آخرین پست‌های Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ) (@guragez) در تلگرام

پست‌های تلگرام Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)
# ይህ የዘቢዳር ቻናል የሀገራችን ብሎም የጉራጌ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካ፣ ኪነ ጥበብ፣ ታሪክ፣ ርዕዮት እና ሁለንተናዊ መልክ የሚዳሰስበት የመገናኛ የመወያያ እና የመጦመርያ አውድ ነው!
4,316 مشترک
4,371 عکس
73 ویدیو
آخرین به‌روزرسانی 06.03.2025 10:20

آخرین محتوای به اشتراک گذاشته شده توسط Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ) در تلگرام

Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

04 Dec, 16:23

903

አቶ ታዬ ከእስር ቢለቀቁም “ማስክ ባደረጉና በታጠቁ ሰዎች ተወስደዋል ተባለ

አቶ ታዬ ደንደዓ ዛሬ ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም. አመሻሹን ከማረሚያ ቤት ብለቀቁም ቤተሰቦቻቸውን ሳይቀላቀሉ ከማረሚያ ቤቱ በራፍ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ለዶይቼ ቬለ ገለጹ፡፡ ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ታዬ ደንደዓ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም. የዋስትና መብት ተጠብቆላቸው ከእስር እንዲለቀቁ በፌዴራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በተወሰነላቸውም መሰረት ቤተሰቦቻቸው በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት የሕግ ሂደቶቹን ባለፉት ሁለት ቀናት አጠናቀው አቶ ታዬ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር አመሻሹን 11 ሰዓት ላይ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ብለቀቁም የፀጥታ ኃይሎች የማረሚያ ቤቱ በራፍ ላይ ጠብቀው ወዳልታወቀ ስፍራ እንደወሰዱዋቸው ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

04 Dec, 05:58

972

በኢትዮጵያ ግጭቶች እና እገታዎች ተበራክተው የዜጎች ሰላም አደጋ ላይ ከሚገኙባቸው አካባቢዎች አንዱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ነው፡፡
በክልሉ የሰላምና ጸጥታ ያለመረጋጋት ሁኔታው የተባባሰባቸው ቦታዎች ያሉበትን ሁኔታ እና የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ምንድናቸው የሚለውን ጠይቀናል፡፡
እንቁጣጣሽ ኃ/ማርያም
አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት!

💬 8545

Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/

Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1

Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1

@Arada_Fm
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

03 Dec, 16:39

1,190

በአቢሲኒያ ፍላይት እና በቲናው አበባ ልማት አክሲዮን ማህበር ለሚገነባው የአየር መንገድ ማረፊ ግንባታ የሚውል የቦታ ርክብክ መደረጉን የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን በዛሬው ዕለት በፌስቡክ ገፁ አጋርቶናል።

ግንባታው በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ዳርቻ ቀበሌ የሚካሔድ ሲሆን የአየር መንገድ ማረፊያውም በአጭር ጊዜ ተገንብቶ ወደ ስራ እንደሚገባም አልሚዎቹ ተናግረዋል፡፡

ይህ ግንባታ በኢትዮጵያ በግል አልሚዎች የሚለማ የመጀመርያው የአውሮፕላን ማረፊያና መኮብኮቢያ ይሆናል ሲል IGA ዘግቧል።
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

30 Nov, 06:32

1,940

የጉራጌዎች የሸንጎ ቡና አጠጣጥ ሥነ-ሥርዓት
የገፓት/የውኴር ቃዋ(የሸንጎ ቡና)

በሲሳይ ዓለሙ [email protected]

ጉራጌዎች መሸት ሲል ተጠራርተው የሚጠጡት ቡና "የገፓት ቃዋ" እያሉ ይጠሩታል፡፡ እናቶች ተራቸውን ጠብቀው ቡና ያፈላሉ፡፡ በገፓት/የውኴር #ቃዋ ድርድር የላቸውም፡፡ ከበድ ያለ ችግር እንኳ ቢያጋጥማቸው ተራቸውን ውልፍት አያደርጉትም፡፡

