آخرین پست‌های Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ) (@guragez) در تلگرام

پست‌های تلگرام Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)
# ይህ የዘቢዳር ቻናል የሀገራችን ብሎም የጉራጌ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካ፣ ኪነ ጥበብ፣ ታሪክ፣ ርዕዮት እና ሁለንተናዊ መልክ የሚዳሰስበት የመገናኛ የመወያያ እና የመጦመርያ አውድ ነው!
4,316 مشترک
4,371 عکس
73 ویدیو
آخرین به‌روزرسانی 06.03.2025 10:20

آخرین محتوای به اشتراک گذاشته شده توسط Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ) در تلگرام

Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

20 Dec, 11:37

4,264

ኢዘዲን ካሚልን ለመምረጥ ወደ አጭር ቁጥር 9355 በቴክስት BIW02 ብለው ይላኩ። እኔን መምረጣችሁ የሚያረጋግጥ መልዕክት በቴክስት ይደርሳችኋል።

"ለተሰጠኝ እድል ሁሉ አመሰግናለሁ። ለመጀመሪያ ጊዜ በአንቴክስ ኢትዮጵያ ሸላሚነት በተዘጋጀው BIWs Prize የሽልማት ፕሮግራም በኢኮኖሚ ዘርፍ እጩ በመሆን የ10 ሚሊዮን ብር ውድድር ላይ እየተወዳደርኩኝ እገኛለሁ። ከዚህ ቀደም በሰራኋቸው በ37 የስራ ፈጠራ ሆነ በወደፊት ህልሜ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክተልኛል ብዬ የማስበው በዚህ ውድድር ላይ በመወዳደሬ ደስታ ይሰማኛል። በዚህ ውድድር አሸናፊ የምሆነው እናንተ ድጋፋችሁንና ድምፃችሁን ከሰጣችሁኝ ነው። አብራችሁኝ ስለምትቆሙ አመሰግናለሁ።" Ezedin Kamil - ኢዘዲን ካሚል



ኢዘዲን ካሚልን ለመምረጥ ወደ አጭር ቁጥር 9355 በቴክስት BIW02 ብለው ይላኩ። እኔን መምረጣችሁ የሚያረጋግጥ መልዕክት በቴክስት ይደርሳችኋል።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

19 Dec, 07:39

2,976

ኢሳት ቲቪ በዜና አሳላፊዋንና በቪዲዮ ኤዲተሩን ከስራ አገደ።

ከሰሞኑ በጉራጌ ዞን እኖር ኤነርና መገር ወረዳ ቆስየ/ቆሴ ከተማ ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የተከሰተውን ጥቃት አስመልክቶ የተሰራ ዜናን ርዕሰ በምታነብበት ጊዜ በዜናው ይዘት ስትሳለቅ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በቲክቶክ ገጿ መልቀቋን ተከትሎ ብዙሃኑን ማስቆጣቱ ይታወቃል።

ኢሳት ይሄን ድርጊት ተከትሎ የዜና አሳላፊዋ ትግስት ተስፋዬ (ቲና) እና ቪዲዮውን አሳልፎ የሰጣት ባለሙያ ከስራ አግዷል።

ጣቢያውም በተፈጠረው ክስተት ህዝቡን ይቅርታ ጠይቋል።

የዜና አሳላፊዋ በትላንትናው ዕለት በቲክቶክ ገጿ ህዝቡን በይፋ ይቅርታ መጠየቋን መዘገባችን ይታወሳል።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

18 Dec, 16:00

2,702

ብንዘገይም አሁም እድሉ አለን!

አሁን አሁን ኢትዮጵያ የምትከተለው የንግድ ስርዓት በልምድ ወይም ከዚህ ቀደም በርካቶች ስኬታማ በሆኑበት አካሔድ ብቻ እንደማሆን ብዙዎች ከረፈደም ቢሆን እየተረዱት ነው፡፡

ከዚህ ቀደም የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አስተዳደር መደበኛ ስራዎችን መካሔድ በጀመሩበት ሰሞን (ከ4 አመት በፊት) ስለ ኢኮኖሚ ሪፎርምና መሰል ጉዳዬች አጀንዳ መሆን ሲጀምሩ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች በመሰባበሰብ መጪውን ጊዜ እንደ ጉራጌ ላሉ የንግዱ ማህበረሰብ ፈታኝ ጊዜ እንደሚሆን መላምታቸውን በጥናት ጭምር አስደግፈው ያሳስቡ ነበር፡፡

