Últimas Postagens de Medina Tube || መዲና ቲዩብ (@medinatube) no Telegram

Postagens do Canal Medina Tube || መዲና ቲዩብ

Medina Tube || መዲና ቲዩብ
3,667 Inscritos
228 Fotos
58 Vídeos
Última Atualização 01.03.2025 10:58

O conteúdo mais recente compartilhado por Medina Tube || መዲና ቲዩብ no Telegram


ከሚኒ ኬክ እስከ የሰርግ ኬክ እንሰራለን!
#ለልደት
#ለኒካ
#ለሰርግ
#ለምርቃት ለተለያዩ ዝግጅቶች የናንተን ፍላጎት ለሟሟላት ትዛዛቹን እየጠብቅን ነው።
አድራሻችን :-ለቡ ጀም አንድ
TELEGRAM
https://t.me/lihamcake

TIK TOK
tiktok.com/@liham.cake
ይዘዙን ባሉበት እናቀርባለን!

☎️☎️☎️ ለማዘዝ
0934303143
0943372899 ይደውሉ

አብሬት || አብሬድ
____የጦሪቃው አውራድ ጎርፍ መፍሰሻ

አብሬድ ማለት ከአውራድ የተያዘ ሲሆን የጦሪቃችን አውራድ ጎርፉ የሚፈስበት ቦታ ነው::
<ቀደሠላሁ ሢረሁ>
▪️
አብሬቶች ድቅድቅ ባለው ጨለማ ወቅት 7ቤት ጉራጌ ሁላ ለአምልኮ ከሚጟዝላቸው ፥ ከሚገብርላቸው ፥ እንደ ንጉስ ከሚያዩዋቸው ከጣኦት አምላኪያን መሪ ቤተሰብ የወጡ ፀሀይ ናቸው:: ተተኪ የሀይማኖቱ መሪ ይሆናሉ ተብሎ ሲጠበቁ ኑረል ኢማንን ይዘው ብቅ ያሉ ፥ ሺርክን ከስሩ መንግለው የጣሉ ፥ ለኸልቁ እንደ ፀሀይ የበሩ የአላህ ኑር ናቸው:: ሠይዲ አባ ራሙዝ በአንዱ መድሀቸው መሽረብ ሸይኻቸውን ሠይድ ባኡ ሳኒ <በድቅድቁ ጨለማ መካከል የበሩ ፍጹም የሆኑ ሙሉ ጨረቃ> ብለው ያወድሷቸዋል::

▪️ሠላም ዐለይከ ሸምሠል ዲነል ኪራሚ
▪️በድሩል ዘማን ፊ ወሰጢ ዞላሚ

በጉራጌ እና አጎራባቾቹ ላይ ያለ ሙስሊም ሁሉ የሁዋላ ታሪኩን ቢያጤን አራት እና አምስት አባቱን ወደሁዋላ ቢቆጥር ከመቶ መቶ ወይንም ዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንቱ ጨለማ ላይ የነበረ ህዝብ ነበር:: ሙሉ ሰባት ቤት ጉራጌ ማለት ይቻላል መብረቅ አምላኪ ህዝብ ነበር:: በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መልኩ ለዛሬው ማንነታችን ለሂዳያችን ሰበብ ከአብሬት ሸይኾች አንዱ ሆነው እናገኛዋለን:: በተለይም ለጉራጌ ማህበረሰብ:: ነገር ግን ከአብሬት የወጣው ፀሀይ በጉራጌና አጎራባቾቹ ብቻ ተገድቦ የቀረ አይደለም:: ብዙሀኑን የሀገራችንን ክፍሎች አካሎ ከሀገር ውጪም ፀሀያቸው በርቷል::
▪️
በታላቁ የረጀብ ወር በእነዚህ ከዋክብቶች ሀሪማ ሐረመል አብሬት የከውኑ ሁላ ንጉስ የነብያችንﷺ መውሊድ እጅግ ደማቅ በሆነ መልኩ ይከበራል:: የጦሪቃው አውራድ እንደ ጎርፍ ይፈሳል ፥ የአላህ ራሕመት ይዘንባል ፥ የነብያችንﷺ ኑር ይንቧቧል ፥ መላይካው እንደ ጉድ ይወርዳል ፥ የታላላቅ አውሊያዎች ሩሕ ይሀደራል። ከሚታየው የማይታየው ታዳሚ ይበልጣል:: እናልህ ወዳጄ አብሬት ለመግባት ጟዝህን ጠቅልል ከዚህ ማኢዳ ተቋደስ::

