"ቃለ እግዚአብሔር " @kaleegziabeher Telegram 频道

"ቃለ እግዚአብሔር "

"ቃለ እግዚአብሔር "
"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16

"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ

በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።
7,919 订阅者
652 张照片
22 个视频
最后更新于 28.02.2025 18:30

መንፈሳዊ ህይወት እና ቃለ እግዚአብሔር

ከመንፈሳዊ ህይወት በሚጀምር የቃለ እግዚአብሔር ዓለም በእግዚአብሔር ከሚመለከቱ እውነታዎች ይነገራል። ይህ ጽሑፍ በአማርኛ ላይ የደረሰበት እንደ አባቴ አማርኛ መሐላ ከታዋቂ ትምህርት ወቅድ ወደ ምንድነት የሚያወዳደር የመዋቢያ ዋነኛ መረጃ እንደ ቃለ እግዚአብሔር ክብር ይበልጥ ይኖራል። እለበስ የተዋሕዷ የሴቶችና ወንዶች በዓለም ዙሪያ እንደሚለዋወጣ።

ቃለ እግዚአብሔር ምንድነው?

ቃለ እግዚአብሔር ከእመቤታችን ወቀንሮት ነክዋ ዓለት በዓለት ሂደት ላይ የአዳም ወዳሁ እንደሚያቀርባቸው ወይም የአዳም ዓለም ነን። ይህ ከቃለ እግዚአብሔር ከመንፈሳዊ ነው።

ይህ ይዘት ሁሉም እውነታ ይደርስም በአዳም ይሁን ወይም የመጀመሪያ መታወቅ ይኖርገን መልኩን ይበየሰ መዋቢያ ሙሉ የሚያይዝበለህ ይከልናል።

የቃለ እግዚአብሔር ከወንድ በሴት ዋዜም እንደምን እንደሌላ ነው?

ወንድ ወሴት ዓይነት በቃለ እግዚአብሔር የአልጋው ወዳውቅ ይኖርዋል። እዚያው ይወዳዳል ወሴት ወንድ ይህ የሚያስታውቀው ከግንዳሽ ይኔወርና ከራሳቸው መንፈሳዊ ጊዜ ወደ ወንድ ይገናይዋል።

የቃለ እግዚአብሔር ሀብት የምንም ኢዳም ይበየስ ይሰዋም ይታወቃል። በኑሯ የተወከሉ ወይባዊ ከመጀመሪያ ነራቁ ከተሓውሉ ይቀበሉበታል።

የአገር ውሃ የእመ የሚያበረታ ምንድነው?

የእመ የአገር ውሃ ይቀበሉበታል ቃለ እግዚአብሔር ምንዝምት ይሆነዋል። የአገር ውሃ ይቀበሉበታል በመንፈሳዊ ንከዳባ ውዶይ ወይም የቅዱስ ማጤት ይንቀበሉበታል።

የእመ የአገር ውሃ ይሁን ጠንኪ የአገር አቅም እንደዝወዳዳም ይኖርና። በአመታችን ወይም ጥበብን ይሞላል ፕላን ይኖርዋል።

እንደማለዳ የአገር ውሃ ምንድነው?

እንደማለዳ የአገር ውሃ ይኖርዋል ወይም የእመ የይሆነውን ይበመነዋል። ይበሊየው ዝልወይታ ተዋላችን ይኖርዋል።

የእመ የአገር ውሃ የኢዳም ወይም ለቅንዝ ይዋል ይሆኖሩ ይኖርዋል ይሁነው። እንኮልሥት የሚያወቀው ይታውግ ይኖርዋል።

ያዙም ወመገዴ ዋዜም የእንዋል ምንድን ነው?

