Habib Kedir

@habib_kedir


Habib Kedir

22 Oct, 17:48


በመርካቶው የእሳት አደጋ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው
***
ሀብት ንብረት ብቻ አይደለም የወደመው
ብዙ ወንድሞቻችን ሆስፒታል ናቸው
ዛሬ ሆስፒታል ሄደን በህክምና ያሉ ወንድሞችን ጠይቀናል።
መውጫ አጥተው ህይወታቸው ያለፈም አሉ።
በተቻለ መጠን ከነዚህ ወገኖቻችን ጎን መቆም አለብን
***
በአካልም፣ በስልክም ያገኘናቸው ተጎጂዎች በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥም ሆነው ከአንደበታቸው የሚወጣው አልሀምዱሊላህ ብቻ ነው።
ለፈተና በማይገበሩ፣
ሁሉም ነገር ለበጎ ነው በሚሉ ብርቱ ሰዎች ላይ የአላህ እዝነትና ራህመት ይስፈን።
***
ለሞተባችሁ ሶብርን
ህክምና ላላችሁ አፊያን
ንብረት ለጠፋባችሁ የተሻለውን ፈጣሪ ይወፍቃችሁ🤲
***

Habib Kedir

21 Oct, 21:03


መርካቶ የተከሰተው እሳት አደጋ ልብን ይሰብራል።
በብዛት የምናውቃቸው ወገኖቻችን ሀብት ንብረት ወድሟል
ሀዘኔን ከመግለፅ ውጪ ማፅናኛ ቃል እንኳን የለኝም
አላህ በተሻለው ይተካላችሁ

Habib Kedir

19 Oct, 16:41


#ተሞሽረዋል
መብሩክ በሏቸው

ፉአዴ እንኳንም ለወግ ማዕረግ በቃህ
መብሩክ አልፍ መብሩክ ብያለሁ
ወንድሜ ፉአድ አጫሉና ነኢማ አብድረህማን ዘመናችሁ ሁሉ የስኬትና የሀሴት ይሆንላችሁ
ባልና ሚስት ካንድ ወንዝ ይቀዱ የለ?
ውቦች ናችሁ ማሻአላህ

Habib Kedir

19 Oct, 06:55


ኢማም ሲዴ
ታሪኩን ስሙ

Habib Kedir

17 Oct, 19:05


#ሼር አድርጉት
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አርቲስቶች
ፕሮግራም አላቸው
***
አርት የማህበረሰብን ባህል፣ ወግና ታሪክን ወደ ትውልድ ማሻገርያ መሳርያ ነው። አርት ህዝብን ከህዝብ በማቀራረብ ለሰላም ያለው ፋይዳም ከፍተኛ ነው።
****
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አርቲስቶች የህዝባቸውን ባህል ለማስተዋወቅ ብዙ መስዋዕትነት ይከፍላሉ። ስለ ራሳቸው ሳይኖሩ ስለ ማህበረሰብ ገፅታ ይኳትናሉ፣ ነገር ግን እምብዛም ትኩረት የሚሰጣቸውና የሚረዳቸው የለም።
እናም እናበርታቸው
***
በመጪው እሁድ ማለትም ጥቅምት 10/2017 ዓም በአዲስ አበባ በአምባሳደር ሲኒማ አንጋፋ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አርቲስቶች የሚሳተፉበት ፕሮግራም ተዘጋጅቷል።
***
በርካታ ወጣት ድምፃዊያን የሚሳተፉበት ታሪካዊ ኮንሰርት ነው። እሁድ ከቀኑ 7 ሰአት ጀምሮ አምባሰደር እንዳትቀሩ።
አዘጋጁና አስተባባሪው ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ከድር ሁሴን ሲሆን ከድር በስልጤ፣ በቀቤና፣ በጉራጌ፣ በሀላባ፣ በማረቆና በሀድያ የባህል ስራዎቹ የሚታወቅ ታታሪና ሁለመናውን ለአርት የሰጠ ሰው ነው።
ኮሜዲያን ያሲኖን እና መኪዩ ናስር ወማን ጨምሮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ወጣትና አንጋፋ አርቲስቶች በጋራ ይታደማሉ።
***
ጥቅምት 10 እለተ እሁድ ከቀኑ 7 ሰአት ጀምሮ አምባሰደር አዳራሽ በቀቤንኛ፣ በስልጢኛ፣ በጉራጊኛ፣ በማረቆና በሀላቢኛ የባህል ስራዎች ይደምቃል።
ታዋቂ አርቲስቶች ሁሉም ይሳተፋሉ።
አርትን እናበርታ
አርቲስቶቻችንን እንደግፍ
መድረኩን እንታደም
***

Habib Kedir

11 Oct, 06:12


I'm on Instagram as @habibkedir2021. Install the app to follow my photos and videos. https://www.instagram.com/invites/contact/?igsh=15fri963le4w7&utm_content=v24d0st

Habib Kedir

05 Oct, 09:55


መልካም በዓል
የኦሮሞ ወንድሞቻችን

Habib Kedir

04 Oct, 06:40


መስከረም 24
የቀቤና ልዩ ወረዳ በኢፋ የተመሰረተበት ቀን ነው
እንኳን አደረሳችሁ
***
ይህን ቀን እንድናይ ብዙዎች ተሰውተዋል
ብዙዎች ታስረዋል፣ ተሰቃይተዋል
ይህ ሲሆን ማየትን ሲናፍቁ የነበሩ አባቶች አልታደሉም
የህብረት፣ የመከባበር፣ የአንድነትና የመናበብ ተምሳሌት የሆነውን የመስከረም 24 የነፃነት በዓላችንን ማሰብ፣ ማክበርና ለትውልድ እንዲያልፍ ማድረግ ጥቅሙ ብዙ ነው።
***
የትውልዱ ገድልና የህዝቡ ጥንካሬ መገለጫ የሆነውን ይህን ቀን በቀቤና ልዩ ወረዳ አስተዳደር ደረጃ በተለያየ ኩነት ቢከበር የህዝቡን ልዕልናና ሞራል መገንባት ይሆናል።
መስከረም 24 በሀሴት የተሞላችሁ፣ የደስታ እንባ ያነባችሁ ወገኖች ትውስታችሁን አጋሩን
እንኳንም አደረሰን
***

Habib Kedir

26 Sep, 14:10


በመላው ዓለም የምትገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን መልካም የደመራና የመስቀል በዓል ይሁንላችሁ

Habib Kedir

25 Sep, 22:43


ዋልታ ቲቪ ስለ ወልቂጤ ዘገባ አብዝቷል።
ጋዜጠኛ ስሜነህ እና አቶ እንዳለ ብዙ ዋጋ ከፍለው አከባቢውን የሚያረጋጉ የፀጥታ ሀይሎችን የሚወቅስቡት መንገድ ግልፅ አይደለም።

Habib Kedir

24 Sep, 17:36


የከምባታ ህዝብ የ2017 የመሳላ ዘመን መለወጫ በአል በድምቀት እየተከበረ ነው
የከምባታ ወንድሞቻችን መልካም የዘመን መለወጫ በዓል ይሁንላችሁ