ባለተረኛዋ እማወራ ልክ ከምሽቱ 12፡30 ሲሆን ቃዋ የማፍላት ዝግጅቷን ትጀምራለች፡፡ ቀኑ ለምሽት ሥፍራውን ሲለቅ፣ ርቆ የሄደም ሲመለስ፣ #ደቦ ሥራ ላይ የነበሩት አባወራዎች ወደየቤታቸው ሲገቡ፣ ገበያ የሄዱት እማወራዎችም ግብይታቸውን አጠናቅቀው ከተመለሱ በኋላ፣ ከብቶችም ወደማደሪያቸው፣ በጎችና ፍየሎችም ወደ ጋጣቸው ከገቡ በኋላ ነው ቃዋ የሚጠጣው፡፡

ጉራጌዎች በማህበራዊ ኑሮዋቸው እጅግ ጠንካሮች ናቸው፡፡ የተጣላም ካለ እርቅ የሚያወርድበት፣ ያጣም ለአባላቶቹ ችግሩን ተናግሮ #መፍትሄ የሚያገኝበት ሰዓት ነው፡፡

አራስ፣ ለቅሶ፣ ሰርግ፣ ታማሚ ወይም በእድሜ የጃጀ ሰው በአካባቢያቸው ካለ ለእነዚህ ጉዳዮች ቅድሚያ ሰጥተው ጉዳዩ በተከሰተበት ቤት ሰብሰብ በማለት #ሸንጎ ያስመሻሉ፡፡ ሃዘንተኛም ሃዘኑን እስኪወጣለት ድረስ ያስተዛዝናሉ፡፡ የገፓት ቃዋቸውንም በእነዚያ ቤቶች ያደርጋሉ፡፡ ሰባት ቤት ጉራጌዎች አንዲት እናት ወልዳ ሁለት ወር እስኪሞላት ድረስ "#ጭን" እያሉ ይጠሩዋታል፡፡ አራስ ማለታቸውን ነው፡፡ ከአመጋገብ ጀምሮ ለአራስ የተለየ ትኩረት በመስጠት እንክብካቤ ይደረግላታል፡፡

የገፓት ቃዋ ጠጪ አባላቶች በተረኛዋ #ቡና አፍዪ እማወራ ቤት ይሰባሰባሉ፡፡ በእድሜ የገፉ አባቶች ከወተት ሰባት እጅ የነፃው ጋቢያቸውን ትከሻቸው ላይ አጣፍተው ከካቧት፣ ዮስጥየ ፣ጂፐ እና ከዳነራ በተዘጋጀው ምንጣፍ ላይ ያርፋሉ አሊያም ጋደም ይላሉ፡፡ ካቧትና ዮስጥየ ከእንሰት ኮባ የሚዘጋጁ ሲሆኑ #ጂፐ ደግሞ ከቃጫና አንጨት ከሚባል እፀዋት ይዘጋጃል፡፡ ዳነራ ከቆዳ የሚዘጋጅ ሲሆን ቆዳው እጅግ የተከበሩ ባለሙያዎች ፍቀው አለስልሰው የሚያዘጋጁ ነው በተለምዶ "ነፉረ" በመባል ይታወቃሉ፡፡

ጉራጌዎች ሦስት አይነት ቤቶች ይሠራሉ፡፡ የመጀመርያው #ጎየ በጣም ትልቅ ቤትነው፡፡ በነገራችን ላይ ጉራጌዎች በተለይም የቤቱ አባወራና እማወራ ከከብቶቻቸው ጋር በአንድ ጎጆ ጥላ ሥር በጎየ (በሰፊ) ቤት ነው የሚያድሩት፡፡ በዚሁ ጎየ ቤት ውስጥ ከብቶች የሚታሰሩበት ቦታ "ጋድር" ተብሎ ይጠራል፡፡

ከጋድር ፊት ለፊት የሚገኘው ሰዎች ቡና የሚጠጡበት እና የሚያርፉበት ሥፍራ ቃቀት እያሉ ይጠሩታል፡፡ #እንግዳ ተቀብለው የሚያስተናግዱበት፣ ድግስ የሚያሰናዱበትና ልጆች የሚያጠኑበትና የሚዝናኑበት እጅግ ያማረና የተዋበ ቤት እልፍኝ(ኽራር) ይባላል፡፡ ሦስተኛውና አነስ ያለው ቤት ዘገር ብለው ይጠሩታል፡፡ ዘገር ለኩሽና፣ ለከብቶች መኖ ማከማቻና ለመሳሰሉ አገልግሎቶች እንደ መጋዘን ይጠቀሙበታል፡፡

