Последние посты "ቃለ እግዚአብሔር " (@kaleegziabeher) в Telegram

Посты канала "ቃለ እግዚአብሔር "

"ቃለ እግዚአብሔር "
"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16

"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ

በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።
7,919 подписчиков
652 фото
22 видео
Последнее обновление 28.02.2025 18:30

Похожие каналы

TIKVAH-ETHIOPIA
1,535,964 подписчиков

Последний контент, опубликованный в "ቃለ እግዚአብሔር " на Telegram


መንፈሳዊ ጉባኤ:
ወንድም እህቶቼ እንኳን አደረሳችሁ

🙏🙏🙏🙏ይህንን ያውቃሉ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
❖ ❖ ❖እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት ተወልዶላችኋል ሉቃ.2፥11   ❖ ❖ ❖
     ❖ ❖ ❖ እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡  ❖ ❖ ❖
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

       ❖ ❖ ❖ " ጌና" ❖ ❖ ❖
ጌና እና ልደት {ዋዜማና ክብረ በዓል }
/የተለያዩ ቀናት/ ቢኾኑም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ጌና ልደትን እየተካ እንጠቀምበታለን ፤ ነገር ግን ይህ ሊስተካከል ይገባዋል፡፡ ልዩነት ስላለውም የኢትዮጵያ ብርሃን የተባለው አፈ ጳዝዮን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለጌናና ለልደት ለ2ቱም በዓላት ለየብቻቸው በመጽሐፈ ምሥጢር ድርሰት ደርሶላቸዋል፡፡
#ጌና ፤ የልደት በዓል ዋዜማ ቀን ሲኾን በዚህ ቀን ‹‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ›› የተባለለትን ‹‹የገና ጨዋታ›› እንጫወታለን፤ የምንጫወትበት የኳሱ ስያሜ ‹‹ሩር›› ሲባል ስያሜውን ያገኘው፤ ሰብዓ ሰገል እልፍ እልፍ ሠራዊት አስከትለው የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ ፍለጋ ወደ ንጉሡ ሔሮድስ ደርሰው ነበርና ፤ ሔሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ፈልጎና በውስጡ ሸሽጎ ለሰብዓ ሰገል ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ስታገኙትም ንገሩኝ ብሎ ሰድዷቸዋል ፤ ነገር ግን በዚያው ሳይነግሩኝ እንዳይሄዱ በማለት እነርሱ ሳያውቁ  ‹‹ሩር›› የተባለ ሰላይ በመሃላቸው አስገብቶ ነበርና ሰብዓ ሰገልን ይመራቸው የነበረው ኰከብ ተሠውሮባቸዋል ፤ ሰብዓ ሰገል ሠራዊታቸውን ቢያጣሩ ከመሃከላቸው የተቀላቀለ ሩር የተባለ የሔሮድስን ሰላይ አገኙ ይህንንም ሰላይ የሰብዓ ሰገል ሠራዊት አንገቱን በሰይፍ ቀልተውታልና ያን ለማስታወስ ዛሬ በገና ጨዋታ ላይ ሩር የተባለው ኳስ የሔሮድስ ሰላይን ‹‹ሩር›› እንዲያስታውስ አባቶች ሥርዐትን ሠሩ፡፡

     ❖ ❖ ❖ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ❖ ❖ ❖
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አይደለም፡፡ ከጥንት ከመሠረት ጀምሮ በመላእክት ፤ በነቢያት ሲነገር ፤ ሲሰበክ የመጣ ነው እንጂ፡፡ ማቴ.1፥18፡፡ ሰው የመሆኑን ምሥጢር ለመጀመሪያ ጊዜ በማዕከለ ገነት የተናገረ እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡
አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ ወጥቶ ዕፀ በለስን በልቶ ከጸጋ እግዚአብሔር በተራቆተ ጊዜ /አዳም ኮነ ከመ አሐዱ እምኔነ/ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ዘፍ.3፥22 ብሎ ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው እንደሚሆን ተናግሯል፡፡ በዚህ ቃል መሠረት /መሪነት/ ቅዱሳን መላእክት ምሥጢረ ትንቢት ተገልጾላቸዋል፡፡ እነሱም የተገለጸላቸውን ምሥጢረ ትንቢት ኀላፍያትንና መጻእያትን ለሚናገሩ ነቢያት ነግረዋቸዋል፡፡ ቅዱሳን ነቢያትም ከእግዚአብሔር ያገኙትን ከመላእክት የሰሙትን መነሻ አድርገው በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ምሳሌያት በተለያዩ ዘመናት የወልደ እግዚአብሔርን ሥጋዌ ሰብከዋል /ገልጸዋል/ ዕብ.1፥1፡፡ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፡፡