ይህንን በመረዳት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የማህበረሰቡ ተወካይ የመንግስት አካላት፣ የንግዱ ማህበረሰብ እና የዘርፉ ባለሙዎችን የሚያገናኝ የስብስብ መድረክ በመፍጠር መጪውን ጊዜ የሚዋጅ የቢዝነስ ማህበረሰብ ለመገንባት ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

አሁን በሀገራችን እየታየ እና እየሆነ ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ በቃል ሆነ በሰነድ አስደግፈን #በጉራጌ_ጎየ ማህበር በኩል መላምታችንን ለማስረዳት ብንጥርም ብዙዎቹ ባለሀብቶች ነገሩን ለመረዳት ብዙ ፍቀደኛ አልነበሩም፡፡

የሆነው ሁሉ ሆኖ አሁንም ጊዜው ቢዘገይም አረፈደምና የዝያኔ ለጉዳዩ ያሳብናቸው አካላት ሆኑ አብዛኛው የንግዱ ማህበረሰብ ብዙ የተቸገሩበት አሁናዊ ሁኔታ እና መጪውን ጊዜ የሚዋጅ ምክክሮች፣ የሀገሪቱን የማክሮ ኢኮኖሚን አካሔድና መዳረሻን ያገናዘበ አዳዲስ የቢዝነስ አሰራሮች እና ሪፎርሞች የሚያስፈልጋቸው ወቅት እንደሆነ መረዳት ተገቢ ነው፡፡

ይህንን ኃላፊነት መወጣት ያለባችሁ አካላትም በተለይም ነገሩን የሚያሳስባችሁ ወገኖች መንገድ የሚያሳዩ ተቋማት በመፍጠርና ብቃት ያላቸው ባለሙዎች በማሰባሰብ ማህበረሰባችሁን ሊደርስበት ከሚችለው የሀብት፣ የአይምሮ ጤና እና ማህበራዊ መሰረት መናጋት አደጋ ልትታደጉት ያስፈልጋል፡፡

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

18 Dec, 15:13

1,646

የወልቂጤ ከተማ የእግር ኳስ ቡድን የአሰልጣኞች ሽግሽግ አደረገ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድሩን እያካሄደ የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ የእግር ኳስ ቡድን በዛሬው ዕለት የአሰልጣኞች ሽግሽግ ማድረጉ ተገለጸ።

ክለቡ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዝርክርክ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ምክንያት ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲወርድ ከተደረገ በኃላ እያስመዘገበ ባለው ደካማ ውጤት ሳቢያ የቡድኑን ዋና እና ምክትል አሰልጣኝ ከ20 እና ከ17 ዓመት በታች ያለውን ቡድን እንዲያሰለጥኑ ወስኗል።

በዚህም መሰረት የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ የነበረው አቶ ሶሬሳ ካሚል ከ20 ዓመት በታች ምክትል አሰልጣኝ የነበረው አቶ አይቼው አባይ ደግሞ ከ17 ዓመት በታች ያለውን ቡድን የሚያሰለጥኑ መሆኑ ለአሰልጣኞቹ የደረሳቸው ደብዳቤ ይገልጻል።

ከ20 ዓመት በታች አሰልጣኝ የነበረው አቶ አብድልሃኒ ተሰማ ዋናውን ቡድን በምክትል አሰልጣኝነት ይዞ ከነገ ጀምሮ ጨዋታዎችን እንዲመራ የቡድኑ ኃላፊዎች ውሳኔ አስተላልፈዋል።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

17 Dec, 15:22

2,168

የኢሳቷ ጋዜጠኛ ነገር

በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ ፀያፍ የሆነ ድርጊት ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት የሙያ ፍቃድ የሚሰጥ ቢሆን ኖሮ በቀጥታ ፍቃድ የሚያስነጥቅ ድርጊት ነበር።

በእርግጥ ነውር የሆኑ የልጅቱ ንግግር እና ድርጊት ላይ ድርጅቱ (ኢሳት) የሚወስነውን ውሳኔ የሚጠበቅ ቢሆንም የዜና ማሰራጫ ስቱዲዮ እጅግ የተከበረ ቦታ አድርገው ለሰሩ እና ለሚሰሩ ጋዜጠኞች አንገት ያስደፋ፣ ሙያውን ለመቀላቀል ለሚያስቡም መጥፎ ትምህርት የሚሆን ነው።

