KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ / @kmuelearning Channel on Telegram

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

@kmuelearning


Kotebe University of Education Community / አዲስ ነገር መረጃ /

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ / (Amharic)

ቶረከፐ ዩኒቨርሳቶች ትምህርት ተማሪ የቶረከፐ ዩኒቨርሳቶች ምክር ቤት አስተማሪ ለተማሪዎች የህዝብ አቅም እንዲሆን የቶረከፐ (KUE) እና መከላከል አስተዳዳሪ ቢያንስ ሼርቢሊንጊና እጅግ ተማርኛ ከዩኒቨርሳቶች በሚሆንበት ምክር ቤት ፕሮግራም ሆስፒታል ለመሆኑ ወጥቷል። ይህ ሼርቢሊንጊ ትምህርት እና ትምህርት መከላከል በሆቴል መባቻ መሳሪያና አቃላላ ምክርታቸውን ከተከፋፈ የሚጠቀሙ ትምህርት ቢትልን አፕሊኬሽን ምንም አልተማመርም ፣ ምንም ኢንፖሽን ምንም ሾዬርና። እና እንደገና ውስጥ ያሉ ቦላዮችና ቶረከፐ ዩኒቨርሳቶች እጅግ ከተቸጋሪ በታች በመከላከልና በትምህርት መቆየታ ላይ ለመሆኑ ሼርቢሊንጊን እንዲሆን ውጤቷል። እንደገና ከተቸጋሪ እንዲቆየታ እና በመከላከል በትምህርት መረጃና መረጃ ለማቅረብ ተከማች ከሼርቢሊንጊሆስፒታል ጋር ያግዝሁት እና መረጃን ከፈለግን እና ከተቆጣጠር በኋል ሼርቢሊንጊን እንደገና ለመዋናው ውጤቷል።

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

08 Feb, 03:47


* ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ስለሳይንስ ላቦራቶሪ አጠቃቀም ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል*
===================
በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ እና አጎራባች ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የግል እና የመንግስት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የፊዚክስ፣ የኬሚስትሪ እና የባዮሎጂ መምህራን ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡
ዶ/ር ቅድስት ዮሐንስ ፤ የምር/ማ/አገ/ጊ/ም/ፕ እንዳሉት እንደዚህ ዓይነት ሥልጠናዎች ለተሻለ የመማር ማስተማር ሥራ ያላቸው አስተዋጽኦ ከሚባለው በላይ ነው።

👉የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት_

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

06 Feb, 11:15


List of Summar Modality Exit Exam Takers at Kotebe university of Education:

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

05 Feb, 14:48


‹‹ ልጆች ከካርድ ውጤት በላይ ናቸው ››

#Ethiopia | እንደ ሰኔ 30 ባይሆንም ግማሽ ሴሚስተር ውጤትም ውጥረቶች አሉት፡፡ በልጆች ማንነት እና ልጆች አጥንተው በሚያገኙት ውጤት መካከል ሰፊ ልዩነት አለ፡፡

በአሪዞና ስቴት ዩኒቨርስቲ የተካሄደ ጥናት ወላጆች ይበልጥ ትኩረት የሚሰጡት ለልጆቻቸው ነው ወይንስ ለልጆቻቸው የፈተና ውጤት የሚለውን መፈተሸ ነበር፡፡

የጥናቱ ግኝት ለልጆቻቸው ትኩረት ከመስጠት ይልቅ አጥንተው ለሚያገኙት የትምህርት ውጤት ይበልጥ ትኩረት የሰጡ ወላጆች በልጆቻቸው ሊያዩ የጓጉትን ሳያገኙ ቀሩ፤ ልጆቻቸው ያስመዘገቡት ውጤት አነስተኛ ሆኖ ተገኘ፡፡

ልጆች አጥጋቢ ውጤት እንዲያመጡ ማበረታታት መልካም ሆኖ ሳለ የልጅን መሰረታዊ ፍላጎት ( መወደድ፣ መደመጥ፣ ትኩረት ማግኘት፣ የጋራ ጊዜ …) ችላ ተብሎ ለፈተና ውጤት ይበልጥ ትኩረት መስጠት ሚዛናዊነት ይጎድለዋል፡፡

💡 ምክረ ሃሳብ

👉 ልጅ ከፍተኛም ሆነ ዝቅተኛ የትምህርት ውጤት ቢያመጣ ከካርድ ውጤት በላይ ነው፡፡ ወላጅ ለልጁ አስተማማኝ ደህንነት እንዲሰማው ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

👉 የካርድ ውጤት ዝቅተኝነት የወላጅ ፍቅርን ሊያሳጣ አይገባም፡፡ ውጤት ሊለዋወጥ ይችላል፤ የወላጅ ፍቅር ግን ከሁኔታ ሊያልፍ ይመከራል፡፡

👉 የልጅን ድክመት ማገዝ፤ ሙከራዎችን ማበረታታት ያስፈልጋል።

👉 ያለ ዓላማና ያለአቅም ወደዚህ ምድር የመጣ ልጅ የለም፡፡

መውጫ
✍️ ልጆች ምንም ዓይነት ውጤት ቢያስመዘግቡም ለራሳቸው ያላቸውን ክብርና ራስ መተማመን አንውሰድባቸው፤ እንደምንወዳቸውና ከጎናቸው እንደሆንን እናረጋግጥላቸው። ይህ የልጆችን አለም ይቀይራል።

[ https://t.me/childdevtnetwork ]
✍️ ብርሃኑ በላቸው አሰፋ
የክቡር ልጆች ደራሲ

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

05 Feb, 06:28


FAITH Project Holds Third General Assembly at Kotebe University of Education

🇪🇺🇪🇹🇪🇺🇪🇹🇪🇺🇪🇹🇪🇺🇪🇹🇪🇺🇪🇹🇪🇺🇪🇹🇪🇺🇪🇹🇪🇺🇪🇹

The FAITH project, coordinated by Kotebe University of Education and funded by the European Union, successfully held its third General Assembly (GA) on February 4, 2025.

Under the theme "Ethiopian Applied Science Universities are: F(itted), A(djusted), I(nnovative), T(rendy), and H(olistic) to Meet the Labor Market," the assembly provided a platform to evaluate the project's progress and discuss its future direction.

Dr. Berhanemeskel Tena, President of Kotebe University of Education, opened the workshop with a welcoming speech, highlighting the successful rollout of the project across three applied science universities in Ethiopia over the past year. He emphasized that the completion of Work Projects 1, 2, and 3 has not only demonstrated strong performance but also strengthened institutional capacity for future initiatives.

Dr. Berhanemeskel also underscored the vital role of the FAITH project in enhancing Ethiopia’s educational system. He noted that EU-funded projects, compared to those with other organizations, have been more flexible and practical in their implementation. Expressing gratitude to the European Union for its financial support, he also acknowledged the participating universities for their valuable contributions. Additionally, he conveyed the EU’s commitment to further strengthening support and achieving even greater results in the future.

Dr. Ephrem Tekle, FAITH project coordinator at Kotebe University of Education, praised the project's effectiveness while emphasizing that the next phase will require significant effort. He highlighted the importance of collaboration among stakeholders to ensure continued success.

The General Assembly also facilitated discussions on challenges encountered during implementation and potential solutions. Participants included representatives from universities and institutions in Germany, as well as Minsistry of Education, Wolaita sodo University, Jigjiga University, and Kotebe University of Education.

