Últimas Postagens de Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ) (@guragez) no Telegram

Postagens do Canal Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)
# ይህ የዘቢዳር ቻናል የሀገራችን ብሎም የጉራጌ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካ፣ ኪነ ጥበብ፣ ታሪክ፣ ርዕዮት እና ሁለንተናዊ መልክ የሚዳሰስበት የመገናኛ የመወያያ እና የመጦመርያ አውድ ነው!
4,341 Inscritos
4,379 Fotos
73 Vídeos
Última Atualização 07.03.2025 11:07

Canais Semelhantes

Soccer Ethiopia
87,387 Inscritos
Asfaw abreha
9,834 Inscritos

O conteúdo mais recente compartilhado por Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ) no Telegram

Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

03 Nov, 17:13

2,591

ስለ ጉራጌ ሌላኛው መልክ ማወቅ የሚፈልግ ማስታወሻ ይዞ ሊያደምጠው የሚገባ ቪዲዮ ነው። እንዳያመልጦ!

ይህ በመስል የተቀነባበረው የአንድ ምሁር የድምፅ ቃለ መጠይቅ ከ1966ቱ አብዮት መባቻ እስከ ቅድመ ኢሕዲግ የነበሩ የጉራጌ ሊሂቃን የፖለቲካ ርዕዮት፣ ሀገራዊ ተሳትፎ እና የወቅቱን ሁኔታ ከማህበረሰቡ የባህል ስሪት ጋር አስተሳስሮ ለመቃኘት የተሞከረበት ግሩም ዳሰሳ ነው።

አላማው ከትላንት ለመማር ለዛሬውም ዳራ እንዲሆን በማሰብ እንዲሁም የማህበረሰባችን የፖለቲካ ታሪክ ለመሰነድ መነሻ እንዲሆን በመሆኑ እንዲያደምጡት እና አስተያየት እንዲሰጡበት ሀሳቡን ከወደዱት ደግሞ ለሌሎችም እንዲያጋሩት በአክብሮት እንጠይቃለን!

https://youtu.be/lGso6lQCloQ?si=-vUJKJDPsu1T9Czl

ሰብስክራይብ ማድረጉ እንዳይረሳ!

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

03 Nov, 07:50

1,818

ይህ በፎቶ የምታዩት ልጅ በእኖር ወረዳ ኧሰኸር በሚባል ቀበሌ የተወለደ ሲሆን ስሙ ሙሃጅር አህመድ ይባላል እድሜው 23 ነው። በአሁን ሰአት በደም ካንሰር ተይዞ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተኝቶ እየታከመ ይገኛል። ቤተሰቡ ምንም የማሳከም አቅም የሌላቸው በመሆኑ የበኩላችሁ እንድትወጡ በፈጣሪ ስም እንማፀናለን። አሳካሚው ወንድሙ አብዱልሰመድ አህመድ

ስልክ ቁጥር 0911786544
የባንክ አካውንት 1000362457468 አብዱልሰመድ አህመድ ሁሴን

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

01 Nov, 16:34

838

ተወላጆች ያሰባሰቡትን ቁሳቁሶች ለየደቤ ት/ቤት አስረከቡ።

ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ የሆኑ የደቤ ቀ/ገ/ማህበር ነዋሪዎች ከተለያዩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ያሰባሰቧቸውን የተለያዩ ቁሳቁሶችን በትምህርት ቤቱ በመገኘት ማክሰኞ ጥቅምት 19/2017 ዓ.ል የት/ቤቱ የወላጅ ኮሚቴዎችና የመንግሰት ኃላፊዎች በተገኙበት ለትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች አስረክበዋል።

ቁሳቁሶቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር በሆኑት አቶ ዘሪሁን ብርሃኑ አማካኝነት የተሰባሰቡ ዲስክ ቶፕ ኮምፒተሮች ፣ የኮምፒውተር ጠረጴዛዎች፣ ፕሪንተሮችና አጋዥ የመማሪያ መጽሐፍቶች መሆናቸውን ታውቋል።

