Latest Posts from Farankaa - ፈረንካ (@farankaa) on Telegram

Farankaa - ፈረንካ Telegram Posts

Farankaa - ፈረንካ
The primary goal of this page is to enhance the financial literacy of Ethiopians by offering valuable insights on investment, banking, insurance, capital markets, and taxation.
1,818 Subscribers
276 Photos
2 Videos
Last Updated 09.03.2025 03:43

Similar Channels

Ahmed Habib Alzarkawi
18,713 Subscribers
Capitalethiopia
16,638 Subscribers
Ethiopian Business Review
3,351 Subscribers

The latest content shared by Farankaa - ፈረንካ on Telegram

Farankaa - ፈረንካ

07 Mar, 13:04

313

ማህበራዊ ግዴታን እንደማስታወቂያ...

ተቋማት ከትርፍ ባሻገር በተለያየ መንገድ ማህበራዊ ግዴታቸውን መወጣታቸው፣ በተለያዩ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ፣ በድርቅ ምክንያት፣ በድህነት ምክንያት ለተቸገሩ ወገኖች ከትርፋቸው ቀንሰው ማካፈላቸው፣ ለማህበረሰቡ መልሰው መስጠታቸው የሚያስመሰግናቸው ተግባር ነው።

ይሁንና ይሄንኑ ዜና ለማስታወቂያ ለመጠቀም እርዳታ የሚሰጣቸውን ግለሰቦች ፎቶግራፍ እያነሱ እና እየቀረጹ በየማህበራዊ ድረገጻቸው ማካፈላቸው በተለይም በረመዳንና በወርሀ ፋሲካ የጾም ወራት፣ ልግስና እና በድብቅ መስጠት በሚሰበክባቸው ወራት ሁኔታው ከማስታወቂያ ይልቅ ማሳቀቂያ ስለሚሆን እንዲሁም ዓላማውን ያልመታ የማስታወቂያ ሙከራ ከመሆን የዘለለ ትርፍ ስለማያስገኝላቸው ከእዚህ ድርጊት ቢታቀቡ ብዬ ቀና ምክሬን አስተላልፋለሁ።
Farankaa - ፈረንካ

06 Mar, 15:58

453

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዋጅ
Farankaa - ፈረንካ

04 Mar, 09:50

676

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ የተሰጡ ብድሮች ላይ የብድር ወለድ ጭማሪና ቅናሽ አድርጓል።

ማስታወሻ፣

ባንኩ...

📌የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤት ላይ ምንም ዓይነት የወለድ ጭማሪ አላደረገም (ይሄ ያስመሰግነዋል።)

📌 የእርሻ ብድር ላይ የወለድ ቅናሽ አድርጓል (ይበል የሚያሰኝ ነው)

📌 በኤክስፓርት ብድሮች ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አድርጓል (ይሄ ባንኩ ደንበኞቹን በሌሎች ባንኮች ሊያስቀማው ይችላል)

በአብዛኞቹ ብድሮች ላይ የተደረገው ጭማሪ 1% መሆኑ ባንኩ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረጉን የሚያሳይ ነው።
Farankaa - ፈረንካ

03 Mar, 05:26

741

የህይወት አሳዛኝ እውነታ...

ጠማሞች አንዳችም ሳያገኛቸው ቀጥተኞች ሁሌም እንደተቀጠቀጡ ይኖራሉ።

መልካም ቀን!
Farankaa - ፈረንካ

02 Mar, 09:51

726

የሥራ እድል በኢቲዮ ካፒታል ሶሉሽንስ /ECS/
Farankaa - ፈረንካ

02 Mar, 08:09

620

A legacy of strength and Unity, Adwa!

የኢትዮጵያውያን የጥንካሬና የአንድነት ቅርስ፣ አድዋ!