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

05 Feb, 04:09


የዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ስፖርት ውድድር የስፖርት ዓይነቶችና የተሳታፊ ስፖርተኖችን ቁጥር በማሳደግ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ አስታወቁ።
-----------------------------------

(ጥር 28/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ሳንስና ቴክኖሎጂ የኒቨርስቲ ሲካሄድ የቆየው የስፖርት ፌስቲቫል በሐዋሳ የኒቨርስቲ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በውድድሩ መዝጊያ ላይ እንደገለጹት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስፖርት ውድድር ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተጠናክሮ የሚካሄድ ይሆናል።

የትምህርት ሚኒስቴር ውድድሩ ተሳታፊ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በስፖርት አይነቶችና የተሳታፊ ስፖርተኞችን ቁጥር በማሳደግ የበለጠ ደማቅና ቀጣይነት ያለው አመታዊ ክንውን ለማድረግ ሰፊ እቅድ መያዙንም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡

የስፖርት ፌስቲቫሉ በተሳታፊ ተቋማትና ተማሪዎች እንዲሁም ለአገሪቱ ዜጎች አንድነት፣ እድገትና ልማት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ታስቦ እንደሚቀረጽም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጨምረው ተናግረዋል።

የውድድሩ አስተናጋጅ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳው በበኩላቸው በእግር ኳስ በቴኳንዶ ፣በአትሌቲክስ ፣ በቼዝና በባህላዊ ስፖርቶች የተካሄደው ፌስቲቫል በከፍተኛ ተሳትፎና በመልካም ስፖርታዊ ጨዋነት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስፖትር ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አባይ በላይሁን በበኩላቸው ውድድሩ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የሚያስችል በመሆኑ የዘርፉ ባለድርሻዎች በትኩረት ሊሰሩበት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡።

በውድድሩ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ አጠቃላይ አሸናፊ ሲሆን በወንዶች እግር ኳስ ወሎ ዩኒቨርስቲ ፣ በሴቶች አትሌቲክስ መከላከያ ፣ በወንዶች አትሌቲክስና ባጠቃላይ አትሌቲክስ ሐረማያ፣ በወርልድ ቴኳንዶ ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ አሸናፊዎች ሲሆኑ የአዲግራት ዩኒቨርስቲ የምስጉን ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የውድድሩ አሸናፊዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጠሹኔና እና ሌሎች እንግዶች እጅ የዋንጫ ተበርክቶላቸዋል።

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

05 Feb, 03:32


https://www.linkedin.com/posts/mitiku-k-kayamo_bmtblhblzbnmbmtbpkbqdbph-activity-7292574331199467520-IPd1?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

05 Feb, 03:22


*በዩኒቨርሲቲው የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡*

🥸🥸🥸🥸🥸🥸🥸🥸🥸🥸🥸🥸🥸🥸🥸🥸

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ላይ በተደረገው ውይይት፣ የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና በመክፈቻ ንግግራቸው የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙ በተቀናጀ ቡድናዊ ሥራ (team work ) የተመዘገበ የጋራ ውጤት ነው ፤ በመሆኑም ለቀጣይ የተሻለ ሥራ የዚህኛውን ሴኬት፣ ተግዳሮት እና እንዲሁም ለተሻለ አፈፃፀም በተወሰዱት አማራጭ መፍትሔዎችን በደንብ መገምገም ቀጣይ ቀሪ ሥራዎችን በተሻለ ለመከወን ይረዳል ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው የስትራቴጂክ ዕቅድ ጽ/ቤት ሥራ አስፈጻሚ አቶ አስናቀ ጉዲሳ፣ የዩኒቨርሲቲው ቁልፍ አፈጻጸም አመልካቾች ሰነድ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራሮች ጀምሮ ባለው መዋቅር ሁሉ በየደረጃው የተፈራረሙት እና ተግባራዊ ማድረግ የጀመሩት መሆኑን በመጥቀስ፣ በግማሽ ዓመቱ በታየው የሥራ አፈጻጸም የዩኒቨርሲቲው የትኩረት አቅጣጫ ልየታ፣ በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በአስተዳደር ዘርፍ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን አመልክተዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎችም የሆኑት (የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች) በሪፖርቱ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ፣ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በመሠረት ልማት ግንባታም ሆነ በሌሎች ዘርፎች እየታዩ ያሉ ለውጦች እና ስኬቶች አስደሳችና የተሻለ ምቹ የትምህርት ተቋም ለመፍጠር ማናጅመንቱ እያደረገ ያለውን ጥረት ተቋሙ ገና አሁን የዩኒቨርሲቲ ገጽታ እየተላበሰ ያለ በመሆኑ አመስግነው ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል። አያይዘውም የሀገሪቱን የትምህርት እና የመምህርነት ሙያ ችግር ለመፍታትም በጥናት ላይ የተመሠረተ ምክረ ሃሳብ ለማቅረብ የሚያስችል ሥራ መሥራት ለነገ የማይባል እንደሆነ በማንሳት አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም ፕሬዚዳንቱ መድረኩን ሲያጠቃልሉ ቀደም ሲል በበጀት ዓመቱ ለማሳካት የታቀደውን ሙሉ ለሙሉ ያሳካ መሆኑን በመግለጽ፣ ነገር ግን በተገኘው ውጤት መዘናጋት ሳይሆን በቀሪዎቹ ጊዜያትም የዓመቱን ጠቅላላ ዕቅድ በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀም በርብርብ እና በኃላፊነት ስሜት መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

_👉የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት_

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

02 Feb, 06:16


The Exit Exam Program of different subjects for Tir 26-30 at KUE

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

02 Feb, 04:51


ከጅማሮው (1971 ዓ.ም ) ጀምሮ በተለያዩ አመታት ከባህርዳር መ/ኮሌጅ በፔዳጎጂካል ሳይንስ (Pedagogical Science) ተመርቀው ሀገራቸውን እስከጡረታ ካገለገሉ እና በማገልገል ላይ ካሉ የፔዳ ፍሬዎች (በከፊል) ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲን በጎበኙበት ወቅት።
🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓

🏆እናንተ የፔዳ ትሩፋት ፔዳጎጂክሶች፦ ለትምህርት ሥርዓታችን የምትነበቡ ተንቀሳቃሽ ቤተመጽሐፍቶቻታችን 📓ናችሁ🏆

ውዶቻችን የትምህርት ልቃውንት፤ አሁንም ዕውቀታችሁ እና በዘመናት ያካበታችሁት ልምዳችሁ ያስፈልገናልና ልታካፍሉን ቃል ስለገባችሁልን በትውልድ ስም እናመሠግናችኃለን🙏

ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር)
የኮትዩ ፕሬዚዳንት

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

23 Jan, 06:52


Members are visiting the under-construction building at KUE, feeling bored.

