آخرین پست‌های Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ) (@guragez) در تلگرام

پست‌های تلگرام Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)
# ይህ የዘቢዳር ቻናል የሀገራችን ብሎም የጉራጌ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካ፣ ኪነ ጥበብ፣ ታሪክ፣ ርዕዮት እና ሁለንተናዊ መልክ የሚዳሰስበት የመገናኛ የመወያያ እና የመጦመርያ አውድ ነው!
4,341 مشترک
4,379 عکس
73 ویدیو
آخرین به‌روزرسانی 07.03.2025 11:07

آخرین محتوای به اشتراک گذاشته شده توسط Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ) در تلگرام

Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

12 Nov, 08:04

443

ማስታወቂያ

ከ1920ዎቹ ጀምሮ የእምድብር 1ኛና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት በጉራጌ እና አካባቢው ድንቅ ምሁራንን ያፈራ፤ አንጋፋ የትምህር ማእከል በመሆንም ለብዙዎች ባለውለታ የሆነ አይን ገላጭ የትምህርት እና የእውቀት ማእከል ነው፡፡

ይህ የትምህርት እና የታሪክ ተቋም አሁን ላይ በአገልግሎት ብዛት የተጎዳና የፈራረሰ በመሆኑ መሰረታዊ ጥገና ፈልጋል፡፡

በመሆኑም ይህንን የታሪክ እና እውቀት ማእከል የሆነው የእምድብር 1ኛና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት መልሶ ግንባታ ላማካሔድ የምክክር፣ የገቢ እና የትምህርት መርጃዎች ማሰባሰቢያ መድረክ ተዘጋጀ በመሆኑ የቀድሞ ተማዎች፤ በጎ ፍቀደኞች፣ የጉራጌ ተወላጆችና ወዳጆች፤ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ሕዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በተግባረ ዕድ ቴክኒክ ኮሌድ እንድትገኙ በበጎነት ተጋብዛችኃል፡፡

በትምህርት ልማት ላይ በጎ አሻራ ማኖር ለምትሹ እና የዚህ ት/ቤት ባለደራዎች ሁሉ በመርኃ ግብሩ ላይ በመገኘት ታሪካዊና ሞራላዊ ግዴታችሁን እንደትወጡ በአክብሮት እየጠየቅን በ0911169836 ወይም 0911879963 በመደወል የበለጠ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

የእምድብር 1ኛና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት መልሶ ግንባታ አስተባባሪ ኮሚቴ

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

11 Nov, 14:40

890

ፍርድ ቤቱ በጀምበር አብዶ መዝገብ ክስ በተመሰረተባቸው ተከሳሾች ምስክር ለመስማት ለታህሳስ 02 ቀጠረ

#ዘቢዳር_ቲዩብ ህዳር 02/2017 ዓ.ል

ከጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ጋር በተገናኘ በቡታጀራ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ለወራት በእስር ቆይተው በዐቃቤ ህግ ክስ የተመሰረተባቸው እነ ጀምበር አብዶ (21 ሰዎች) ቀደም ሲል ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ህዳር ሁለት የዐቃቤ ህግ ምስክር ለመስማት ቀጥሮ የነበረ ቢሆንም ዐቃቤ ህግ ምስክሮችን አሟልቶ ባለማቅረቡ ፍርድ ቤቱ ለታህሳስ 02 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ዐቃቤ ህግ 30 የሰው ምስክሮችን ለማቅረብ አስመዝግቦ የነበረ ቢሆንም በዛሬው ችሎት ማቅረብ የቻለው 3 የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት የነበሩ ፖሊሶችን ብቻ ነው።

ዐቃቤ ህግ ለቀጣይ ቀጠሮ ቀሪ ምስክሮችን አሟልቶ እንደሚያቀርብ የገለፀ ሲሆን ዳኛው በቀጣይ ታህሣሥ 02, 03 እና 04 የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ለመስማት ምስክሮች ለመገኘት ፍቃደኛ ካልሆኑ ፖሊስ አስሮ እንዲያቀርብ አዟል።