#ዘርማዎች (ወጣቶች) በገፓት ቃዋ ላይ ይገኛሉ፡፡ ምድጃውን (ጎርደት) ዙርያ ክብ ሠርተው ቦርጭማ ላይ ቁጭ በማለት ምድጃው መሀል ላይ የሚንቀለቀለው እሳት እየሞቃቸው ያሻቸውን ያወጋሉ፡፡ ጎርደቱ ላይ መሰቀልኛ ተጋድሞ የሚነደው ፍልጥ የሚለቀው ሙቀት ግድግዳና ምሰሶ ላይ ከተለኮሰ የኩራዝ ብርሃን ጋር ሲዳመር የቤቱን የውስጥ ገጽታ ባንዴ ወደ አንዳች ማራኪ እይታ ይቀየራል፡፡

ከብቶቹ ቀን ሲግጡት የዋሉት ሳር አይናቸውን ጨፍነው በመንጋጋቸው ግራና ቀኝ ሲያመነዥኩት አፋቸው ቅኝት (Rhythm) ያለው ድምፅ ያወጣል፡፡ የጉረሮዋቸው ትቦ የላመው ወደ ሆድ ሲያቀብል ሽርክቱ ደግሞ ወደ መንጋጋ ሲያደርስ ሲታይ #ፊልም የመመልከት ያህል ከመምሰል በተጨማሪ ተፈጥሮን አለማድነቅ አይቻልም፡፡

የተጣደው ቡና ቱፍ ብሎ እስኪሰክን ድረስ እማወራዋ ላሟን አልባ ትኩስ ወተት ከሸክላ በተሠራ "እንጃባ" ለሽማግሌዎቹ ትሠጣቸዋለች፡፡ #ሽማግሌዎቹ ማጀትሽ አይጣ፣ ከዓመት ዓመት ወተት አያሳጣሽ ብለው ይመርቋታል፡፡ ላሚቷም "ትትረፍ" ተብላ ትመረቃለች(ክፉ አይንካሽ ውለሽ ግቢ ማለታቸው ነው)፡፡

ለዘርማዎች ዮሸር ኤብ (እርጎ) ይሰጣቸዋል፡፡ ለልጃ ገረዶች (#ዘየዎች) ትኩስ ለጋ ቂቤ አናታቸው ይቀባሉ፡፡ ዘርማዎች ከዮሸር ኤብ በተጨማሪ ቄሳ (አይቤ) ይበላሉ፣ አጓት ይጠጣሉ፡፡

ሲኒ ይጎዘጎዛል፡፡ ቤት ያፈራውን የቡና ቁርስ ይቀርባል፡፡ በትልቅ #ጀበና የተፈላው ቡና መቀዳት ይጀምራል፡፡ ቀን በሥራ ላይ ታች እያለ ሲዳክር የዋለ ጉልበት አደብ ገዝቶ የተቀመጠበት ሰዓት ነው፡፡ እናቶች ጠበቅ አድርገው ወገባቸውን ካሰሩበት መቀነት (አዝጋርት) ተላቀው እረፍት የሚያደርጉበት ጊዜ ነው፡፡ ቡና በኡፋ ቂቤ ወይም ቡና ብቻ እንደየ ፍላጎቱ ተቀድቶ ይዳረሳል፡፡
አንዱ አባወራ #አረቄ ገዝቶ መርቁኝ ይላል፡፡ ቡናቸውን ፉት እያሉ የተለመደው ጨዋታቸውን ያደሩታል፡፡ የሰፈሩ ውሎ በጨዋታ ይገመገማል።

እናቶች በዕለቱ ስለነበረ #ገበያ ውሎ ያወራሉ፡፡ አረቄው ከቀረበ በኋላ በሥራና በተለያዩ ምክንያቶች ከአጠገባቸው ርቀው ለሚገኙ ቤተሰቦቻቸው የሄዱበት ቦታ እንዲቀናቸው ከክፉ እንዲሰውራቸውና ሃሳባቸውንም እንዲሞላላቸው አጥብቀው ይመርቃሉ፡፡

ጉራጌዎች ባህላዊ የሆነ የአረቄ አወጣጥ ዘዴ አላቸው፡፡ በተለያየ መንገድ ለተለያዩ ጥቅሞችና ለመድሀኒትነት የሚያገለግል አረቄ ያዘጋጃሉ፡፡ ከብቅልና ከጌሾ በተጫማሪ ከተለያዩ #እፀዋቶችና ሥራስሮች መጥነው የሚያዘጋጁት አረቄ ለደም ግፊት፣ ለሆድ ቁርጠት፣ ለኮሊስትሮል እና ለአላስፈላጊ ውፍረት ፍቱን መድሀኒት ነው ብለው ያስባሉ፡፡

