❝አትገረምም!❞
*********
አየህ አገልግሎት ገደብ የለውም! ዕድሜ፣ ቦታ፣ ስራ፣ ትዳር፣ ሁኔታ፣ ሌላውም ምክንያት አይገድበውም። ይህን መልዕክት የምትመለከተው ወንድሜ ሆይ ያኔ በልጅነት ሰንበት ትምህርት ቤት ያሳለፍከውን ጊዜ አስብ፤ መልዕክቱን የምታነቢውም እህቴ፣ ያን የማይረሳ የአገልግሎት ዘመን አስቢው! ዝማሬ ለመቆም፣ መዝሙር ለማጥናት፣ ያሬዳዊ ዝማሬን አጥንቶ ለማቅረብ፣ ድራማ እና ጭውውት ለመስራት፣ አልባሳት ለብሶ ለመዘመር፣ በየበዓላቱ በአልባሳት ደምቆ ቄጤማ እና ዘንባባ ይዞ በየከተማው እየዘመሩ ለመሄድ፣ በየወርሃዊ የዝክር መርሐግብሮች ላይ ጸበል ጸድቅ ለመቃመስ፣ በየልቅሶው ቤት አጽናኝኝ እመአምላክ እያሉ እየዘመሩ ሐዘንተኞችን ለማጽናናት፣ የታመሙትን ድውይ ነኝ አንተ አድነኝ እያሉ እየዘመሩ በሽተኞች በሽታቸውን እንዲረሱ ለማድረግ፣ በየሰርጉ ላይ መርአዊ ሰማያዊ እያሉ ለማጀብ፣ በየንግሱ ታቦታቱን በአልባሳት አሸብርቆ ለማጀብ ያለህን ፍቅር እና ፍላት ቅናት እና መነሳሳት አስበው ወንድሜ። እስኪ ትዝ ይበልሽ እህቴ!
ዛሬስ? ዛሬማ ትልቅ ሆንና! መንግስት ሰራተኞች ደመወዝተኞ ሆንና! ዛሬማ ጊዜ የለንማ፣ ትላልቆች ሆነን አግብተን ወልደን ከበድና፣ ዛሬማ ዕድሜያችን ገፍቶ አልባሳት ለብሶ ማገልገል ያሳፍረናላ፣ ጡረታ ወጣና! ያሳዝናል።
ግን የቤተክርስቲያን ፍቅር እና አገልግሎት በእውቀት ለገባው ምንም ነገር ላለማገልገል ምክንያት አይሆነውም። ብዙዎች መንፈሳዊው እውቀት ላይ ደካሞች ስለሆኑ ተበተኑ። የገባቸው ግን ምንም አይገድባቸውም። ልክ እንደኚህ አባት! ለአባታችን ረዥም እድሜ ከጤና ጋር ያድልልን!
ንሽኩር ረቢና!
24/11/2013 ዓ.ም (ቅዳሜ)