የተከሳሾች ጠበቃ አቶ ጌዲኦን ቦጋለ በበኩላቸው ዐቃቤ ህግ በቀጣይ ቀጠሮ ምስክሮችን አቅርቦ ምስክርነት ማስደመጥ ካልቻለ የተወሰኑ ደምበኞቻቸው ክሳቸውን እየተከታተሉ ያለው የዋስትና መብት ተነፍገው በማረሚያ ሆነው በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት መዝገቡን እንዲያቋርጠው ጠይቀዋል።

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

11 Nov, 03:37

1,005

ተገኝታለች
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

08 Nov, 16:41

1,479

#አፋልጉን
እህታችን አማረች ገብሬ በቀን 28/02/17 ከቤት እንደወጣች አልተመለሰችም ።ትንሽ የአእምሮ ህመም ያለባት ሲሆን በእለቱ ከምትኖርበት አሸዋ ሜዳ አካባቢ ከቤት ስትወጣ የለበሰችው ቡኒ ጃኬትና ጥቁር በነጭ ነጠብጣብ ጉርድ ቀሚስ ነበር።ይህች እህታችን ያያችሁ በዚህ ስልክ አሳውቁን። በ0911929247 / 0911041775
በተሰቦቿ።

መረጃውን ለሌሎች በማጋራት ተባበሩን።

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

08 Nov, 10:37

2,027

"የገጠር ኮሪደር" የኢትዮጵያ ገጠሮችን በጉራጌ ጀፎረ ዲዛይን ለመስራት ያለመ ይመስላል።
/በመሐመድ አብራር\

እውነት ከሆነና ከተሳካ ይህ እርምጃ በኢትዮጵያ ገጠሮች የአገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን አቅም ይኖረዋል።

የጀፎረን ጥበብ መቅዳት ግን ቀላል የሚሆን አይመስለኝም። ጀፎረ በዘመናት ሂደት ከማህበረሰብ ስልጣኔና ባህላዊ ህግ ጋር እያደገ የመጣ ልዩ የጉራጌ ገፅታ እንደመሆኑ በቀላሉ በሌሎች አካባቢዎች ይደገማል የሚል እምነት የለኝም። ከወጪ አንፃርም ቢሆን ቀላል ኢንቨስትመንት የሚጠይቅ አይሆንም። ከጉራጌ ጀፎረዎች አንዳንዶቹ በጥንት ዘመን ገደላማና የተሸረሸሩ ቦታዎች በአፈር በመሙላት የተስተካከሉ መሆናቸው ይታወቃል።

ጉራጌ በመንደሩ ሲኖር እንደማህበረሰብ በጋራ ሊኖረው ከሚፈልጋቸው ነገሮች አንዱ ጥሩ ጀፎረ ነው። ከመሬቱ የተሻለውን ለጀፎረው ይሰጣል። ለዚህም ነው ጉራጌ እርስ በርሱ ከሚፎካከርባቸው ነገሮችም አንዱ የጀፎረው ደረጃ የሆነው። ደረጃውን የጠበቀ ጀፎረ አንድን አካባቢ ስሙ ከፍ አድርገው ከሚያስጠሩ ነገሮች ዋነኛው ነው። ሰው እራሱ ሲጠራ የእንትን ጀፎረ ልጅ እየተባለ ይጠራል። በሁሉም ቤተ ጉራጌ አካባቢዎች በስፋት፣ ርዝመት፣ በአጥር ደረጃቸው፣ በማረፊያ ጥላቸው፣ ወዘተ… ስመ ጥር የሆኑ ጀፎረዎች እንዳሉ ልብ ይሏል።

