ብዙ ጊዜ……………
📖ቁርኣን በተደቡር እና ብዙ ለመቅራት ፈልገን ሙስኸፉን ከፍተን ቁጭ ስንል ቶሎ ይደክመናል፤ ሞራላችን ይሞታል፤ ይጫጫነናል፤ ጥፍጥናው አይመጣልንም፤ ለማስተንተን አይከፍትልንም፤፤፤ ብዙ ብዙ ነገር።
ይህ ሁሉ የሚሆነው……………
በኢማናችን ማነሰ እና መድከም ቢሆንም;
የተሻለ ነሻጣ፣ ጉጉት እና አቅም እንዲኖረን አንዲት ተሞክሮ ላካፍላችሁ።
የቁርኣን ነሻጣችሁ ቀንሶ ጥፍጥናው አልመጣ ብሎ ሲያስቸግራችሁ………
ለየት ባለ መልኩ ስለ 📖ቁርኣን የተፃፉ አጫጭር ሪሳላዎች ገረፍ ገረፍ አድርጋችሁ አንብቡ።
📚ስለ ቁርኣን ቱሩፋት፣
📚የቁርኣን በላጭነት፣
📚የቁርኣን ሙእጂዛ፣
📚ቁርኣንን ስለ ማስተንተን፣
📚የቁርኣን አሸናፊነት፣
እና በመሳሰሉ ርዕስ ዙሪያ የተዘጋጁ ኪታቦች አየት አርጉ።
የዛኔ……………
"ይህ ሁሉ ክብር፣ እልቅና እና ተኣምራት ያለው የእኔ መተዳደሪያ የሆነው፣ አንብቤ ልረዳው የምችለው 📖ቁርኣን ነውን?" የሚል ጉጉት ውስጣችሁ ይፈጠርና በአላህ ፍቃድ ቁርኣን እየጣፈጣችሁ ማንበብ ትችላላችሁ!!
🌙ረመዷን ሙባረክ🌙
https://t.me/hamdquante