آخرین پست‌های Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ) (@guragez) در تلگرام

پست‌های تلگرام Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)
# ይህ የዘቢዳር ቻናል የሀገራችን ብሎም የጉራጌ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካ፣ ኪነ ጥበብ፣ ታሪክ፣ ርዕዮት እና ሁለንተናዊ መልክ የሚዳሰስበት የመገናኛ የመወያያ እና የመጦመርያ አውድ ነው!
4,316 مشترک
4,371 عکس
73 ویدیو
آخرین به‌روزرسانی 06.03.2025 10:20

آخرین محتوای به اشتراک گذاشته شده توسط Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ) در تلگرام

Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

05 Mar, 11:51

726

ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ ‼️

ምንም ዓይነት ገንዘብ እንዳትልኩ⚠️⚠️⚠️

ይህ zerihun girma መልዕክት ነው‼️

ሰላም ሰላም ወንድም እህቶቼ 🙏 የ ቴሌግራም አካዉንቴ በሌሎች ድረገጸች ሀክ ተደርጎ በስሜ ገንዘብ ልመና እያደረጉ ስለሆነ እኔ አለመሆኔን እንድታዉቁልኝ ለመግለፅነዉ ተጠንቀቁ።
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

03 Mar, 09:44

1,376

ከጉራጌ ክልልነት ጥያቄ ጋር በተገናኘ እና ወልቂጤ ከተማ ላይ ተፈፅሞ በነበረው ጥቃት ሳቢያ ከዓመት ለዘለለ ጊዜ በግፍ በእስር ቆይተው የነበሩ ወጣቶች ዛሬ ከእስር ተለቀቁ።

#ዘቢዳር_ሚዲያ የካቲት 24/2017

አቃቤ ህግ ክሱን በማቋረጡ ምክንያት ዛሬ ከእስር የተለቀቁት የዞንና የክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ታረቀኝ ደግፌና ሃይደር ሙራድን ጨምሮ ከወልቂጤ ከተማ የታፈሱ ወጣቶች መሆናቸው ታውቋል።


Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

12 Feb, 12:10

2,321

ሃገር የራሷን ዜጋ ወደ ሃገርህ አትመለስም ብላ መከልከል ትችላለች?
***
በዳንኤል ፍቃዱ / ጠበቃና የህግ አማካሪ/

•የኢትዮጵያ ዜጎች ወደ ሀገራቸው የመመለስ መብት በሕገ መንግሥት እና በአለም አቀፍ ሕግ የተጠበቀ ነው።
•የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 32(1 እና 2)
•ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ በመረጠው የሀገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመሥረት፣ እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር የመውጣት ነጻነት አለው።
•ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደ ሀገሩ የመመለስ መብት አለው።
•የሰብአዊ መብቶች ሁለንተናዊ አዋጅ (UDHR, አንቀጽ 13) እና የሲቪል እና ፖለቲካዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን (ICCPR, አንቀጽ 12(4)) ዜጎች ወደ ሀገራቸው የመመለስ መብትን ያረጋግጣሉ ።
  •ይህ መብት ለግለሰቦች ብቻ ሳይሆን ለቡድኖችም (ለምሳሌ ስደተኞች) የሚተገበር የሆነበት ሁኔታ በሕግ ባለሙያዎች መካከል ውይይት ያለበት ነው ።
•የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 12(3)
• ብሔራዊ ደኅንነትን፣ የኅብረተሰብ ሰላም፣ የሕዝብን ጤና ወይም ሞራል ወይም የሌሎችን መብቶችና ነጻነቶች ለመጠበቅ ሲባል በዚህ ቃል ኪዳን ከሰፈሩት ድንጋጌዎች ጋር በሚስማማ አኳኋን በሚወጣ ሕግ መሠረት ካልሆነ በስተቀር ከላይ በተጠቀሰው መብት ላይ ምንም ዐይነት ገደብ አይደረግም፡፡
•የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ስምምነት:-  ስደተኞች በፀጥታ ምክንያት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ካለመቻላቸው ጋር በተያያዘ ጊዜያዊ ጥበቃ ይሰጣቸዋል።

•የመመለስ ሂደትን የሚገድቡ ሁኔታዎች

"የአንድ ሀገር ዜጋ በመሆን ብቻ ከተረጋገጡ ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ድንጋጌ ውስጥ ዜጋው ወደ ትውልድ ሀገሩ በፈለገ ጊዜ የመመለስ መብትን መከለከል/መገደብ ከመሠረቱ ሕገወጥ ተግባር ስለመሆኑ"


•የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች የቃልኪዳን ሰነድ

•አንቀጽ 13/2/ ‘‘ማንኛውም ሰው የራሱን ሀገር ጨምሮ በማንኛውም ሀገር የመግባትና የመውጣት መብት አለው ’’ ይላል
• ዓለም አቀፍ የሲቭልና ፖለቲካዊ መብቶች የስምምነት ሰነድ
•  አንቀጽ 12/2/ ‘‘ማንኛውም ሰው የራሱን ሀገር ጨምሮ በማናቸውም ጊዜ ለቆ የመውጣት መብት አለው፡፡’’
• አንቀጽ 12/3/ ከላይ የተጠቀሱት መብቶች በማናቸውም መንገድ ወይም ሁኔታዎች ሊገደቡ የማይችሉ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ ለሕዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል፤ ለብሔራዊ ደህንነት ሲባል፤ ለሕዝብ ጤናና ሥነ ልቡና ሲባል፤ ወይንም ለሌሎች ሰዎች መብቶችንና ነፃነቶችን ለመጠበቅ አስፈላጊ መሆኑ ካልታመነ በቀር መብቶቹ ሊገደቡ የማይችሉ መሆናቸው ተደንግጓል፡፡
•አንቀጽ 12/4/ ከላይ የተገለጹት ልዩ የገደብ ምክንያቶች ቢኖሩም ‘‘ማናቸውም ዜጎች በዘፈቀደ እና በኃይል ተግባር ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ ሊከለከሉ አይገባም’’ በሚል ያትታል፡፡

አንድ ሃገር የራሷን ዜጋ ወደ ሃገርህ አትመለስም ብላ መከልከል ትችላለች ። ይህ ይሆን ዘንድ የሚደርግ ውሳኔ የሚወሰደው በዚያ ሃገር አዋጆች እና የስርዓተ ፍትሕ ሂደቶች መሰረት ነው። በተለይ የሚከተሉት ሁኔታዎች ክልከላን ሊያስከትሉ ይችላሉ፦
1. የዜጎች መብቶች፦ ዜጎች የራሳቸውን ሃገር  የመግባት እና የመውጣት መብት እንዳላቸው ይታወቃል።  የሃገር መንግስት ይህን መብት የሚገድብ  ውሳኔ  ለማወጅ የሚያስፈልገው በሕግ የተደነገገ ምክንያት ሊኖረው ይገባል።
2. የስርዓተ ፍትሕ ሂደቶች፦ የሃገር መንግስት የራሱን ዜጋ ወደ ሃገርህ አትመለስም ብሎ ለማከልከል የሚወስደው  ውሳኔ  በሕግ የተደነገገ ሂደት ይኖረዋል። ይህ ዜጋ የሚያቀርበውን የሕግ አቤቱታ የመስጠት እድል ይኖረዋል።
3. የሃገር ደህንነት፦ የሃገር መንግስት የራሱን ዜጋ ወደ ሃገርህ አትመለስም ብሎ ይከልከል የሚችለው የሃገር  ደህንነት ይጠበቅ ወይም የሕዝብ ጤና የሚያሳስበው ይሆን ይችላል።

በቅርቡ የወጣው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት ጉዳዮች አዋጅ፦ በአዋጁ ላይ እንደተመላከተው ወደ ኢትዮጵያ የሚበሩ ማናቸውም አየር መንገዶች የተጓዦችን ስም ዝርዝር ከ3 ቀን በፊት ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የማሳወቅ ግዴታ አለበት ይላል።
ሲጠቃለል የዜጎች ወደ ሃገር መመለስ መርህ / principle/ በመሆኑ በሰፊው ተተርጉሞ ክልከላው ልዩነት / exception/ በመሆኑ በጠባቡ ሊተረጎምና ሊተገበር ይገባል።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

04 Feb, 16:59

2,716

አስራ አምስት ወራትን የተሻገረው ችሎት ለመጋቢት 01 ተቀጠረ።

#ዘቢዳር ሚዲያ:- ጥር 27/2017

በዛሬው ዕለት በፌደራል ተዘዋዋሪ ችሎት በእነ ጀምበር አብዶ መዝገብ አቃቤ ህግ ክስ የመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች መዝገብ ለተጨማሪ ጊዜ ለመጋቢት 01, 2017 ተቀጠረ።

አቃቤ ህግ 30 የሰው ምስክሮች አሉኝ ብሎ አስመዝግቦ የነበረ ቢሆንም ከ10 የሰው ምስክሮች በላይ የምስክርነት ቃል ማሰማት ሳይችል ቀርቷል።

ፍርድ ቤቱ ችሎቱን ለመጋቢት 01 የቀጠረው አቃቤ ህግ ክሱን ያስረዱልኛል ብሎ ባቀረባቸው የሰነድና የተንቀሳቃሽ ምስሎች ላይ የተከሳሽ ጠበቆች ምላሽ ለመስማት መሆኑን የተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት አቶ ጌዲኦን ቦጋለ ለዘቢዳር ሚዲያ አሳውቀዋል።