እንደ ጉራጌ ጀፎረ ያለ ኮሪደር ሲታሰብ ከሞላ ጎደል ጀፎረን የፈጠሩትና ጠብቀው ያቆዩት የወልና የግል የአስተሳሰብና የህግ ማዕቀፎች መቅዳት ይጠይቃል። እነዚህ ደግሞ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በቀላሉ የሚቀዱ አይደሉም።

ጀፎረ ትልቅ ሃብት ነው፤ የችግኝ እርሻም የመኪና መንገድም አታድርጉት የምንለው በምክንያት ነው። ጀፎረ የሚዳሰስ፣ የሚታይ ቋሚ ቅርስ ነው። የጉራጌን መንደር ልዩ መገለጫ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ስልጣኔ እየጨመረ በመጣ ቁጥር ተፈላጊነቱና ዋጋው እያደገ የሚሄድ ትውልድና ዘመን ተሻጋሪ የወል ሃብት ነው።

ለመሆኑ ጀፎረን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ተጀምሮ የነበረው እንቅስቃሴ ከምን ደረሰ? ፎቶው ከጉራጌ ክልል ነው!

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

06 Nov, 06:58

1,764

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን በዱግዳ ወረዳ የተገደሉና ቤት ንብረታቸው የወደመባቸው ተጎጂዎች ስም ዝርዝር

በኩሬ ጋሌ ቢጢሰና ደርባ አካባቢ ቤትና ንብረት ብቻ የወደመባቸው ሰዎች ዝርዝር

ሙላቱ ሳሙኤል፣ ተዘከረኝ ሳሙኤል፣ አቡ ሃብቴ፣ የሟች ታሪኩ መንግስቱ ቤት፣ ጥላሁን ከበደ፣ ፎሊስ አርጎ፣ ቦጋለ ፈለቅ፣ አቡ ወልዱ፣ ዱቱ ጉርሜሳ፣ ዘነበ ጉርሜሳ፣ የሟች ማሩ ገብረሰምበት ቤት፣ መቻል አሰፋ፣ ጃርሶ ሲማ፣ አድማሱ አብሹ፣ ደረጀ አብሹ፣ ተስፋዬ አብሹ፣ ኑሬ አብሹ፣ ሲሳይ ወልዱ፣ ኩርፋ ሃዋስ፣ ሃብታሙ ማቶ፣ ደጂ ሞላ፣ ሞላ ጃምቦ፣ አለማሁ ነጋሽ፣ መሰለ ነጋሽ፣ ተሙኔ ገላሼ፣ ብርዞ ፈይሳ፣ በላቸው ማቶ፣ ሞላ ኪዳኔ፣ ምትኩ ወገኔ፣ ለሚ ኢሬሳ፣ ወርጂ ጂማ፣ አሰፋ ዶሬ፣ ታደለ መቻል፣ ጌታቸው ወልዴ፣ አበጋዝ በዳሳ ፎሌ፣ ጉታ በዳሶ፣ አቡ ትላሁን፣ መላኩ ዘርጋ፣ መቴ ኦብሴ፣ ሶሬሳ መቴ፣ አባቤ ሞላ፣ ጋዲሳ አባቤ፣ አለሙ ሶሬሳ፣ አደባይ ሶሬሳ፣ ብርሃኑ መኮንን፣ ስለሺ መኮንን፣ ዘነበ ስለሺ፣ አቡሌ ሰጤ፣ ሶሬሳ ባቲ

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

05 Nov, 17:33

2,018

በምስሉ ላይ የሚታየው ወንድማችን ሙፍቲህ አህመድ ፊሊዶሮ ቤሮ ሰፈር መታወቂያውን እቤት ውስጥ ጥሎ ጠፍቶብናል። ሙፍቲህ የአእምሮ ህመምተኛ ነው። ለአላህ ብላችሁ ይሄን መረጃ በማሰራጨት ተባበሩን። አይቼዋለሁ ወይም ያለበት አውቃለሁ የሚል ሰው ካለ በ0912634651/0953441764 እንድተሳውቁን በአላህ ስም እንጠይቃቸዋለን።
ፈላጊ ቤተሰቦቹ