ለመላው ኢትዮጵያውያን፣ ለመላው ጥቁር ህዝቦችና ጭቁን ህዝቦች እንኳን ለአድዋ የድል በዓል አደረሳችሁ!
------

የምስል ምንጭ፣ Artificial Intelligence
Farankaa - ፈረንካ

01 Mar, 07:31

716

የአዲስ አበባ ገቢዎች አስተዳደር የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎችን የታክስ ማሳወቅና ክፍያን በተመለከተ አዲስ ህግ አውጥቷል። በአዲሱ ህግ መሰረት ግብር ከፋዮች በስማቸው ወይም በተቋማቸው ስም በእንግሊዝኛ የፊደል ቅደም ተከተል መሰረት ክፍያቸውን እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ሲሆን ይሄንን ማድረግ ያስፈለገው በወር መጨረሻ ላይ የሚከሰት የኔትወርክ እና የስራ መጨናነቅን ለመቀነስ እንደሆነ አስተዳደሩ አሳውቋል።

በእዚሁ መሠረት...

📌ስማቸው/ስያሜአቸው ከእንግሊዝኛ ፊደል ኤ/A እስከ ጂ/G የሚጀምር ግብር ከፋዮች ሪፖርታቸውን ወር በገባ በመጀመሪያ ሳምንት ያሳውቃሉ።

📌ስማቸው/ስያሜአቸው ከእንግሊዝኛ ፊደል ኤች/H እስከ ኤን/N የሚጀምር ግብር ከፋዮች ሪፖርታቸውን ወር በገባ በሁለተኛው ሳምንት ያሳውቃሉ።

📌ስማቸው/ስያሜአቸው ከእንግሊዝኛ ፊደል ኦ/O እስከ ቲ/T የሚጀምር ግብር ከፋዮች ሪፖርታቸውን ወር በገባ በሶስተኛ ሳምንት ያሳውቃሉ።

📌ስማቸው/ስያሜአቸው ከእንግሊዝኛ ፊደል ዩ/U እስከ ዜድ/Z የሚጀምር ግብር ከፋዮች ሪፖርታቸውን ወር በገባ በአራተኛው ሳምንት ያሳውቃሉ።

አስተዳደሩ በተቀመጠላቸው የግብር አከፋፈል ቅደም ተከተል መሠረት የማይከፍሉ ግብር ከፋዮች ላይ ቅጣት እንደሚጥል አሳውቋል።
Farankaa - ፈረንካ

26 Feb, 09:12

874

ትላንት ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 60 ሚሊዮን ዶላር ለመሸጥ ባዘጋጀው የውጪ ምንዛሪ ጨረታ ላይ 27 ባንኮች ተሳትፈው ባንኮች በአማካይ አንዱን ዶላር በ135.6185 ከብሔራዊ ባንኩ ለመግዛት ዋጋ አስገብተዋል። አስቡት እንግዲህ ይህ አማካይ ዋጋ ነው። ከፍ ያለም ዝቅ ያለም የጨረታ ዋጋ ያስገባ ባንክ አለ።

ዛሬ ላይ የትልልቅ ባንኮችን የውጪ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ ዋጋ ለመመልከት የሞከርኩ ሲሆን አብዛኞቹ ባንኮች በአማካይ አንዱን ዶላር 125 ብር ገደማ ገዝተው በ127 ብር አካባቢ ይሸጣሉ።

ይሁንና በ135 ብር የገዙትን ዶላር በ127 ብር መሸጣቸው በየትኛውም የሂሳብ አመክንዮ ሊገባኝ ያልቻለ ነገር ነው። የሆነ የተዘበራረቀ ነገር አለ፣ ማንም ሊያስረዳኝ ያልቻለ።

ማነው 20 ሺህ ብር የገዛውን በግ በነጋታው 15 ሺህ ብር የሚሸጥ?

ግራ የገባ ነገር!
Farankaa - ፈረንካ

26 Feb, 05:18

761

አንዳንድ ነገሮች ብዙ ያስገርሙኛል...