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

07 Jan, 16:07


https://youtube.com/shorts/DkP-fDHg4lI?si=mRBQlkoCiGV9-RMY

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

07 Jan, 15:09


ቤንዚን በሊትር 101.47 ብር ሲገባ ናፍጣ በሊትር 98.98 ብር ሆኗል።

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ተወስኗል።

በዚሁ መሰረት ፦

➡️ አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር፣

➡️ አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር፣

➡️ አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር፣

➡️ የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር፣

➡️ አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር

➡️ አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር ሆኖ እንዲሸጥ ተወስኗል።

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

02 Jan, 02:30


የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የበላይ አመራሩ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት የሚከናወኑ ቁልፍ ተግባር አመልካቾች ርክክብ አደረጉ።
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️

የኢ.ፊ.ዴ.ሪ ትምርህርት ሚኒስቴር ከሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቦርድ ሰብሳቢዎች እና ፕሬዚዳንቶች ጋር በየተልዕኮአችን ለ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም KPI: Performance Contract Agreement” መፈራረሙ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መነሻነትም ዛሬ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም በዩኒቨርስቲ ደረጃ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ከምክትል ፕሬዝዳንቶች እና ከጽ/ቤት ሃላፊ ጋር በየዘርፎቻቸው ካስኬድ በተደረጉ የበጀት ዓመቱ ዕቅድ ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ላይ “Performance Contract Agreement” ተፈራርመዋል፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ መክፈቻ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ባስተላለፉት መልዕክት እንደሀገር የተጣለብን ኃላፊነት ከፍተኛ ነው ። በዚሁ እምነት የኮንትራት ውሉ የትምህርት ዩኒቨርሲቲውን ተሻጋሪ በሆነ ጠንካራ መሠረት ላይ ለመመሥረት እያደረግን ያለነውን ጥረት የሚደግፍ፤ ሥራን በቁልፍ ተግባር በመለየት በጊዜ ለክቶ በየደረጃው ላሉ አመራሮች በመስጠት የተጀመረውን ተቋማዊ ለውጥ የሚያሳልጥ ነው ብለዋል።

የኮንትራት ውሉን በዩኒቨርሲቲያችን ቦርድ ሰብሳቢ እና ፕሬዚዳንቱ በኩል ከትምህርት ሚኒስቴር የበላይ አመራር ጋር እንደተፈራረምን እንዴት ወደታች እንደምናወርድ የካስኬዲንግ ሥራውን በየዘርፉ በተልዕኮ እና ስትራተጂካዊ ተነሳሽነት(Strategic initiative) በመለየት ለኮንትራት ውሉ የማስፈፀሚያ የድርጊት መርሀግብር ቀርፀን የተንቀሳቀስን ሲሆን ሁሉም የዩኒቨርሲቲ ካውንስል አባላት በተገኙበት በኮንትራት ውሉ ዓላማ፣ አስፈላጊነት ከፊርማው በኃላ ሊኖር ስለሚችለው ኃላፊነትና ተጠያቂነት እንዲሁም ክትትል እና ድጋፍ ወዘተ ቀርበው የጋራ አረዳድ የመፍጠር ሥራ ከተሠራ በኃላ የመፈራረሙ ተግባር ተከናውኗል።

ቁልፍ የውጤት አመላካቾችን ወደየዘርፎቹ ካስኬድ የማድረግ ሥራው (ቀሪው የፊርማ ሥነሥርዓት) ከጥር 5 በፊት እንዲጠናቀቅ የጋራ መግባባት ተደርሷል።

👉የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

25 Dec, 09:34


የዩኒቨርሲቲዎች በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ የሚመደብ ይሆናል -ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብላቸው በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለፁ።

በትምህርት ዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በተቀናጀ መልኩ ማሻሻል የሚያስችል ስምምነት ተፈርሟል።

ስምምነቱን ትምህርት ሚኒስቴርና 47 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የቦርድ ሰብሳቢዎችና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ፈርመውታል።

የትምህርት ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት፥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በመሰረታዊነት ለመቀየር የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ወሳኝ ነው ብለዋል።

በተለይም ብቃት ያለው የሰው ሃይል ለማፍራትና ፋይዳቸው የጎላ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን ለማውጣት ጥራት ላይ መስራት ግዴታ መሆኑ በስምምነቱ ተካቷል ብለዋል።

ስምምነቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትክክለኛ መንገድ የሚሰሩና ተጠያቂነት ያለባቸው እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ሀገር የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በሳይንሳዊ ምርምር የሚያግዙ መሆን እንዳለባቸውም ነው የተናገሩት።

በሀገር የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑና የዜጎችን ህይወት እንዲቀይሩ ሁሉም ተቋም ሃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት አለበት ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብላቸው በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ ይሆናል ያሉት ሚኒስትሩ፥ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡ እኩል በጀት የሚመደብበት አሰራር ይቀራል ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የተጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃትና በጥራት እንዲፈፅሙ በተለይም ሙስናን ማጥፋት ግዴታ መሆኑንም አንስተዋል።

ሙስና የትውልድ ጸር በመሆኑ ለትውልዱ አርዓያ የሚሆን ዩኒቨርሲቲ መፍጠር እንደሚገባም አንስተዋል።
(ኢዜአ)

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

24 Dec, 12:01


የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ስራ በውጤታማነት ለመፈጸም የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ ነው።
…………………………………… // ……………………………..

በትምህርት ሚኒስቴርና በሁሉም የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል ነገ ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም የሚፈረመው ስምምነት ተቋማት ብቃትና ችሎታ ያላቸው ምሩቃንን በማፍራት ሂደት ውስጥ ተጠያቂነትን ከማስፈን ባለፈ ውጤታማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል እንደሆነ ተጠቁሟል።

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒሰትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች / Key Performance Indicators / 47 ዩኒቨርስቲዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ድርድር ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት ከተያዘው 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሳይንሳዊና ዓለም አቀፋዊ መለኪያች ላይ ያተኮረ እድገት እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ዩኒቨርስቲዎች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪና ለስራ ገበያው የሚመጥን ብቃትና ችሎታ ያላቸው ምሩቃንን ማፍራት እንዲችሉ ከተያዘው 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ስራን በውጤት መምራት ወደሚያስችል ስርዓት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተቋማቱ ስራን በውጤት መምራት ወደሚያችል ስርዓት ማስገባት በሙያዊና ክህሎታዊ ስራዎች እንዲሁም በልህቀት ላይ በማተኮር የአገሪቱን ችግሮች መፍታት የሚችሉ ችግር ፈቺ ምርምሮችን በማድረግ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚን የማልማት ስራ ላይ የበኩላቸውን ወሳኝ ሚና እንዲጫወቱ እንደሚያስችላቸው ክቡር አቶ ኮራ ገልጸዋል፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግልጽነትና ተጠያቂነትን ያሰፈነ አመራር እንዲከተሉ ፣ አገሪቱ ለምታወጣው ሀብት ተመጣጣኝ ውጤት እንዲያስገኙ የአፈጻጸም አቅማቸው እንዲገመገምና ለስኬቱም እውቅና እና ሽልማት እንዲያገኙ እንደሚያግዝም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አመልክተዋል፡፡
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ስራን በውጤት መምራት ወደሚያችል ስርዓት ለማስገባት ሚያስችለው / KPI / ስምምነት 47ቱም የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶችና የቦርድ ሰብሳቢዎች  ከትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር በነገው እለት በሚኖር ስነ ስርዓት በይፋ ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

18 Dec, 14:23


https://www.linkedin.com/posts/mitiku-k-kayamo_bmtblhblzbnmbmtbpkbqdbph-activity-7274833342905159680-xEbi?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

12 Dec, 11:46


https://www.linkedin.com/posts/etartificialintelligenceinstitute_ethiopia-artificialintelligence-technology-ugcPost-7272646024484016129-n48q?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