አቶ ዘሪሁን ቁሳቁሶችን ነዋሪነታቸውን በሃገረ እንግሊዝ ያደረጉ ወዳጆቻቸው በማስተባበር የተገኙ እንዲሁም አጋዥ መጽሐፍቶችን ደግሞ ከኢትዮጵያ ቤተ-መጽሐፍትና ቤተ መዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር) እና ከዛጎል የመጽሐፍ ባንክ የተለገሱ መሆናቸውን ገልፀው ምስጋና አቅርበዋል።


ከየደቤ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተጨማሪም ከወመዘክር የተለገሱ ለሰስየና ግራር ትምህርት ቤቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ መቶ (100) አጋዥ መጽሀፍት ተበርክቷል።

ትምህርት ቤቱም በተለያየ ጊዜ ድጋፍ ለሚያደርጉ ግለሰቦች የምስጋና የምስክር ወረቀት አበርክቷል።

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

30 Oct, 18:39

1,005

"ድሃ የሚበላውን ቢያጣ የሚገብረውን አያጣም"
(በውስጥ መስመር የተላከ)


በዚህ ሳምንት ብቻ በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ የንግድ ማዕከሎች ነገዴዎችን የሚያስጨንቁ የተለያዩ ዘመቻዎች እየተደረጉ ነው። በአንዳንድ የንግድ ማዕከላት (ይርጋ ኃይሌን ጨምሮ) ሙሉ ሸቀጦች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ተወስደዋል። በርካታ ሱቆች ታሽገዋል። ሌሎቹን ትቼ በራሴ የተከሰተውን አንድ ምሳሌ ብቻ ላንሳ።

ጉዳዩ የተፈፀመው መርካቶ ውስጥ በሚገኝ አንድ የንግድ ማዕከል ውስጥ ነው። የገቢዎች ሰራተኞች በብዛት ሆነው ወደ ምሰራበት የንግድ ማዕከል ገቡ። ከቢሮ ተፈርሞ የወጣ አንድ አይነት ደብዳቤ በዛ አድርገው ይዘዋል። ከዚያ እያንዳንዱ ሱቅ እየገቡ ከቢሮ ይዘው የመጡትን ደብዳቤ ለባለሱቆች እያስፈረሙ መስጠት ጀመሩ።

እኔ ያለሁበት ሱቅ ደረሱ። ንግድ ፈቃድ፣ ዜድ ሪፖርት ጠየቁኝ። ሰጠኋቸው። በያዙት ደብዳቤ ለ… ተብሎ በተፃፈው ቦታ ስሜን ፅፈው ፈርም ብለው ደብዳቤውን ሰጡኝ። ከመፈረሜ በፊት ደብዳቤውን ላንብበው አልኳቸውና ተቀበልኳቸው። ርዕሱ "የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ" ይላል። የደብዳቤው ዋና ይዘት ሲነበብ «… ድርጅትዎ ለፈፀመው ሽያጭ ደረሰኝ በአግባቡ የማይሰጥ መሆኑ ተረጋግጧል። በመሆኑም ይህንን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል…" አይነት ነገር ነው።

ፈርም ሲሉኝ አልፈርምም አልኳቸው። ለምን አትፈርምም ሁሉም እየፈረመ ነው አሉኝ። "ምንም በማላውቀው ጉዳይ እንዴት ወንጀለኛ ነኝ ብለህ ፈርም ትሉኛላችሁ? ለመሆኑ ደረሰኝ ሳልቆርጥ ስለመሸጤ ማስረጃ አላችሁ? አልኳቸው። የለንም አሉኝ። ታዲያ የምን ማስጠንቀቂያ ነው? የምን የመጨረሻ ማስጠንቂያ ነው? ምን ዓይነት አሰራር ነው? ምን እየተካሄደ ነው?… ብዙ ጥያቄ አቀረብኩ።

