Learn English Ethiopia

@learnenglish_ethiopia


Welcome to the learning of English

Learn English here!
For Questions @Mr_Sofiy

Learn English Ethiopia

21 Jan, 00:26


Alternatives "I have no idea"
"ምንም ሃሳብ የለኝም" ማለት ስትፈልጉ 👇

👉 I'm not sure.
👉 I have no clue.
👉 I'm in the dark.
👉 I'm not informed.
👉 I have no concept.
👉 I'm not up to date on that.
👉 I'm not aware of that.

@LearnEnglish_Ethiopia
@LearnEnglish_Ethiopia

Learn English Ethiopia

21 Jan, 00:26


ንፅፅር ለመግለፅ የምንጠቀምባቸው

Comparatively - ከሌላ ጋር ሲነፃፀር

Eventhough - ቢሆንም

In contrast - በንፅፅር ፣ በተቃራኒው

Whereas - ሲሆን ፣ በተቃራኒው

On the contrary - በተቃራኒው

However - ነገር ግን

Instead - በሱ ፈንታ ፣ ከ ___ ይልቅ

On the other hand - በሌላ በኩል

@LearnEnglish_Ethiopia
@LearnEnglish_Ethiopia

Learn English Ethiopia

21 Jan, 00:25


Before was was was was was is😁

@LearnEnglish_Ethiopia
@LearnEnglish_Ethiopia

Learn English Ethiopia

21 Jan, 00:25


20 Common Phrasal Verbs

Share 🤙
@LearnEnglish_Ethiopia
@LearnEnglish_Ethiopia

Learn English Ethiopia

21 Jan, 00:24


Tenses • የ ጊዜያት ሰዋስው

Tense ማለት ድርጊትን በጊዜ የምንለካበት ወይም የምንገልፅበት የሰዋስው ክፍል ነው።

There are only three basic tenses in the English language: the past, the present and the future:
3 መሰረታዊ የጊዜያት ሰዋስው ያሉ ሲሆን እነሱም Past (ያለፈ ጊዜ) ፣ Present (የአሁን ጊዜ) እና Future (የመጪው ጊዜ) ናቸው።


3ቱም መሰረታዊ የጊዜያት ሰዋስው በውስጣቸው 4 ተጨማሪ የጊዜያት ሰዋስው አሏቸው፦ Simple, Continuous, Perfect እና Perfect Continuous ናቸው።

1) ለዛሬ ስለ Past Tense እንመለከታለን።

A) Past simple

🕰 ባለፈ ጊዜ የተሰራ ነገርን ለመግለፅ እንጠቀምበታለን።

አወንታዊ - S + V2 + Obj
Eg: He watched a movie.

አሉታዊ - S + didn't + V1 + Obj
Eg: He didn't watch a movie.

ጥያቄ - Did / Didn't + S + V1 + Obj
Eg: Did he watch a movie?
Didn't he watch a movie?


🕰 Conditional type 2 ላይም እንጠቀምበታለን

Eg: If I found her address, I would send her a gift.

🕰 ወይም ተከታታይ የሆኑ ባለፈ ጊዜ የተፈፅጸሙ ድርጊቶች ለመግለፅም እንጠቀምበታለን።

Eg: I got up, had breakfast and then went to school.

Past Continous, Past Perfect and Past Perfect Continous....
ይቀጥላል

Share 🤙
@LearnEnglish_Ethiopia
@LearnEnglish_Ethiopia

Learn English Ethiopia

21 Jan, 00:24


​​🔘 Who • ማን - ነገርን ማን እንደሰራው ለመጠየቅ ወይም አንድ ሰው ማን እንደሆነ ለማወቅ
Example 1: Who was disturbing the class?
ክፍሉን እየረበሸው የነበረው ማን ነው?
Example 2: Who is the President of Ethiopia?
የኢትዮጲያ ፕሬዝደንት ማን ነው?

🔘 What • ምን - መረጃ ለመጠየቅ ወይም አንድ ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅ
Example 1: What does your father do?
አባትህ ምንድነው የሚሰራው?
Example 2: What is your favourite sport?
የምትወደው የስፖርት አይነት ምንድነው?

🔘 When • መቼ - ድርጊት የሚፈፀምበት/የተፈፀመበት ጊዜ ለማወቅ
Example 1: When will you come home?
መቼ ነው ወደ ቤት የምትመጣው?
Example 2: When did you send the money?
ገንዘቡን የላክከው መቼ ነው?