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

05 Nov, 17:00

1,846

የመርካቶና የመርካቶ ነጋዴዎች አጭር ታሪክ
/መላኩ ይርዳው/

የመርካቶ ምስረታ መነሻው የፋሺስት #ጣልያን ወረራ ነው፡፡ ጣልያኖች ኢትዮጵያን በወረሩበት ወቅት (በ1928 ዓ.ም) ነጭና ጥቁር ተቀላቅሎ እንዳይገበያይ በመፈለግ ለራሳቸውና ለሌሎች ነጮች የሚሆን የገበያ ማዕከል ፒያሳ፣ አራት ኪሎና ካዛንችስ ላይ ሲመሰርቱ ለጥቁሩ (ኢትዮጵያዊው) ማህበረሰብ አዲስ ከተማ ተብሎ በሚጠራው ጫካ በነበረ ስፍራ መርካቶ ኢንዲጂኖ በሚል ስያሜ አዲስ የገበያ ማዕከል መሰረቱ፡፡ መርካቶ ማለት በጣልያንኛ ገበያ ማለት ነው፡፡

በወቅቱ ሀገራችን ውስጥ ንግዱን የተቆጣጠሩት ጣልያኖች፣ አረቦች፣ የመኖች፣ አርመኖችና ህንዶች የበነሩ ቢሆንም ከውጭ ነገዴዎቹ ስር ሆነው የሚሰሩና የራሳቸው ንግድ የነበራቸው ጥቂት ጉራጌዎች ነበሩ፡፡ #ጉራጌዎቹ በአብዛኛው የተሰማሩት ልብስ ስፌት ላይ ሲሆን ከጅምላ አከፋፋይ የውጭ ዜጋ ነጋዴዎች ሸቀጥ እየተረከቡ የሚቸረችሩም እንደነበሩ ታሪክ ያስረዳል፡፡

ጣልያን #ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ከእንግሊዝ ጦር ጋር በመተባበር ከሀገር ካስወጡትና ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ወደ ሀገር ተመልሰው መንግስት ከመሰረቱ በኋላ በከተማው ህዝቡን የሚፈልገውን ሸቀጥ የሚያቀርቡና አገልግሎት የሚሰጡ በቂ ሱቆችና የአገልግሎት ማዕከላት ስላልነበሩ 75 ወጣት ኢትዮጵያዊያን ተመልምለው ሱቅ በደረቴ እና ሊስትሮ እንዲሰሩ ተደረጉ፡፡

በዚያ ዘመን በአብዛኛው የሀገራችን ህዝብ እንዲህ አይነት ስራዎችም ሆነ አጠቃላይ የንግድ ስራ እንደ ነውር ይታይ ስለነበር ሀሳቡን ተቀብለው ወደ ስራ የገቡት አብዛኞቹ ጉራጌዎች ነበሩ፡፡ ከነዚህ ምልምሎች ውስጥ በኢትዮጵያ የአንተርፕረነርሺፕ ታሪክ ትልቁን የማዕዘን ድንጋይ ያስቀመጡት ቀኝ አዝማች #ተካ_ኤገኖ ይገኙበታል፡፡

በ1928 ዓ.ም በጣሊያኖች ሀሳብ የተመሰረተው መርካቶ መነሻ ሀሳቡ የጣልያኖች ቢሆንም ከምስረታው እስከ እድገቱ የጉራጌዎች የእጅ ስራ ውጤት ነው፡፡ በጣልያን ወረራ ዘመን (1928-1933) ከመርካቶ #ነጋዴ|ዎች በቀር ገንዘብ የሚያንቀሳቅስ የሀገሬው ሰው እምብዛም ስለ ነበር በወረራው ወቅትም ሆነ ጣሊያን ከሀገራችን ከወጣ በኋላ ዳግም ወደ መንበሩ የተመለሰው የጃኖ ሆይ መንግስት መሰረቱ እስኪጸና ሀገሪቷ ለሚያስፈልጋት ነገር ሁሉ እጇን የምትዘረጋው ወደ መርካቶ ነበር፡፡