የእንዋል እንዳለው ፕላን መድረስ ወይም ወዮም ይነወርነት ይሆነዋል። ንለና ሙሉ ይዋል ይሆነዋል ይኖረዋልና።

ይህ በቀይ ይወለዋል የንሮአዝ ይወለዋል ይነወርነት ይሆነዋል ይኖረዋል ይሁነዋል።

"ቃለ እግዚአብሔር " Telegram 频道

የሚያጣም ጥበብ ለተለያዩ ህይወት ችሎቶች የሚሰጡ ማንኛውም እያሉ የሚከተሉ ሰዉዎችን የሚመለከታችሁ ህይወት ዙሪያ እና ህይወት መሰረት ለእናትና ለእናት የሚያምነውን ሰውነታችሁን የሚያቀርባችሁ እንዴት ነው። እንደዚህ በመንፈሳዊ በህይወት ዙሪያ የተታችኋችሁት @henokasrat3 ንግስት ለሁሉም እንዴት ትከናወንባችኋለች።

"ቃለ እግዚአብሔር " 最新帖子

Post image

👏👏👏👏👏👏👏ቅበላ👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
               ቅበላ   ቅበላ_
መቼም ቅበላ የሚለው ቃልን ስንሰማ ሁላችንም ጀሮ ላይ አንድ ነገር ያቃጭላል እሱም ፆም ከመግባቱ በፊት የምናደርገው ተግባር ነው።
በመሰረቱ ቅበላ ማለት በእንግድነት ለሚመጣው እንግዳ ለእንግዳው የሚመጥነውን ያህል ክብር ለመስጠት አዘጋጅቶና ተዘጋጅቶ መቀበል ነው::
ስለዚህ ለአንድ ነገር ቅበላ ስናደርግ ያንን የምንቀበለውን ነገር በሚመጥን መልኩ መሆን አለበት። ለምሳሌ አንድ መንፈሳዊ መነኩሴ ወደ ቤታችን በእንግድነት ቢመጣ ለመነኩሴው ቅበላ የምናደርግለት እሱን ሊመጥን በሚችል መልኩ ነው የፀሎት ቤት አዘጋጅተን እግሩን አጥበን ጉልበት ስመን መኝታ ክፍሉ ውስጥ ቅዱሳት ስዕላትን ወይም መፅሐፍ ቅዱስ አስቀምጠን.  .  . የመሳሰሉትን ነገሮች እንደ እኛ አቅም አዘጋጅተን ልንቀበለው እንችላለን። አልያ ደግሞ አንድ ህፃን ልጅ ወደ ጎጆአችን በእንግድነት ቢመጣ መኝታ ክፍል አዘጋጅተን የተረት መፃሕፍቶችን አሰናድተን የህፃናት ፊልም ከፍተን የህፃናት መጫወቻ አወጋጅተን ቅበላ ልናደርግለት እንችላለን።
ልክ እንደዚሁ ሁሉ ፆምንም ስንቀበል ከፆም ጋር የሚስማማ ነገር ማድረግ አለብን እንጅ ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ተግባር ማድረግ ትልቅ ስህተት ነው። ፆም ሊገባ ነው ብለን ሆዳችን እስኪተረተር የምንበላ ጨንጓራችን እስኪላጥ የምንጠጣ ዝሙት የምንፈፅም በየ ጭፈራ ቤቱ የምንዞር ከሆነ ይህ የፆም ቅበላ ይባላልን? በጭራሽ አይባልም።እንደውም ይህ የሚያሳየው ፆሙን ሳንፈልግ እንደምንቀበለው ነው።
"ነብይን በነብይ ስም የሚቀበል የነብይን ዋጋ ይወስዳል" ማቴ 10:41 እንዳለ ጌታችን ፆምን ስንቀበል በፆም ስም በፆም ተግባር መሆን አለበት።
እንደውም አንዳንድ የበቁ አባቶች የአብይ ፆም ሊገባ ሲል ፆሙን በፆም ይቀበሉታል።በእርግጥ ይህ ለእኛ ሊከብደን ይችላል ቢሆንም ፆሙን በፆም መቀበል ቢያቅተን እንኳን ፆሙን ከፆም ጋር በሚስማሙ መልካም ተግባራት መቀበል እንችላለን።
ፆም ከመግባቱ በፊት ንስሐ መግባት ፣ የበደሉንን ይቅር ማለት ፣ የበደልናቸውን ይቅርታ መጠየቅ ፣ የተጣላናቸውን መታረቅ ፣ መመፅወት ፣ ፆሙ የበረከት እንዲሆንልን መፀለይ ፣ መንፈሳዊ ምግባራትን መላበስ ፣ ከመጠን ያለፈ ደስታን ከራስ ማራቅና የመሳሰሉትን ከእኛ ጋር የሚስማሙትን መንፈሳዊ ተግባራት ከንስሐ አባታችን ጋር ተመካክረን ተግባራዊ በማድረግ ቅበላ ማድረግ ይኖርብናል።