የ"ዜና አንባቢዋ" የሚገርመው ሌላኛው ድርጊት ደግሞ የሆነ የተለየ ነገር እንዳደረገች ጀብደኛ ሰው በራሷ ቲክ ቶክ ገፅ ላይ ነውሯር እዩልኝ ስሙልኝ በማለት የለቀቀችው መሆኑ ነው።

በመሆኑም ልጅቱ የፈፀመችውን ስህተት ተረድታ ይቅርታ እንደምትጠይቅና የጋዜጠኝነት ሙያ ስነ ምግባር አክብራ እንደምትሰራ ተስፋ አለን።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

16 Dec, 17:00

2,021

ባንኮቻችንን ስንፈትሽ ...
....
/መላኩ ይርዳው/Melaku Yirdaw
በቅርቡ የፋይናንስ ሴክተሩን ቅርጽ ሊቀይሩ የሚችሉ ሁለት አዋጆች ይጸድቃሉ። የባንክ ስራ አዋጅ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ። እነዚህ ሁለት አዋጆች የባንኪንግ ሴክተሩን ለውጭ ገበያ ክፍት ከማድረግ አንስቶ ብሔራዊ ባንክ ባንኮችን በአንድ የማጠቃለል (merging) መብት የሚሰጡ ናቸው።

የውጭ ባንኮች ፍቃድ ጫፍ ላይ የደረሰና የአዋጁ መጽደቅ ብቻ በመጠባበቅ ላይ የሚገኝ ጉዳይ ነው። የባንኮች merging ደግሞ ከሚቀጥለው የፈረንጆች ዓመት (2025) ጀምሮ የሚጠበቅ ነው። ምክንያቱም የባንኮች አነስተኛ ካፒታል 5 ቢሊየን ብር እንዲሆን የተወሰነና ነባሮቹ ባንኮች በ2025፣ አዳዲሶቹ ባንኮች በ2027 እንዲያሟሉ ተቀምጦላቸዋል።

በዚህ ጊዜ ውስጥም ሆነ ተጨማሪ ጊዜ ቢሰጥ ካፒታላቸውን ወደ 5 ቢሊየን ማሳደግ የማይችሉ ባንኮች አያሌ ናቸው። ስለዚህ የኢት. ብሔራዊ ባንክ አዲሱ አዋጅ በሚሰጠው መብት መሰረት አንዳንድ ባንኮች በፈቃዳቸው አልያም እሱ በሚያቀርብላቸው አማራጭ መሰረት merge መሆናቸው አይቀሬ ነው። እነዚህ ሁለት አዋጆች ቆሞ ቀርነትና ልማዳዊነት የሚታይበት የባንኪንግ ኢንደስትሪው ሪፎርም ለማድረግ እድል ይሰጣሉ።

የባንኪንግ ኢንደስትሪው ከፍተኛ ሪፎርም የሚፈልግ ኢንደስትሪ ነው። በኔ ግምገማ ኢንደስትሪው ቢያንስ ሶስት መሠረታዊ ስብራቶች ያሉበት ነው።

1. ዘገምተኝነት (stagnant/non-dynamic) መሆን -

የባንኮቻችን የባህል እና የሙያ እድገታቸው ዘገምተኛ (non-dynamic) እና አንዱ ካንዱ ተመሳሳይ ነው። ኢንደስትሪው ላይ የዚህ ባንክ ባህል፣ ቀለም፣ መለያ (Identity) የሚባል ነገር የለም። ሁሉም ባንኮች አንድ አይነት ናቸው። ይህ መቀረፍ ያለበት ስብራት ነው።

ዛሬ ላይ ያለው የባንኮች ተቀማጭ ገንዘብ የመሰብሰቢያ ስትራቴጂ (deposit mobilization strategy) እና የማበደሪያ መንገድ ከ15 ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ነው። የዲፖዚት ሞቢላይዜሽን ስትራቴጂው መንገድ ላይ መንገደኛን እያስቆሙ አካውንት ከማስከፈት እና ይቆጥቡ ይሸለሙ የሚል ማስታወቂያ ከማስነገር የተሻገረ አይደለም። ከዚህ ከፍ ካለ መጠኑ ከፍ ላለ ገንዘብ በድርድር ላይ የተመሰረተ ወለድ ማቅረብ ነው። የባንኮች የዲፖዚት ሞቢላይዜሽን ስትራቴጂ ገንዘብን ከምንጩ አድኖ ማምጣት እና ሰጥቶ መቀበል ላይ የተመሰረተ አይደለም።