ትላንት በዋለው ችሎት አቃቤ ህግ ማስረጃ አላገኘሁባቸውም በማለቱ ፍርድ ቤቱ በአቶ ጃፈር ተማም በድሩ እና በአቶ ትጉነህ ትዛዙ ላይ የተመሰረተው ክስ እንዲቋረጥ ወስኗል። በቅርቡ አቶ Jafer Temam Bedru እየደረሰባቸው የነበረውን ተደጋጋሚ እስር፣ ዛቻና ማስፈራራት ሽሽት ከሃገር መሰደዳቸው ይታወቃል።

በተመሳሳይ አቶ ጀምበር አብዶ ላይ በተናጠል ተመስርቶ የነበረው ተደራቢ ክስ አቃቤ ህግ ማስረጃ አላገኘሁም በማለቱ ፍርድ ቤቱ በዛሬው እለት ክሱ እንዲቋረጥ ወስኗል።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

31 Jan, 12:07

3,600

እኛን ሚመለከቱ መረጃዎች የት ነው የተከማቹት?

AI ወይም ሰው ሠራሽ አስተውሎት በሰው ልጆች ልክ መገንዘብ ወይም መማር የሚችልበት የዘመናችን ድንቅ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሆኖ ተከስቷል፡፡ በዚህ ምክንያት ከአሁን በኃላ እንደ ግለሰብ ሆነ ማህበረሰብ ከፍ ሲልም አንደ ሀገር በሁሉም ማህበራዊ ሚድያዎች የምናሰፍራቸው እያንዳንዱ ቃላትና ፎቶ ወይም የትኛውንም አይነት መረጃ በማንነታችን ብየና ውስጥ ወሳኝ ሚና አለው።

የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ለጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡ ከማስቻሉ በተጨማሪ ውስብስብ የሒሳብ ቀመር እንዲፈቱ ያስችላል፤ በጤና፣ በግብርና፣ በትምህርት እና በሌሎችም ዘርፎች ጥቅም ላይ የሚውሉ አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡ የእነዚህ ነገር ሁሉ መገኛው ከእያዳችን የሚወሰዱ መረጃዎች ድምር ውጤት ነው፡፡ ለዚህም ነው ዳታ ወይም መረጃ አስፈላጊነት የነዳጅ ወይም የከበሩ ማእድናት ያክልነው የሚባለው፡፡

ለዚህ ጥሩ አብነት ስሞኑን በአለም ላይ መነጋገርያ የሆነው "ዲፕሲክ" "DeepSeek" የተሰኘው AI መተግበርያ አለምን በመረጃ ስርአት ውስጥ ቻይና ያላትን አቅምማሳየቷ ነው፡፡
ይህ ቴክኖሎጂ በርካታ የቋንቋ ሞዴሎችን በመያዝ የሚቀርብ በመሆኑ ለቋንቋ፣ ለታሪክ፣ ለባህል፣ ለኪነ ጥበብ እና የኢኮኖሚ እድገትም አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በተሸለ መልኩም በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ከሌሎች መሰል ቻትቦቶች በተሻለ አገልግሎት እየሰጠም ነው፡፡

እኛ_ግን_የት_ ነን?_ ይህ ቴክኖሎጂ የእኛስ ቋንቋ ጉራግኛ እንዲጠቅም ምን እናድርግ? ብሎ መቆዘም የግድ አስፈላጊ ነው! በተለይ የአፋን ኦሮሞ እና የትግርኛ ቋንቋዎች ዛሬ ላይ የሚድያና የስራ ቋንቋ ከመሆን ተሸግረው የዲጂታል ቋንቋ የሆኑት የብሔረሰቦቹ ተወላጆች በዘመናት መካከል ለጉዳዩ በሰጡት ትኩረት ነው፡፡

መተገበርያዎቹ ጥሩ አገልግሎት የሚሰጡት የተከማቸ እና ጥራት ያለው መረጃ ሲገኝባቸው በመሆኑ ለዲጂታሉ አለም ስለ ጉራጌ የምንጽፈው፣ የምንናገረው፣ የምናጋራው ምስል ምን አይነት ነው? ስለ ጉራጌ በዲጂታሉ አለም በቂ መረጃ ማግኘት ይቻላል ወይ? አሉ የምንላቸው መረጃዎች ጥራታቸውና ብዛታቸው እንደው ምን ያክል ነው ብለን ብንጠይቅ መልሱ በጣም ቀላል ነው፡፡

በአጠቃላይ ስለ ጉራጌ አለም በቅጡ እንዲረዳና ሆነ እኛም እንድንገለገልበት በዘመኑ ቴክኖሎጂዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ መሆን በቂ እና ጥራት ያላቸው መረጃዎችን በስፋትና ማሰራጨት በማህበራዊና እንደ ታሪክ እና ፖለቲካ ባሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተሻለ ግንዛቤ ያላቸው አካላት በጉዳዩ ላይ መሪ ተዋንያ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ይህ ካሆነ ግን ዲጂታል አለሙ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እርግጠኛ እና ሙሉ መረጃ የሚመግቡ አካላት የበዙበት በመሆኑ ከሀገርም ሆነ ከአለም ስርአት ውስጥ እየተገለልን መምጣታችን አይቀርም፡፡

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

29 Jan, 07:24

2,204

ማረዳ ፊት አውራሪ ሳፎ ጀጀነ!