በዚህ መሰረት የሚፈፀም ቅበላ ፆሙ ከመግባቱ በፊት መንፈሳችን እንዲዘጋጅ ከማድረጉም ባለፈ እግዚአብሔር ከፆሙ በፊት አስቀድሞ እንዲባርከን ያደርጋል።
ወዳጄ ሆይ የአንተ ቅበላ ከየትኛው ነው? መቼም በስካር በከርስ መሙላት በጭፈራና በዝሙት ቅዱሱን እንግዳ #ፆምን እንደማትቀበል ተስፋ አደርጋለሁ።
አበው "ከምግብ ብቻ በመከልከል እንጾማለን አትበሉ .. ከክፉ ግብር መራቅ ጾማችንን ትክክል ታደርጋለች" ይላሉ::
በዚህም የአባቶቻችን ልጆች እንባላለን አባቶቻችን የወረሷትን መንግስት በእውነት እንወርሳለን::
.
.
.
ኦ ጌታ ሆይ! ቸሩ አምላኬ ሆይ ሀጢያቴ እንደ ምድር አሸዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝቶ በደሌ ስፍር መለኪያ ጠፍቶለት ክፉዋ ምላሴ ፤ የተበረዘው ጭንቅላቴ ፤ የደነደነው ልቤ ሳያሰለችህ ሳያስቀይምህ ቀናትን በሳምንታት ሳምንታትን በወራት ወራትን በአመታት ተክተህ ለዚህች ቀን ስላደረስከኝ በደካማ አንደበቴ አመሰግንሀለሁ።
እንደ እውነቱ ዘመኑ ዓመተ ምህረት ባይሆን ኑሮ እኔ ገና ድሮ ነበር የምቀሰፍ! ገና ድሮ ነበር የምጠፋ! ግን አምላኬ ሆይ አንተ እንደ ሰው ስላልሆንክ ለፍርድ አልቸኮልክም በፍቅር ታገስከኝ በስስት ዓይንም ተመለከትከኝ።
ኦ አምላኬ ሆይ! እኔዋ ደካማይት ልጅህ ያለፈውን ፆም በቅጡ ሳልጠቀምበት ፍቃድህን ሳልፈፅም ደካሞችን ሳልረዳ የደከሙትን ሳልጎበኝ ያዘኑትን ሳላፅናና የሰጠህኝን ቅዱስ ቀናት እንዲሁ በከንቱ አሳለፍኩ።
ጌታ ሆይ እኔ ደካማ እንደሆንኩ ታውቃለህ አንተ እኮ የልብና የኩላሊትን የምትመረምር ቅዱስ አምላክ ነህ። እናም ድካሜን ታውቃለህ ስንፍናዬን ታውቃለህ አምላኬ ሆይ ታዲያ እንደዚህ ደካማ ሰው ሁኜ ፆምህን እንዴት ልፆም እችላለሁ? እንዴት 40 የፆም ቀናት በፍቃድህ ላሳልፍ እችላለሁ?
የድንግል ልጅ አማኑኤል ሆይ አንተ ካልረዳኸኝ አንተ ካልደገፍከኝ ታዲያ ይህን ነገር እንዴት ልወጣው እችላለሁ? አንተ እኮ መቅደላዊት ማርያምን ወደ ቅድስትነት ሙሴ ፀሊምን ከገዳይነት ወደ ባህታዊነት ሳኦልን ወደ ሰባኪነት ለውጠሀል። ጌታዬ ሆይ ታዲያ እኔን አንተ ካላገዝከኝ በእኔ አቅምማ እንዴት ይሆናል?
የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒአለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በእናትህ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በቅዱሳን መላዕክት አማላጅነት በፃድቃን ሰማዕታት ፀሎትና ምልጃ እያመንኩና እየተማፀንኩ ከሰይጣን ፍላፃዎች ሁሉ እንድትታደገኝና ለደካማዋ ልጅህ ትደርስላት ዘንድ በሀጢያት በተዳደፌ አንደበቴ እለምንሀለሁ!
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ፆሙ የበረከትና የፍሬ እንዲሆንልን ከወዲሁ እመኛለሁ!