ባንኮች ለሚያበድሩት ብድር ወለድ በቀን (daily base) የሚያሰሉ ሲሆን ለቆጣቢው ወለድ የሚከፍሉት ግን ወሩን ሙሉ ለተቀመጠ ገንዘብ ብቻ ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው December 2 ላይ ገንዘብ ቢያስቀምጥ እና January 31 ላይ ቢያወጣው ገንዘቡ ለ60 ቀናት ባንክ ተቀምጧል፤ ነገር ግን ከሁለቱም ወሮች ላይ 1 1 ቀን ስለጎደለ በዚህ ተቀማጭ ገንዘብ ላይ ምንም ወለድ አያገኝም። ባንኩ ግን ካበደረው የ60 ቀን ወለድ አግኝቶበታል። ይህ አሰራር ገንዘቡን ባንክ በማስቀመጡ የግሽበት ዱላ ለሚያርፍበት ቆጣቢ ጉዳቱ ድርብርብ ይሆናል።

ባንኮች ለገንዘብ አስቀማጩ ለገንዘቡ ጥበቃ ከማድረግ የዘለለ የሚያቀርቡት ማበረታቻ የላቸውም፤ ገንዘብህን ስጠኝና እኔ ልጠቀምበት አይነት ነው ነገሩ። የማበደሪያ መንገዱም ቢሆን ከ15 ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ነው። ብድር የሚሰጠው ለተመሳሳይ ሴክተር በተመሳሳይ ክራይቴሪያ ነው። በተደጋጋሚ ለኢንደስትሪው ለጋነት እንደማሳያ የሚቀርበው የቋሚ ንብረት መያዣ (collateral) ጉዳይም ይበልጥ እየጠነከረ እንጂ እየላላ/እየተሻሻለ አልሄደም። ይሄ የገዢው ባንክ አስገዳጅነት እንዳለውም ልብ ይሏል።

2. ተደራሽነት/የሀብት ስርጭት ( resource allocation) -

የባንኮች ሀብት (resource) ተደራሽነቱ እጅግ የተገደበ ነው። ባለሙያ ያልሆነም ሰው የሚያውቀውም ከአመሰራረታቸው የሚጀምረው የብሔር፣ የአካባቢ፣ የሀይማኖት፣ የጾታ ... ቡድንተኝነት በሪሶርስ ስርጭቱ ኢ-ጤናማነት ላይ የጎላ ተጽእኖ አለው።

ከዚህ ባሻገር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ህዳር 2017 ዓ.ም ባወጣው financial stability ሪፖርት በሰኔ 2016 ዓ.ም ዴታ መሰረት ባንኮች ካበደሩት ጠቅላላ ብድር ብር 1.5 ቲሪሊየን ውስጥ 3.5 ፐርሰንቱ የተበደሩት አስር የግል ባለሀብቶች ናቸው። ይህ ማለት 10 የግል ባለሀብቶች የተበደሩት ብድር ብር 52.54 ቢሊየን ነው። በአማካይ እያንዳንዳቸው ብር 5.3 ቢሊየን ተበድረዋል ማለት ነው። ይህ ቁጥር ከአገሪቷ ኤክኖሚ እና የማበደር አቅም አንጻር ትልቅ ቁጥር ነው። ከአስሮቹ ቀጥሎ ያሉት ሀያ ባለሀብቶች የተበደሩትን ብንጨምር ፐርሰንቴጁ በጣም ከፍ ማለቱ አይቀርም። የውጭ ምንዛሬ (foreign currency) ስርጨቱም ከዚህ የተለየ አይደለም።

ተደራሽነቱ በዚህ ልክ የተገደበው የብድር ስርጭት በወረቀት ደረጃም ቢሆን ክፍት የሆነው ለነጋዴው ብቻ ነው። ሠራተኛው እና ገበሬው ለባንክ ብድር ባዕድ ናቸው ማለት ይቻላል።
ከሚሰሩበት ባንክ በጥቅማጥቅም መልኩ ብድር ያገኙ የባንክ ሠራተኞችን ጨምሮ አጠቃላይ በባንኮች የብድር ስርዓት ውስጥ ያሉ ተበዳሪዎች ቁጥር 300 ሺ አካባቢ ነው። በማንኛውም መልኩ ከባንኮች ብድር ያገኘው ኢትዮጵያዊ የህዝቡ 0.3% ብቻ መሆኑ ነው። ከነዚህ ተበዳሪዎች ውስጥ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ተበዳሪዎች ቁጥር 0.5% ብቻ ሲሆን እነዚህ 0.5 ፐርሰንቶቹ ተበዳሪዎች የብድሩ 75% ወስደዋል። የተቀረው 99.5% ተበዳሪ የደረሰው የጠቅላላ የባንኮች ብድር 25% ብቻ ነው። ይህ ቁጥር የሚያሳየው የኢትዮጵያ ባንኮች ሪሶርስ ከጥቂት ነጋዴዎች ውጪ ላለው ህዝብ የተፈቀደ እንዳልሆነ ነው።