ሀሪቷ በፋሺስት ጣሊያን ወረረራ ስር በነበረችበት ወቅት የመርካቶ ነጋዴዎች ገንዘብ እያዋጡ በየጫካው እየተዋደቁ ለነበሩ አርበኞች ይልኩ ነበር፡፡ ጣልያን ተወግዶ #ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ከስደት ከተመለሱም በኋላ ለመንግስት ማቋቋሚያ ገንዘብ ይሰጡ ነበር፡፡ ለቤተ-መንግስት ምንጣፍ ከማቅረብ አንስቶ ለጦር ሰራዊቱ ለሁለት ዓመት ደሞዝ የከፈሉት የመርካቶ ነጋዴዎች እንደ ነበሩ ታሪክ ከትቦታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከጣልያን ወረራ በኋላ ወደ መንበሩ የተመለሰው የጃኖ ሆይ መንግስት ከነዚህ ባለሀብቶች ለበርካታ ዓመታት ገንዘብ ይበደር ነበር፤ ሂደቱም አባ ሀና የተባሉ ሰው ያስፈጽሙት እንደ ነበር ተጽፈፏል፡፡

#ጥበቡ_በለጠ በሰራው አንድ ዶክመንተሪ ላይ ‘‘የመርካቶ ነጋዴዎች በፋሺስት ወረራ ወቅትና ከወረራው በኋላ ስርዓተ-መንግስቱ እስኪጠናከር ሀገራቸውን በገንዘብ እየደጎሙ ሀገር ያቆዩ ባለታሪኮች እንደሆኑ ዜና ገድላቸው ያወሳል፡፡’’ ይላል፡፡

የመርካቶና የመርካቶ ነጋዴዎች ታሪክ ‘‘ከእንጦጦ ሀሙስ ገበያ እስከ መርካቶ’’ በተሰኘው የብርሃኑ ሰሙ መጽሐፍ በጥልቀት ተጽፏል፡፡ ከዚህ ባሻገር የአዲስ አበባ #ዩኒቨርሲቲ የድህረ-ምረቃ መመረቂያ ጥናታቸውን ከመርካቶ ተነስተው በ50ዎቹ 800 ሰራተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራውን፣ የኢትዮጵያ መንግስት ከአለም #ባንክ ብድር እንዲያገኝ ለናሙና ያሳየው የነበረውን ትልቅ የአግሮ ኢንደስትሪ ድርጅት የመሰረቱት ቀኝ አዝማች ተካ ኤገኖንና የመርካቶ አባት በመባል የሚታወቁትን ቀኝ አዝማች ሞላ ማሩን ታሪክ ላይ የሰሩት የታሪክ ተመራማሪው አቶ መኮንን ተገኝ ታሪኩን ከትበው አስቀርተውታል፡፡

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

05 Nov, 15:01

1,502

እናትና ልጅ በእሳት አደጋ ሕይወታቸውን ተነጠቁ።
===============================

በሸገር ከተማ ወለቴ ዘጠኝ ቁጥር መታጠፊያ በተለምዶ ሃረር ዳቦ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 ዓ.ል ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ በንግድ ቦታዎች ላይ በተነሳ ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ አደጋ አንድ ህፃን ልጅ እና እናት ተቃጥለው ሕይወታቸው ሲያልፍ በቆርቆሮ/ኮንቴነር የተሰሩ ሱቆች ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል።

እናት ውስጥ የቀረችውን ልጇን ልታወጣ በገባችበት እሳቱ እዛው አስቀርቷታል።

እሳቱ ሳይዛመት እና የበለጠ ጉዳት ሳያደርስ በአካባቢው ማህበረሰብ ርብርብ መቆጣጠር ተችሏል።

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)

