Latest Posts from Habib Kedir (@habib_kedir) on Telegram

Habib Kedir Telegram Posts

Habib Kedir
5,789 Subscribers
4,408 Photos
460 Videos
Last Updated 01.03.2025 15:35

Similar Channels

Tsegaye R Ararssa
15,254 Subscribers
Jl Siinan (Abbaa Sardaa)
5,087 Subscribers

The latest content shared by Habib Kedir on Telegram


ይህን ተቋም እንደግፍ
🌴 #አንሷር የየቲሞችና የአቅመ ደካሞች መርጃ ማህበር ወልቂጤ
***
ይህ በጎ አድራጎት ማህበር ከተቋቋመ አጭር ግዜ ቢሆንም ያደረጋቸው እንቅስቃሴዎች በርካታ ናቸው።
አቅመ ደካሞዎችና ተረጂ ህጻናትን በየቀበሌው እየዞሩ የሚብሱትን ይለያሉ
ረመዳን ያሲዛሉ፣ ያስፈታሉ፣
ቤት ያድሳሉ፣ ይሰራሉ፣
የሚቀመስ ለሌላቸው እህል ያቀርባሉ፣
ሰዎች ጾም ወለው እንዳያድሩ ይተጋሉ፣
የትምህርት ቁሳቁስ ለህጻናት ያቀርባሉ፣
ልብስ ያለብሳሉ የሚስኪኖችን እምባ ያብሳሉ
🙏ከዚህ በላይ የሚያስደስት ተግባር የትም የለም
***
ይህን የሚያስተባብሩ ወንድሞች ፍጹም በሆነ ቅንነትና በነጻ ተግባራቸውን ይፈጽማሉ፣
የያዙት ግዙፍ ሀሳብ ነው
በራስ አቅም ነው ስራውን የሚሰሩት፣ የሚያግዛቸው ሀገር በቀልም ይሁን የውጭ ድርጅት የለም።
ሁላችንም ይህን ማህበር እንደግፍ፣ በጎ ተግባራቸውን ባለንበት እናግዝ።
***
ዛሬውኑ አባል እንሁን በአካልም እንጠይቃቸው
ጽህፈት ቤታቸው
👉 ወልቂጤ ኢሊናም መንደር አንሷር መስጅድ አጠገብ
👉የየቲም ጉዳይ የኔም ጉዳይ ነው።
**
ለበለጠ መረጃ📞
አድራሻችን :-
0913501394/0928675572/0941987681
ሞባይል ባንኪንግ
💰💵የማህበሩ አካውንት 💵💰
💶ንግድ =1000528883595
💴ዘምዘም =0021312320101
💷ሂጅራ =1003087020001
ቴሌብር
0941987681 ሪያድ ያሲን
አንሷር የየቲሞች እና አቅመ ደካሞች መርጃ ማህበር/ወልቂጤ
🏝 ••⇣⇣. 🏖 ••⇣⇣
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞. ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫??𝐦~group
⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣

https://t.me/+k5QVT8mMR85iYzg0

በአከባቢያችን የእሳት አደጋ እየከፋ መጥቷል
ትናንት በጉብሬ በተከሰተ አደጋ በርካታ ቤቶች ወድመዋል

ተመሳሳይ ክስተት እየተደጋገመ መጥቷል። በትኩረት ትክክለኛውን መንስዔ ለማረጋገጥ መጣር ወሳኝ ነው።
***
በአደጋው ሀብት ንብረት የወደመባችሁ ወገኖቼ በሙሉ ፈጣሪ አላህ በተሻለ ይታካላችሁ

የረመዷን ቱሩፋት
***
ተዓምር መስራት የማይሰለቻቸው ሀላባዎች ከ1 ሺ በላይ ለሆኑ
ጧሪ፣ ቀባሪ ለሌላቸው እንዲሁም ለየቲሞች የረመዷን አስቤዛ በዚህ መልኩ አዘጋጅተዋል
ህዝቤ ከቀናህ በዚህ ቅና
***
ሀላባዎች በዚህ የደግነትና የእዝነት ወር እውነተኛ እዝነት አሳይታችኋል እንኳን አደረሳችሁ