መንግስት "ግብር በየወሩ ማስከፈል የጀመርኩት ግብር ከፋዮች በኦንላይን እንዲያሳውቁ አቅም ስለፈጠርኩ ነው" ካለ ወራት ተቆጥረዋል። ወፍ የለም። ከወሬ የዘለለ አቅምም ያለ አይመስልም።

በጠዋቱ የግብር ክሊራንስ ለመውሰድ በአዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በአንዱ ተገኝቻለሁ።

የክሊራንስ ፎርሜን ሞልቼ የሰጠኋት፣ ሰው ለማናገር እንኳ የምትጠየፍ የቅ/ፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኛ "ከአምና ጀምሮ የከፈልከውን የግብር ደረሰኝ ይዘህ ናና ዳታ ቤዝ ላይ አስገቡልኝ በላቸው።" አለች - እየተዘባነነች።

"ዳታ ቤዝ ላይ የከፈልኩትን ግብር በወቅቱ ማስገባት የማን ኃላፊነት ነው?" - ስል ጠየቅኩ።

"እዚህ የተቀመጥኩት ለጭቅጭቅ አይደለም። የግብር ክፍያ ማስረጃ አምጣና ዳታ ቤዙ ላይ እንዲያስገቡልህ አድርግ" - አለች በቁጣና በግልምጫ ታጅባ። ቁጣዋን ላየ ዳታ ቤዙ ላይ መረጃውን በትክክል capture የማድረግ ኃላፊነት የእኔ፣ የግብር ከፋዩ ይመስል ነበር።

በንዴት በግኜ መልስ ልሰጣት ቀና ስል ከጀርባዋ በኮምፒውተር ተተይቦ ግድግዳ ላይ ከተለጠፈ፣ "ግብር ከፋዮቻችን ንጉሶቻችን ናችሁ!" ከሚል ጥቅስ ጋር ተፋጠጥኩ። (ብዙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ እንዲህ አይነት በየግድግዳው፣ በየካውንተሩ ላይ የተለጠፉ ጥቅሶች ገጥመውኛል፣ ነገሩ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ሆነ እንጂ)


"ወገኞች!" - አልኩና በሆዴ...

"ለማንኛውም አስጽፈሽ የለጠፍሽው ጥቅስ እውነታውን ስለማያሳይ 'ግብር ከፋዮቻችን ማላገጫዎቻችን ናቸው' በሚል ቀይሪው" - ብያት በመንግስት እራሴን በቴክኖሎጂ አዝምኛለሁ የሚል ውሸት ውስጤ እየበገነ ከአምና ጀምሮ የከፈልኩት የግብር ደረሰኝ ለመሰብሰብ ወደ ቢሮዬ ተመለስኩ።
Farankaa - ፈረንካ

24 Feb, 07:08

750

በእርጋታ ያንብቡ...

🌼በመሶባችሁ እንጀራ ካላችሁ፣ ሰውነታችሁን መሸፈኛ ልብስ ካላችሁ፣ እራሳችሁን የምታሳርፉበት እና የምትተኙበት መጠለያ ካላችሁ በዓለም ላይ ካሉ 75% ሰዎች የተሻለ ሀብታሞች ናችሁ።

🌼በኪስ ቦርሳችሁ ገንዘብ ካላችሁ እና ያሻችሁ ቦታ መሄድ የምትችሉ ከሆነ በዓለም ላይ ካሉ 18% እጅግ ሀብታሞች መካከል ናችሁ።

🌼ዛሬን በህይወት ካላችሁ እና ጤናማ ከሆናችሁ ሳምንቱን ይህቺን ዓለም ከሚሰናበቷት 1 ሚሊዮን ሰዎች የተሻለ ተባርካችኋል።

🌼ይሄንን መልእክት አንብባችሁ ከተረዳችሁ በዓለማችን ከሚኖሩ 3 ቢሊዮን የሚጠጉ ማንበብ የማይችሉ እና ዓይነ-ስውራን የተሻለ እድለኞች ናችሁ።

ህይወት ሁሌም የምናጉረመርምባት አይደለችም። ህይወት ሌሎች በሺህዎች በሚቆጠሩ የምናመሰግንበት እና የምንደስትባቸው ነገሮችን የተሞላች ናት።

ምንጭ ኢንተርኔት