12 Dec, 07:51


የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር (ከደመወዛቸው) ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ለመለገስ ቃል ገቡ፡
መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የካቲት አንድ ቀን 2017 ዓ.ም የሚያካሂደውን ታላቅ የእርዳታ ማሰባሰብ መርሐግብር ለማስተዋወቅ ዛሬ ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተገኘ ሲሆን፣ በማዕከሉ መስራች የክብር ዶ/ር ቢንያም በለጠ የተመራው ቡድን ከዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት፣ መምህራን ፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና ተማሪዎች ጋር ማዕከሉን ማገዝ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዷል፡፡
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና፣ የመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር በየጎዳናው የወደቁ ወገኖቻችንን በርህራሄ በማንሳትና በመደገፍ ለሚያደርገው እጅግ የተቀደሰ ተግባር አመስግነው፣ ይህንን ዓላማም መደገፍ ለራስ ማበደር በመሆኑ፣ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንትና ማህበረሰብ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ትናንት ሀገራቸውን በትጋትና በቅንነት ያገለገሉ ባለውለታዎችን ዛሬ አቅም ማጣት፣ ዕድሜ እና ሁኔታዎች ጥሏቸው ጧሪ ደጋፊ ያጡትን ከየወደቁበት ከየጎዳናው በማንሳት በመደገፉ እያደረጉ ያሉትን በጎ ተግባር እግዚአብሔር በሠጠን ፀጋ ሁሉ ያለመቆጠብ ከማዕከሉ ጎን በመቆም እንድንደግፍ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል ፡፡

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

10 Dec, 05:15


Kotebe University of Education, in collaboration with the European Union (EU), launched the "Study in Europe Fair 2024" today. This two-day exhibition, running from December 9th to 10th, 2024, aims to connect Ethiopian students with opportunities to pursue higher education in European institutions.

Dr. Berhanemeskel Tana, President of Kotebe University of Education, emphasized the significance of the fair, stating, "This event is not only a great opportunity for students but also a catalyst for the transformation of our country." European Union Ambassador to Ethiopia, Sofie, highlighted the cultural exchange benefits of the program, saying, "The Study in Europe Fair promotes intercultural understanding alongside academic excellence."

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

05 Dec, 07:32


Kotebe University of Education hosted a discussion forum on "Ethics in Education." The event featured a presentation by Roger Tirazona, Head of the Department of Ethical Education at the University of Malta. The forum was attended by esteemed guests, including the Ambassador of the Republic of Malta, Ronald Micallef, and representatives from the United Nations. Faculty and students of the university actively participated in the insightful discussions.

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

28 Nov, 08:21


19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን “ሀገራዊ መግባባትን ለብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ።
==================================
በበዓሉ መክፈቻ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና እንደተናገሩት ከ80 በላይ በሆኑ ብሔረሰቦች ባጌጠች ሀገር የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ስናከብር ምን ያህል ውበት ፣ ምን ያህልስ ሀብት እንደሆነ እንገነዘባለን። ይህንን ሀብት እንዴት ለተሻለ ሀገረመንግስት ግንባታ እናውለው የሚለው ግን በሠፊው የሚያወያየን ነው።
በተለይ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በብዝሃ ባህል እና ብዝሃ ቋንቋ እንዲሁም በብዝሃ ማንነት ውስጥ አንዳቸው የሌላቸውን ልዩነት ጌጥ አድርገው ወደፊት የሚረከቧትን ትልቋን ኢትዮጵያ ዛሬ ካምፓስ ውስጥ ሳሉ አብሮነትን እና መከባበርን የሚለማመዱበት ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ሁላችንም የየራሳችንን ማንነት ባከበረ ሁኔታ ብሔራዊ አንድነታችንን በጠንካራ መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችሉንን ሁለንተናዊ አስተሳሰብ ማጎልበት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው ብዝሃ ባህል፣ ብዝሃ ቋንቋ እና ብዝሃ ማንነት በአጠቃላይ የየራሳችን ልዩ መገለጫዎቻችን ዕዳ ሳይሆኑ ተመንዛሪ ምንዳ ናቸው ፤ በህብረ ብሔራዊነት አብሮ መኖር አንዳችን ለሌላችን ስጋትና አጉዳይ መሆን ሳይሆን ክንድና አስቻይ፣ ጉልበትና ሙላት ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ደቻሳ አበበ “የብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት በኢትዮጵያ፡- ተግዳሮቶች እና የመፍትሄ ሃሳቦች” በሚል ርዕስ ባቀረቡት የውይይት መነሻ ሃሳብ፣ ፌዴራሊዝም የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ሥልጣን ተከፋፍለው ሳይለያዩ በሀገራዊ አጀንዳ ዙሪያ አብረው የሚሰሩበት በመሆኑ ባለፉት ዓመታት በአተገባባር ሂደት የታዩትን ችግሮች በማረም ሀገርን እንደ ሀገር ማስቀጠል፣ ታሪካዊ ኩነቶችን ለበጎ ዓላማ መተርጎም፣ ለሀገራዊ አንድነትና ለማህበረሰባዊ ትስስር ማዋል፣ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጋ ኢትዮጵያዊ ነኝ ለማለት የሚችልበትን ስሜት እንዲላበስ ማስቻል እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው በተከበረው 19ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ በተካሄደው ውይይትም የፌዴራሊዝምን እውነተኛ ዓላማ ከግብ ለማድረስ አመለካከት ላይ መስራት እንደሚያስፈልግ አስተያየት ተሰጥቷል፡፡

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

22 Nov, 17:53


Skip to content

 Menu
Northwestern Polytechnical University Chinese Government Scholarship 2025
November 6, 2024 by Scholarship Provider
Northwestern Polytechnical University Chinese Government Scholarship 2025 (NWPU CSC Scholarship 2025) is accepting applications for a Master & Ph.D. degree to Study at Northwestern Polytechnical University, China. Northwestern Polytechnical University offers many scholarships for international students around the world.
Teaching Language will be either Chinese or English, depending upon the degree you are enrolled in at Northwestern Polytechnical University. Chinese University Program is a full scholarship established by the Ministry of Education in China to support Chinese universities in specific provinces or autonomous regions to enroll outstanding international students for graduate studies in China.
Northwestern Polytechnical University is a National Key University, directed by the Ministry of Industry and Information Technology of the People’s Republic of China, located in Xi’an, Shaanxi, China. The main campus is located in Beijing. Study Duration for  Master (2-3) Years and Ph.D. (3-4) Years.
Northwestern Polytechnical University Chinese Government Scholarship 2025 Details
UniversityNorthwestern Polytechnical UniversityCountryChinaStudy LevelMaster & PhDDeadline31 Jan 2025
Duration:
The duration of Master (2-3) years and Ph.D. degree (3-4) Years.
Eligibility for Master & PhD
Applicants must be non-Chinese nationality in good health.
Must be an International Student out of China, or graduates of Chinese universities are eligible to apply for this scholarship.
Excellent performance in study.
Applicants should have good ability in scientific research
Applicants for Master’s degree students must be under the age of 35, and doctoral degree students must be under the age of 40.
Also, Apply: Nanjing University CSC Scholarship 2025 China | Study in China
Financial Coverage NWPU CSC Scholarship:
The Northwestern Polytechnical University of China Covers the following expenses:
Full tuition fee
Comprehensive Medical Insurance
Accommodation Fee
Registration Fee
Monthly stipend for  Master (3000 RMB) for doctoral Students (3500RMB).
Available Fields/Majors for Master & PhD
Northwestern Polytechnical University offers many degree programs in English as well as in Chinese for Master and Ph.D. Degree Students.
Application Materials for NWPU Scholarship
The following documents are required for the Northwestern Polytechnical University scholarship:
Degree and Transcript (must be attested by a notary public)
Passport Size Photo
Scanned Copy of Passport
Two Letters of Recommendations
Personal Statement or Study Plan or Research Proposal
Proof of Language Proficiency
Photocopy of Foreigner Physical Examination Form
Acceptance Letter (Optional)
Or any other supporting documents
Language Requirements:
Chinese medium courses: report of HSK4 or above (score: 210 or above, valid for two years), English level certificate.
English medium courses: IELTS (5.5 or above) or TOEFL (80 or above) report (valid for two years);Or English proficiency certificate provided by previous academic institutions.
Agency Number:
The agency number of Northwestern Polytechnical University is “10699”. Type B
How to Apply for this Scholarship:
The process of this scholarship is online, please check the link below to apply online or check the official announcement of the scholarship.
Important Note: 600 RMB Application fee and no Need Acceptance Letter
Step 1:
Must fill out the Chinese Scholarship Council(CSC) application form.
For more details: Chinese Government Scholarships 2025-2026 [CSC Scholarship]
Step 2:
Apply at Northwestern Polytechnical University Online portal http://admission.nwpu.edu.cn
Step 3:
Pay 600 RMB application fee