ያዘጋጁት የሀላባ ዞን ሙስሊም ወጣቶች ጀመዓ (ዳሩ ሰላም) ይሰኛሉ።

ረመዷን ሙባረክ
እንኳን አደረሳችሁ

🌴🌴🌴

ሀቢብ
"ቴምር እኮ ቅንጦት ነው"
አለችኝ።
***
የተሻለ ኑሮ አለው የሚባል ሁሉም ቤቱ ውስጥ የጎደለውን እየፈለገ ያሟላል።
ብዙ ሰው ለወር የሚበቃ አስቤዛውን ቀድሞ ሸምቷል ወይም እየሸመተ ነው።
***
ከአጠገባችን፣ ከአከባቢያችን ያላስተዋልነው ብዙ ነገር አለ።
ረመዳን በመምጣቱ ቢደሰትም መላ ቅጡ ጠፍቶበት እጁን አጣጥፎ የተቀመጠ መዓት ሰው አለ።
ወትሮም በነበረው ችግር ላይ ተዳምሮ ፆሙ ሁለት ፆም የሚሆንበት በርካታ ሰው አለ።
***
እስቲ አንዴ እራሳችንን እንፈትሽ፣ ዞር ዞር ብለን አከባቢያችንን እንቃኝ አባት፣ እናት፣ ወንድም፣ እህት፣ አክስት፣ አጎት፣ ጎሮቤትና ዘመድ ሆነው ረመዳን ጭንቅ የሆነባቸው የሉም? ስንቶቻችን ጠይቀናቸዋል?
ዛሬ አንድ ስልክ ደውዬ ሰላምታ ተለዋውጠን ረመዳን እንዴት ነው፣ ቴምር ምናምን አላችሁ ብዬ ጠየኩኝ፣ አይ ሀቢብ "ቴምር እኮ ቅንጦት ነው" የሾርባ ቅንጬ እንኳን የለንም አለችኝ።
***
ይሄውላችሁ የኛ ቤት ሙሉ ላይሆን ይችላል፣ የጎደለም ነገር ይኖር ይሆናል። ከኛ በጣም የሚብስ፣ ፆሙ ስጋት የሆነበት፣ ረመዳን መጣልኝ ሳይሆን መጣብኝ ብሎ የሚሰጋ ብዙ ሰው ከአከባቢያችን፣ ከአጠገባችን ይኖራል።
***
ዙርያችንን እንቃኝ፣ ምንም የሌለው ብዙ ሰው አለ። ለረመዳን ከሸመትነው አስቤዛ እናካፍል፣ በጣም የተቸገሩ ወገን፣ ዘመድ አዝማድና ጎሮቤቶችን እንጠይቅ።
አቅሙና ፍላጎቱ ያላችሁ አምስት የሚሆኑ በአከባቢያችን በነበረው ችግር ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ቤተሰቦች አሉ፣ ፆም ማስያዝ የምትፈልጉ ስልክ እሰጣችኋለሁ። አምስት ሰው ቢገኝ ለአምስቱም ቅንጬ፣ ዱቄት፣ ዘይት፣ ስኳር እና ቴምር ቀጥታ ማበርከት ይቻል ነበር፣ ይህ አስቤዛ እስከ 8 ሺ ያወጣል ለአንድ ቤተሰብ ፆም ያሲዛል 5 ሰው ይኖር ይሆን?
***
በህይወት ሳለን እንረዳዳ
ዙርያ ገባችንን እንቃኝ

አላሁ አክበር!
ወንድማችን አብዱልከሪም ናስር በጠዋቱ አስደስቶናል፣ 20 ሺ ብር ለወንድማችን ድጋፍ
ማሻ አላህ
ወንድሜ ረመዳንህን ብሩህ ያድርግለህ
አላህ ያስደስትህ🙏🙏

ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ
በወልቂጤ ስለወልቂጤ ካወራችው የተወሰደ…
👉1 ህዝቡን እንመልከት የኔነት ስሜትን አስወግደን፣ የኛ እንበል

👉2 ስሜትን ማሸነፍ አለብን፣ በጣም በእርጋታ ነገሮችን መመልከት አለብን

👉3 በከተሞች እድገት ሁሉም ህዝብ ተጠቃሚ መሆን አለበት

👉4 ታሪክ እንደሚያሳየን የትኛውም ከተማ ከሰማይ ወርዶ አልተፈጠረም።

👉5 ከተሞች ሲመሰረቱ ካንድም ከሌላ ተቆርሰው የተፈጠሩ ናቸው

👉6 እኛ እናልፋለን፣ ጥሩ ዘር እየተከልን እንለፍ፣ Fairness, Justice መኖር አለበት፣ እውነት እንናገር፣ ስለ እውነት እንኑር

በጣም ምርጥ ንግግር🙏

ማሻ አላህ ወንድማችን አቡ መርየም 300 ብር🙏🙏 አላህ ጨምሮ ጨማምሮ ይስጥህ

አዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል
***
የግብርና ምርቶች ባዛር እየቀረበ ይገኛል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መዋቅሮችም አከባቢው ያፈራውን ይዘው ቀርበዋል።
ከበርበሬ እስከ አቮካዶ፣ እህል፣ ጥራጥሬ የቀረ የለም።
የቀቤና ልዩ ወረዳም በባዛሩ የተሳተፈ ሲሆን መልከዓ ምድሩ የሚያበቅላቸውን የግብርና ምርቶች አቅርቧል። በተለይ ነጭ ማኛ ጤፉ ገራሚ ነው።
አዲስ አበባና አከባቢው የምትገኙ ጎብኟቸው በርካሽ ሸምቱ
****

ገራሚ አይገልፀውም
***
ይህ አስደማሚ ትዕይንት የሀላባ ህዝብ ለእስቴድየም መገንቢያ እያደረገ ያለውን ርብርብ የሚያሳይ ነው
መሰል ህዝባዊ ህብረትን አለማድነቅ ይከብዳል
***
መሰረተ ልማት አጣን ብለው አያማርሩም
ፕሮጀክት ነድፈው፣ ሀሳብ አፍልቀው መንገድ ይሰራሉ፣ ውሀ ያወጣሉ፣ የትምህርት ተቋም ይገነባሉ፣ ሆስፒታል ይሰራሉ፣ ባህላዊ እሴት ይገነባሉ።
ለመቀበል ሳይሆን ለመስጠትም ይሰለፋሉ
***
የምር መንፈሳዊ ቅናት አደረብኝ
ሀላባዎች ሁሌም የአንድነት ምሳሌና ዓርአያ ናችሁ
አቦ ዘራችሁ እንደ ምድር አሻዋ ይብዛ
***