05 Nov, 07:25

1,814

ዳንኤል ታደሰ

ዳንኤል ታደሰ ከእናቱ ከወ / ሮ ፋንታዬ ሩፋኤል እና ከአባቱ ከፊታውራሪ ታደሰ ማርቆስ በአዲስ አበባ ከተማ ታኅሳስ 23 ቀን ፣ 1934 .ም . ተወለደ:: የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን የተከታተለው አዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን እና እንዲሁም ሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት ነበር። ዳንኤል፣ በሊሴ ገብረማርያም ቆይታው ከክፍሉ በተደጋጋሚ ከፍተኛውን ውጤት በማምጣት የትምህርት ቤት ጓደኞቹ ያስታውሱታል ።

በመስከረም 1952 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ፣ በፈረንሳይ የትምህርት ሥርዓት ባካሎሪያ የተባለውን ፈተና በአጥጋቢ ውጤት ካለፈ በኋላ የነጻ የትምህርት ዕድል አግኝቶ ወደ ፈረንሣይ አገር አቀና። በዚያን ወቅት የ18 ዓመት ወጣት ነበር ።

በመጀመሪያ ትምህርቱን የተከታተለውም ፣ ፈረንሳይ በሊዮን ከተማ በሚገኘው የሊዮን የተግባር ሳይንስ ኢንስቲትዩት ነበር። በዚህ ተቋም ትምህርቱን ለአራት ዓመታት ከተከታተለ በኋላ በ1955 ዓ.ም. በምህንድስና የባችለር ኦፍ ሳይንስ ዲግሪውን ተቀበለ። ለትምህርት በነበረው ፍቅር የተነሳ የምህንድስና ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ ፓሪስ በመሄድ ብዙ እውቅ የአገር እና የድርጅት መሪዎችን በማፍራት በሚታወቀው የፖለቲካል ሳይንስ ብሔራዊ ኢንስቲትዩት በመግባት ትምህርቱን ለሁለት ዓመታት ከተከታተለ በኋላ በኢኮኖሚክስ ሳይንስ ተጨማሪ ዲግሪ አገኘ ።

በፓሪስ ቆይታው ወቅት በአውሮጳ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር ውስጥ ኃይሌ ፊዳን ከመሳሰሉ በንቃት ከሚሳተፉት የፖለቲካ ግንባር ቀደም ተማሪዎች መሃል አንዱ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በፓሪስ የአፍሪካ ተማሪዎች ፌዴሬሽን ውስጥ የጎላ ሚና ነበረው። በዚህም ተሳትፎው በኋላ የጊኒ እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መሪ ለመሆን ከበቃው አልፋ ኮንዴና ፣ እንዲሁም ከእውቁ የሴኔጋል የታሪክ ተመራማሪ ከሼክ አንታ ዲዮፕ ጋር እጅግ የቅርብ ትውውቅ እና ጓደኝነት አፍርቶ ነበር።

በ1958 ዓ.ም. ዳንኤል በፓሪስ የነበረውን ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ወደ አገሩ ተመልሶ በመጀመሪያ በኢትዮ ጂቡቲ የምድር ባቡር ኩባንያ ፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲሁም የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ በሙያው አገልግሏል። ከጥቅምት 1961 እስከ ግንቦት 1961 ዓ.ም. ፈረንሣይ አገር ተጨማሪ ስልጠና ወስዷል ። ዳንኤል፣ በነሐሴ 1960 ዓ.ም. የተቋቋመውን የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄን ( መኢሶን ) ከመሰረቱት ጠንሳሽ አባላትና መሪዎች መሃል አንዱ ነበር።