አ    ብ    ሬ    ት ..... ረ  ጀ  ብ

አላህ ይውስደን እዚህ የተከበረ ቦታ🤲🤲
@MEDINATUBE

ይህ መቃብር የማን ይመስልሀል?

10.4 ቢሊዮን ዶላር ባለቤት ባለፀጋ የኩዌታዊ ታዋቂው ነጋዴ የናስር አል-ከራፊ መቃብር ነው።

ተመልከት አንድ ሳንቲም አብሮት አልተቀበረም ገንዘቡ ለወራሾች ጥሎት ነው የሄደው አላህ ይዘንለት መቃብሩም ከሌሎች የተለየ አይደለም ኢስላም የሀብታም እና የድሀ መቃብር ልዩነት የለውም።

ሀብት ያላችሁ አብሯችሁ ለማይቀበረው ገንዘብ ለተቸገሩት አጉርሱ ለታረዙት አልብሱ ሞት ሳይቀድማችሁ።
ሰጥቸህ ነበር ምን ሰራህበት ጥያቄ አለብህና።
@MEDINATUBE

ዐርባ የሶለዋት ጥቅሞች
===============
ኢማም ኢብኑል‐ቀዪም [ረሒመሁላህ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«ዐርባ ሶላት ዐለን‐ነቢይ [ﷺ] ጥቅሞች: ‐
❶ የአላህን ትእዛዝ መፈፀም።
❷ አላህም በነቢዩ [ﷺ] ላይ ሶለዋት ስለሚያደርግ ከአላህ ድርጊት ጋር መሳሰል። በእርግጥ የእኛና የአላህ ሶለዋት የተለያየ ነው። [የአላህ ሶለዋት እዝነት ሲሆን ከኛ ሲሆን ደግሞ ዱዓ ነው።]
❸ ከመላኢካዎች ጋር መመሳሰል።
❹ አንድ ጊዜ ሶለዋት ያደረገ ሰው አላህ ዐስር ሶለዋት ያደርግበታል።
❺ ሰውየውን አላህ በዐስር ደረጃዎች ከፍ ያደርገዋል።
❻ ዐስር ሐሰና (የበጎ ሥራ ምንዳ) ይፃፍለታል።
❼ ዐስር ኃጢኣት ይሰረዝለታል።
❽ የዱዓን ተቀባይነት ያስገኛል።
❾ የሙስጦፋን [ﷺ] ምልጃ ያገኛል።
❿ ወንጀልን ለማሰረይ ምክንያት ይሆናል።
⑪ ሰውየውን አላህ ከጭንቀት ይገላግለዋል።
⑫ በቂያማ ቀን ሰውየው ከነቢዩ [ﷺ] ቅርብ ይሆናል።
⑬ ድኻ ለሆነ ሰው ሶለዋት የሶደቃን ቦታ ይሸፍናል።
⑭ አስቸጋሪ ጉዳይን ያገራል።
⑮ የአላህና የመላኢካዎችን ሶለዋት ያስገኛል።
⑯ ሰውየውን ከወንጀል ያፀዳዋል። ንፅህናን ያላብሰዋል።
⑰ ሰውየው ከመሞቱ በፊት በጀነት እንዲበሰር ያደርጋል።
⑱ ከቂያማ ቀን ድንጋጤ ይጠብቃል።
⑲ ሰውየው የረሳውን ነገር እንዲያስታውስ ያደርገዋል።
⑳ ለሰላምታው የነቢዩን [ﷺ] ምላሽ እንዲያገኝ ያደርገዋል።
21. ስብሰባን ያሳምራል። ሶለዋት የተደረገበት ስብሰባ በቂያም ቀን ቁጭት አይከተለውም።
22. ድህነትን ያስወግዳል።
23. ስስትን ያስወግዳል።
24. አፍንጫው ይታሽ (ውርደት ይንካው) ብለው ነቢዩ [ﷺ] ካደረጉት ርግማን ይድናል።
