ፡- የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጸሐፍ ግዢን ይመለከታል
ከላይ በርዕሱ ጉዳዩን ለመግለጽ እንደተሞከረው የማጂክ ካርፔት ት/ቤት ለተማሪዎች በቁጥራቸው መጸሐፍ ገዝተው ያቀረቡ ሲሆን ነገር ግን አብዛኛው ተማሪዎች እና ወላጆች መጸሐፍ ያልገዙ ሲሆን ከትምህርት ቢሮ በወረደው መመሪያ መሠረት የተማሪ መጸሐፍት ጥምርታ አንድ ለአንድ መሆን እንዳለበት ያዛል በዚህ መሠረት የማጂክ ካርፔት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለተማሪዎች በቂ መጸሐፍት ገዝቶ ያቀረበ ሲሆን ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች እስከ አርብ 15/02/2016 ዓ.ም ተማሪዎች መጸሐፍ በመግዛት መጸሐፍቱን መጠቀም ያለባቸው መሆኑን እያሳወቅን ሰኞ መጸሐፍ ይዞ የማይገኝ ተማሪ ክፍል የማናስገባ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ በተጨማሪም የክፍል ኃላፊዎች እና የትምህርት ዓይነት መምህራን (Subject Teachers) መጸሐፍ ይዘው ያልመጡ ተማሪዎችን ለቢሮ ሪፖርት እንድታደርጉ ስንል እናሳስባለን፡፡
ት/ቤቱ

MAGIC CARPET SCHOOL ETHIOPIA

21 Oct, 18:54


#AddisAbaba #Education

“ በሂሳብና እንግሊዘኛ መፅሐፍት ላይ እጥረት በመታየቱ ተጨማሪ ህትመት እየተካሄደ ነው ” - አ/አ ትምህርት ቢሮ

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት መፅሐፍ ማሳተም ላይ እንደ አገር በተለያዩ ትምህርት ቢሮዎች ክፍተቶች እንዳሉ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት በ2017 የትምህርት ዘመን መፅሐፍትን አሳትሞ ለተማሪዎች ማዳረስ ተቻለ ? ሲል ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጥያቄ አቅርቧል።

የቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በሰጡት ቃል፣ “ በተወሰኑ ትምህርቶች ላይ፤ ሂሳብና እንግሊዘኛ መፅሐፍት  እጥረት በመታየቱ ምክንያት ተጨማሪ ህትመት እየተካሄደ ነው። ሪዘርቭም እያደረግን እንገኛለን ” ሲሉ ተናግረዋል።

የመፅሐፍት እጥረቱ በምን ደረጃ ነው ? ሲል ቲክቫህ ላቀረባቸው ጥያቄ በምላሻቸው፣ “ ይህንን ሬሽዎ በተለይ ከግል ትምህርት ቤቶች አካባቢ ላይ ያለ ችግር ነው ” ብለዋል።

“ እነርሱም መፅሐፉን ወስዶ ለማሰራጨት ፍላጎት ማጣት፣ ይሄ ደግሞ የራሳቸው መፅሐጽት አትመው ለመሸጥ ከሚመነጭ ነገር ስለሆነ እሱ ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እየወሰድን ትምህርት ቤቶች ወስደው ለተማሪዎቻቸው ተደራሽ እንዲያደርጉ አድርገናል ” ነው ያሉት።

“ ከሁለተኛ ደረጃና ቅድመ አንደኛ ደረጃ በስተቀር ለሁሉም አንድ ለአንድ ተዳርሷል ” ሲሉም ተናግረዋል።

“ ለሁለተኛ ደረጃም ትምህርት ሚኒስቴር አሳትሞ ሰሞኑን ባስገባው መሠረት ለሁሉም ተማሪዎች ማዳረስ ተችሏል" ያሉት ኃላፊው፣ " ባለፉት ሁለት ዓመታት በከፍተኛ ኢንቨስትመንት ተማሪዎቻችን ጋር ተደራሽ ለማድረግ ተሞክሯል” ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ ከተማሪዎች ምገባ ጋር በተያያዘ መጋቢ እናቶች ከኑሮ ውድነቱ ጋር በተያያዘ የሚከፈላቸው ገንዘብ አነስተኛ መሆኑን ይገልጻሉ።

ይህንኑ በተመለከተ ምን እየተሰራ እንደሆነ ማብራሪያ የጠየቅናቸው ዘላለም (ዶ/ር)፣ “ በተማሪ 22 ብር የነበረው በዚህ ዓመት ወደ 32 ብር አሳድጎላቸዋል። ስለዚህ ያ ጥያቄ ተመልሷል ማለት ነው ” ብለዋል።

“ በቀን 800 ሺሕ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ ይመገባሉ ” ሲሉ ተናግረዋል።