ሰራተኞቹም "እኛ አስፈርሙ ተብሎ የተሰጠን ነው። ጥያቄ ካለህ ቢሮ ሄደህ መጠየቅ ትችላለህ። አሁን ፈርም አሉኝ። "ይቅርታ በማላውቀውና በማላምንበት ጉዳይ አልፈርምም። በማላውቀው ጉዳይ ወንጀለኛ ነኝ ብዬ አልፈርምም" አልኳቸው። የሱቁን ቁጥር መዝግበው ሄዱ።

መንግስት ነጋዴውን ለመበዝበዝ እያደረገ ያለው ዘመቻ ስታይ "ድሃ የሚበላው ቢያጣ የሚገብረው አያጣም" የሚለውን የፊውዳል ስርዓት የሚያስንቅ እየሆነ ነው። ከመሬት ተነስቶ ተጠንቀቅ?!

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

28 Oct, 13:05

1,963

"ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል" ተግባራዊ እያደረገው ያለው የገጠር #መሬት መጠቀሚያ እና የግብርና ስራ ገቢ #ግብር አዋጅ ምን ምን ይዟል?

በሥራ ላይ የነበረውን የደቡበ #ብሄር ብሄረሰቦች ክልል መንግስት የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያ እና የግብርና ሥራ ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 122/2000 የተካውና በአዲሱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተግባራዊ እየተደረገ ያለው አዲሱ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያ እና የግብርና ሥራ ገቢ ግብር አዋጅ 27/2016 ምን ምን ጉዳዮች ይዟል?

አዲሱ #አዋጅ አርሶ አደሩ በይዞታ ባለቤትነት ከሚያስተዳድረው መሬት እና በመሬቱ ላይ ከሚያመርተው ምርት ለመንግስት በየአመቱ መክፈል የሚገባውን ኪራይና ግብር ተምኗል። የመሬቱ ደረጃ፣ ለመስኖ ያለው ተደራሽነት፣ መሬቱ ጥቅም ላይ የዋለበት አላማ፣ እና መሰል መመዘኛዎች ለተመኑ ዋነኛ ግብአቶች ተደርገዋል።

አዲሱ አዋጅ የገጠር መሬት መጠቀሚያ #ክፍያ (ኪራይ) በተመለከተ የሚከተለውን ተመን አስቀምጧል። (ምስል 1 ይመልከቱ)

የግብርና ስራ #ገቢ ግብርን በተመለከተም (ምስል 2 ይመልከቱ)

በተጨማሪም ማንኛውም የገጠር መሬት የመጠቀም መብት ያለው ሰው ለምርት ባይጠቀምም #በሄክታር የመሬት መጠቀሚያ ክፍያ 350.00 (ሦስት መቶ ሃምሳ) ይከፍላል።

ማንኛውም የገጠር መሬት የመጠቀም መብት ያለው አርሶ አደር ለምርት ባይጠቀምም በሄክታር ለግብርና የገቢ ግብር #450 ብር በሄክታር

ይህ ማለት አንድ ሄክታር መሬት ያለው አርሶ አደር ለመሬት መጠቀሚያ እና ለግብርና ስራ ግብር በአመት በትንሹ 800 (350+450) ብር ይከፍላል ማለት ነው። በተጨማሪም ከ0.1 ሄክታር በታች ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ከግብር እና ኪራይ ክፍያ ነፃ ይሆናሉ።

የመሬት መጠቀሚያ እና የግብርና #ስራ ገቢ ግብር በመሬት ስፋት፣ በምርት መጠንና አይነት፣ በመሬቱ አይነት፣ ወዘተ የሚሰላ ሲሆን በየአመቱ የሚከፈል ይሆናል።