    የጌታችን ልደት በትንቢተ ነቢያት ፦
👉 ከዓበይት ነቢያት መካከል አንዱ የሆነው ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ የሚከተለውን ትንቢት ተናግሯል፡፡
"እነሆ ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች ( ኢሳ.7፥14፣ ሕዝ.44፥1) ፡፡ በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና የተወልደው አማኑኤል ጌታ ነው፡፡ ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ነቢዩ በጎላና በተረዳ ነገር “ሕፃን ተወልዶልናል ወልድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፡ ስሙም ድንቅ መካር ኀያል አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል“ በማለት የሚወለደው ሕፃን የባሕርይ አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ሥልጣን የባሕርይ ገንዘቡ እንደሆነ እና ለሥልጣኑም ወሰን ድንበር እንደሌለው ተናግሯል፡፡
👉 ከደቂቀ ነቢያት መካከል አንዱ ሚልክያስም በቤተልሔም ስለመወለዱ፡-
"የኤፍራታ ምድር አንቺ ቤተልሔም ከይሁዳ አለቆች ከቶ አታንሽም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና" (ሚክ.5፥2፣ ማቴ.2፥6) ብሏል፡፡
👉• ነቢየ እግዚብሔር ቅዱስ ዳዊትም "እነሆ በኤፍራታ ሰማነው ዛፍ በበዛበትም ቦታ አገኘነው እንግዲህስ ወደ እግዚአብሔር ማደሪዎች እንገባለን ብሎ የወመለዱን ምሥጢር ተናግሯል" (መዝ.131፥6)
👉• ነቢዩ ዕንባቆምም "አቤቱ ድምፅህን ሰምቼ ፈራሁ ሥራህንም ዐይቼ አደነቅሁ በሁለት እንስሶች መካከል አየሁህ ዘመኑ እንደደረሰ አድርጌ አውቅህአለሁ ዘመኑም በደረሰ ጊዜ ተገለጥክ" ብሎ በቤተልሔም በረት በተወለደ ጊዜ አድግና ላኅም እስትንፋሳቸውን እንደሚገብሩለት (ዕንባቆም 3፥1) ተናግሯል፡፡
ከዚህ በኋላ የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ እግዚአብሔር መልአኩን ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ድንግል ማርያም በመላክ አብሥሯታል፡፡ “ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል" በማለት፡፡ ሉቃ. 1፡32
እመቤታችንም በብዙ ኅብረ አምሳል ትንቢት ሲነገርለት፤ ምሳሌ ሲመሰልለት፤ ሱባኤ ሲቆጠርለት የነበረውን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በቤተልሔም ግርግም  ወለደችው፡፡
ይህንንም ብስራት በቤተልሔም ዋሻ መንጋቸውን ነቅተውና ተግተው ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች መጋቤ ሐዲስ አብሣሬ ትስብዕት ቅዱስ ገብርኤል ፤ እነሆ ዛሬ መድኀኒት በዳዊት ከተማ ተወልዶላችኋል ይኸውም ቡሩክ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሚያርቅ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ የሚያድል ከዓለም በፊት ንጉሥ የነበረ ዛሬም ከዳዊት ባሕርይ /ዘር/ በቤተልሔም ዋሻ ዓለምን ለማዳን የተወለደ የዳዊት ልጅ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ ተወለደ ሲል አበሰራቸው፡፡ (መዝ.73፥12)
💥 የጌታችንን ልደት ስናነሣ ሁለት ልደታት እንዳሉት እናምናለን፡፡ እኒሁም ልደታት /ልደት ቀደማዊና/ /ልደት ደኃራዊ/ ናቸው፡፡