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

22 Nov, 17:53


Step 4:
No need to send Hard copies just fill the online form.
OFFICIAL SCHOLARSHIP LINK CSC Scholarship 2025
Related

Yunnan Normal University Chinese Government Scholarship 2024

Lanzhou University Chinese Government Scholarship 2024 – without IELTS

Wuhan University Chinese Government Scholarship 2025 – Study in China
CategoriesAsia, China, Fully Funded Scholarship 2025, Master, PhD, Study Level
Stipendium Hungaricum Scholarship in Eotvos Lorand University 2025
East China University of Science and Technology CSC Scholarship 2025 – Fully Funded
Leave a Comment
Comment
NameEmailWebsite
Save my name, email, and website in this browser for the next time I comment.
 Notify me of follow-up comments by email.
 Notify me of new posts by email.



Subscribe to Blog via Email
Enter your email address to subscribe to this blog and receive notifications of new posts by email.
Email Address
Subscribe
For Promotions
Use this Email:
[email protected]



Terms and Conditions
 
Privacy Policy
 
Disclaimer
 
Contact Us
© 2024 Techs Tour - Home

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

21 Nov, 03:59


አዲስ ዌብሳይት ተመርቆ ሥራ ላይ ዋለ፡፡
ኮትዩ
🏑🏑🏑🏑🏑🏑🏑🏑🏑🏑🏑🏑🏑🏑

ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ የተመረቀው አዲሱ የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ዌብሳይት በዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ከፍተኛ ትኩረት፣ ድጋፍና ክትትል ለውጤት የበቃ ሲሆን፣ የተቋሙ የአይሲቲ ባለሙያዎች፣ የኮምፒዩተር ሳይንስ መምህራንና ተመራማሪዎች እንዲሁም የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት አስተባባሪዎች በቴክኒካል ዝግጅቱ የተሳተፉበት ነው፡፡
የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና የዌብሳይቱን በይፋ መመረቅ ባበሠሩበት ወቅት እንደገለጹት፣ ዌብሳይቱ ቀድሞ የነበረውን ክፍተቶች በመፈተሽ፣ ዓለምአቀፍ ተሞክሮዎችን በማመሳከር እና የጥራት ደረጃዎችን መነሻ በማድረግ የተሠራ በመሆኑ የዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮ፣ ትኩረቶች፣ የመማር ማስተማር እና ሁሉንም አገልግሎቶቹን በሀገርአቀፍ እና በዓለምአቀፍ ደረጃ የሚያስተዋውቅ በመሆኑ ከዓመቱ ታላላቅ ተግባራት መካከል አንዱ ሆኖ የሚመዘገብ ነው ብለዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዘለቀ ቢዮሮ እና የክፍሉ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ማቲያስ አድማሱ በምረቃ ሥርዓቱ ላይ ዝግጅቱ ያለፈበትን ዝርዝር ሂደትና ስለአጠቃቀሙ በዝርዝር አስረድተዋል። አዲሱ ዛሬ በይፋ የተመረቀው ዌብሳይት ከበፊቱ በበለጠ በርካታ የተቋሙን መረጃዎች በተሟላ መልኩ ለመስጠት የሚያስችል ደረጃውን የጠበቀ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

በምርቃቱ ማጠቃለያም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና፣ በዌብሳይት ዝግጅቱ ላይ የተሳተፉትን አካላት የተሠጣቸውን የማዘጋጀት ኃላፊነት በሚገባ ስለተወጡ አመስግነው፣ ለእያንዳንዳቸው የማበረታቻ ሽልማት አበርክተዋል ፡፡

የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

06 Nov, 08:50


መምህራንን "Innovative Pedagogy" ብቁ የማድረጉ ተግባር መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ።
(ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም)
👭👫👭👫👭👫👭👫
በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፣ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና ኑፍ አፍሪካ ምርምርና ስልተጠና ተቋም ቅንጅት መምህራንን በ "Innovative Pedagogy" ለማብቃት ሲሰጥ የቆየው ዘርፈ ብዙ ተግባር ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም የተገመገመ ሲሆን፣ መምህራን ከዘመኑ እጅግ ፈጣን እና ተለዋዋጭ ቴክኖሎጂ ጋር ራሳቸውን እንዲያዋሕዱና ብቁ ሆነው እንዲገኙ ማስቻል የምርጫ ጉዳይ እንዳልሆነ የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው፣ ቢሮው በዚህ ረገድ ዕቅድ ይዞና ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልጸው፣ ዩኒቨርሲቲው ይህንን አጅግ አስፍቶና አጠንክሮ እንዲሄድበት አደራ ብለዋል።

በዚህ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ትምህርት ጥራት እና ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በመሆን በገመገሙበት መድረክ፣ ጊዜውን የሚመጥንና ዓለም የደረሰበትን የማስተማር ስነ ዘዴ በመጠቀም በማስተማር በትምህርት ጥራቱ ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ከስምምነት ተደርሷል።

የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

02 Nov, 15:31


የቋንቋ መምህራን አሳታፊና ሳቢ የማስተማር ስነዘዴዎችን መጠቀም እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡
🩸🩸🩸🩸🩸🩸🩸🩸🩸🩸

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ትብብር የተዘጋጀ ስልጠና፣ በአዲስ አበባ ከተማ አፋን ኦሮሞ እና አማርኛ ቋንቋዎችን እንደሁለተኛ ቋንቋ ለሚያስተምሩ መምህራን በመሰጠት ላይ ነው፡፡