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

24 Oct, 19:21

3,292

ልናቃጥል ነው፣ መቃጠሉ ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ክፍፍል ይፈጥራል፣ ቢያቃጥሉት ደስተኛ ላለመሆኔ እርግጠኛ መሆን አልችልም፣ እሳቱን ለማጥፋት ሚሊዮን ብሮች ክፈሉ፣… ከፓርቲ መሪዎች እስከ አክቲቪስቶች በአደባባይ የተሰሙ ማስፈራሪያዎችና የደስታ መግለጫዎች ናቸው።

ግና ይህንን ያወገዘ፣ ለነዚህ አካላት ተዉ ያለ መንግስትና የመንግስት ተቋም የለም።

አንድ ደሳሳ ጎጆ አፍርሰው ለመገንባት፣ አለያም 5 ኪሎ ዘይት ለመስጠት የወዳደቁ ሰፈሮች ከመገኘት የማይቦዝኑት ትላልቅ ባለስልጣናት በመርካቶ ሰዎች ላይ ምነው ዝምታቸው በዛ? መርካቶ ምነው ራቀቻቸው?

ለምን?

በመሐመድ አብራር

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

22 Oct, 15:15

869

#የሸማ ተራው #የእሳት ቃጠሎ አደጋ አስመልክቶ የተለያዩ ኃላፊነት የጎደላቸው ፅሁፎችና መልዕክቶች አይተናል።

ህንፃውን ያቃጠለው #መንግስት ከሚለው ጀምሮ እንኳን ተቃጠለ፣ ያቃጠልነው እኛ ነን የሚሉ ግለሰቦች ሳይቀር በአደባባይ ማየት ተችሏል።

ከሁሉም አስገራሚው ግን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) #ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ግርማ ጉተማ (እራሳቸውን አባ ጨብሳ እያሉ ይጠራሉ) ያሰፈሩት አስተያየት ብዙዎችን ያሳዘነና ያስደነገጠ ሆኗል።

ሰውዬው ያሰፈሩት ሃሳብ ከላይ በምስል ተያይዟል። በዚህ ዙሪያ አቶ ግርማም ሆነ የሚመሩት #ፓርቲ ማብራሪያ ሊሰጡ አይገባም ትላላችሁ?
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

22 Oct, 07:25

1,368

አስቸኳይ መልሶ ማቋቋም ለወገኖቻችን!!!

የመርካቶው ውድመት የብዙዎች የህይወት ዘመን ጥሪት ወደ አመድነት የቀየረ ክስተት ነው። በዚህ ሰዓት በርካቶች የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተዋል።

አላስፈላጊ ጣት መጠቋቆም ንብረቱ ለወደመበት ወገን የሚፈይደው ነገር የለም። ትኩረታችን ሁሉ መልሶ ማቋቋም ላይ ይሁን። የከተማ አስተዳደሩም አደጋው ያደረሰው ጉዳት መረጃ ከማሰባሰብ ጎን ለጎን የተቀናጀ የመልሶ ማቋቋም ስራ ይጀምር።

የመንግስት ቀና ድጋፍና አመራር ካለ ወገኖቻችንን በአጭር ጊዜ መልሶ ማቋቋም ይቻላል። ባለሃብቱና መላው ህዝብ ቀና ትብብር እንደሚያደርግ አያጠራጥርም። የመንግስት አቅምና ቁርጠኝነትም የሚለካው አደጋው ለመቆጣጠር ካደረገው ጥረት ይልቅ ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም በሚያደርገው ጥረት እና ስኬት ልክ መሆን አለበት።

ትኩረታችን ሁሉ አስቸኳይ መልሶ ማቋቋም ለወገኖቻችን የሚል ይሁን!
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

18 Oct, 14:23

1,997

የሚሰሩ እጆችን እናበረታታ!