23 Feb, 21:05
852
Post image

መንፈሳዊ ጉባኤ:
❖ ❖ ❖ ኪዳነ ምህረት (የካቲት 16) ❖ ❖ ❖
               ❖ ❖ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ❖
   ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡ ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችም እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄዘንድ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መትተህ ልምናዬን ትሰማኝ  እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡ እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጸውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡ ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበ አቡየ ሕያው ወበመንፈስ ቅዱስ ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል፡፡
   ሌላው በላዔ ሰብ በአማርኛ ሰው በላ ማለት ነው፤ ትክክለኛ ስሙ ግን ስምዖን ይባላል ቅምር በሚባል አገር የሚኖር እጅግ ባለጸጋ ነበር፤ እንደ አብርሃም እንግዶችን እየተቀበለ ድሆችን እየመገበ የሚኖር ጻድቅ ነበር፤ ሰይጣን በዚህ ስራው ቀናበት ሊፈትነውም በሦስት አረጋዊ ሽማግሌዎች ሥላሴ ነን ብሎ ተገለጠለት ልክ እንደ አብርሃም፤ ሐዋርያው ጳውሎስ ሰይጣን የብርሃን መልአክ መስሎ ይመጣል እንዳለ፤ እርሱም ሥላሴ መስለውት ተቀበላቸው ተንከባከባቸውም፤ ምግብ አቀረበላቸው ምግብ አንበላም የምንጠይቅህን ግን ትፈጽምልን ዘንድ ቃል ግባልን አሉት ቃል ገባላቸው እንግዲያውስ የምትወደን ከሆነ አንድያ ልጅህን ሰዋልን አሉት፤ መጀመሪያ ደነገጠ ኃላ አብርሃም ልጁን ሊሰዋ አልነበረምን እኔንም ሊፈትኑኝ ይሆናል ብሎ ለማረድ ተዘጋጀ፤ ተው የሚለው ድምጽ አልሰማም፤ አረደው አወራረደው ይዞላቸው ቀረበ፤ መጀመሪያ ቅመስልን አሉት ቀመሰው ወዲያው እነዚያ ሰዎች ተሰወሩበት እርሱም አህምሮውን ሳተ ተቅበዘበዘ ከዚያ በኃላ ምግብ አላሰኘውም የሰው ስጋ እንጂ መጀመሪያ ቤተሰቦቹን በላ ከዚያም ጓደኞቹን ጦርና የውኃ መንቀል ይዞ ከቤቱ ወጣ ያገኘውን ሰው እየገደለ ይበላል የበላቸው ሰው ቁጥር 78 ደረሰ፤ በመንገድ ተቀምጦ የሚለምን በደዌ የተመታ አንድ ደሃ አገኘ ሊበላው ወደ እርሱ ተጠጋ ግን ቁስሉን አይቶ ተጸየፈው፤ ደሃውም “ስለ እግዚአብሔር ከያዝከው ውኃ አጠጣኝ” አለው “ዝም በል ደሃ” ብሎት አለፈ፤ “አረ በውኃ ጥም ልሞት ነው ስለ ጻድቃን ስለ ቅዱሳን” አለው አሁንም ዝም ብሎት ሄደ ለሦስተኛ ጊዜ “ስለ አዛኝቷ ስለ ድንግል ማርያም” አለው፤ ሰውነቱን አንዳች ነገር ወረረው “አሁን የጠራከውን ስም እስኪ ድገመው ስለ ማን አልከኝ” አለው፤ ስለ አዛኝቷ ስለ እመቤቴ ማርያም አለው፤ ይህቺስ ደግ እንደሆነች በምልጃዋም ከሲኦል እንደምታወጣ ህጻን እያለው እናትና አባቴ ይነግሩኝ ነበር፤ በል እንካ አለው እጁን ዘረጋለት ጥርኝ ውኃ ጠብ አደረገለት ወደ ጉሮሮው አልወረደም የተሰነጠቀ እጁ ውስጥ ገባ እንጂ፤ በለዔ ሰብ ከዚያች ደቂቃ በኃላ አዕምሮው ተመለሰለት እንዲህም አለ “በአንድ ዋሻ ውስጥ ገብቼ ስለ ኃጢያቴ አለቅሳለሁ ስጋዬ ከአጥንቴ እስኪጣበቅ እጾማለሁ ወዮሊኝ ወዮታም አለብኝ አለ፤ ወደ ዋሻ ገባ ምግብ ሳይበላ ውኃም ሳይጠጣ 21 ቀን ኖሮ በርሃብ ሞተ ይላል ተአምረ ማርያም። ጨለማ የለበሱ ሰይጣናት እያስፈራሩ እያስደነገጡ ነፍሱን ወደ ሲኦል ሊወስዷት መጡ፤ እመቤታችን ፈጥና በመካከላቸው ተገኘች፤ ልጄ ወዳጄ ይህችን ነፍስ ማርሊኝ አለችው እናቴ ሆይ 78 ነፍሳትን የበላ እንዴት ይማራል አላት፤ የካቲት 16 ቀን በጎልጎታ የገባህልኝ ቃል ኪዳን አስብ ስምሽን የጠራ መታሰቢያሽን ያደረገን እምርልሻለው ብለኸኝ የለምን አለችው፤ እርሱም እስኪ ይህቺን ነፍስ በሚዛን አስቀምጧት አለ ቢያስቀምጧት ጥርኝ ውኃው መዝኖ ተገኘ፤ ስላንቺ ስል ምሬታለው ሰባት ቀን ሲኦልን አስጎብኝታችሁ ወደ ገነት አግቧት አላቸው። ቦታሽ እዚህ ነበር እያሉ ሲኦልን አስጎብኝተው ወደ ገነት አገቧት። ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን።
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
በዕለቱ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚቀርበውን የምስጋና ቃል እንደሚከተለው አቅርበናል መልካም በዓል፡፡
           ❖ ❖ ❖ ዋዜማ ❖ ❖ ❖
ሃሌ ሉያ (፬) ርግብየ ይቤላ በእንተ የዋሃታ፤
በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ፤
እንዘ አመቱ እሞ ረሰያ ፤
ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤
          ❖ ❖ ❖ ምልጣን ❖ ❖ ❖
እንዘ ዓመቱ እሞ ረሰያ ፤
ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤
        እግዚአብሔር ነግሠ
        እንተ ክርስቶስ በግዕት እንተ ታስተርኢ እምርኁቅ ብሔር፤
        በቤተልሔም አስተብረከት ዕጓለ አንበሳ ግሩመ ወለደት፡፡
           ❖ ❖ ❖ ይትባረክ ❖ ❖ ❖
እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፤
ቃል ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ፡፡
           ❖ ❖ ❖ ሰላም ❖ ❖ ❖
ሃሌ ሉያ (3) ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋትሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤
የሐንፁ አሕዛብ አረፋተኪ በዕንቊ ክቡር፤
ወመሠረትኪ በወርቅ ንጹሕ ይሰግዱ ለኪ ውስተ ገጸ ምድር፤
በእንተ ዕበየ ክብርኪ አምላከ ፳ኤል ውእቱ ረዳኢኪ
ዘአድኀነኪ እምእደ ጸላዕትኪ፤
ወረሰየ ሰላመ ለበሐውርትኪ፡፡
         ❖ ❖ ❖ መልክአ ሥላሴ ❖ ❖ ❖
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፡
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፡
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል ፡
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል
          ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ፤
እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፤
ከመ ትኩኒ ተንከተመ ለዉሉደ ሰብእ ለሕይወት ዘለዓለም፤
ለኪ ይደሉ ከመ ትኩኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ፤
ኦ መድኀኒተ ኵሉ ዓለም ፤
ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡
         ❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት ❖ ❖ ❖
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ;
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪየኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡
         ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኀኒት ለነፍስ ወሥጋ፤
እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ፤
ወኃጥአን ይስዕንዎን፤ ዘእንበለ ትብጻሕ ግብተ አሠንዩ ፍኖተ፤
ይፈኑ ለክሙ እመቅደሱ ረድኤተ መድኀኒተ መቤዛዊተ እሞ ቅድስተ፡፡

❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት ❖ ❖ ❖
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማልዎ በኮከብ፤
ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ፤
ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኀኒት ዘዐርብ፤
ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ሕሊና ቀዳማይ አብ፤
አመ እምገነቱ ተሰደ በኃዘን ዕፁብ፡፡
         ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም ፤
አመ ይሰደድ እምገነት፡፡
          ❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት በዓል ❖ ❖

23 Feb, 04:00
994
Post image

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

''... ወደ ባሕር ጣሉኝ....''
የፈጣሪ ዓለማት መጋቢ ዓለማት የእግዚአብሔር ልጆች ሁላችሁ ኦርቶዶክሳውያን በአላችሁበት ሠላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ
ወገኖች  ከአባቶች እንደተማርን የችግሮቻችን ሁሉ መክፈቻው ቁልፍ እጃችን ላይ ነው እና እንበርታ ።
ተወዳጆች ሆይ ዛሬ ሀገር እና ቤተክርስቲያን ከገቡበት የመከራ ማጥ እንዲወጡ ሁላችን ራሳችን ልናይ ይገባል።
ወዳጆቼ መጪውን የነነዌ ፆም  እራሳችንን ልንፈትሽ ነብዩ ዮናስ  እኔን ወደ ብሀሩ ጣሉኝ እንዳለ።
ቤተክርስቲያን እና ሀገር አሁን ላሉበት ችግር መንስኤው እኔ ነኝ እኔ ንስሀ ብገባ ፣ የይቅርታ እና የፍቅር ሠው ብሆን የዓለም ማዕበል ጸጥ ይላል ምድሪቱም ታርፋለች  በሚል ታላቅ እምነት እራሳችንን በአምላክ ደጅ እንጣል  ነብዩ ዮናስ
“... ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንዳገኛችሁ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፥ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል አላቸው። ዮናስ 1፥12 እንዳለ የኢትዮጵያ ውጫዊ እና ወስጣዊ ችግር እንዲፈታ የችግሩ ባለቤ እኔ ነኝ  በማለት እራሳችን በካህኑ እግር ስር በመጣል ፆመ  ነነዌን በአግባብ በመጠቀም ለሀገራችን እና ለቤተ ክርስቲያናችን እረፍት እስኪሰጥልን ልንተጋ ይገባል እላለሁ ። እናንተስ ምን ትላላችሁ ?
አምላከ ዮናስ በጎውን ሁሉ ያሰማን።
አምላከ ነነዌ ስለ ሕጻናቱ ብሎ ሀገራችንን እና ቤተክርስቲያናችንን ያሳርፍልን።
ገ/ራጉኤል
አዲስ አበባ
30/5/2017ዓ.ም

10 Feb, 11:46
1,857
Post image

https://youtu.be/JR-Oj0cVUHA?si=CQau8SpnXSk5tkg5

26 Jan, 21:20
2,362