ልደት ቀዳማዊ ፦ ቅድመ ዓለም ከአብ አካል ዘእም አካል ባሕርይ ዘእም ባሕርይ ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት የተወለደው ልደት ሲሆን /ነቢዩ ዳዊት እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ "ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽ ባህ መዝ.109፥3 ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ወለድኩህ ፤አንተ ልጄ ነህ እኔም ዛሬ ወለድኩህ" (መዝ.2፥7)
 
ልደት ደኃራዊ ፦ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈፀም በዕለት ሐሙስ ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ እንዲል ቃሉ፡፡ ቅድስት ድንግል ከምትሆን ከእመቤታችን እንበለ ዘርዓ ብዕሲ ያለ አባት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም የተወለደው ልደት ነው፡፡

#ለካስ_አባታችሁ : መቅደሱን : አጥነው : እየጠበቁአችሁ : ነበር !!!

....ከዓመታት በፊት በታኅሣሥ ሃያ አራት የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓልን ለማክበር በግብጽ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው ቁስቋም ወዳለው የጻድቁ ቤተ መቅደስ በሌሊት ይደርሳሉ ።

በስፍራው እንደደረሱም ከበሮ ይዘው « የኤቲሳ አንበሳ ተክልዬ ተነሣ» እያሉ እየዘመሩ በዛፎች እስከተከበበው እጅግ ሰፊው የገዳሙ ግቢ የውስጠኛ ክፍል ድረስ የጻድቁ አባታቸውን ስም እየጠሩ ገሠገሡ ።

ይህንን የተመለከቱ የገዳሙ አባቶች በደስታ ተውጠው ሲመለከቱ አንድ አባት ግን እየተንሰቀሰቁ ያለቅሱ ጀመር እኚህ አባት የተክለ ሃይማኖት መቅደስ ያለበትን ቤተ ክርስቲያን ቁልፍ የሚይዙ መነኩሴ ናቸው ።

የሚዘምሩትን ወጣቶች እያዩ በመደሰት ፈንታ ዕንባቸውን ለመግታት አልቻሉም ሁኔታው ግራ ያጋባቸው ኢትዮጵያውያኑ ወጣቶች ዝማሬአቸውን ገታ አድርገው እኚህን አባት ቀርበው የለቅሶአቸውን ምክንያት ለመጠየቅ ተገደዱ ።

መነኩሴውም እንዲህ ሲሉ ከዕንባ ጋር ነገሩአቸው ።

ትናንት ማታ ከሰርክ ጸሎት በኋላ እንደተለመደው ቤተ ክርስቲያኑን ልቆልፍ ስል ከተክለ ሃይማኖት መቅደስ ውስጥ ጢስ ሲወጣ ተመለከትሁ ምናልባት የሚነድ ነገር ይኖር ይሆናል ብዬ ወደ ውስጥ ስገባ መቅደሱ በዕጣን ጢስ ተሞልቷል ።

ምንም የሚነድ ነገር ግን የለም በነገሩ ተገርሜ ቤተ ክርስቲያኑን ቆልፌ ሔድኩ ለካስ አባታችሁ እናንተ ዛሬ እንደምትመጡ አውቀው መቅደሱን አጥነው እየጠበቁአችሁ ነበር !! አሏቸው ።

የኢትዮጵያ : ቤተ: ክርስቲያን : ከመላእክት : ጋር : የዘመረ : ቅዱስ : ያሬድን ከካህናተ :ሰማይ :ጋር :ያጠነ :ተክለ :ሃይማኖትን :ያፈራች :ቤተክርስቲያን :ናት

