Dernières publications de 🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸 (@hamdquante) sur Telegram

Publications du canal 🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው።

✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼
👇🏾👇🏾👇🏾
@hamdquante

አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል
👉🏿 @hamdquante_bot👈🏿
12,295 abonnés
2,253 photos
202 vidéos
Dernière mise à jour 01.03.2025 04:42

Le dernier contenu partagé par 🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸 sur Telegram



     🌙 የት ለመስገድ አስበዋል⁉️

🕌መስጂደል ፉርቃን አላህ ይጠብቃትና ዘንድሮም እንደ አምናው ሰጋጆቿን ለመቀበል ሽር…ጉድ በማለት ላይ ትገኛለች።

  በአላህ ፍቃድ ከዛሬ የመጀመሪያው የረመዷን ሌሊት ጀምሮ የተራዊሕ እና የተኸጁድ ሰላቶች በድምቀት የሚጀመሩ ይሆናል።

በዚህም መሰረት;
  በመጀመሪያው ሌሊት የተራዊሕ ሰላት የሚሰገድ ሲሆን;
👇
👉የለይል ሰላት ከሌሊቱ 7:00 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል‼️

ልብ ይበሉ;
    🕰7:00 ሰዓት ማለት ኢማሙ ተክቢረተል ኢህራም አድርጎ ሰላቱን የሚጀምርበት ነው።
እርሶ ግን ቢያንስ 6:30 መገኘት ይኖርቦታል።


  በሕይወታችን ሌላ ረመዷን ለማግኘታችን ምንም ማረጋገጫ ስለ ሌለን በአላህ እየታገዝን መወጠር ይኖርብናል።

  🕌መስጂደል ፉርቃን
       🛣ዓለም ባንክ ስልጤ ሰፈር


💫አቅምና ነሻጣ ያለው
           የለይል ሰላት 🕰7:00
💫እንቅልፍና ድካም የፈራ
  የተራዊሕ ሰላት ከዒሻ ሰላት ቀጥሎ‼️ ይካፈል

በድጋሚ
         🌙🌙                   🌙🌙
                 ረመዷን ሙባረክ
          🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙

📎 https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio


የረመዷን ድምቀት የእስልምና ውበት
አጉልቶ ማሳያው የሙስሊሞች ሕብረት

ወጥረህ በርትተህ
ዛሬውኑ ጀምር የተራዊሕ ሰላት!!




https://t.me/hamdquante

🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙

ተነስ
ወጥር
ጀምር!!





https://t.me/hamdquante

✴️🌙 ሰበር ዜና ... ሰበር ዜና ⤵️

✴️ 🌙 ...*عاجل ... عاجل*...

*تم رصد هلال رمضان في تمير*

*غداً السبت أول أيام شهر رمضان المبارك*

*{تقبل الله منا ومنكم صالح الاعمال}*

* "الراصد نيوز"

📮 ሱዑዲ ላይ ጨረቃ ስለታየች አላህ
ካለ ነገ ቅዳሜ የረመዷን ፆም ጅማሬ ይሆናል።


💻 አል-ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱድዮ
              የሰለፍዮች ልሳን!!

📎
https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio

🌙
    ስኬታማ የምትሆንበት ረመዷን እንዲሆን ትፈልጋለህ??

እንግዲያውስ……………
  "የሕይወቴ የመጨረሻው ረመዷን ሊሆን ይችላል" ብለህ ጹመው!!



ሞት አፋፍ ላይ ያለ ሰው ታውቃለህ??
  በጣም ወሳኝ እና አስፈላጊ የሚላቸው ቃላቶች መርጦ እንጂ አይናገርም፤

  አንተም ለቀጣዩ ረመዷን ስለ መድረስህ ምንም ማስተማመኛ የለህምና  
የመጨረሻህ ረመዷን እንደሚሆን በማሰብ በጥንቃቄ ተጠቀምበት።




https://t.me/hamdquante

🌙
   ስለ ታላቁ ረመዷን ከታላቁ ሸይኽ……

🌙ما نصيحتكم للمسلمين بمناسبة اقتراب شهر رمضان؟
የረመዷን ወር መቃረቡን አስመልክተው ለሙስሊሞች ምን ይመክራሉ?


الجواب:
🌙الواجب على المسلم يسأل الله أن يبلغه رمضان وأن يعينه على صيامه وقيامه، والعمل فيه،
  አንድ ሙስሊም አላህ ለረመዷን ወር እንዲያደርሰው እና አድርሶትም ጾሙ ላይ፣ ስግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘው አላህን መለመን አለበት።

🌙 لأنه فرصة في حياة المسلم: مَنْ صَامَ رَمَضَانَ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ ، مَنْ قَامَ رَمَضَانَ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ ،
ምክንያቱም፦
   ይህ ወር ለአንድ ሙስሊም በሕይወቱ የሚያገኘው ትልቅ ዕድል ነው። ረሱልﷺ እንዲህ አሉ:-
  «ረመዷን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የጾመ ያለፈው ወንጀሉን ይማርለታል። ረመዷን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የሰገደ ያለፈው ወንጀሉን ይማርለታል።»

🌙فهو فرصة في حياة المسلم قد لا يعود عليه مرة ثانية.
ይህ ወር ምን አልባትም ላይመለስ የሚችል ዕድል ነው።