ዛሬ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም፣ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተጀመረውን ስልጠና የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና፣ የቋንቋ መምህራን አሳታፊና ሳቢ የማስተማር ስነዘዴዎችን መጠቀም እንዳለባቸው ገልጸው፣ ይህም ተማሪዎች ለቋንቋው ፍቅርና ፍላጎት ኖሯቸው እንዲማሩት እንደሚያደርግና ሥርዓተ ትምህርቱ ዓላማው ያደረጋቸውን የመማር ግቦች በአጭር ጊዜ ውስጥ በሚፈለገው ጥራት እንደሚያሳካ ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው የተዘጋጀው ባለፈው አንድ ዓመት በአአከተማ ትምህርት ቢሮ ሥር ባሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ሲሠጥ በቆየው እንደሁለተኛ ቋንቋ ትግበራ ሂደት ላይ በተደረገው ጥናት በተለዩት ችግሮች ላይ ተመስርቶ ከቢሮው ጋር በቅንጅት እየተሰጠ ያለ የአቅም ግንባታ ሥልጠና መሆኑን የገለጹት ፕሬዘዳንቱ፣ መምህራን የቋንቋ ትምህርትን ከባህል፣ ስነቃሎች፣ እሴቶች እና ትውፊቶች ጋር በማስተሳሰር ተማሪዎች ከክፍል ውጪም በተለያዩ ማህበራዊ መስተጋብሮች ውስጥ ቋንቋውን እንዲጠቀሙ ማስቻል እንዳለባቸውም አመልክተዋል፡፡
የሀገር ውስጥም ሆነ የውጪ ቋንቋዎችን መማር ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት ጠቃሚ፣ እንደግለሰብም የተለያዩ ዕድሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ፣ እንደመምህር የተማሪዎችን አመለካከት ከዚህ አንጻር መቃኘት፣ ራስን በንባብ፣ በትምህርትና ስልጠና ማብቃት፤ በዚህም አሠራሮችን መለወጥና ማሳደግ እንዲሁም ዘመኑ ከሚጠይቀው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕውቀት ጋር አብሮ መራመድ እንዳለባቸውም ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና አሳስበዋል፡፡

ስልጠናውን አብረው የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው፣ የሥርዓተ ትምህርቱ ዓላማ ልሳነብዙ የሆነን ትውልድ መገንባት መሆኑን ገልጸው፣ የቋንቋዎችን ብዝሀነት መቀበል እንደሀገር የተጀመረውን ለውጥና እድገት በማስቀጠል ረገድ ከፍተኛ ሚና ስለሚኖረው መምህራን የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ የተማሪዎቹ ውጤታማነትም በመምህራኑ ብቃት ላይ የሚመሰረት በመሆኑ ይህንን የአቅም ግንባታ ሥልጠና ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመሆን ለማዘጋጀት ችለናል ፤ በመሆኑም በቀጣይ በተሻለ የማስተማር ስልት እና ብቃት በተማሪዎች ውጤት የሚገለጽ የተሻለ ለውጥ እንጠብቃለን ብለዋል።

በዩኒቨርሲቲው ለ2 ቀናት በሚሰጠው በዚህ ስልጠና ላይ 883 የአፋን ኦሮሞ እና የአማርኛ ቋንቋዎች መምህራን በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

01 Nov, 05:28


*ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሴት ተመራማሪዎችን በተለየ እያበረታታ መሆኑ ተገለጸ፡፡*

ዩኒቨርሲቲው ስታፉን ከልየታው (differentiation) ጋር በሚገባ ለማስማማት በተለያዩ ርዕሠ-ጉዳዮች ላይ አከታትሎ ሥልጠናዎችን እየሠጠ ይገኛል።

በዚሁ መሠረት ሴቶች በምርምር ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ አርአያ ሊሆኑ ጭምር በሚችሉ ምሁራን ለዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራን ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም የተዘጋጀውን የምርምርና ሕትመት ክህሎት ሥልጠና ተሠጥቷል።
ሥልጠናውን ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው የምርምር፣ ህትመት፣ ስነምግባርና ሥርጸት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ኤፍሬም ተክሌ፣ በሴት መምህራን ዘንድ የማህበራዊ ተሳትፎ ጫና በመኖሩ ተቋሙ የምርምር ተሳትፏቸውን ለማሳደግ ሴቶች በዋና ተመራማሪነት የሚሳተፉበት የምርምር ፕሮጀክት ማዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥርዓተ ትምህርት መምህርትና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር እንጉዳይ አደመ ሲሆኑ፣ ሴት መምህራን በሚገጥሟቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ሳይረቱ ጠቃሚና ወደተግባር ሊለወጡ የሚችሉ ምርምሮችን በትኩረትና በተከታታይ ማካሄድና ማሳተም እንዳለባቸው ጠቁመው፣ በዚህም ዕውቀታቸውን ከማስፋት ባለፈ የአካዳሚክ ማዕረጋቸውን እንዲያሳድጉ አሳስበዋል፡፡
የሴት መምህራንን የጥናትና ምርምር ክህሎት ለማሳደግ የተዘጋጀው ይህ ሙያዊ ስልጠና ቀጣይነት ያለው መሆኑ ተገልጽዋል፡፡
_ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት_

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

30 Oct, 18:05


https://www.linkedin.com/posts/etartificialintelligenceinstitute_%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%AD%E1%89%B2%E1%8D%8A%E1%88%BB%E1%88%8D-%E1%8A%A2%E1%8A%95%E1%89%B0%E1%88%88%E1%8C%80%E1%8A%95%E1%88%B5-%E1%89%B4%E1%8A%AD%E1%8A%96%E1%88%8E%E1%8C%82-%E1%88%B2%E1%8A%90%E1%88%B3-%E1%8A%A0%E1%89%A5%E1%88%A8%E1%8B%89-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%8A%90%E1%88%B1-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%88%8C%E1%88%8B-activity-7257331876346912768-sRDl?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

30 Oct, 17:59


https://www.linkedin.com/posts/pkprabhakar_research-academic-phd-activity-7256260629542428672-ZlrK?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

25 Oct, 04:22


https://abroaducate.com/scholarship/2025-fully-funded-japanese-government-mext-scholarships-at-asia-pacific-university/

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

25 Oct, 04:07


በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ሙሉ ድጋፍ የሚደረግላቸው ተማሪዎች በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ማምጣት እንዳለባቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት አሳሰቡ፡፡

🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ችግረኛ ህፃናትን ሰብስቦ በሙሉ ሃላፊነት ዓመታዊ ሙሉ አልባሳት ( የቀን እና የሌሊት አልባሳትን ጨምሮ) ፣ የትምህርት ቁሳቁስ እና ወርሃዊ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ለሚያሳድጋቸው የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በ14/02/2017 ዓ.ም ልዩ ልዩ የትምህርት ቁሳቁስና አልባሳት አበርክቷል። በዚሁ ወቅት የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ተማሪዎቹ በትምህርታቸው በርትተው የላቀ ውጤት በማምጣት ነገ ከጥገኝነት የተላቀቀ የተሻለ ህይወት እንዲኖራቸው በትምህርታቸው የበረቱ እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አልማዝ ደብሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ ተማሪዎቹ በትምህርታቸው እንዲበረቱ፣ በዘላቂነት ለውጤት እንዲበቁና ስኬታማ ሆነው ራሳቸውን እንዲችሉ እየተደረገ ያለው እገዛ ከአሁን በኋላ በተዘጋጀው የማስፈፀሚያ መመሪያው መሠረት የሚከናወን መሆኑን አሳስበዋል።

_የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት_

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

25 Oct, 03:36


*An Aviation Club was established at Kotebe University of Education Science Shared Campus.*
*********
The founding ceremony was held today, October 14, 2017 at the Science Shed Campus, as the founder and president of the aviation club, student Jinenus Berhanemeskel, stated that the main purpose of the aviation club established today is to create opportunities to enable students with special talent and interest in the field to turn their theoretical knowledge into practice. .
Student Jinenus said colleagues from the aviation industry are willing to help us, hence, the establishment of the club will help students to get better knowledge by combining theory and practice.
Kotebe University of Education Astronomy Researcher Dr. Getnet Feleke and KUE-STEAM Center Director, Dr. Thewodros Mulugeta attended the inauguration and gave a motivational speech to the students.

