አሏህ ብሎ ያለው ቀና በል አትዘን
የሰላም የፍትህ አርማና ማዕዘን
ደግነት ብቻ ነው ሙሀመድ ያዘዘን
የኛ ነብይ..ﷺ
ራሱን ለአሏህ ሽቅብ ቀና አድርጎ
ከረሂሙ ጌታ እዝነቱን ፈልጎ
በሙሽሪኮች በደል እየደረሰበት
ስሙ እየጎደፈ ዋሽተው ቀጥፈውበት
ፍፁም በሌለበት እየተወቀሰ
ጌታየ ህዝቦቼን ብሎ ያለቀሰ
ሙሀመድﷺ
የስልጣኔ አርማ የእድገት ከፍታ
ስሙ እማይረሳ ለሰከንድ ላፍታ
እንኳን ላመነበት በመንገዱ ፀንቶ
አያውቅም ጠላቱን በክፋት አንስቶ
ከመጥፎ ከልክሎ መልካሙን ያሳያል
ከማንም ከምንም ሙሀመድ ይለያል
መከራው ሲጠና በአሏህ ይወከላል
ችግር ሲደራረብ ሀስቢየሏህ ይላል
መደምደሚያው ነብይ ስሙ ማን ይባላል?
«ውዶቼ ሶለዋት እናውርድ
መልካም ኢስነይን
✍️የሙሂቡን ግጥም
@MEDINATUBE