25. ወደ ጀነት መንገድ ያስገባል። ሶለዋት የተወ ሰው ደግሞ ከጀነት መንገድ ይርቃል።
26. ከስብሰባ ክርፋት ያድናል። ምክንያቱም አላህና መልክተኛው [ﷺ] የማይወሱበት ስብሰባ ሁሉ የከረፋና የገማ ነው።
27. ኹጥባንም ሆነ ሌላን ንግግር ያሳምራል።
28. ሰውየው በሲራጥ ላይ የሚኖረውን ብርሃን ያበዛለታል።
29. ሰውየውን ከጭካኔ ያፀዳዋል።
30. ሶለዋት የሚያደርግ ሰው በምድርም ሆነ በሰማይ መልካም ስም እንዲኖረውና እየተወደሰ እንዲኖር ያደርገዋል።
31. ሶለዋት የሚያበዛ ሰው የተባረከ ይሆናል። ስራውና እድሜውም በረካ ይሆንለታል።
32. የአላህን እዝነት ያገኛል።
33. ሰውየው ለአላህ መልክተኛ ﷺ ያለው ፍቅር ዘውታሪ እንዲሆን ያደርጋል።
34. ዘውታሪ የሆነ የአላህ መልክተኛን [ﷺ] ውዴታ ያገኛል።
35. ቀና መንገድ መመራትን (ሂዳያ) ያገኛል። ቀልቡም ህያው ይሆንለታል።
36. የሰውየው ስም በነቢዩ [ﷺ] ፊት እንዲጠራ ያደርጋል።
37. በሲራጥ ላይ የሰውየው እግር እንዲፀና ያደርጋል።
38. ሰውየው የነቢዩን [ﷺ] ሐቅ በከፊል እንዲወጣ ያግዘዋል።
39. ሶለዋት አላህን መዝከርና ማመስገንን ያካተተ በመሆኑ ሰውየው ከአመስጋኞችና ከዛኪሮች ተርታ እንዲመደብ ያደርገዋል።
40. ሶለዋት ዱዓም ነው። ምክንያቱም በሶለዋቱ ሰውየው አላህ በሚወዳቸው እና በመረጣቸው ነቢይ ላይ ውዳሴውን እንዲያደርግ መለመን ማለት ነው። በዚያውም ሰውየው ጉዳዩ እንዲፈፀምለትና ጭንቀቱ እንዲወገድለትም እየተማፀነ ነው።
--------------------------
📚 «ጀላኡል‐አፍሃም ፊ ፈድሊስ‐ሶላቲ ወስ‐ሰላሚ ዐላ ኸይሪል‐አናም ﷺ»

አህባቦቼ በዱኣ እና በዚክረ ሶላት ዓለ ነብይ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንበርታ



ፋጢመቱ✍️✍️✍️
@MEDINATUBE


ሰላት የሌለው በምን ይረጋጋል??
ሰላት ባይኖረንስ በምን እንረጋጋ ነበር??


«يا بلالُ، أقِمِ الصَّلاةَ، أرِحْنا بها»
«ቢላል ሆይ! እስኪ ኢቃም በልና በሰላት አሳርፈን።»

@MEDINATUBE

ጭንቅ የበዛበት ሰለዋት ያብዛ የጋለ ብረት ውሃ ውስጥ እንደ መንከር እያየው ያሁሉ ጭንቅ ይወገዳል ።
@MEDINATUBE

የፍቅር ሐይል ግን ዐጂይብ ነው.. ሩሀችንንና ጀሰዳችንን የሚያጣምር አንዳች ውበት... ናፍቆቱ የማያልቅ፤ ውዴታው የማይሰለች፤ ትውስታው የሚነዝር አንዳች ነገር!