ኔሁ እንዴ! ዘንድረ ታረፋም ተመስቀር ውጤ ገኔንየ ንዥነ።

ቶቶት የዘርማ ማመረንዳ በህርም ህርም አት ግዝየ ያስራጅን "የገናኸ ሀርም፤አትኸር" ማረዳ ዘድር የ6ተነ ግዝየ በሰባት ቤት በጟታ አፈር ዛራ ይውሪ ንቃር ቀልብ ይሽን ድብርንየ ይወርድቴ። በህሜማንዳ የገነንዳ ይሽሮ ጀፎረም ናዠነቴ ተህም ገነንዳ ምር ትመስር ኸማ ተጨራ ንኽነም ናትኸነቴ።

ማረዳሁታ ንቃር ገነሁና ይረምዶ ንቅ ኮረምቶ/ሶሬሳ ሰብ ተዘርማ እማቴ ያሮ የኸሬ ንቃር የኽን ያሰራ ቃር አስራጀት ያነወ የኽሬ እናመንጠናሁ።

☑️መቸው? በባሁ:-
እንተጎጎት (የካቲት 8&9)
📣ያርም ይትዠቦርቤ የመኪና ዋጋ፣ሸረትም፣ካናቴራ ደበረምታ=2800ብር

የትመዝገቦት:
📲0913155230
📲0936261036
📲0923576123
"ቶቶት፤ ይፈዝ ከረ"
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

15 Jan, 12:41

3,307

ባለፈው ቅርብ ጊዜ

እንኳንስ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ክልል ካልሆንክ የአምቡላንስ ተሽከርካሪ ሳይቀር በኮታ ነው የምትከፋፈለው ብለን ነበር።

ለማስረጃነት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተወሰደውን ከስር ያለው ምስል ይመልከቱ። "ብለን ነበር!" ብለን ግን አንሰላችም፤ በየጊዜው በሚፈጠሩ ቁምነገሮች ሙግታችንን በማስረጃ አስደግፈን እናቀርባለን።

"ክልል ዘመን አመጣሽ ፋሽን ነው" ያለው ማን ነበር?። የማክሰሚያ ፕሮጀክቱ ያለ ጥርጥር phaseout ያደርጋል።

የታሪክ ሽምያ እና ቅሚያ እያደረገ ባለ ማህበረሰብ መካከል እየኖሩ ሀገራዊ ድርሻን በመጠየቅ ጊዜያዊና ቋሚ ጥቅሞችን ከማስከበር ለአፍታም መዘናጋት አያስፈልግም።

#ኬር #ወገሬት

Via አብዱረዛቅ ነስሩ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

09 Jan, 05:36

4,885

ጥር 4 በአዲስ አበባ ከተማ!
ለሐዋሪያት ሆስፒታል!

ዕሁድ ጥር 04/2017 በአዲስ አበባ ከተማ ብሔራዊ ቲያትር አጠገብ በሚገኘው ራስ ሆቴል አዳራሽ ለሐዋሪያት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና መሳሪያዎች ለማሟላት ተወላጆችና ወዳጆችን ያሳተፈ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይደረጋል። ፕሮግራሙ በወረዳው አስተዳደር የሚመራ ሲሆን ከጠዋቱ 3:30 የሚጀምር ይሆናል።

በቦታው በመገኘት ድጋፋችንን እናሳይ! በአካል መገኘት የማንችል ደግሞ የወረዳው አስተዳደር በሚያስተዳድራቸው የሂሳብ ቁጥሮች የአቅማችንን ድጋፍ እናድርግ!

СВЕ:- 1000650277523
NIB:- 7000054845068

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

09 Jan, 05:00

2,189

Ethiopis TV program/ኢትዮጲስ የገና በዓል ከአላዛር ጋር/የልጆች መማሪያ አፕልኬሽን ሰርቷል።#Andnet...
https://youtube.com/watch?v=7fz9noAoAvs&feature=shared
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

08 Jan, 09:33

2,111

https://www.youtube.com/watch?v=1KcXG3teW8A&t=369s&ab_channel=%E1%88%93%E1%88%AA%E1%8B%B2%E1%8C%82%E1%89%B3%E1%88%8D%2FHariDigital