Report: Executive Office of the Public and International Relation

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

15 Oct, 13:32


https://www.linkedin.com/posts/saheedkolawole_65-ongoing-fully-funded-scholarships-for-activity-7250823357074489344-HNls?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

15 Oct, 13:05


መስማት ለተሳናቸው የሬሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ
****
(ኢ ፕ ድ)

በ2016 ዓም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው በመንግስት ተቋማት የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የማለፊያ ውጤትን ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት፤

👉 የተፈጥሮና ማሕበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከስድስት መቶ 192፣

👉 የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከስድስት መቶ 186፣

👉 በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ ወንድ ከሰባት መቶ 224፣

👉 በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮና ማሕበራዊ ሳይንስ ሴት ከሰባት መቶ 217 እና በላይ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓም

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

12 Oct, 23:51


Channel name was changed to «KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /»

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

12 Oct, 23:45


https://www.linkedin.com/posts/saheedkolawole_it-is-the-application-period-for-fall-2025-activity-7250426640499982336-E-nO?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

12 Oct, 11:56


https://www.linkedin.com/posts/scholarshippk_1-mcgill-university-scholarships-in-canada-activity-7249629764339073024-nvOG?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

12 Oct, 06:51


https://www.linkedin.com/posts/mitiku-k-kayamo_bmtblhblzbnmbmtbpkbqdbph-bmtblhblzbnmbmtbpkbqdbph-activity-7250594271391539200-7_dX?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

12 Oct, 06:49


https://www.linkedin.com/posts/dagemworku_apply-bloblz-scholarship-activity-7249701833223417857-N8c-?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

10 Oct, 05:57


https://opswatacademy.com/introduction-critical-infrastructure-protection?utm_source=Facebook&utm_medium=ICIP+-+Free+Course+Program+-+Oct%2724&utm_campaign=TopCount&utm_term=Cybersecurity+related&utm_content=Post+1+-+Urge+users+to+enroll+the+free+course+-+Square+-+Use+existing+post&fbclid=IwZXh0bgNhZW0BMAABHRTORa5Q7RxHE1J1HRLogT2Cj9xYBLFfoXasNGnjWAtHx1McUYHkZQLkLw_aem_gdQzknpsn7f_qSrPLhjIQg&utm_id=120211540502430497

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

10 Oct, 05:54


https://www.facebook.com/share/dLZ7BGTyGJbnGBN4/?mibextid=xfxF2i

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

09 Oct, 23:38


https://www.facebook.com/share/Bg84GajJdYSuMsp4/?mibextid=oFDknk

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

09 Oct, 23:27


በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሚካሄዱ ምርምሮች የዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮ ማዕከል ያደረጉ መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡


“A Training on “Thematic Research: Concepts and Practices” በሚል ርዕስ ዛሬ መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ ለዩኒቨርሲቲው መምህራን የተሰጠውን ስልጠና በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና፣ በዩኒቨርሲቲው የሚካሄዱ ምርምሮች የዩኒቨርሲቲውን አዲሱ ተልዕኮ እና የሀገራችንን የትምህርት አቅጣጫዎች ማዕከል ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ምርምሮቹ በተለይ የሀገሪቱን የትምህርት ጥራት ችግር መንስኤዎች፣ ተግዳሮቶች የሚለዩ እና ተጨባጭና ተተግባሪ መፍትሔዎችን የሚያፈልቁ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ስልጠናውን የሰጡት፣ በትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሠራዊት ሀንዲሶ፣ የመንግስትን የጥናትና ምርምር ዋና ዋና ትኩረቶች፣ ለጥናትና ምርምር የተለዩትን ጭብጦች፣ የተቀመጡ ማዕቀፎችን እና አሠራሮችን አብራርተው፣ ከዚህ አንጻር የሚካሄዱት ምርምሮች የሀገሪቱን የትምህርት ችግሮች በሚፈታ መልኩ የተደራጁና ተገቢውን ጥራት ያሟሉ ሊሆኑ እንደሚገባ ጠቁመው፤ ይህንንም ለማሳካት ለምርምር የሚውልን በጀትና ሀብት ሀገራዊ ጠቀሜታ ባላው መልኩ መጠቀም፣ ምርምሮችን በጋራ መስራት እና ከዩኒቨርሲቲው ሀገራዊ ተልዕኮ ጋር ማቀናጀት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

08 Oct, 17:19


https://www.facebook.com/100064682287722/posts/pfbid0BTzWwrpa4FS53Svbk47RNhTEnoiHwnGFguPojVFCvMpcxchkSLu5ogiUojp7vXVQl/?mibextid=CDWPTG

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

08 Oct, 13:42


ትውልድ የሚገነባው እንደዚህ የተሻለ የሠራውን የበለጠ እንዲሠራ፤ የደከመው ቁጭት እንዲፈጥር እየተደረገ ሲኮተኮት ነው። ላለፉት ሙሉ ጊዜያቸውን ሳያባክኑ ዕውቀት ለመሸመት ያዋሉ፣ የትምህርት ቤታቸውን አመራር እና መምህራኖቻቸውን የሠሙ፣ የቤተሰባቸውን ከእነሱ ጋር ዋጋ መክፈል ለውጤት ያበቁ፣ እነዚህ በዕውነት ክብር ይገባቸዋል። ምንም ነገር ሳያዘናጋቸው "ለምን ይሄ " ብለው ተመራምረው ከፊሉን ደፍነው ከፊሉን ሰቅለው በዓመቱ ብሔራዊ ፈተና እጅግ የላቀ ውጤት አስመዝግበው የዩኒቨርሲቲውን ትምህርት ቤት ብሎም የከተማውን ስም ያስጠሩ ናቸውና በመሸለማቸው ደስ ብሎናል ።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮም ክትትላችሁን፣ ድጋፋችሁን እና የላቀ ውጤት ያመጡ ትጉኃንን መሸለማችሁ ነገ ሺዎች ተሸላሚዎችን ለመፍጠር አነሳሽ ከመሆኑም በላይ የነገን ትውልድ ዛሬ እየተከላችሁ ነውና ሥራችሁ አኩሪ ነው ። ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነችን፣ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱን እና ማናጅመንታቸውን ላደረጉት ሞራል ገንቢ ማበረታቻ በራሴ እና በዩኒቨርሲቲው ማናጅመንት ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር )
ፕሬዚዳንት

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

03 Oct, 10:24


እንኳን ለእሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የመልካ ወይም የሆራ እሬቻ በገዳ ሥርዓት መሠረት ክረምት አልፎ መስከረም ሲጠባ የሚከበር የምስጋና በዓል ነው፡፡ እሬቻ የእርቅ፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የህብረትና የአንድነት ተምሳሌት ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ያለ ምንም ልዩነት ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድም እህቶቹ ጋር በአንድነት ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል
የብዝሃነታችንም መገለጫ ነው፡፡
ስለሆነም ለመላው ህዝባችን እንኳን ለእሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ፤ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ፣ የህብረት እና የአንድነት እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ!

ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር)
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

Baga Ayyaana Irreechaaf Nagaan Geessan!*
🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝
Irreechi Horaa bu’uura sirna Gadaatiin yeroon gannaa darbee birraan bari’u kan ayyaaneffamu ayyaana galataati. Irreechi Araara,
Nagaa, fakkii gamtaa fi tokkummaati. Uummanni Oromoo garaagarummaa tokko malee Obboleeyyan isaa uummata
Itoophiyaa mara waliin kan ayyaaneffatu ayyaana woliiniiti.