#ከግዮን_ወንዝ_መጽሐፍ_የተወሰደ

ግሩም ምስጢር ያለው ወፍ
"ከራድዮን ወፍ ይባላል
ከራድዮን ነጭ ወፍ ሲሆን በሊቃውንት ዘንድ የታወቀ ነው። ጠቢባን በድካም ፈልገው አድነው ይይዙታል፣ የታመመ ሰው
ቢኖር ያቀርቡታል ፤ እሱም በሽተኛውን ትኩር ብሎ ያየዋል የማይድን ለሞት የቀረበ ከሆነ ፊቱን አዙሮ ይመለሳል፣ ቀኑ ገና
ከሆነ ግን አፉን ከፍቶ ከበሽተኛው አፍ እስትንፋሱን ይወስዳል፣ በልዑል እግዚአብሔር ኃይል የሰውየው ደዌ ሙሉ ለሙሉ
ወደ ወፉ በእስትንፋሱ ይተላለፋል። ሰውየው ይድናል ወፉ ይታመማል።
ፊት ነጭ የነበረው እንደ ከሰል ይጠቁራል፣ ህመም ሲሰማው ወደ አየር ይነጠቃል ሲብስበት ወደ ባህር ራሱን
ይወረውራል። በባህር 3 መዓልት 3 ሌሊት ቆይቶ ጽጉሩን መልጦ አዲስ ተክቶ፣ድኖ፣ታድሶ፣ኃያል ሆኖ ይወጣል።
ይህ ፍጥረት በዕለተ። ሃሙስ እግዚአብሔር ፈጥሮታል።
ስለምን ፈጠርው ቢሉ የወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስን ሞትና ትንሳዔ ለማያምኑ ትምህርት ምሳሌ አብነት ይሆን ዘንድ
ሥላሴ ይህን ወፍ የማዳን ኃይል ሰተው ፈጥረውታል።
ትንታኔ፦
ከራድዮን ወፍ ---- የክርስቶስ ምሳሌ
የታመመው ሰው --- የአዳም ዘር ምሳሌ ሲሆን
ወፉ በዐይኑ መመልከቱ --- በክርስቶስ ላመነ ሁሉ ድኅነት ምህረት ማግኘቱ ምሳሌ
ወፉ መታመሙ---- ክርስቶስ ስለ እኛ በደል መታመሙ ምሳሌ።
መጥቆሩ ---- ስለእኛ ቤዛ ከኀጢአተኛ የመቆጠሩ ምሳሌ
ወፉ ወደ ላይ መውጣቱ---- ክርስቶስ ከፍ ብሎ መሰቀሉ ምሳሌ
ወፉ በባህር 3ቀን 3ሌሊት መኖሩ ----ክርስቶስ በከርሰ መቃብር 3ቀን 3 ሌሊት መቆየቱ ምሳሌ
ከራድዮን ወፍ ታድሶ ኃያል ሆኖ ከባህር መውጣቱ ---ክርስቶስ በሲዖል የነበሩ ነፍሳትን አድሶ አንጽቶ ገነት አስገብቶ፤
እርሱም ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው በለበሰው ሥጋ ወደ ቀደሞ መለኮታዊ ሥልጣኑ ኃይሉ መቀመጡ ምሳሌ
ነው።
..........
እንግዲህ ምን እንላለን ሥላሴ  አስቀድመው የአዳምን መበደል ሞትም እንዲመጣበት ያውቃሉና ገና ዓለም ሲፈጠር
እግዚአብሔር አንድያ ልጁን አሳልፎ ለመስጠት ዝግጁ እንደ ነበር የከራዲዮን ወፍ አፈጣጠር ምስክር ሆነን።
እግዚአብሔር ፍቅር ነው የምንለው ለዚህ ነው።
ይቆየን
ቸርነቱ ፍቅሩ ምህረቱ አይለየን
ምንጭ የሥነ ፍጥረት አንድምታ፣ መጽሐፈ አክሲማሮስ፤
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
ስመ ዖፍ ጥሩ ነጭ መልከ መልካም ወፍ የክርስቶስ አርኣያ የሰውነቱ አምሳል ፊላሎጎስ መጽሐፍ ተመልከት፡፡
ለዘተወልደ እምድንግል ምንተ ንብሎ ናስተማስሎ አርዌ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ ከራድዮን ዖፍ ጸዐዳ ንጉሠ ይሁዳ
እምዘርዐ ዳዊት ዘመጽአ (ድጓ)፡፡