ቀስ በቀስ #ሸንጎው እየተገባደደ ይሄዳል፡፡ የቡና ጠጪ አባላቶቹ አልፎ አልፎ እራትም አንድ ላይ ይመገባሉ፡፡ የበሰለ ጎመን በደቃቁ ተከትፎ ከአይቤ ጋር በቂቤ ያጣፈጡት ዝማሞጃት ከቆጮ ጋር ሲበላ እንደ ማር ከመጣፈጡ በላይ ለሰውነት አንዳች እርካታ ይሰጣል፡፡ እንደ ወቅቱ ሁኔታ የጎመን #ክትፎ አዘጋጅተው፣ በግ አርደውና ጠላ ጠምቀው ተሰባስበው የሚያከብሩት በዓላቶችም አሉ፡፡ከምሽቱ 4፡00 ሲሆን የገባት ቃዋ ተጠናቅቆ ወደየ ቤቶቻቸው ያመራሉ፡፡

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

29 Nov, 17:09

1,626

ሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የቀድሞ ተማሪዎች እና ተወላጆች ለቡራት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለላይብረሪ ህንፃ ግንባታ 1.8 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡

#ዘቢዳር_ሚዲያ ህዳር 20/2017 ዓ.ል

ነዋሪነታቸውን በሰሜን አሜሪካ ያደረጉ የአማርድ የቀድሞ የቡራት ተማሪዎች እና የአካባቢው ተወላጆች ማህበር አባላት ማህበሩ በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ በሚገኘው ቡራት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሊያስገነባው ላቀደው የላይብረሪ ህንጻ ማሰሪያ የሚውል ብር 1,800,000 (አንድ ሚሊየን ስምንት መቶ ሺህ) ብር አሰባስበው ገቢ አድርገዋል፡፡

ይህንን ያለው የጌታ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሲሆን እነዚህ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የጌታ ወረዳ ተወላጆች ያደረጉት ድጋፍ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነ እና በት/ቤቱ መማሪያ ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት ላይ ከዚህ የላቀ ገንዘብ እንዳበረከቱ የማህበሩ ዋና ጸሐፊ አቶ መላኩ ይርዳው ገልፀውልናል።
 
ይህ ማህበር በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ ከሚገኙ 6 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ አንዱ በሆነው ቡራት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሩ የቀድሞ ተማሪዎች የአካባቢው ልማት ወዳድ ተወላጆችን በማስተባበር አካባቢውን ለማልማት በ2012 ዓ.ል ያቋቋሙት ሀገር አቀፍ ሲቪክ ማህበር መሆኑን የገለፁልን የማህበሩ ፀሐፊ አክለውም ማህበሩ በተቋቋመበት 2012 ዓ.ል ለቡራት ት/ቤት 210,000 ብር ወጪ በማድረግ የተማሪዎች መቀመጫ ዴስክ፣ የላይብረሪ ወንበርና ጠረጴዛ ያማሏ ሲሆን ለጌታ ወረዳ ለኮቪድ መከላከያ ብር 50,000 ድጋፍ አድርጓል አውስተዋል ማህበሩ እስካሁን የሰራቸውን ስራዎች በዝርዝር ገልፀውልናል።

ማህበሩ በ2013 ዓ.ል ብር 530,000 ወጪ በማድረግ ት/ቤቱ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ለማሳደግ በቅድመ ሁኔታነት የተቀመጡ እና ለመማር ማስተማር አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች የቤተ-ሙከራ መገልገያዎች፣ የቤተ- ሙከራና የላይብረሪ ሼልፎች፣ ዴስኮች፣ መጻህፍት፣ ጋዎንና የስፖርት እቃዎች አሟልቷል።

በተጨማሪም በዚሁ ዓመት ከ600,000 ብር በላይ ወጪ በማድረግ አራት ክፍሎች ያሉት ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውል መለስተኛ አንድ ብሎክ ህንጻ አስገንብቷል።

በ2014 ዓ.ል የቡራት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ (fund rising) እቅድ አዘጋጅቶ የዞኑ እና የወረዳው አስተዳዳሪዎችን ያሳተፈ ስኬታማ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም (ቴሌቶን) አከናውኗል።

በ2015 ዓ.ል የዞኑ እና የወረዳው የመንግስት አመራሮች እና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት በተገኙበት የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቱ መማሪያ ህንጻዎች ግንባታ አስጀምሯል። ግንባታው በተያዘለት እቅድ መሰረት ተጠናቅቆ ከ2016 ዓ.ል ጀምሮ ከፊሎቹ ክፍሎች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ አሁን ያለው ቤተ-መጻህፍት ደረጃው የጠበቀ ባለመሆኑ በሌላ ህንጻ ለመቀየር እየተሰራ ሲሆን ሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የማህበሩ አባላት ከዚህ ቀደም ዋናው ግንባታ ላይ እና ቅድመ ግንባታ ላይ ካደረጉት ድጋፍ በተጨማሪ ለቤተ-መጻህፍቱ ግንባታ 1.8 ሚሊየን ብር ገቢ አድርገዋል።  

ማህበሩ በቀጥታ አካውንቱ ወጪ ሳይደረግ በበጎ አድራጎት የተገኙ የአይነትና የሙያ ድጋፎችን ጨምሮ 25 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ይህንን ት/ቤት ከወረዳው አስተዳደር ጋር በመተባበር ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የሚገኙ የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ለማስመረቅ ለጥር 2017 ዓ.ል ቀጠሮ ይዟል።

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

29 Nov, 10:55

1,377

የዳጪ ሃሙስ ገበያ ነዋሪዎች ከ8 ወር በላይ የመብራት አገልግሎት በመቋረጡ ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን ገለፁ።

#ዘቢዳር_ሚዲያ ህዳር 20, 2017 ዓ. ል

በምሥራቅ ጉራጌ ዞን #ሶዶ ወረዳ የዳጪ ሃሙስ ገበያ ነዋሪዎች ከግንቦት ወር 2016 ዓ.ል ጀምሮ የመብራት አገልግሎት በመቋረጡ ለከፋ #ማህበራዊና #ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋልጠናል ሲሉ ለዘቢዳር ሚዲያ ተናገሩ።

የከተማውና የአጎራባች #ቀበሌ ነዋሪዎች ወፍጮ የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ለማግኘት ብዙ ኪሎሜትሮችን ለማቋረጥ መገደዳቸውን ተናግረዋል።

የነዋሪዎችን #ቅሬታ መነሻ በማድረግ የከተማውን ሊቀመንበር አቶ አዳነ ነጋሽን በስልክ ያነጋገረችው #ዘቢዳር ሚዲያ ችግሩ እውነት ስለመሆኑ ከሊቀመንበሩ አረጋግጣለች።

የችግሩ መንስኤ የትራንስፎርመር #ብልሽት መሆኑን በመግለፅ "ችግሩ ከተፈጠረ ጀምሮ በተደጋጋሚ ለወረዳ ፣ለዞንና ለክልል ብናመለክትም 'ጠብቁ #ትራንስፎርመር ሲገኝ እናንተ ቅድሚያ እንድታገኙ እናደርጋለን' ከማለት የዘለለ ምላሽ ማግኘት አልቻልንም ሲሉ ገልፀዋል።

ኃላፊው አክለውም ከተማዋ የመብራት ተጠቃሚ መሆኗን ተከትሎ በርካታ ወጣቶች በተለያየ የሙያ ዘርፍ በስራ ዕድል #ፈጠራ ተሰማርተው የነበረ ቢሆንም በአሁን ሰአት ስራ አጥ ሆነው መቀመጣቸውን ተናግረዋል።

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

29 Nov, 03:51

2,164

ከ3 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ 8 ሺ የጉራጊኛ ትምህርት መጽሀፍቶች ታትመው ለወረዳና ከተሞች መሰራጨታቸው የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታወቀ፡፡

ህዳር 26/2017 ዓ.ል

መምሪያው የመፅሀፍቶች እጥረት ለመቅረፍ 8 ሺህ በዞኑ መንግስት የታተሙ የጉራጊኛ መፅሀፍቶች ለወረዳና ከተሞች ማሰራጨት መቻሉ ገልፀዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ መብራቴ ወ/ማሪያም እንደገለፁት የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል በአጭር ጊዜ ከታቀዱ እቅዶች አንዱ የመማሪያና ማስተማሪያ መፅሀፍት ተደራሽ ማድረግ ነው፡፡

በመሆኑም ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የመጽሀፍት ችግር ለመቅረፍ እንደ ዞን መላው ህዝባችንና ባለሀብቱ በማሳተፍ ከ75 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ ከ2 መቶ 55 ሺ በላይ ከ1-6ኛ ክፍል መፅሀፍ ተባዝቶ መሰራጨቱ አስታውሰዋል፡፡

እንደ አቶ መብራቴ ገለፃ ይህ ጅምር ይበልጥ በማጠናከር በ2017 እንደዞን ከ100 ሚሊየን ብር በላይ መላው ህዝባችን በማሳተፍ ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል መፅሀፍ ለማሳተም ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱ ጠቁመዋል።

ከእነዚህም አንገብጋቢ የነበረው ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ክፍል የጉራጊኛ የአፍ መፍቻ ትምህርት መፅሀፍ የዞናችን መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመደበው በጀት በአጭር ጊዜ 8 ሺህ መፅሀፍቶች ታትመው ተሰራጭተዋል ብለዋል፡፡

በዞናችን የጉራጊኛ ቋንቋ በቅድመ መደበኛ በሙከራ ደረጃ በመጀመር እና አጠናክሮ ለማስቀጠል ሰፊ ስራዎች ተሰርቷል ተብሏል።

የጉራጊኛ ቋንቋ በሙከራ ደረጃ በመነሳት በተሰሩ ስራዎች በአሁን ሰአት በሁሉም ቅደመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች እና በአንደኛ ክፍል እንደ አንድ የትምህርት አይነት እየተሰጠ ሲሆን በ2ኛ ክፍል ደግሞ በ18 ትምህርት ቤቶች የሙከራ ትግበራ ስራ መጀመሩ ተናግረዋል።

ለዚህም መጽሀፍቶች የማሳተም ፣ለመምህራን ስልጠናዎችን የመስጠት እና ልዩ ልዩ ድጋፎች መደረጋቸው ተናግረው ተማሪዎችም የበለጠ ደስተኛ ሁነው በመማር ላይ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል።

መረጃውን ያገኘነው ከዞኑ የመንግሰት ኮሚኒኬሽን ነው።
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

27 Nov, 14:02

1,595

ይህንን ቻናል ተወዳጁት ታተርፉበታላችሁ!

እስኪ ስለዚህ አስገራሚ የቴሌግራም ቻናልህ ከተሰጡ ምስክርነቶች አንዱን እናጋራችሁ!

ወንድሜ ክብሩ፤ የቴሌግራም ቻናልህ አስገራሚ ነው፡፡ ብዙ የሚነበቡ Extracts ፖስት አድርገሃል፡፡ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ “ማራኪ አንቀጾች” ብለን እንደምናወጣው ዓይነት ነው፡፡ ምስሎችና የመጽሐፍ ሽፋን ቢኖረው ደግሞ ቻናሉን የበለጠ ሳቢና ማራኪ ያደርገዋል፡፡

የማራኪ አንቀጾቹን እጥር ምጥን ማለት ወድጄዋለሁ፡፡ ከአዳዲስ መጻሕፍት ብቻ ሳይሆን ከድሮዎቹም የተመረጡ አንቀጾች ፖስት መደረጋቸው ሸጋ ነው፡፡ የእንደዚህ ያሉ ቻናሎች መበራከት የተፋዘዘውን የንባብ ባህልና ልማድ ያነቃቃሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ዘመኑ የዲጂታል ነውና፡፡

ይኼን የመሰለ ግሩም ቻናል በርካታ ተከታዮችና ጎብኚዎች ሊኖሩት ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ስለዚህም በስፋት ፕሮሞት መደረግ አለበት፡፡ Kibru Books የቴሌግራም ቻናል፣ ፌስቡክ ቢኖረውም ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

በነገራችን ላይ አዳዲስ መጻሕፍት ሲታተሙና ሲወጡ ዜናው እንዲሰራና መረጃው ለንባብ ምዕመኑ እንዲደርስ ብትልክልኝ ደስ ይለኛል፡፡ አሪፍ መጻሕፍት ሲወጡ (በተለይ አንተ ያነበብካቸው) አልፎ አልፎ ብትልክልኝም አይከፋኝም፡፡ ለማንበብም ለማስተዋወቅም፡፡

በነገራችን ላይ አዲስ አድማስ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ አሁን ላይ መጻሕፍት ላይ ሪቪው በመሥራት፣ መጻሕፍትና ንባብን ፕሮሞት እያደረገ ይገኛል፡፡ አስተውለህ ከሆነ በአንድ ዕትም ቢያንስ ሁለት የመጻሕፍት ሪቪዎች እየወጡ ነው - በዩኒቨርስቲ የሥነጽሁፍ መምህራን በጥልቀት የተሰሩ፡፡

አዲስ አድማስ ላለፉት 25 ዓመታት ለሥነጽሁፍና ባጠቃላይ ለጥበብ ሰፊ ቦታና ልዩ ትኩረት በመስጠት ከአሜሪካው ኒውዮርከር ጋር ይስተካከላል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

ግን ሳልጠየቅ ይሄን ሁሉ የምለፈልፈው ለምንድን ነው? አንዳንድ ቀን እኮ ይሄው ነው፡፡ ለማንኛውም አንባቢን ያብዛልን፡፡ ያለመጻሕፍትና ንባብ አገርን መገንባት ዘበት ነውና፡፡

በሥራህ ሁሉ ስኬትን እመኝልሃለሁ፡፡

https://t.me/kibrubook
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

27 Nov, 06:56

770

የሕግ ባለሙያውና ጠበቃው ምን ገጠማቸው ?

" ቅስም ይሰብራል ! " - የሕግ ባለሙያና ጠበቃ አንዷለም በውቀቱ


🔴 " ሰፈሩ መፍረሱና  መልሶ መልማቱ ላይ ተቃውሞ የሌለውን ኮሚኒቲ በ2 እና በ3 ሰአት እያዋከቡ ማስወጣት መውደቂያውን ሳያውቅ ማሳቀቅ መጨረሻው ይሄ ነው !! "

የሕግ ባለሙያና ጠበቃ የሆኑት አንዷለም በውቀቱ ዛሬ እጅግ ቅስማቸውን የሰበረ ክስተት እንደገጠማቸው ገልጸዋል።

ነገሩ እንዲህ ነው ...

ባለፈው አርብ " ፒኮክ መናፈሻ " አካባቢ አትክልት በማምረት ስራ የሚተዳደሩ ቤተሰቦችና ልጆቻቸው ቢሯቸው ይመጣሉ።

እነዚሁ ነዋሪዎች " ሰፈሩ ለልማት ሊነሳ ነው እየተባለ ነው። ከወላጆቻችን ዘመን ጀምሮ በአካባቢው ለ73 አመታት ቆይተናል። ድንገት ተነሱ ብንባል ምን ይዋጠን!? " ሲሉ ይገልጹላቸዋል።

እሳቸውም " መጀመሪያ የምትሄዱበትን ቦታ ማመቻቸት የመንግስት ግዴታ ነው። ያ ሳይሆን ለማስነሳት እንቅስቃሴ የሚደረግ ቢሆን ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርቤ እግድ እንዲሰጣችሁ አደርጋለሁ ! " ብለዋቸው ይለያያሉ።

ቅዳሜ ጉዳዩ የሚታይበትን አግባብ ሲያዘጋጁ እንደዋሉ የሚናገሩት የሕግ ባለሙያው ፤ እሁድ ጠዋት ግን ስልክ ይደወልላቸው። በዚህም " ከቤተክርስትያን ስንመለስ ቤታችን እየፈረሰ አገኘነው " ሲሉ እነዚሁ ቤተሰቦች ይነግሯቸዋል።

እሳቸውም ከባልደረባቸው ጋር ወደ ቦታው ሄዱ።

አፅናንተዋቸው " መትረፍ የሚችለውን ለማስቆም እንሞክራለን " ይሏቸዋል።

እስከ ማታ ድረስ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጨምሮ ለሚመለከታቸው አካላት የህግ አቤቱታዎችን ሲያዘጋጁ ያመሻሉ።

ሰኞ ጠዋት ኮሚኒቲው ህጋዊ የህብረት ስራ ማህበር ያላቸው በመሆኑ በማህበራቸው ስም ሊቀመንበሩ አቶ ዱላ ኑርጋ ውክልና እንዲሰጧቸው እንደተነጋገሩ የሕግ ባለሙያው አመክተዋል።

ትላንት ከሰአት ሊቀመንበሩ የጠበቃ ውክልና ለመስጠት የማህበሩን የመመስረቻ ጽሁፍ ስላጡት ለማክሰኞ ጠዋት እንደሚሰጧቸው ቀጥሮ ይይዛሉ።

ዛሬ ጠዋት ሊቀመንበሩ አቶ ዱላ ከቤታቸው ሲወጡ ግን የማህበሩ አባላት ሰፈር ውስጥ ለማፍረሻ የመጣ ዶዘር ቆሟል።

ሌሎች አባላቶች ውክልና ለመስጠት ውልና ማስረጃ እየጠበቋቸው ነበር።

እንደ ሕግ ባለሙያው ማብራሪያ ሊቀመንበሩ አብራቸው ከቤት የወጡትን ባለቤታቸውን " መጣሁ እየሄድሽ ጠብቂኝ ! " ብለዋቸው ወደ ቤት ይመለሳሉ።

በኃላም በአንዲት ቀጭን ሲባጎ እራሳቸውን አንጠልጥለው  እንደተገኘ አስረድተዋል።

የሕግ ባለሙያው ዛሬ ጠዋት 3:00 ላይ አቤቱታውን ይዘው የአቶ ዱላን ስልክ ሲጠብቁ እንደነበር ገልጸዋል። መጨረሻው ግን ፍጹም አሳዛኝ ነው የሆነ።

" ሰፈሩ መፍረሱና  መልሶ መልማቱ ላይ ተቃውሞ የሌለውን ኮሚኒቲ በ2 እና በ3 ሰአት እያዋከቡ ማስወጣት መውደቂያውን ሳያውቅ ማሳቀቅ መጨረሻው ይሄ ነው " ሲሉ የሕግ ባለሙያው ሁኔታውን በሀዘን ገልጸዋል።

" አቶ ዱላ ለ20 አመት ያህል በሊቀመንበርነት ያገለገሉትን ከ70 አመት በላይ በአንድ ቦታ የቆየውን ለፍቶ አዳሪ ማህበረሰብ ' ፌይል አደርጌያቸዋለሁ ' ብለው እራሳቸውን አጥፍተዋል " ያሉት የሕግ ባለሙያው " እኔም ያንን ኮሚኒቲ ፌይል አድርጌዋለሁ። ትላንት አቤቱታውን ባስገባ ምናልባት ሊቀመንበሩ ከውሳኔው ይቆጠብ ይሆን?! ከጠዋት ጀምሮ በሰቀቀን ውስጥ ነኝ! ቀብራቸው ነገ ይፈጸማል! ነፍሳቸውን ፈጣሪ ይቀበላት!! " ሲሉ ቃላቸውን ደምድመዋል።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

26 Nov, 18:20

1,469

#ይህ በምስሉ የምትመለከቱት ሃይደር ሙባሪክ የተባለ በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ ተወልዶ ያደገ ገና ዕድሜው በ20ዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኝ ሮጦ ያልጠገበ ወጣት ሲሆን በአጥንት ኢንፌክሽን ለረጅም አመታት እየተሰቃየ ይገኛል ። በብዙ ሆስፒታሎች ህክምና ለማድረግ ተሞክሮም በቀላሉ የሚታከም እንዳልሆነ ሙሉ ኦፕሬሽን እንደሚያስፈልገው ዶክተሮች አረጋግጠዋል። ታዲያ ለህክምናው 1,200,000 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ብር የተጠየቀ ሲሆን ቤተሰቦቹ ይህንን ገንዘብ ስሌላቸው ልጃቸው በገንዘብ እጥረት ምክኒያት እግሩን በወጣትነት እድሜው እያጣው እንደሆነ እያዩ እናት በለቅሶ አባትም በጭንቀት ተውጠዋልና ልጄን አድኑልኝ ያላችሁን ተባበሩኝ ሲሉ እጃቸው ወደ ደጋግ የሃገር ልጆች ዘርግተዋልና እናግዛቸው።
የባንክ ቁጥር:-
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000629694351 ሃይደር ሙባረክ
1000295596515 ሙባሪክ ሸሪፍ

ለበለጠ መረጃ +251910525319
ደውለው ማውራት እና አብሽር ማለት ይችላሉ።
# የላካቹበት ደረሰኝ አስተያየት መስጫው ላይ ብታሰፍሩልን ለኸይር ማነሳሻ እንጠቀመዋለን 🙏🙏

#ፖስቱ ሰዎች ጋር እንዲደርስ ሼር በማድረግ እንድትተባበሩ በፈጣሪ ስም ትጠየቃላችሁ 🙏🙏