Kanaafuu ummatni keenya marti baga ayyaana Irreechaatiin nagaan isin gahe jechaa, Ayyaanni kun kan naga’aa, kan
jaalalaa, Kan gammachuu, akka nuuf ta'un hawwa.

Dr. Birhaanamasqal Xannaa
Pirazidaantii Yuunivarsiitii Barnootaa Kotobee

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

02 Oct, 08:18


#Dv_ሎተሪ ዛሬ መስከረም 22/2017 ይጀምራል
የአሜሪካ diversity visa ወይንም DV ሎተሪ ይጀምራል።
አንደኛ

ማንኛውንም የሚሞላ ሰው የግድ 12ኛ ክፍል የጨረሰ መሆን አለበት። ወይንም በትንሹ 2 አመት በፈጀ ስልጠና ወይም ትምህርት ካለፉት አምስት አመታት ሁለት አመታት የስራ ልምድ ያለው መሆን ይጠበቅበታል።

12 ያጠናቀቀ እና ያላጠናቀቀ ግን የሆነ ስልጠና ይወስዳል ወይንም ትምህርት ለምሳሌ ላብራቶሪ ተማረ እንበል ትምህርቱን በአንድ አመት ቢጨርስ ለdv አይሆንም። ነገር ግን በትንሹ ሁለት አመት ቢማር መስፈርቱን ያሟላል ይህም ማለት አንድ ሰው ትልቅ ፋብሪካ ጥገና ቢሰራ ጥገናውን ግን ለመማር 6 ወር ወይንም አመት ቢፈጅበት መስፈርቱ በትንሹ 2 አመት የስልጠና እና ትምህርት ጊዜ ስለሚል ውድቅ ይደረጋል።

2 እና ከዛ በላይ አመት የተማረ ከሆነ ደግሞ ባለፉት 5 አመታት ማለትም ከ2011-2016 ባለ ጊዜ ውስጥ ስራ ላይ የነበረና 2 አመት ያገለገለ መሆን አለበት።

የተፈቀዱ የስራ አይነቶችን ለማወቅ በኤምባሲው የተቀመጠውን ጥቆማ

onetonline.org ድህረገፅ ላይ በመግባት Job family ሚለውን ተጭናቹ የስራ ዝርዝሮችን ማየት ይቻላል።

#ሁለተኛ

አመልካቾች የግድ 18 አመት የሞላቸው መሆን አለባቸው። ፎርሙንም አንዴ በትክክል ሞልቶ submit ማድረግ ማስገባት ሲገባ የተደጋገመ ሙሌት በመስሪያ ቤታቸው ቴክኖሎጂ ስርአት ውድቅ የሚደረግ ይሆናል።

እዚህ ጋር submit ብለነው ቀይ ምልክት እና ያልተሟላ መረጃ እንዲሁም እንዳልተቀበለን ካሳወቀን መስፈርቶችን እያሟሉ እና እያስተካከሉ ደጋግሞ መሙላት ይቻላል ያልተፈቀደው ከተቀበለ በውሃላ የሚደረጉ ድግግሞሾችን ነው።

ተቀብሎ submit ካደረገ በውሃላ ራሱ confirmation code ካልተሰጠን ስላልተመዘገብን ጥቂት ከጠበቅን በውሃላ ዳግም መሞከር ይቻላል። ቁጥሩን ካገኘን በውሃላ ግን ዳግም መሞከር ውጤታችን ውድቅ እንዲደረግ ያደርጋል።

#ሶስተኛ

ባለትዳር የሆኑ ሰዎች የግድ ባልም ሚስትም ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ካሟሉ የተለያየ ወረቀት በየግል መሙላት ይችላሉ ካላሟሉ ግን የሚያሟላው ባልም ይሁን ሚስት ቅፁን ከሞሉ በውሃላ ሌላኛውን በጥገኛ ማስመዝገብ ይችላሉ። ሚስትና ልጆች ወይንም ባልና ልጆች የግድ ስማቸው መሟላት አለበት።

ልጆቹ ያላገቡ እና እድሜያቸው ከ21 አመት በታች መሆን አለበት ይህ DV እስከሚሞላበት ቀን ድረስ።

#አራተኛ

አንድ አመልካች በሌላ መንገድ ወደአሜሪካ ለመግባት እየሞከረ ከሆነ በትምህርት ፣ በጤና ፣ በፖለቲካ ጥገኝነት ተመዝግቦ ጉዳዩ በሂደት ላይ ያለም ቢሆን DV መሙላት እና የነፃ እድሉ ተጠቃሚ መሆን ይችላል። DV እድል በነፃ ቢሆንም እድለኞች ከደረሳቸው በውሃላ ወደአሜሪካ ለመሄድ የቪዛ ክፍያ መፈፀም አለባቸው።

ፎርሙንም ማንኛውም ሰው ለሌላ ሰው መሙላት ሲችል ሂደቱ እንደተጠናቀቀ መመዝገቡን ለማረጋገጥ

dvprogram.state.gov ላይ በመግባት check status የሚለውን በመጫን የሚሰጠውን የወረቀት ቁጥር ተጠቅሞ ማረጋገጥ ይችላል።

#አምስተኛ

አሸናፊዎች ከላይ ባለው ሊንክ ማለትም በ dvprogram.state.gov በመግባት የDV አዘጋጅ የሃገሪቱ ስርአተ-ክፍል ሰዎችን በማንኛውም መንገድ ለማግኘት አይሞክርም ( email , facebook , telegram) በመሳሰሉት የእንኳን ደስ አላቹ መልእክት አይልክም።

በመሃል confirmation code ቢጠፋባችሁ ባስገባችሁት email አድራሻ የመለያ ኮዱን እንዲልክላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።

#ስድስተኛ

ፎቶ ፎቶቤት መነሳት የምትችሉ ሲሆን ምንም አይነት ፈገግታ ፣ የፀጉር መገልገያ (ሻሽ መሰል ጨርቆች) ፣ የአይን መነፅር ፍሬም አይንን መከለል የለበትም ፣ የጆሮ ጌጦች የማይፈቀዱ ሲሆን ለdv የምትጠቀሙት ፎቶ አሁናዊ ሁኔታችሁን ለማወቅ እንዲረዳ ቢበዛ ከስድስት ወር ወዲህ የተነሳቹት ፎቶ መሆን አለበት። scan ድደርጋችሁ የምትጠቀሙ ከሆነ ለማስተካከል

123passportphoto.com/upload_photo.php

ድህረገፅን መጠቀም ትችላላችሁ።

ባለፉት አምስት አመታት ከ50 ሺህ በላይ ዜጎቻቸውን በማስወጣት በ2025 የDV ሎተሪ ቻይና ፣ ናይጄሪያ ፣ ፓኪስታን ፣ ባንግላዲሽ ፣ ቻይና ፣ ደቡብ ኮሪያ ፣ ቬትናም ፣ ሜክሲኮ ፣ ቬንዙዌላ ፣ ጃማይካ ፣ ሆንዱራስ ፣ ኮሎምቢያ ፣ካናዳ እንዲሁም ብራዚል ያልተፈቀደላቸው ሃገራት ናቸው።

DV 2026 55,000 ( ሃምሳ አምስት ሺህ) እድለኞችን ይቀበላል

መልካም እድል!

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

26 Sep, 15:11


ኢትዮጵያዊን በአንድነት ተሰብስበው ለሚያከብሩት የደመራ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ !

#መልካም_በዓል

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

26 Sep, 10:32


http://t.me/MIDROCINVESTMENT

4,413

subscribers

238

photos

4

videos