ሌላኛው በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ የሚጠቃለል ጉድለት የብድር ስርጭቱ ከነጋዴዎቹም ውስጥ ንግዳቸው ሸቀጥ ከማምረት እና መሸጥ ውጪ ላሉ ሙያዊና ቴክኒካል ለሆኑ ቢዝነሶች ቦታ የሌለው መሆኑ ነው። ለምሳሌ ቴክኖሎጂ የነገው አለም እንደሚረከብ እና በነገው የአለም ኤክኖሚ ውስጥ ቴክኖሎጂ ወሳኝ ሚና/ድርሻ እንዳለው እየታወቀ ቴክኖሎጂ ለሚያቀርብ/ለሚያመርት ድርጅት ብድር የሚሰጥበት ፕላትፎርም የለም። ለሌሎች የአዕምሮ ውጤቶች ብድር ማማግኘትም የማይታሰብ ነው።

ይህ የባንኮች የሪሶርስ ስርጭት ጥበት ሌላኛው የባንኮቻችን ስብራት ነው።

3. በሚገባው ልክ ውጣታማ አለመሆን (Inefficiency) -
በአማካይ 75% የባንኮች ገቢ ከብድር ወለድ የሚገኝ ነው። የባንኮች የብድር መጠን (total outstanding loan) ስለማይቀንስ ገቢያቸው በቋሚነት የሚገኝ ሆነ እንጂ የባንኮች ገቢ ከባንኮቹ የእለት ከእለት የስራ ጥራትና ፈጠራ ጋር የሚገናኝ ቢሆን የባንኮቹ እድገት ቋሚ ላይሆን ይችል ነበር። ይህ የገቢ አለመዋዠቅ ስራቸው ልማዳዊነት እንዲጫነውና የእለት ከዕለት ስራቸው ውጤት በተናጥል እና በጥልቀት እንዳይገመግሙ/ለይተው እንዳያውቁ አድርጓቸዋል።

ለምሳሌ አንድ ባንክ የተጠየቀውን ወጪ/ዝውውር በሙሉ በተጠየቀበት ቅጽበት መክፈል በቻለበት ወር እና 50 ፐርሰንቱን በተጠየቀበት ቅጽበት መክፈል ባልቻለበት ወር በትርፉም ሆነ በባንኩ የሼር ዋጋ ላይ ያሳየው መቀነስ/አለመቀነስ የሚያውቁበት ሁኔታ የለም። ይሄ ልማዳዊነት ባንኮቹ ኤፊሸንት እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል።
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

16 Dec, 17:00

2,274

ሌላኛውና ዋነኛው የኢንደስትሪው ኢን-ኤፊሸንሲ መገለጫ ባንኮቹ ለሼር ባለድርሻዎቻቸው የሚከፍሉት የሼር ድርሻ ትርፍ (dividend) ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት (ከኢንሹራንስ እና ከማይክሮ ፋይናንስ) ያነሰ መሆኑ ነው። የኢትዮጵያ ባንኮች አማካይ ዓመታዊ ዲቪደንድ 25% አካባቢ ነው። የኢንሹራንሶች አማካይ ግን ከ30% በላይ ነው። ሀገሪቷ ላይ ካለው የዋጋ ግሽበት አንጻር 25% ዲቪደንድ እንደ ጥሩ ትርፍ የሚወሰድ አይደለም።