🌹ያ..የዘይነልዉጁድﷺ ፍቅር...ዱንያ ላይ በሚኖረን ቆይታ ህይወታችንን ሙሉ እሳቸውን አለመናፈቅ አይቻለንም። የናፍቆታችንን ሮሮ ለማስታገስ...አሏህ ይወፍቀንና ጀነት ላይ እስክናገኛቸው በትንሹም የሚያረግብልን ደግሞ ሰለዋት ነው!

« أَوْلَى النَّاسِ بِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَكْثَرُهُمْ عَلَىَّ صَلاَةً »

«የዉመል ቂያማ ላይ ለኔ ቅርቡ ሰው ማለት እኔ ላይ ሰለዋትን የሚያበዛው ነው»አሉ ዘይነልዉጁድﷺ♥️

🌹اللهم صلّ وسلم وبارك على سيدنا محمد النبى الأمي الزكي البهي الصفي النجي الوفي وأمطر علينا سحائب لطفك الخفي وحبك الجلي وعلى آله وصحبه وسلم🌹

@MEDINATUBE

በነጠላ ስም እየጠራሁ የትኛውንም ሙስሊም አላከፍርም ' ሳዳቶቻችን እንደማያከፍሩት!

እንኳን ጭፍን ተከታዩን   ኢብኑ ተይሚያን እንኳን እማያከፍሩ ትላልቅ ኡለማኦች  ብዙዎች ናቸው ? እሚገርመው እነሱን ያላከፈረንም ማክፈር የመጣልን ግዜ ነው-   በአቂዳ ተመሳስለከው በ አካሄድ ያልተመቸህን ሁላ በቃ ልታከፍረው አስበሃል ?     እስኪ መወራረፉን ትተን በአደብ እናውራ  ' ምን ጃሂል ብንሆንኮ  "ካፊር" እሚለው ቃል ሳንቀራም ያስደነግጠናል

   ሳዳቶቹ ከወሃቢያም ጋር ቢሆን እምንወያይበትን ስልት እና አደብ  ሲጠቁሙ "ማንንም አንተ ካፊር አትበል 'በጅምላ ይሄ አስተምህሮ ለጥመት ይዳርጋል" ብለህ ሂድ ብለው ማስተማራቸውን በበቂ ማስረጃ ማቅረብ ይቻለናል -እናቀርባለንም በአላህ ፍቃድ!  ግን ከመከባበር ጋር በአደብኛ!     ህጻናት ሲሳደቡ አደቡን ማስታወስ እንጂ ሌላ ምን አለ ?

                   የዛሬ 4 አመት አካባቢ በወሃብያዎች ጉዳይ  ስሜታዊ ሆነን በጀመዐ እያወራን ሸይኽ ኸይሩዲን አል ቀጥበርይ (አላህ ይጠብቃቸው) አስተውለውን       አደብ እንዳልሆነ  ቆጣ ብለው የነገሩኝን አልረሳም ' እኛ በስሜታዊነት ስንቆጣ    እነሱ በብስለት ደረጃዎች ሺ እጥፍ ይቀድሙናል.... ቀጥተኛ መንገድ እንዲመሩ ከፈለግክ  እንደነሱ ችኩል አትሁን  ብለው ከአደብ አንጻር መርሳት የሌለብኝን ጠቆሙኝ.... ይህንን ይበልጥ  እምንረዳው እናት አባታችን የወሃቢያ ሸይኽ አሳስቱኣቸው  በአንድ ቤት እየኖርን እንዴት ከነሱ ጋር መኑኣኑኣር እንዳለብን  ስናስብ ነው - ዘለል ሲድ ደግሞ የነቢ ኡመት መሆን ያለውን ክብር ከትልልቆቹ አንደበት ስንሰማ!