ከየካቲት 1966 ዓ.ም. ሕዝባዊ አብዮት በፊትና ከዚያም በኋላ በአገር ቤት የመኢሶንን የኅቡዕ እንቅስቃሴዎች በማቀናበር እና በግንባር ቀደምነት በመምራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው። በ1966 ዓ.ም. በኀቡዕ ይበተኑ የነበሩ ጽሕፎችን በመጻፍና አርትኦት በማድረግም ይሳተፍ ነበር። በተለይም “ ሽሙጥ ” ተብላ ትታወቅ የነበረችውና በድብቅ “እንዳመቻት” የምትበተን ተወዳጅ የፖለቲካ አቃቂር ጋዜጣ አዘጋጅም ነበር።

ዳንኤል በየካቲት 1968 ዓ.ም የከተማ ልማት እና ቤቶቸ ሚኒስትር ሁኖ ተመደበ። የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን በሚንስትርነት ከመቀላቀሉ በፊት የወጣው የከተማ ቦታ እና ትርፍ ቤት ዓዋጅ መሠረታዊ ቸግሮቸ እንደነበሩበት በመገንዘብ ጉድለቶቹን ለመቅረፍ ዳንኤል ያቀረበውን የማሻሻያ ረቂቅ ዓዋጅ ሥልጣን ላይ የነበረው የደርግ መንግሥት ሳይቀበለው ቀረ።

በነሐሴ 1969 ዓ/ም አጋማሸ መኢሶን ሂሳዊ ድጋፍ የሚለውን የትግል መሥመር ትቶ የታውቁ መሪዎቹን እና አባላቱን ኅቡዕ ማስባት ሲገደድ ዳንኤልም የቤቶች እና የከተማ ልማት ሚስትርት ሥልጣኑን፣ ባለቤቱን እና ሦስት ጨቅላ ልጆቹን ትቶ ከአዲስ አበባ ብዙ ሳይርቅ ሙሎ ወረዳ ለጊዜው በስውር እንዲቀመጥ ተወሰነ። እርሱ በኅቡዕ የነበረበት ስፍራ፣ የመኢሶን ጠቅላይ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ የነበረው ዶ/ር ከበደ መነሻ፣ ምትኩ ተርፋሳ፣ ደንቢ ዲሣሣ እና ደምበል አየለ ይገኙብት ነበር።

ነሐሴ 30 ቀን 1969 ዓ/ም ዳንኤል እና ጓዶቹ ያሉበት ስፍራ በደርግ የፀጥታ ሃይሎች ተከቦ እጅ እንዲሰጡ ሲጠየቁ ዳንኤል እና ዶ/ር ከበደ ከእነርሱ ወጣት የነበሩትን እና ያነሰ ድርጅታዊ ኃላፊነት የነበራቸውን ጓዶች አሰናብተው፣ እነርሱም ተሰነባብተው በያዙት መሣሪያ እራሳቸውን ሰዉ።

ይህ የግል ምቾታቸውን ትተው ለድርጅቱ ዓላማ መሳካት ከከፈሉት ዋጋ በተጨማሪ በሕይወታቸው የከፈሉት የመጨረሻው መስዋዕትነት ነበር።
ዳንኤል ለአገር የሚጠቅም እምቅ የአዕምሮ ጉልበትና ልምድ ነበረው። ቢሆንም ግን ይህቺ ሕዝቦቿ ከችግርና መከራ ተላቀው በደስታ እንዲኖሩባት የሚመኛትን አገሩን ሳያይ በለጋ የ35 ዓመት እድሜው ተቀጠፈ።

ዳንኤ ብዙ ስቃይ እና ሰቆቃ ከደረሰባትና ዛሬ በሕይወት ከምትገኘው የትዳር አጋሩ ከወ/ሮ እንጉዳይ በቀለ ሁለት ወንድ ልጆች እና አንዲት ሴት ልጅ እፍርቷል።

የመኢሶን ሰማዕታት
በጓዶቻቸው የተዘጋጀ
ገፅ70-72

የአባቱን ታታሪክ በጨረፍታ በዚህ ማስፈንጠሪያ ታገኙታላችሁ 👇🏽

https://www.facebook.com/share/vxQb23jDALgRyoK6/?mibextid=WC7FNe

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