🌙فالمسلم يفرح بقدوم رمضان ويستبشر به، ويستقبله بالفرح والسرور، ويستغله في طاعة الله ليله قيام، ونهاره صيام وتلاوة للقرآن والذكر فهو مغنم للمسلم،
  ሙስሊም የሆነ ሰው ረመዷን ሲመጣ ይደሰታል፣ ተስፋም ያደርጋል፣ በደስታ ይቀበለዋል፣ ዕድሉን በደንብ በመጠቀም በአላህ ትዕዛዝ ላይ ያሳልፈዋል። ሌሊቱን በመቆም፣ ቀኑን በመጾም፣ ቁርኣን በመቅራት እና አላህን በማውሳት ያሳልፈዋል። ትልቅ ዕድል ነው።

🌙أما الذين إذا أقبل رمضان يعدون البرامج الفاسدة والملهية والمسلسلات والخزعبلات والمسابقات ليشغلوا المسلمين فهؤلاء جند الشيطان، الشيطان جندهم لهذا،
  እነዝያ ግን ረመዷን ሲደርስ አዘናጊ ፕሮግራሞች፣ ፊልሞች፣ ዝባዝንኬዎች እና ውድድሮችን የሚያዘጋጁት; እነርሱ የሸይጣን ወታደሮች ናቸው። ሸይጣን ነው ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸው ያስታጠቃቸው።

🌙فعلى المسلم أن يحذر من هؤلاء ويحذر منهم،
  ሙስሊሞች ከእነዚህ ሰዎች መጠንቀቅና ማስጠንቀቅ ይኖርባቸዋል።

🌙رمضان ما هو وقت لهو ولعب ومسلسلات وجوائز ومسابقات وضياع للوقت.
  ረመዷን የፍንጥዝያ፣ የጨዋታ፣ የፊልም እና የውድድር ወር አይደለም።
[ሸይኹል ዓላማህ  ሷሊሕ አል_ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸው]


     🤲አላህ ለተከበረው
         🌙🌙🌙🌙🌙🌙
        🌙የረመዷን ወር🌙
         🌙🌙🌙🌙🌙🌙 በሰላም ያድርሰን






https://t.me/hamdquante

🤲
    አላህ ደርሰው ከሚጾሙት ያድርገን🤲



https://t.me/hamdquante


    "ከዚህ በፊት መስጂድ ውስጥ በሚሰገድ ጊዜ ብዙ ኢማሞች እየቀሩ ያለቅሱ ነበር: እነርሱ ሲያለቅሱ ከኋላ ያሉ ሰጋጆችም አብረው ያለቅሱ ነበር። አሁን አሁን ግን የሚያለቅስ ኢማም የለም: ኢማሞቹ ቢያለቅሱ እንኳ ተከትሎ የሚያለቅስ ማእሙን የለም። ለምን??"
   ብሎ ሲጠይቅ አንዱ ሰማውና ምን ቢለው ጥሩ ነው……………
:
:
:
:
:
:
"ሁሉም ተነቃቅተው ነው።"


🤲አላህ ቀልባችን ያርጥብልን🤲


ለማንኛውም……………
  ዛሬም ተራዊሕ ሊጀመር ይችላልና ነሸጥ ብላችሁ ተዘጋጁ!!

https://t.me/hamdquante

🌙
     ረመዷን ከማብሰር የበለጠ ሰዎች የሚያስደስት ነገር ምን አለ ከቶ??

ረመዷን መጣላችሁ!!
  أتاكم رمضان شهر مبارك




https://t.me/hamdquante


    ከባድ ፆታ ናቸው እኮ……………
 
  ጾሙን ዋለና ከፉጡር በፊት ዱዐ ተቀባይነት አለው በሚባለው ሰዓት ላይ ቁጭ ብሌ ለላጤ ጓደኛው ዱዐ እያደረገ ነው;
🤲"አላህ ሆይ! ጓደኛዬን የተከበረች እና ከተከበረ ቤት የወጣች፣ መልኳ ያማረ፣ ኢማኗ የሰመረ፣ ወላጅ እና ተወዳጅ የሆነች ሷሊሕ ሚስት ስጠው"🤲 ብሎ ሲለምን ጓዳ የነበረችው ሚስቱ ትሰማዋለች።

በቁጣ ከፊቱ ቆማ  "አስተዋይ ብትሆንማ ለጓደኛህ አላህ ጤና፣ ስራ፣ ኢማን እና ሀብት እንዲሰጠው ነበር የምትለምንለት" አለችው።

"አልሃምዱሊላህ! ጓደኛዬ ሁሉም ነገር ሞልቶታል ሚስት ብቻ ነው የጎደለው" አላት።

  ለዱዐ ያነሳቸው እጆቹ ሰብስባ ይዛ "ሁለተኛ አሁን የሰማሁህ ዐይነት ዱዐ ለጓደኛህ ስታደርግ እንዳልሰማህ" አለችው።


"እህእ! ምንድን ነው ለጓደኛዬ በለመንኩበት እንዲህ ያበሰጫጨሽ?" ብሎ በአግራሞት ሲጠይቃት
:
:
:
:
:
  "አንተ ለወንድምህ ዱዐ ስታደርግ መላኢካ "ለአንተም እንደዛው" እንደሚልህ አታውቅምና ነው??!!" ብላው እርፍ






https://t.me/hamdquante