ይህ ማስታወቂያ በሐዋርያት ከተማ ተደራጅተው በእንጨትና ብረታ ብረት ስራ የተሰማሩ ወጣቶችን ለማበረታታት ያለምንም ክፍያ የተሰራ ነው። እርሶም በማጋራት የበኩሎን አስተዋፅዖ ያድርጉ🙏

በምሁር አክሊል ወረዳ ሀዋርያት ከተማ በፈርኒቸር እና በብረታ ብረት ስራዎች ቀዳሚ የሆነው ይናም ቲናም የቤት እና የቢሮ እቃዎች ማምረቻ ለደንበኞቹ እጅግ ጥራት ያላቸውን የአልጋ፣ ብፌ፣ ቁም ሳጥን፣ የምግብ ጠረጴዛዎችና ወንበሮች፣ የህንፃ በሮች፣ የህንፃ መስኮቶች፣ የህንፃ የውስጥ ለውስጥ ታሙቡራታ በሮች፣ የግቢ ኢሚቴሽን በሮች እንዲሁም ጥራት ያላቸው የቢሮ መደርደሪያ ሼልፎች በጥራት እንሰራለን ይላል።

ይናም ቲናም የቤት እና የቢሮ እቃዎች ማምረቻ ፤ ቤታችንን በምን እናስውበው ብለው እንዳይጨነቁ እኛ እንጠበብበታለን ስራን ማክበር ዋናው መገለጫችን ነው ደንበኞቻችንን በማክበር ፍላጎቶቻቸውን ማሟላት ከምንም ነገር በላይ ትኩረት የምንሰጠው ነገር ነው።

አድራሻ፦ሀዋርያት ከአብይተም ሆቴል ጎን
ስልክ ቁጥር +251911581968/+251943096948
ስራ አስኪያጅ አህመደል ተሰማ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

18 Oct, 08:08

1,235

በምስራቅ ጉራጌ ዞን ጥያ ከተማ 3 ሰዎች ታግተው ሲወሰዱ አንድ የባንክ ጥበቃ በጥይት ተመቶ ቆስሏል።

#ዘቢዳር_ሚዲያ:- ጥቅምት 08/2017

"በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል" በምስራቅ ጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ #ጥያ #ከተማ ላይ ጥቅምት 05 ቀን 2017 በግምት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ ታጣቂዎች የግለሰቦች ቤት በመግባት 3 የአካባቢውን ነዎሪዎች አግተው ወስደዋል።

ታጋቾቹም አንድ #መምህር ፣ አንድ የሃይማኖት አባት እና አንድ መንግስታዊ ባልሆነ በጎ አድራጎት ድርጅት (World Vesion) በጥብቅ ስራ ተቀጥሮ በመስራት ላይ የነበረ ግለሰብ ሲሆኑ በከተማው የሚገኘው የንብ #ባንክ ለመግባት ሞክረው ሳይሳካላቸው ቢቀርም የባንኩን የጥበቃ ሰራተኛ በጥይት አቁስለውት ተሰውረዋል።

በሌላ መረጃ በተመሳሳይ ሰዓት በወረዳው #ሱተን በሚባለው ከተማ ታጣቂዎቹ ጥቃት ለመፈፀም ሞክረው የነበረ ቢሆንም የአካባቢው ነዋሪ አፀፋ በመመለሱ የተኩስ ልውውጥ ተደርጎ ታጣቂዎችን ማባረሩ ታውቋል።

በአካባቢው መከላከያ ሠራዊት እንዲሰፍር ከተደረገ በኃላ በአንጻራዊነት መረጋጋት ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም ችግሩ እልባት ሳይሰጠው #መከላከያ ሠራዊት እንዲወጣ መደረጉ ለታጣቂ ቡድኖች መልካም አጋጣሚ ፈጥሮላቸዋል ሲሉ ዘቢዳር ያነጋገረቻቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገልፀዋል።

ከአምስት ቀን በፊት በዚሁ ወረዳ #አማውቴ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ አንድ አዛውንትና ለጥየቃ የመጣች ሴት ልጃቸው በእነዚሁ ታጣቂ ቡድኖች መገደላቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