***
የውጭ ባንኮች ቢገቡ ምን ፋይዳ አለው? ለማን?
....
ከላይ እንዳነሳሁት የባንክ ኢንደስትሪው ለውጭ ባንኮች ክፍት የሚሆንበት ጊዜ እጅግ ተቃርቧል። ሆኖም ገበያው ቢከፈትስ የውጭ ባንኮች ሳያመነቱ ይገባሉ ወይ የሚለው ላይ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። ከገቡስ የትኞቹ ባንኮች ናቸው ለመግባት ፍላጎት ሊያሳዩ የሚችሉት የሚለው መሠረታዊ ጉዳይ ነው። ለማንም ግልጽ የሆነው ነገር ኢትዮጵያ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት፣ ከፍተኛ የአቅርቦትና የፍላጎት አለመጣጣም ያለባትና ከፍተኛ ያልተነካ እምቅ አቅም ያላት ሀገር መሆኗ ነው። ኢትዮጵያ ለየትኛውም ኢንደስትሪ ትልቅ ገበያ ነው። እነዚህ መልካም እድሎች ቢኖሩም ለጠቅላላ ቢዝነሱ እና ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) መቀጨጭ ምክንያት የሆነው የሰላም እጦቱ እና የፓለቲካ ብልሽቱ የውጭ ባንኮች የኢትዮጵያን ገበያ እንዲገፉት ሊዳርግ የሚችል ተግዳሮት ነው።

የሚገቡት ባንኮች ጤነኛ የቢዝነስ ሞዴል እና ርዕይ ያላቸው ባንኮች ከሆኑ ለሀገሪቷና ለህዝቡ እንዲሁም ለባንኪንግ ኢንደስትሪው ትልቅ በረከት ነው።

የውጭ ባንኮች ከገቡ -
1. ካፒታል ይዘው ስለሚገቡ ከፍተኛ የፋይናንስ እጥረት ላለበት የሀገሪቷ ኢኮኖሚ ተጨማሪ የካፒታል injection ለኤክኖሚው ትልቅ በረከት ነው።
2. ከኛ የተሻለ/የዘመነ የባንኪንግ ኢንደስትሪ ባህል ይዘው ይመጣሉ። ይህ ለኢንደስትሪው መዘመን ትልቅ አስተዋጽኦ አለው።
3. ተጨማሪ የውድድር መልካም እድል፣ ተጨማሪ ጉልበት ይዘው ይመጣሉ። ቢዝነስ የሚያድገው በውድድር ነው። የውድድር መኖር ደግሞ ኢንደስትሪው እንደ ኢንደስትሪ ያሳድገዋል። ኢንደስትሪው ሲያድግና አማራጮች ሲፈጠሩ ባንኮቹም ህዝቡም/ተጠቃሚውም ተጠቃሚ ናቸው።
4. አሁን ባሉት ባንኮች ቦታ የሌለው 99.7% የኢትዮጵያ ህዝብ ተመልካች የሚያገኝበት እድል ይፈጠራል።

እናም የውጭ ባንኮች ቢገቡ ለኢትዮጵያ ኤክኖሚ ተጨማሪ ጉልበት ነው። ጠቀሜታው ለሀገርም ለባንኪንግ ኢንደስትሪውም እድገት ሁነኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ከማንም በላይ ተጠቃሚው ግን ከሀገሪቷ ባንኮች ሪሶርስ ተቋዳሽ ያልሆነው ሰፊው (99.7%) የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። ከውጭ የሚገቡ ባንኮች አሁን ከባንክ ብድር ስርዓት ውጪ ለሆነው እና ብድር ቢያገኝ የመክፈል አቅም ካለው (ሠራተኛውና ገበሬው) ህዝብ ውስጥ 10% ተደራሽ ማድረግ ቢችሉ ለሀገሪቷ ኤክኖሚ እና የግለሰቦች የኑሮ መሻሻል ትልቅ paradigm shift ነው።
ይቅናን!!!

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

15 Dec, 09:43

1,907

ኢሳት ቲቪ በጉራጌ ዞን በእኖር ኤነርና መገር ወረዳ ቆስየ ከተማ የጉራጌ ተወላጆች ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት አስመልክቶ የሰራው ዘገባ።
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

15 Dec, 06:29

1,821

በወልቂጤ ከተማ ያለ ደረሰኝ ግብይት ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰቦችን ታሰሩ።

#ዘቢዳር_ሚዲያ ታህሣሥ 05/2017

ዛሬ በወልቂጤ ከተማ በጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ አማካኝነት በተደረገ ድንገተኛ ቁጥጥር ያለ ደረሰኝ ግብይት ፈፅመዋል የተባሉ ግለሰቦችን ዞን ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነ ታውቋል።

የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ድንገተኛ ቁጥጥሩን ያካሄደው ከዞኑ ፖሊስ ጋር በቅንጅት መሆኑ ተገልጿል።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

05 Dec, 06:14

708

የጎጎት መጽሐፍ ትረካ
https://youtu.be/MWZeyu5ddR8?si=ismhFugkwoOoRoBR