         ለማንኛውም እንኳን እኔን እንጭጭ  ዒልም ፈላጊው እነ ሙሐመድ ሙተወሊይ አሻዕራዊይ  ፣ ኢማም  ረመዳን አልቡጢይ ፣የሻም ሱፊይ ሙሐዲሶች በጅምላ ' የአዝሃር  ሊቃውንት ሌላም ብዙዎቹ  ከዘመናችንም የየመን ተሪም አህለልበይቶች  ከማክፈር ዘመቻዎች አልተረፉም......  ከጦሪቃ መሻይኾች በነቅሸበንዲያው እነሸይኽ ናዚም አል ሃቃኒይ 'ሸይኻቸውን ሸይኽ አብዱላህ አዳጊስታኒይ እና ደረሶቻቸው "ከራሳቸው ከአብደሪይ ጦሪቃ ሪፋኢያዎች  በሃኡዲን ረዋስ እና መሻይኾቻቸው ' ከቃዲሪያም በርካታ እውቅ መሻይኾች " ኢብኑ ተይሚያን ሙብተዲዕ ከማለት ውጪ በካፊርነት አይገልጹም" ከሻዚሊያው አሁን ካሉት ሸይኽ ሙሐመድ ፈውዚይ አል ከርከሪይ ጀምሮ በሲልሲላው ያሉት ሳዳቶች  ሙስሊምን ከማክፈር የተቆጠቡ ናቸው (የሐበሻ ኡለማኦችን አቋም  እስኪ እናንተው ንገሩን?)
         

                ጌታው  የኡመቱ ዐሊም ' ሙሂቡ ማዲሀ ረሱሉ ' ቃዲ ዩሱፉ ነብሃንይ ይህንን 'የአላከፍርም' አካሄድ አንጸባርቀው "ጃሂል" ባስ ብሎም ካፊር  ተበለው የለም?  ነብሃኒይ የነቢው ገበር  "ኪታቦቼን ሁሉ ሳንሱር ያረጉልኝ የመዲናው ሙስጦፋ ናቸው" ያሉቱ ዩሱፍ አነብሃንይ.......  በኪታቦቻቸው " ኢብኑ ተይሚያ ረሂመሁላህ" ስላሉ ብቻ ካፊር የተባሉት? 
                            ብቻ የአካሄድ ልዩነት ላይ በ መከባበር መጓዝ ለኛው  እሚበጅ ይመስለኛል'ካልሆነ በአብደርይ (ሸይኽ አብዱላህ አልሃረሪይ ረሂመሁላህ) እና ቀዳሚ የአሻዒራ ሱፊያ ት/ቤቶች መሃከል የተፈጠሩ አለመስማማቶች አሉ የሚሉ ኡለማኦችን ኪታብ ለመግለጥ  ግድ ይሆናል  ወላሁ አእለም.....        አስተያየቶቻሁን እጠብቃለሁ

ሰላም ይድረሶት ሆዴ
@MEDINATUBE

#ሰይዲ  ሁስኒ ሱልጣን  አዲስ || መንዙማ
@MEDINATUBE
@medina_tube

ሙስሊም ሆነህ አረንጓዴ ልብስ ስታይ ውስጥህ የሚረበሽ ከሆነ ቢቀራብህ መልካም ነው:: የጀነት ሰዎች ልብስ ውስጥ በቁርአን ብዙ ቦታ የተጠቀሰው አረንጓዴ ልብስ ነው:: ወርቅ እና ሀር ለወንድ ተከልክሏል:: አረንጓዴ ልብስ ግን አልተከለከለም:: የነቢያችን صلى الله عليه وسلم ጥምጣም አረንጓዴ ነበር:: አሁንም ድረስ ቱርክ ሙዚየም ውስጥ አለ:: የኢማም ዐሊይ رضي الله عنه ጥምጣምም አረንጓዴ ነበር:: አረንጓዴ መልበስ የነቢያችን صلى الله عليه وسلم እና የጀነት ሰዎች ሱና ነው:: አላህ አድንቆ ነው የነገረን::
@MEDINATUBE