ክፍል 1
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው።
ቂብላ قبلة ማለት ቋንቋዊ ትርጉሙ በአጭሩ "አቅጣጫ" "direction" ማለት ሲሆን!
ሃይማኖታዊ ትርጉሙ ደግሞ ፊታችንን ወደ "አንድ አቅጣጫ" በመዞር "ለ-አምላካችን ለ-አላህ" አምልኮትን "ውዳሴን" የምናቀርብበት መንገድ ነው።
አምላካችን አሏህ ለሁሉም ኡማህ ሶላታቸውን ሲሰግዱ ፊቶቻቸውን የሚያዞርበት ቂብላ direction አድርጎላቸዋል።
وَلِكُلٍّۢ وِجْهَةٌ هُوَ مُوَلِّيهَا ۖ
ለሁሉም እርሱ (በስግደት ፊቱን) የሚያዞርባት አግጣጫ አለችው፡፡
(📗2 : 148)
:-እኛ ሙሥሊም ወደ ካዕባህ ፊታችን አዙረን መስገድ ከመጀመራችን በፊት ፍልስጤም ውስጥ ወዳለው ወደ መስጂደል አል-አቅሷ ነበር የምንሰግደው።
عَنِ الْبَرَاءِ، رضى الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم صَلَّى إِلَى بَيْتِ الْمَقْدِسِ سِتَّةَ عَشَرَ شَهْرًا أَوْ سَبْعَةَ عَشَرَ شَهْرًا
"በራዕ (ረ•ዓ) እንደተረከው ነቢዩ (ሰዐወ) ወደ "መስጂደል አቅሷ" "ለ-አስራ ስድስት" ወይም "ለ-አስራ ሰባት" ወራት ሰግደው ነበር።
{📗ቦኻሪ መጽሐፍ 65 ሐዲስ 13}
:-ከዛም አምላካችን አሏህ ወደ መስጂደል አቅሷ የነበረውን የስግደት አቅጣጫ ወደ ከዕባህ እንድናዞር አዘዘን።
قَدْ نَرَىٰ تَقَلُّبَ وَجْهِكَ فِى ٱلسَّمَآءِ ۖ فَلَنُوَلِّيَنَّكَ قِبْلَةًۭ تَرْضَىٰهَا ۚ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ ۚ وَحَيْثُ مَا كُنتُمْ فَوَلُّوا۟ وُجُوهَكُمْ شَطْرَهُۥ ۗ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ لَيَعْلَمُونَ أَنَّهُ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّهِمْ ۗ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا يَعْمَلُونَ
የፊትህን ወደ ሰማይ መገላበጥ በእርግጥ እናያለን፡፡ ወደምትወዳትም ቂብላ እናዞርሃለን፡፡ ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ (ወደ ካዕባ) አግጣጫ አዙር፡፡ የትም ስፍራ ብትኾኑም (ስትሰግዱ) ፊቶቻችሁን ወደርሱ አግጣጫ አዙሩ፡፡
(📗2 : 144)
እኛ ሙስሊሞች ወደ ካዕባህ ፊታችን አዙረን የምንሰግደው "አላህ ስላዘዘን ነው" እንጂ ካዕባህ ይጠቅመናል ወይም ይጎዳናል ብለን አይደለም። ሐጀሩል አስወድ ጥቁር ድንጋይ ነው በራሱ መጥቀምም ሆነ ጉዳት ማድረስ አይችልም።
عَنْ عَابِسِ بْنِ رَبِيعَةَ، عَنْ عُمَرَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّهُ جَاءَ إِلَى الْحَجَرِ الأَسْوَدِ فَقَبَّلَهُ، فَقَالَ إِنِّي أَعْلَمُ أَنَّكَ حَجَرٌ لاَ تَضُرُّ وَلاَ تَنْفَعُ، وَلَوْلاَ أَنِّي رَأَيْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يُقَبِّلُكَ مَا قَبَّلْتُكَ
ዓቢስ ኢብኑ ረቢዓህ (ረ•ዓ) እንደተረከው ዑመር ወደ ካዕባህ መጥቶ ሐጀሩል አስወድን ሳመውና "አንተ "የማትጠቅምም" "የማትጎዳም" ጥቁር "ድንጋይ" እንደሆንክ አውቃለሁ" ነቢዩ ሲስሙህ ባላይ ኖሮ ባልሳምኩህ ነበር አለው።
{📗ቦኻሪ መጽሐፍ 25 ሐዲስ 83}
:-ባይብልም ላይ ቢሆን ወደ አንድ አቅጣጫ ዞሮ መስገድ የተለመደ ነው።
ወደ መረጥሃትም ወደዚህች ከተማና እኔም ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው ቢጸልዩ፣
ከማደሪያህ ከሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ ልመናቸውንም ተቀበል፤ ርዳቸውም።
(📗1 ነገሥት 8:48)
እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ አንተንም በመፍራት፣ *ወደ ተቀደሰው መቅደስህ እሰግዳለሁ።*
(📗መዝሙር 5:7)
ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ።
{📗መዝሙር 138:2)
እነዳዊትና ሰለሞን እንዲሁም በጊዜው የነበረው ሕዝብ ወደ አንድ አቅጣጫ ዞሮ መስገዱ ጣዖት አምልኮ ነበረን?
አይ እነርሱ እኮ ፊታቸውን ወደ ቤተ መቅደስ አዙረው ሰገዱ እንጂ የሰገዱት ለእግዚአብሔር ነው ለቤተ መቅደሱ አይደለም ካላችሁ!
እንግዲያስ እኛ ሙሥሊሞችም ሶላት ስንሰግድ ፊታችንን ወደ አንድ አቅጣጫ ወደ ካዕባህ አዙረን ስንሰግድ የምንሰግደው ለ-አሏህ ነው እንጂ ለካዕባህ እንዳልሆነ ተረዱ።
ኢንሻ አሏህ ይቀጥላል...
✍ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/ewnet_lehulum