🔘 Where • የት - ቦታ ለማወቅ
Example 1: Where is your home?
ቤትህ የት ነው?
Example 2: Where were you yesterday?
ትላንት የት ነበርክ?

🔘 Why • ለምን - ምክንያት ለማወቅ
Example 1: Why are you so sad?
ለምንድነው እንደዚ ያዘንከው?
Example 2: Why haven't you called?
ለምንድነው ያልደወልከው?

🔘 Which • የትኛው - ለምርጫ እንጠቀምበታለን
Example 1: Which of these is the best mobile?
ከነዚ የትኛው ነው ምርጥ ሞባይል?
Example 2:Which is your book?
ያንተ መፅሐፍ የትኛው ነው?

🔘 Whose • የማን - ባለቤትነት ለማወቅ
Example 1: Whose bag is this?
ይህ ቦርሳ የማን ነው?
Example 2: Whose bike is that?
ያቺ ሳይክል የማን ናት?

🔘 How • እንዴት - ነገሮች እንዴት እንደሚሰሩ ሂደታቸውን ለማወቅ ፤ ሰዎች እንዴት እንደሆኑ ለማወቅ (ጤናቸው/ሁኔታቸው) እና እና ዋጋ ወይም ብዛት ለማወቅ
Example 1: How does the remote work?
ሪሞቱ እንዴት ነው የሚሰራው?
Example 2: How is your sister doing?
እህትህ እንዴት ናት?
Example 3: How much did it cost?
ስንት ተከፈለበት?

Share 🤙
@LearnEnglish_Ethiopia
@LearnEnglish_Ethiopia

Learn English Ethiopia

21 Jan, 00:23


Tense 🫡

ልዩነቱን በደንብ ተመልከቱት !👆

SHARE 🤙
@LearnEnglish_Ethiopia
@LearnEnglish_Ethiopia

Learn English Ethiopia

21 Jan, 00:22


Proverbs • ምሳሌያዊ ንግግሮች

One is never too old to learn
ዋን ኢስ ነቨር ቱ ኦልድ ቱ ለርን


ለመማር/እውቀት ለመቅሰም የእድሜ ገደብ የለውም።

A closed mouth catches no flies.
ኤ ክሎዝድ ማውዝ ካችስ ኖ ፍላይስ


ዝም ባለ አፍ ዝምብ አይገባበትም

A good conscience is a soft pillow.
ኤ ጉድ ኮንሸንስ ኢዝ ኤ ሶፍት ፒሎው


ንፁህ ህሊና ምቹ ትራስ ነው

Dead men tell no lies
ዴድ ሜን ቴል ኖ ላይስ


የሞተ ሰው ምንም ምስጢር አያወጣም ለማለት እንጠቀምበታለን።

Easier said than done
ኢዝየር ሰይድ ዛን ዳን


ለመናገርማ ቀላል ነው የሚከብደው ለመስራት ነው

እንግሊዘኛን በቀላሉ ለመማር 🤙
@LearnEnglish_Ethiopia
@LearnEnglish_Ethiopia

Learn English Ethiopia

21 Jan, 00:22


Idioms • ፈሊጣዊ ንግግሮች

Cloud nine • ክላውድ ናይን
በጣም መደሰት

Eg: She was on cloud nine when he proposed to marry her.
የጋብቻ ጥያቄ ሲያቀርብላት በጣም ተድስታ ነበር።

Mean the world to • ሚን ዘ ዎርልድ ቱ
በጣም አስፈላጊ ወይም በጣም ውድ

Eg: His daughter means the world to him.
ለእሱ ልጁ በጣም ውድ ናት/ዓለሙ ናት።

Chase rainbows • ቼዝ ረይንቦውስ
የማይሆን ነገርን መከተል/መፈልግ

Eg: She is trying to get in to Oxford, but I think she is chasing rainbows.
ወደ ኦክስፎርድ ለመግባት እየሞከረች ነው ግን ሲመስለኝ የማይሆን ነገር ነው።

Give a hard time • ጊቭ ኤ ሃርድ ታይም
ለአንድ ሰው ማናደድ ወይም ነገሮች ከባድ ማድረግ

Eg: Her boss is giving her a hard time.
አለቃዋ ነገሮች እያከበደባት ነው።

Caught red handed • ከውት ሬድ ሃንድድ
እጅ ከፍንጅ መያዝ

Eg: He was caught red handed when he was stealing the diamond.
አልማዙን ሲሰርቅ እጅ ከፍንጅ ነበር የተያዘው።

@LearnEnglish_Ethiopia
@LearnEnglish_Ethiopia