እጅግ በጣም በጣም ግሩም የሆነ ትምህርት ነው። ብታዳምጡት ብዙ ታተርፉበታላችሁ፣ ለሌሎችም ሼር አድርጉ።

https://youtu.be/WPMsnzwy0Js?si=lM220hfrAGQL_uxQ

እጅግ በጣም በጣም ግሩም የሆነ ትምህርት ነው። ብታዳምጡት ብዙ ታተርፉበታላችሁ፣ ለሌሎችም ሼር አድርጉ።

ታህሳስ ፫ በታዕካ ነገስ በዓታ ማርያም ታላቋ ገዳም እንገና
          ።።።።   እንኳን አደረሳሽሁ።፡።።።።

✝️እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት (በዓታ ማርያም ውስተ ቤተ መቅደስ) ዓመታዊ መታሰቢያ ታላቅ የንግሥ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን፤ አደረሳችሁ።

✝️ታህሳስ ፫ በአታ ለእግዝእትነ ማርያም ውስተ ቤተመቅደስ

“እበውዕ ቤተከ ምስለ መባእየ” ፤ “ከመባዬ ጋራ ወደ ቤትህ እገባለሁ።” መዝ. ፷፭(፷፮)፥፲፫

እመቤታችን አባቷ ኢያቄም እናቷ ሐና ይባላሉ። በፈቃደ እግዚአብሔር በብስራተ መልአክ ወልደዋታል። የብፅዓት ልጅ ናትና ሶስት ዓመት ሲሆናት ይህች ልጅ አንድ ነገር ብትሆን ከእግዚአብሔርም ከልጃችንም ሳንሆን እንዳንቀር ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ወስደን እንስጥ ብለው መባዕ ጨምረው ወደ ቤተመቅደስ ይዘዋት ሄዱ።

ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ መጥቅዕ መጥቶ ሕዝቡን ሰብስቦ የምግቧ ነገር ይያዝልኝ አለ። ወዲያው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ ይዞ ረቦ ታየ። ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ መስሎት ዛሬስ ክብሬን በሰው ፊት ሊገልጸው ነው ብሎ ሊቀበል ተነሣ። መልአኩ ወደ ላይ ራቀበት። የእርሱ ተወራጅ ስምዖንም እንኪያስ ለእኔ የመጣ ይሆናል ብሎ ቀረበ። ራቀበት። ካህናቱም ሕዝቡም በተራ ቢቀርቡ ራቀባቸው። ምናልባት ጥበበ እግዚአብሔር አይመረመርም ለዚህች ብላቴና የመጣ እንደሆነ እንይ ሐና ትተሻት እልፍ በይ አሏት። ትታት እልፍ አለች።

ድክ ድክ እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ በሰው ቁመት ልክ ከመሬት ከፍ አድርጎ መግቧት ዐረገ። የምግቧ ነገር ከተያዘልንማ ትግባ እንጁ ብለው ከመካነ ደናግል አስገቧት። “ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ዐሠርተ ወክልዔተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት” ይላል። ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየተመገበች መላእክት  እየጎበኟት ፲፪ ዓመት በቤተ መቅደስ ኖራለች።

የእናታችን ምልጃና ጸሎት አይለየን፤ ረድኤት በረከቷን ያሳድርብን፤ ከበዓሏ በረከትም ያሳትፈን። የዓመት ሰው ይበለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

https://www.facebook.com/share/19tuiw5Qai/?mibextid=xfxF2i

ስራ መስራት እንደሚገባን እንዳንሰንፍ የሚያስተምር ጥሩ የ10 ደቂቃ ትምህርት ነው። በተለይ ሴቶችም መጠበቅ ሳይሆን መስራት እንደሚገባቸው በደንብ አስተምሮናል።

https://youtu.be/RS8nWUhDkoc?si=J8A1w7RI8NW_My8i

ህዳር 21 ታቦተ ጽዮን የምትከብርበት ዕለት

ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል መዝ 86+5
ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ  ይፈሩ መዝ 128+5
እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና ይላል መዝሙረኛው እግዚአብሔር የመረጣትን መጥላት ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት ነው

በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት፦

1 ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት ነው

2 ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት ነው

3 አበው  ነቢያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነቢዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ነቢዩ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተ መቅደስ፣ ነቢዩ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ያዩበትን ዕለትነው

4 ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት ነው

5  በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን ዕለት ነው

6 ለታቦተ ጽዮን ማደሪያ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ ነው

7 በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ ነው
መልካም በዓል

እግዚአብሔር ተስፋ አድርግ
                            
ለመንጋው ሁሉ በጎ እንደሚመኝ እንደ መልካም እረኛ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ በሙሉ ያለምንም ጥርጥር #በዝምታ_ይሠራል ። ይሁን እንጂ ሰዎች በመከራ ውስጥ ሆነው የእግዚአብሔር መልስ ከዘገየባቸው እንደማይሠራ  አድርገው ያስባሉ ። እነርሱ እግዚአብሔር አይሠራም ብለው በሚያስብበት  ሰዓት ሁሉ እርሱ ግን ለእነርሱ #በጥልቅ_እየሠራ ነው ። ሰዎች ይህንን ስለማይገነዘቡ የእግዚአብሔርን ሥራና የሥራውን ውጤት ፈጥነው ለማየት ይፈልጋሉ ። እነዚህ ሰዎች ግን በእምነታቸው ያመኑትን በዓይናቸው እስኪመለከቱ ድረስ ሊቆዩ ይገባቸዋል ። " እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ፤ በርታ ልብህም ይጽና ፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ። " [መዝ 26*14 ] ።
እግዚአብሔርን እንዴት እንጠብቅ?

እግዚአብሔርን የሚጠብቅ ሰው እርሱን በተስፋ ፤ በእምነት ፤ በተሞላ ሙሉ ልብና ያለምንም ድካም ይጠብቀዋል ። ይህ በመሆኑም እንደዚህ ዓይነቱ ሰው እግዚአብሔር በመካከል ገብቶ እንደሚሰራና ሁሉም ነገር ለበጎ እንደሚሆን ያምናል ። " እግዚአብሔር ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን ።" [ ሮሜ 8*28] ። " እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም ይሄዳሉ አይደክሙም " [ኢሳ 40*31] ። ኃይላቸው በመከራ የተናወጠባቸው ሁሉ እግዚአብሔርን በተስፋ በመጠባበቅ ኃይላቸውን ያድሳሉ ማለት ነው ። " ጎልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል " የሚል ቃል ተጽፋል [ መዝ 102*5] ። ስለሆነም ማንም ቢሆን እግዚአብሔር #እምነት በተሞላ ብርቱ ልብና በእርሱ ላይ በመተማመን ይጠብቀዋል ።
ነገር ግን አንድ ሰው እግዚአብሔር እርምጃ እንደሚወስድና እርምጃውም ግልጽና ኃያል እንደሆነ መተማመን አለበት ። ከዚሁ ጋር እርምጃው በተመቻቸ ሰዓት ፍሬያማ በሆነ መንገድ የሚከናወን ነው ። እግዚአብሔር አንድ የሆነ እርምጃ ለመውሰድ ከወደደ ምንም የሚጠባበቀው ሰዓት አይኖርም ። ኢየሱስ ክርስቶስ " ... አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም አላለምን ? /ሐዋ 1*7/ ። አንተ ችግርህን እግዚአብሔር እንደሚያቃልልህ በማመን መቼ ለችግርህ መፍትሔ እንደሚሰጥህ ሳታስብ በእርሱ እጅ ላይ ብቻ ጣለው ። ችግርህን እግዚአብሔር በጊዜው እንደሚያቃልለው መጠባበቅ የአንተ ሥራ አይደለም ።