በተያያዘም በትምህርት ቤት አካባቢዎች ያሉ ሱስን የሚያበረታቱ ቤቶች እንዳሉ፣ ይህም ተማሪዎችን ከዓላማቸው የሚያደናቅፍ ከመሆኑ አንጻር በቂ ትኩረት ተሰጥቷል? ሲልም ቲክቫህ ጥያቄ አቅርቧል።

ዘላለም (ዶ/ር) በምላሻቸው፣ “ትክክል ነው። የተማሪዎችን ሀሳብ፣ ልቦና የሚሰርቁ ጉዳዮች በትምህርት ቤት አካባቢዎች እንዳይኖሩ ባለፉት ዓመታት ጠንካራ እርምጃ ወስደናል” ብለዋል።

“ ከ3000 በላይ የሚደርሱ የተለያዩ መማር ማስተማር ሂደቱን ሊያውኩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ እርጃ ተወስዷል ” ብለው፣ “ አሁንም እንደዛ አይነት ፍላጎቶች በትምህርት ቤቶች ብቅ ብቅ እንዳይሉ መልሶ ጠንካራ እርምጃና ክትትል ያስፈልጋል ” ሲሉ አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

MAGIC CARPET SCHOOL ETHIOPIA

16 Oct, 12:23


ቀን፡- 06/02/2017 ዓ.ም
ማሳሰቢያ
ለማጂክ ካርፔት ትምህርት ቤት ወላጆች
የመፅሃፍ ግዢ እንድትፈፅሙ ማሳወቅን ይመለከታል
የመፅሃፍ ክፍያ የሚፈፀመው ትምህርት ቤት መሆኑ እያሳወቅን
በየክፍል ደረጃው ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የመፅሃፍቶቹ ጥቅል ዋጋ በሚከተለው መልኩ በመመልከት ከነገ ሃሙስ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት ቤት በመገኘት መፅሃፍቶቹ መግዛት የምትችሉ መሆኑ እናሳስባለን፡፡
1ኛ ክፍል 605 ብር
2ኛ ክፍል 660ብር
3ኛ ክፍል 810 ብር
4ኛ ክፍል 885 ብር
5ኛ ክፍል 913 ብር
6ኛ ከፍል 824 ብር
7ኛ ክፍል 1620 ብር
8ኛ ክፍል 1400 ብር
9ኛ ክፍል 2780 ብር
10ኛ ክፍል 3590 ብር
11ኛ ክፍል ናቹራል ሳይንስ 2485 ብር ሶሻል ሳይንስ 1900 ብር
12ኛ ክፍል ናቹራል ሳይንስ 2345 ብር ሶሻል ሳይንስ 1965 ብር
ትምህርት ቤቱ

MAGIC CARPET SCHOOL ETHIOPIA

11 Oct, 08:37


⭐️12ኛ ክፍል ምርጫ በተመለከተ

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በ 'Remedial' ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ ሞልተው እንዲጨርሱ መገለጹ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ " አንዳንድ ትምህርት ቤቶች በሲስተም ችግር ምክንያት የተማሪዎቻችንን የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርስቲ ምርጫ መሙላት ተቸግረናል " ባሉት መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር የምርጫ መሙያ ጊዜውን እስከ ረቡዕ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

🔤🔤🔤🔤  🔤🔤🔤
ቻናላችን ይህ ነው
👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/dam76

MAGIC CARPET SCHOOL ETHIOPIA

10 Oct, 10:36


👉የድጋሜ ማሳሰቢያ

የዩንቨርስቲ ምርጫን በተመለከተ

👉የ12ኛ ክፍል የዩንቨርስቲ ምርጫ ለማካሄድ ፖርታሉ እየሰራ ስላልሆነ  በትግስት ጠብቁ!!

✍️ተማሪዎች በተባለው ቀን ምርጫ ስላልመረጡ ችግሩ ሲቀረፍ የሚመርጡ መሆኑን ግንዛቤ ይፈጠርላቸው!!

MAGIC CARPET SCHOOL ETHIOPIA

07 Oct, 10:33


ማጂክ ካርፔት ትምህርት ቤት እሁድ መስከረም 26/2017ዓ.ም የወላጆች ጉባኤ ያከናወነ ሲሆን በዉይይቱ የ2016ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም እንዲሁም የ6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል የተማሪዎች ዉጤትና በትምህርት አጀማመር ዙርያ ሪፖርት በማቅረብና ወላጆች ሃሳብና አስተያየቶች በመቀበልና የወደፊት አቅጣጫ መመርያ በመስጠት ተከናዉኗል።

MAGIC CARPET SCHOOL ETHIOPIA

05 Oct, 11:28


በሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎቻችን