أحدث المنشورات من እውነት ለሁሉ [truth for all] (@ewnet_lehulum) على Telegram

منشورات እውነት ለሁሉ [truth for all] على Telegram

እውነት ለሁሉ [truth for all]
ይህ ቻናል ዓላማው በማስረጃና በመረጃ በመታገዝ እውነትን ከውሸት በመለየት፣ በአላህ ፈቃድ በጨለማ የሚኖሩ ወገኖችን ብርሃን ወደሆነው ኢስላም መጣራት ነው።

قُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ

[ ሱረቱ ሰበእ - 49 ]
«እውነቱ መጣ፡፡ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም (ተወገደ)» በላቸው፡፡
2,968 مشترك
425 صورة
120 فيديو
آخر تحديث 09.03.2025 03:43

أحدث المحتوى الذي تم مشاركته بواسطة እውነት ለሁሉ [truth for all] على Telegram

እውነት ለሁሉ [truth for all]

02 Mar, 17:44

277

ቂብላ

ክፍል 1

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው።

ቂብላ قبلة ማለት ቋንቋዊ ትርጉሙ በአጭሩ "አቅጣጫ" "direction" ማለት ሲሆን!

ሃይማኖታዊ ትርጉሙ ደግሞ ፊታችንን ወደ "አንድ አቅጣጫ" በመዞር "ለ-አምላካችን ለ-አላህ" አምልኮትን "ውዳሴን" የምናቀርብበት መንገድ ነው።

አምላካችን አሏህ ለሁሉም ኡማህ ሶላታቸውን ሲሰግዱ ፊቶቻቸውን የሚያዞርበት ቂብላ direction አድርጎላቸዋል።

وَلِكُلٍّۢ وِجْهَةٌ هُوَ مُوَلِّيهَا ۖ
ለሁሉም እርሱ (በስግደት ፊቱን) የሚያዞርባት አግጣጫ አለችው፡፡
(📗2 : 148)

:-እኛ ሙሥሊም ወደ ካዕባህ ፊታችን አዙረን መስገድ ከመጀመራችን በፊት  ፍልስጤም ውስጥ ወዳለው ወደ መስጂደል አል-አቅሷ ነበር የምንሰግደው።

عَنِ الْبَرَاءِ، رضى الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم صَلَّى إِلَى بَيْتِ الْمَقْدِسِ سِتَّةَ عَشَرَ شَهْرًا أَوْ سَبْعَةَ عَشَرَ شَهْرًا

"በራዕ (ረ•ዓ) እንደተረከው  ነቢዩ (ሰዐወ) ወደ "መስጂደል አቅሷ" "ለ-አስራ ስድስት" ወይም "ለ-አስራ ሰባት" ወራት ሰግደው ነበር።
{📗ቦኻሪ መጽሐፍ 65 ሐዲስ 13}

:-ከዛም አምላካችን አሏህ ወደ መስጂደል አቅሷ የነበረውን የስግደት አቅጣጫ ወደ ከዕባህ እንድናዞር አዘዘን።

قَدْ نَرَىٰ تَقَلُّبَ وَجْهِكَ فِى ٱلسَّمَآءِ ۖ فَلَنُوَلِّيَنَّكَ قِبْلَةًۭ تَرْضَىٰهَا ۚ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ ۚ وَحَيْثُ مَا كُنتُمْ فَوَلُّوا۟ وُجُوهَكُمْ شَطْرَهُۥ ۗ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ لَيَعْلَمُونَ أَنَّهُ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّهِمْ ۗ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا يَعْمَلُونَ

የፊትህን ወደ ሰማይ መገላበጥ በእርግጥ እናያለን፡፡ ወደምትወዳትም ቂብላ እናዞርሃለን፡፡ ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ (ወደ ካዕባ) አግጣጫ አዙር፡፡ የትም ስፍራ ብትኾኑም (ስትሰግዱ) ፊቶቻችሁን ወደርሱ አግጣጫ አዙሩ፡፡
(📗2 : 144)

እኛ ሙስሊሞች ወደ ካዕባህ ፊታችን አዙረን የምንሰግደው "አላህ ስላዘዘን ነው" እንጂ ካዕባህ ይጠቅመናል ወይም ይጎዳናል ብለን አይደለም። ሐጀሩል አስወድ ጥቁር ድንጋይ ነው በራሱ መጥቀምም ሆነ ጉዳት ማድረስ አይችልም።

عَنْ عَابِسِ بْنِ رَبِيعَةَ، عَنْ عُمَرَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّهُ جَاءَ إِلَى الْحَجَرِ الأَسْوَدِ فَقَبَّلَهُ، فَقَالَ إِنِّي أَعْلَمُ أَنَّكَ حَجَرٌ لاَ تَضُرُّ وَلاَ تَنْفَعُ، وَلَوْلاَ أَنِّي رَأَيْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يُقَبِّلُكَ مَا قَبَّلْتُكَ‏

ዓቢስ ኢብኑ ረቢዓህ (ረ•ዓ) እንደተረከው ዑመር ወደ ካዕባህ መጥቶ ሐጀሩል አስወድን ሳመውና "አንተ "የማትጠቅምም" "የማትጎዳም" ጥቁር "ድንጋይ" እንደሆንክ አውቃለሁ" ነቢዩ ሲስሙህ ባላይ ኖሮ ባልሳምኩህ ነበር አለው።
{📗ቦኻሪ መጽሐፍ 25 ሐዲስ 83}

:-ባይብልም ላይ ቢሆን ወደ አንድ አቅጣጫ ዞሮ መስገድ የተለመደ ነው።

ወደ መረጥሃትም ወደዚህች ከተማና እኔም ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው ቢጸልዩ፣
ከማደሪያህ ከሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ ልመናቸውንም ተቀበል፤ ርዳቸውም።
(📗1 ነገሥት 8:48)
  
እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ አንተንም በመፍራት፣ *ወደ ተቀደሰው መቅደስህ እሰግዳለሁ።* 
(📗መዝሙር 5:7)

ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ።
{📗መዝሙር 138:2)

እነዳዊትና ሰለሞን እንዲሁም በጊዜው የነበረው ሕዝብ ወደ አንድ አቅጣጫ ዞሮ መስገዱ ጣዖት አምልኮ ነበረን?

አይ እነርሱ እኮ ፊታቸውን ወደ ቤተ መቅደስ አዙረው ሰገዱ እንጂ የሰገዱት ለእግዚአብሔር ነው ለቤተ መቅደሱ አይደለም ካላችሁ!

እንግዲያስ እኛ ሙሥሊሞችም ሶላት ስንሰግድ ፊታችንን ወደ አንድ አቅጣጫ ወደ ካዕባህ አዙረን ስንሰግድ የምንሰግደው ለ-አሏህ ነው እንጂ ለካዕባህ እንዳልሆነ ተረዱ።


ኢንሻ አሏህ ይቀጥላል...


ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/ewnet_lehulum
እውነት ለሁሉ [truth for all]

28 Feb, 17:24

357

ውድ የቻናላችን ተከታታዮች
🌙እንኳን ለተከበረው የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ!🌙

አላህ ረመዷንን በትክክል የምንጠቀምበት  ያድርገን!

🌴🍀💫🌙⭐️رمضان مبارك 🌴🍀💫🌙⭐️

🌴🍀💫🌙⭐️Ramadan Mubarak🌴🍀💫🌙⭐️

🌴🍀💫🌙⭐️ረመዷን ሙባረክ🌴🍀💫🌙⭐️
እውነት ለሁሉ [truth for all]

16 Feb, 10:07

640

▣የህፃናት ጋብቻ ክፍል ሁለት ▣

ክፍል 01 ላይ ገና ለአቅመ ሄዋን  ያልደረሰችን ሴት ልጅ ማግባት ላይ የኡለሞች ልዩነት እንዳለበት እና ትክክለኛው አቋም አንድ አባት ሴት ልጁ ለአቅመ ሄዋን ሳትደርስ ያለ ፍላጎቷ እና ያለ ውዴታ ሴት ልጁን መዳር አይፈቀድም] የሚል እንደሆነ እና ይቻላል ያሉ ኡለሞች የጠቀሱት የዓኢሻህ ጋብቻ ማስረጃ ሊሆንላቸው እንደማይችል አይተን ነበር።
➸ ዛሬ ክፍል ሁለት ላይ ደግሞ ገና ያልደረሱ ህፃናትን ማግባት ይቻላል ብለው ያመጡትን ማስረጃ እንይና መልስ እንስጥበት።
አላህ እንዲህ ይላል👇
وَاللَّائِي يَئِسْنَ مِنَ الْمَحِيضِ مِن نِّسَائِكُمْ إِنِ ارْتَبْتُمْ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَاثَةُ أَشْهُرٍ وَاللَّائِي لَمْ يَحِضْنَ ۚ وَأُولَاتُ الْأَحْمَالِ أَجَلُهُنَّ أَن يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ
*"እነዚያም ከሴቶቻቸው ከዐደፍ ያቋረጡት በዒዳቸው ሕግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እነዚያም ገና ዐደፍ ያላዩት ዒዳቸው እንደዚሁ ነው፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው"*፡፡ 
📗አትተሕሪም 65፥4

ዒዳህ” عِدَّة ማለት ሁለት ጥንዶች ከተጋቡ በኃላ ተራክቦ አድርገው ከዚያም አለመግባባት ቢፈጠር ፍቺ ለማድረግ ቢያስቡ ቅድሚያ ነፍሰ-ጡር መሆኗን እና አለመሆኗን ለማረጋገጥ የሚቆይበት የሦስት ወር ጊዜ ቆይታ ነው፤

☝️ ዒዳህ ማለት ከተጋቡ ከተራክቦ በኃላ ያለ ነገር ከሆነ በዚህ አንቀፅ መሰረት ሐይድ(አደፍ) የወር አበባ ያላዩ ሴቶች ዒዳህ እንዳላቸው ስለተነገረ " ለዐቅመ ሄዋን ያልደረሰችን ህፃን ማግባት ይቻላል ይላሉ።
➸ ለዚህ ሹቡሃ መልሳችን
ከላይ ክፍል 01 ላይ እንዳየነው
▸አንዲት ሴት ለአቅመ ሂዋን ምትደርሰው👇
-1.ሀፍረተ ገላ ላይ ፀጉር ማብቀል
-2.ኢሕቲላም(አንድ ልጅ ወይም አንዲት ልጂት ተራክቦ ለማድረግ የሚኖራቸው ፈሳሽ ማምጣት)
-3. አስራ አምስት(15) አመት መድረስ
-4. ለሴት ከ9 አመት ጀምሮ የወር አበባ ማየት
📘አልሙግኒይ ኢብኑ ቁዳማህ 3471 ቅጽ  4 ገፅ 298

አንዲት ሴት☝️ ከነዚህ ምልክቶች አንዱን ካየች ለአቅመ ሂዋን ትደርሳለች አቅመ ሂዋን ለመድረስ የወር አበባ ማየት መስፈርት አይደለም።
የወር አበባ ሳታይ ሌሎች የመድረስ ምልክቶች ቢታይባት ለዐቅመ ጋብቻ ትደርሳለች።
➮ እና አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ከላይ በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ "አደፍ(የወር አበባን) ያላዩት" እያለ የሚጠቅሰው ገና ለአቅመሂዋን ያልደረሱ ህፃናትን ሳይሆን ሌሎች የአቅመ ሂዋን ምልክቶች አይተው የደረሱ ግን በተለያዩ ምክንያቶች የወር አበባ ስላላዩ ሴቶች እንጂ ገና ለአቅመ ሂዋን ስላልደረሱ ህፃናት አይደለም። ምክንያቱም አንዲት ሴት ልጅ አቅመ ሂዋን ደርሳ እድሜዋ ከሀያዎች አልፎ ገና የወር አበባ ላታይ ትችላለች።  ይቺ ሴት የወር አበባ ስላላየች አልደረሰችም ማለት ነው??  No እንደዛ አይባልም። ምክንያቱም የወር አበባ አቅመ ሂዋን የመድረሰ ምልክት እንጂ አቅመ ሂዋን ለመድረስ መስፈርት አይደለም። ሌሎቹ የወር አበባ ሳታይ ሌሎች ምልክቶች አይታ ልትደርስ ትችላለች።የወር አበባን ባታይ እንኳ ስለደረሰች ታገባለች።

➮,እና አላሁ ሱብሐነሁ ወተዓላ "አደፍን(የወር አበባን) ያላዩት ሲል ገና ያልደረሱ ሴቶች እያለን ሳይሆን አቅመ ሂዋን ደርሰው ግን የወር አበባ ያላዩትን ነው።
🚩*ሼይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁላህ* እንዲህ ይላሉ
" አደፍ(የወር አበባ) ያላዩት የሚለውን ገና ለአቅመ ሂዋን ያልደረሱትን ነው ማለት ትክክል አይደለም።ምክንያቱም አቅመ ሂዋን ለመድረስ የወር አበባ ማየት መስፈርት ስላልሆነ። የወር አበባ ሳታይ 15 አመት ቢሞላት፣ሀፍረተ ገላ ላይ ፀጉር በማብቀል ወይም ተራክቦ ለማድረግ የሚኖራቸው ፈሳሽ በማምጣት ለአቅመ ሂዋን ልትደርስ ትችላለች። በዚህ ምክንያት ታገባለች፣ ትፋታለች የወር አበባን ያየችው 20 አመት ከሞላ በኃላ ሊሆን ይችላል።
ይቺ አቅመ ሂዋን የደረሰች የወር አበባ ያላየች ሴት ዒዳዋ ሶስት ወር ነው። አደፍ ያላዩት ሲባል ገና ያልደረሱትን አይደለም።
📘አትተዕሊቅ ዓላ ሶሒሕ አልቡኻሪይ ቅጽ 11 ገፅ 337

አንዳንድ የተፍሲረ ኪታቦች ላይ አደፍ ያላዩት የተባሉት صغيرة small በሚል ተገልጿልና ገና ያልደረሱትን ለማመላከት ነው የሚሉም አሉ።
ለነዚህ ደግሞ ሴት ልጅ صغير small መባሏ አለመድረሷን ብቻ አያመላክትም። صغيىرة small ሆና ልትደርስ ትችላለች። ለምሳሌ የ 9፣10፣11 አመት ልጅ صغيرة small ናት። ይህ ከመሆኑ ጋር ግን ለአቅመ ሂዋን ልትደርስ ትችላለች።

🚩,ኢማሙ ሻፊዒይ ረሒመሁላህ" የ9 አመት ሆነው የወር አበባ የሚያዩ ብዙ ሴቶቸን አይቻለሁ ብሏል
📘 ሱነኑል ኩብራ ጥራዝ 2 ገፅ 432 ሐዲስ 1547
በሌላ ሐዲስ ላይ ደግሞ
"ሰንዓ በሚባለው ሀገር በ9 አመቷ የወር አበባ ያየች በ 10 አመቷ የወለደች ሴት አይቻለሁ" ብሏል።
📘ሱነኑል ኩብራ ጥራዝ 2 ገፅ 433 ሐዲስ 1548
ዓኢሻህ እራሷ በ9 አመቷ የወር አበባ ያየች ሴት ለሚስትነት  ደርሳለች ብላለች
📘 ሱነኑ ቲርሚዚይ ሀዲስ 1109
📘 ሱነኑል ኩብራ ጥራዝ 2 ገፅ 433 ሐዲስ 1548

➮ ስለዚህ በአንዳንድ ተፍሲሮች ላይ صغيرة small መባሉ አቅመ ሂዋንን አለመድረሳቸውን አያመላክትም።

በኢስላም ሴትን ልጅ ሳትደርስ ያለ ፍቃዷ መዳር አይፈቀድም!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لَا تُنْكَحُ الْأَيِّمُ حَتَّى تُسْتَأْمَرَ، وَلَا تُنْكَحُ الْبِكْرُ حَتَّى تُسْتَأْذَنَ ". قَالُوا : يَا رَسُولَ اللَّهِ، وَكَيْفَ إِذْنُهَا ؟ قَالَ : " أَنْ تَسْكُتَ﴾

“አግብታ የፈታችን ሴራ እስኪያማክሯት ድረስ፤ ልጃገረድ የሆነችን ሴት ደግሞ እስኪያስፈቅዷት ድረስ አትዳርም። አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ፍቃዷ እንዴት ሊታወቅ ይችላል? ሲባሉ። ‘በዝምታዋ’ አሉ።”
📘*ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 5136*

➮ ቀጣይ የህፃናት ጋብቻ በክርስትና የሚል ርዕስ አይተን ከዚያ ስለ እናታችን ዓኢሻህ ጋብቻ እናያለን ኢንሻአላህ

➤➤አልሃምዱሊላሂ ረቢል ዓለሚን➤➤

ከላይ የጠቀሰኳቸውን ማስረጃዎች ከኪታብ በማስረጃ ከፈለጉ ይህንን ይጫኑ👇👇https://t.me/iwnetlehullu1/488?single
☝️☝️☝️☝️☝️
እውነት ለሁሉ [truth for all]

11 Feb, 16:58

744

▣የህፃናት ጋብቻ▣

▸በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

▣አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ በዚህ የዱንያ ዓለም  ሴትና ወንድ ፈጥሮ በመካከላቸው ፍቅርና እዝነት ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ እና ተዓምራቶቹ ነው፡፡

وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ።
📗የሮም ምዕራፍ الروم 30:21
የወንድና የሴት ግንኙነት ሀላል(የተፈቀደ) እንዲሆን "ኒካሕ" መታሰር አለበት።
▸وَابْتَلُوا الْيَتَامَىٰ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغُوا النِّكَاحَ
የቲሞችንም ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ ድረስ ፈትኑዋቸው፡፡
[📗አልኒሳእ 4፥6]
☝️ ,ጋብቻ እስከደረሱ ግዜ* በሚለው አንዲት ሴት ለጋብቻ የምትደርስበት ግዜ እንዳለ ቁርአን ይመሰክራል።
▸አንዲት ሴት ለጋብቻ ምትደርሰው
ለጋብቻ የመድረስ ምልክቶች
-1.ሀፍረተ ገላ ላይ ፀጉር ማብቀል
-2.ኢሕቲላም(አንድ ልጅ ወይም አንዲት ልጂት ተራክቦ ለማድረግ የሚኖራቸው ፈሳሽ ማምጣት)
-3. አስራ አምስት(15) አመት መድረስ
-4. ለሴት ከ9 አመት ጀምሮ የወር አበባ ማየት
📘አልሙግኒይ ኢብኑ ቁዳማህ 3471 ቅጽ  4 ገፅ 298

☝️ እነዚህ ምልክቶች ከታዩ ለአቅመጋብቻ ደርሰዋል ይባላል።
ሴት ልጅ እነዚህ ምልክቶችን ካላየች(ዐቅመ ጋብቻን ካልደረሰች) መዳር ወይም ማግባት ይቻላልን? ለሚለው ጥያቄ
▸▸ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁላህ በሶሂህ አልቡኻሪይ ሸርሐቸው ላይ ያስቀመጡትን ላስፍርላችሁ🙌

➸ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁላህ ነቢዩ ዓኢሻን በ 9 አመቷ እንዳገቡ በተጠቀሰበት ሀዲስ ሸርህ ላይ እንዲህ ይላሉ
"አባት ትንሽ ሴት ልጁን ያለ ምርጫዋ ሳትወድ መዳር ይችላል ምክንያቱም ለሷ የሚጠቅመውን በበለጠ ስለሚያውቅ ያሉ ብዙ ኡለሞች ቢኖሩም ኢብኑ ሹብሩማን እና አቡበከር አልአሰም የመሳሰሉት ኡለሞች አንድ አባት ሴት ልጁ ለአቅመ ሄዋን ሳትደርስ ያለ ፍላጎቷ እና ያለ ውዴታ መዳር አይፈቀድም" ብለዋል። ትክክለኛው እና ሚዛን የሚያደፋው ይህንን አይፈቀድም የሚል ነው።
ይፈቀዳል ያሉ ኡለሞች ነቢዩ ዓኢሻን አግብተዋል ብለው ስለዚህ ይፈቀዳል
ብለው የተናገሩት ስህተት ነው። ▸ ምክንያቱም ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዓንሃ የተዳረችው ለተራ ሰው ሳይሆን የሰው ልጆች አለቃ ለሆኑት ለነቢዩ ነው። በዚህም ደስተኛ ነበረች። ለዚህ ማስረጃው👇👇👇
📚 ሶሂህ አልቡኻሪይ 4785 ላይ በተዘገበው ሀዲስ👇
- የነቢዩ ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሚስት ዓኢሻ እንደተናገረችው ነቢዩ ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሚስቶቻቸውን ከእርሳቸው ጋር መቅረትን ወይስ ትዳራቸውን ትተው ከሳቸው መለየትን ባማረጧቸው ግዜ ወደኔ( ዓኢሻ ናት) መጡና ከሳቸው ጋር እንድቀር ወይም እነሱን መተው አማረጡኝ። እኔም " አላህ፣መልእክተኛው፣እና የመጨረሻው አገር እመርጣለሁ"አልኩዋቸው ትለናለች
➸ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዓንሃ ዱንያና ጌጦቿን ሳይሆን አላህና ነቢዩን ሰላሏሁ ዓለይሂ ወሰለም መምረጧ ደስተኛ መሆኗን ያመላክታል። ስለዚህ[አባት ሴት ልጁ ለአቅመ ሄዋን ሳትደርስ ያለ ፍላጎቷ እና ያለ ውዴታ ሴት ልጁን መዳር አይፈቀድም]
📕 አትተዕሊቅ ዓላ ሶሂህ አልቡኻሪይ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁላህ ቅጽ 11 ገፅ 338

በተጨማሪም ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዓንሃ ለትዳር ደርሳ ነበር።
📘አልመብሱጥ ሊስሰርኸሲይ ቅጽ 4 ገፅ 149
ስለዚህ የዓኢሻን ጋብቻ ጠቅሶ ገና ያልደረሱ ህፃናት ማግባት ይፈቀዳል የሚለው አቋም ደካማ ይሆናል።

▸ ተመሳሳይ ሀሳብ ኢማሙ ሰርኸሲይ ከኢብኑ ሸብሩማህ እና አቡበከር አልአሶም ጠቅሷል።
📘አልመብሱጥ ሊስሰርኸሲይ ቅጽ 4 ገፅ 212

▸  እነዚያ ይቻላል ያሉ ኡለሞች" እንደሚቻል ኢጅማዕ አለ ብለው ቢጠቅሱም ኢጅማዑ ትክክል እንዳልሆነ እና ኺላፍ እንዳለበት ከላይ አይተናል።
▧ ይቻላል ያሉ ኡለሞች እራሳቸው  ለዐቅመ ግንኙነት ሳትደርስ መገናኘትን ከልክለዋል።
📘ፈትሁል ባሪ ሸርህ ሶሂህ አልቡኻሪይ ቅጽ 11 ገፅ 347
▧ገና ያልደረሱ ህፃናትን ስለማግባት በኢስላም ሊቃውንት መካከል ልዩነት ቢኖርም ትክክለኛውና ሚዛን የሚያደፋው አባት ሴት ልጁ ለአቅመ ሄዋን ሳትደርስ ያለ ፍላጎቷ እና ያለ ውዴታ ሴት ልጁን መዳር አይፈቀድም]

- ስለ ዓኢሻህ ጋብቻ ደግሞ ቀጣይ ርዕስ ላይ በሰፊው እናየዋለን ኢንሻአላህ


ከላይ የጠቀሰኳቸውን ማስረጃዎች ከኪታብ በማስረጃ ከፈለጉ ይህንን ይጫኑ👇👇
https://t.me/iwnetlehullu1/482?single
☝️☝️☝️☝️☝️
እውነት ለሁሉ [truth for all]

04 Feb, 12:20

618

🔰  ካዕባን አናመልክም፣ወደ ካዕባ አቅጣጫ ለምን እንሰግዳለን ?🔰

➸ በመጀመሪያ እኛ ሙስሊሞች የምናመልከው የምንሰግደው ለአምላካችን አላህ ብቻ ነው
አላህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል👇
فَاسْجُدُوا لِلَّهِ وَاعْبُدُوا
ለአላህም ስገዱ ተገዙትም፡
[📗 ነጅም 53:62]

أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ
وَبَشِيرٌ
(እንዲህ በላቸው)፡- «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ ለእናንተ ከርሱ (የተላክሁ) አስፈራሪና አብሳሪ ነኝ፡፡»
[📗 ሁድ 11:2]
➤➤ ከአንቀፆቹ ምንረዳው ከአላህ ውጭ ያሉ ነገሮች ማምለክ እና መስገድ እንደማይቻል ነው።
➸ እንድናመልከው የታዘዝነው የካዕባን ጌታን አላህን እንጂ ካዕባን አይደለም

فَلْيَعْبُدُوا رَبَّ هَٰذَا الْبَيْتِ
ስለዚህ የዚህን ቤት (የከዕባን) ጌታ ይግገዙ፡፡
[📗 የቁረሾች ምዕራፍ  106:3]

➸ ካዕባ ምንም መጥቀምም መጉዳትም የማይችል የተፈጠረ ነገር ስለሆነ በካዕባ መማል ተከልክሏል።
👇
" አንድ አይሁዳዊ ወደ ነቢያችን መጣና እንዲህ አለ "እናንተኮ ይሄ ነገር የሆነው አንተና አላህ የሻችሁት ስለሆነ ነውበካዕባ እምላለሁ እያላችሁ ሽርክ ትፈፅማላችሁ(በአላህ ላይ ታጋራላችሁ) አላቸው። ነቢዩም ሶሀቦችን መማልን በፈለጉ ግዜ በካዕባ ጌታ እምላለሁ እንዲሉ እና አላህ የሻው ከዚያም አንተ የሻሀው ነገር ነው እንዲሉ አዘዟቸው።
📚 ሱነኑ ነሳኢይ ሀዲስ 3773

➤ ሀዲሱ ላይ በካዕባ መማል መከልከሉ ለካዕባ አምልኮት መስጠት እንደማይቻል  ያሳየናል።

➸ ካዕባ ምንም መጥቀምም መጉዳትም የማይችል የተፈጠረ ነገር ስለሆነ "የካዕባ ባሪያ" ተብሎ መሰየም ተከልክሏል።

  -ዐብዱል ዓምር(የዐምር ባሪያ)፣ዐብዱል ካዕባህ(የካዕባ ባሪያ) ወዘተ እያሉ ከአላህ ውጭ ላሉ አካላት ባርነት በመሰጠት የተሰየመ ስምን መጠቀም ክልክል በመሆኑ ላይ የኢስላም ሊቃውንት ተስማምተዋል
📘መራቲቡል ኢጅማዕ 179
📘ኪታቡ ተውሒድ ገፅ 295
📘 ፈታዋህ ኑሩን ዓላ ደርብ ቅጽ 18 ገፅ 240
➤ ካዕባ አምልኮት የሚሰጠው ቢሆን ኖሮ  የካዕባ ባርያ ማለትን ባልተከለከለ ነበር።

➸ በተጨማሪም  በነቢያችን ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘመን ሀበሻዊው ቢላል ከካዕባ ላይ ወጥቶ አዛን ያደርግ እንደነበረ የታወቀ ነው።
ካዕባ ድንጋዩ  አምላካችን ቢሆን ኖሮ አምላኩ አናት ላይ ወጥቶ አዛን አደረገ ማለት አያስኬድም። አምላክ ብለው ቢያምኑ ኖሮ እላዩ ላይ ባልወጣ ነበር።
🖐በእስልምና ካዕባ ምንም የማይጠቅም የማይጎዳ ድንጋይ ነው ብለን የምናምነው።
ከአላህ ውጭ ማታመልኩ ከሆነ ወደ ካዕባ(መካ ላይ ያለ ድንጋይ) አቅጣጫ ለምን ትሰግዳላችሁ?? ከተባለ

እኛ ሙስሊሞች ወደ ካዕባ ዙረን ምንሰግደው
ለስግደታችን አቅጣጫ ስለሆነ ነው።
የምትሰግዱት ለአላህ ብቻ ከሆነ ካዕባን ማታመልኩት ከሆናችሁ
ለምን ወደ ሌላ አቅጣጫ ለምን አትሰግዱም? ከተባለ
መልሱ:- አላህ ለአቅጣጫችን ካዕባ ያደረገልን የሙስሊሞችን አንድነት ለማስጠበቅ ብሎ ነው። ማለትም ወደ ፈለግንበት አቅጣጫ መስገድ የተፈቀደ ቢሆን ኖሮ
1. ሙስሊሞች አንድ አይሆኑም ነበር(ይለያያሉ)። አላህ ደግሞ አንድ እንድንሆን አዞናል
2. በጀመዓ እንድንሰግድ የታዘዝነውን ሰላት መፈፀም አያስመችም።
ለምሳሌ:-  እኔ መስጂድ ገብቼ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ብሰግድ ሌላው ደግሞ ወደ ሰሜን አቅጣጫ ቢሰግድ ሌላው ወደ ሌላ ከሰገደ በጀማዓ(በህብረት) ስገዱ የተባለው ሶላት መስገድም አያስመችም። አንዱ ወደ ቀኝ ሌላኛው ወደ ግራ ዙረው ጀማዓ ሰላት አያስመችም።
2. ሙስሊሞች አንድ አይሆኑም ጭቅጭቅ ወደዚህ አቅጣጫ ነው ምሰግደው..እያሉ መለያየት ይከሰታል።
➸ አላህ ደግሞ አትለያዩ ብሎ መለያየትን ከልክሎናል።

وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ
የአላህንም (የማመን) ገመድ ሁላችሁም ያዙ፡፡ አትለያዩም፡፡
[ 📗ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 103 ]

🚩ስለዚህ ወደ ካዕባ ምንዞረው ለስግደታችን አቅጣጫ እንጂ ካዕባን ስለምናመልክ አይደለም።
  አይ ወደ ካዕባ ዞራችሁ ስለምትሰግዱ ካዕባን እያመለካችሁ ነው ብለው ድርቅ ካሉ👇
➸ ነቢዩ ሙሀመድ ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ለ 16 ወራት ያህል ወደ ቤይቱል መቅዲስ አቅጣጫ (ፍሊስጢን ላይ የሚገኘው መስጅድ) ሰግደዋል። ይህ ማለት መስጅዱን እያመለኩ ነበር ማለት ነውን?? በፍፁም  የሶላት አቅጣጫቸው ነበረንጂ መስጂዱን እያመለኩት አልነበረም።
ነቢዩ  ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሶላት አቅጣጫቸው ወደ ካዕባ እንዲቀየር ይፈልጉ ነበርና
አላህ ተቀብሏቸው ወደ ካዕባ እንዲቅጣጩ የሚያዝ የቁርአን አንቀፅ ወረደ።
አላህ እንዲህ ይላል
قَدْ نَرَىٰ تَقَلُّبَ وَجْهِكَ فِي السَّمَاءِ ۖ فَلَنُوَلِّيَنَّكَ قِبْلَةً تَرْضَاهَا ۚ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ۚ وَحَيْثُ مَا كُنتُمْ فَوَلُّوا وُجُوهَكُمْ شَطْرَهُ ۗ وَإِنَّ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ لَيَعْلَمُونَ أَنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّهِمْ ۗ وَمَا اللَّهُ بِغَافِلٍ عَمَّا يَعْمَلُونَ
የፊትህን ወደ ሰማይ መገላበጥ በእርግጥ እናያለን፡፡ ወደምትወዳትም ቂብላ እናዞርሃለን፡፡ ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ (ወደ ካዕባ) አግጣጫ አዙር፡፡ የትም ስፍራ ብትኾኑም (ስትሰግዱ) ፊቶቻችሁን ወደርሱ አግጣጫ አዙሩ፡፡ እነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት መሆኑን ያውቃሉ፡፡ አላህም ከምትሠሩት ሥራ ዘንጊ አይደለም፡፡[📗በቀራህ 2:144]
☝️ካዕባ የሰላት አቅጣጫ እንጂ አምላካችን አይደለም።
➸በተጨማሪም አንድ መንገደኛ የካዕባ አቅጣጫ የት እንደሆነ ባያውቅ መጀመሪያ አቅጣጫውን ለማወቅ ይጥራል። ማወቅ ካልቻለ ወደ ፈለገበት አቅጣጫ ይሰግዳል። ይህ ማለት ካዕባን ክዶ ለሌላ ይሰግዳል ማለት ነውን??በፍፁም
ምክንያቱ የምንሰግደው ለካዕባ ሳይሆን ለአላህ ስለሆነ ነው።
አላህ ደግሞ👇

وَلِلَّهِ الْمَشْرِقُ وَالْمَغْرِبُ ۚ فَأَيْنَمَا تُوَلُّوا فَثَمَّ وَجْهُ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ وَاسِعٌ عَلِيمٌ

ምሥራቁም ምዕራቡም የአላህ ነው (ፊቶቻችሁን) ወደ የትም ብታዞሩ የአላህ ፊት እዚያ ነው፡፡ አላህ ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነውና፡፡[📗በቀራህ 2:115]
➸ በተጨማሪም የትኛውም ሙስሊም ሲሰግድ አላህ እንጂ ካዕባ በልቡ ውል አትልም። ምክንያቱም ወደ ካዕባ ሚዞርበት አላማው ለአቅጣጫ እንጂ እሷን ለማምለክ ስላልሆነ ነው።

➸ በእስልምና ቀደምት ነቢያት የሚቅጣጩበት ቦታ ነበራቸው። ለምሳሌ ወደ ቤይቱል መቅዲስ(ፋሊስጢን ላይ ሚገኘው መስጂድ) ይቅጣጩ ነበር። ወደዛ መስጂድ መቅጣጨታቸው እሱን ያመልኩ ነበር ማለት ነውን? በፍፁም የሰላት አቅጣጫ እንጂ ለሷ አምልኮ እየሰጡ አይደለም። ነቢዩ ኢብራሂም(አብረሀም)፣ ልጃቸው እስማዒል እና ሌሎች ነቢያት ወደ ካዕባ ዙረው ይሰግዱ ነበር።
📚መጅሙዕ አልፈታዋ ቅጽ 27 ገፅ 11

☝️እና ቀደምት ነቢያት ወደ ካዕባ ዙረው ሲሰግዱ ካዕባን ያመልኩ ነበር ማለት ነውን? በፍፁም። የሰላት አቅጣጫ እንጂ ካዕባን እያመለኩ አይደለም።
እውነት ለሁሉ [truth for all]

31 Jan, 10:01

671

🔰 ለእያንዳንዱ ሙስሊም በጀነት 72 ሚስት ይኖረዋልን??🔰
➸ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ በዚህ ቅርቢቷ ዓለም የፈጠረን እሱን ብቻ አምልከን ጀነት እንድንገባ ነው።

➸ አላህ እንዲህ ይላል👇
"ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡
(📗ሱረቱ አል-ዛሪያት - 56)

➸ ከሴትና ከወንድ በአላህ አምኖ አላህን ብቻ የሚያመልክና  መልካም ስራ የሚሰራ ሰው በጀነት አይን አይታው፣ጆሮ ሰምታው፣ልብ ላይ ውል ብሎ የማያውቅ ትልቅ ፀጋ ያገኛሉ።
(📗ሱረቱ አል-ሰጅዳህ፣ - 17)
[📚ኢማም ቡኻሪይ ሐዲስ 3244]
እነዚህ ፀጋዎች ለሁለት ይከፈላሉ
1. መንፈሳዊ ፀጋ ሲሆን ጀነት ውስጥ ከሚያገኛቸው ፀጋዎች ትልቁ ፀጋ  የአላህን ፊት ማየት ነው።
2. ሥጋዊ ጸጋዎች ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ደግሞ አላህ ለምዕመናን ያዘጋጀላቸውን (ታይተውም ሆነ ተቀምሰው) የማይታወቁትን ፍራፍሬዎች መብላት፣ ከሚስታቸው ጋር የመኖር ፀጋ ወዘተ ናቸው።
ዛሬ የምናየው የጀነት ሰዎች ስለሚያገኟቸው የጀነት ሚስቶች ነው።
ለሴቶችስ ምን አለላቸው ለሚለው ጥያቄ በኡለሞች የተሰጠውን መልስ👇👇
https://t.me/iwnetlehullu1/357
☝️☝️ ተጭነው ይመልከቱ☝️☝️
ስለ ሌላ ዝርዝር ነገሮች ሌላ ግዜ እናያለን ኢንሻአላህ  አሁን ለእያንዳንዱ ወንድ 72 ሚስት ይሰጠዋል ስለሚለው እናያለን ኢንሻአላህ።
➸ሀዲሱ ኢብኑ ማጃህ ላይ የሚገኝ ሲሆን አላህ እያንዳንዳችሁን 72 ሚስት ያጋባችኃል ይላል።
ይሄ ሀዲስ በትክክል ከነቢያችን ﷺ ተረጋግጧል ወይስ ዶዒፍ(ደካማ) ሀዲሰ ነው የሚለውን እናያለን

➸በሀዲስ ጥናት ላይ ጎልተው ከወጡት እና ከሱ በኃላ አምሳያው እንዳልተነሳ የሚመሰከርለት ሀፊዝ ኢብኑ ሀጀር የሶሂሁልቡኻሪይ ሸርህ በሆነው ፈትሁል ባሪ ኪታባቸው ላይ
"እያንዳንዱ ሙእሚን 72 ሚስቶች ይሰጠዋል፣ከመቶ ሴቶች ጋር ይገናኛል፣5000 ወይም 4000ሚስቶች ወዘተ የሚሉ ሀዲሶችን እየጠቀሰ ሀዲሶቹ ሰነዳቸው ላይ ችግር ድክመት ስላለባቸው ዶዒፍ(ደካማ) መሆናቸውን ጠቅሷል። ደካማ የሆኑበትን ምክንያት እዛው ጠቅሷል።
ወደ 4000 ወይም 5000 ሚስቶች የሚለው ደግሞ በሰነዱ ላይ ስሙ ያልተጠቀሰ ዘጋቢ ስላለ ዘገባው ዶዒፍ ደካማ ነው።
ከዚያ በኃላ የታላቁ ኢማም ኢብኑል ቀይም ንግግር አስከትሎ አመጣና
ኢማሙ " የጀነት ሰዎች በጀነት ሚስቶች አሏቸው ከሚለው ሀዲስ ውጭ ከሁለት ሚስት በላይ ይሰጣቸዋል የሚል ሶሂህ(ትክክለኛ) የሆነ ዘገባ የለም። 
- ትክክለኛው" ለእያንዳንዱ ሙእሚን ሁለት ሚስት አለው የሚለው ነው። ብለዋል
📚ፈትሁልባሪ ሸርህ ሶሂህ አልቡኻሪይ ቅጽ 7 ገፅ 544

ሐፊዝ አቡ ኑዐይም አልአስባሃኒይ
"72 ሚስት ያገኛሉ የሚለው ሀዲስን በጠቀሰበት ላይ ሀዲሱ የመጣበት ሰነድ(ሰንሰለቱ) ላይ ኻሊድ ኢብኑ የዚድ የሚባል ዶዒፍ(ደካማ) የሆነ ዘጋቢ ስላለበት ሀዲሱ ضعيف جدا በጣም ዶዒፍ ነው።የሚል እናገኛለን
📚 ሲፈቱ ሶላት ሊአቢ ኑዐይም አልአስባሃኒይ ገፅ 205 ሀዲስ 370

ከኪታቡ በቀጣይ ገፁ ላይ "73 ሚስት ያገኛሉ የሚለውን በጠቀሰበት ላይ ሀዲሱ የመጣበት ሰነድ(ሰንሰለቱ) ላይ ሐጃጅ ኢብኑ አርጠአህ የሚባል ስህተተ ብዙ እና ሙደሊስ የሆነ ዘጋቢ ስላለበት የሀዲሱ ሰነድ ضعيف ዶዒፍ ደካማ ነው። ኢማሙ ዘሀቢይ "ዘጋቢው ሙንከር የሆኑ(በጣም ደካማ የሆኑ) ሀዲሶችን የሚዘግብ ነው። የሚል እናገኛለን
📚 ሲፈቱ ሶላት ሊአቢ ኑዐይም አልአስባሃኒይ ገፅ 206 ሀዲስ 372
➸ ታላቁ የሀዲስ ሊቅ ኢማሙል አልባኒይ የሶሂህነት መስፈርት ያላሟሉ(ዶዒፍ ሀዲሶችን በሰበሱበት ኪታቦቻቸው ላይ
" 72 ሚስት የሚለውን ሀዲሱን ከጠቀሱ በኃላ "ሀዲሱ ضعيف جدا በጣም ደካማ የሆነ ሀዲስ ነው" ብለዋል
📚 ሲልሲለቱል አሃዲስ አድዶዒፋህ ወልመውዱዓህ ቅጽ 9 ገፅ 456 ሀዲስ 4473
በኢብኑ ማጃህ የተዘገበው 72 ሚሰት የሚለውን ሀዲሱን ዶዒፍ ብለውታል
📚 ዶዒፍ ሱነን ኢብኑ ማጃህ ገፅ 364 ሀዲስ 5002
➸ ታላቁ ኢማም ኢብኑል ቀይም በኪታባቸው ላይ 
- ስለ 72 ሚስት የሚያወራው ሀዲስ የመጣበት ሰነድ(ሰንሰለት) ላይ ኻሊድ ኢብኑ ዘይድ የሚባል ዘጋቢ አለ።
ይህን ዘጋቢ ከሰለፎች ታላላቅ ኡለሞች ዶዒፍ(ደካማ) መሆኑን ተናግረዋል።
*ያህያ ኢብኑ መዒን* ደካማ ነው
*ኢማሙ ነሳኢይ* ታማኝ አይደለም ብሏል።
*ኢማሙ አድዳረቁጥኒይ* ዶዒፍ ነው ብሏል።
* ኢብኑ ዓዲይ" ደግሞ ይሄ ስለ 72 የሚወራው ሀዲስ ሙንከር ተደርጎበታል ብሏል።

-73 ሚስት ይሰጣቸዋል የሚል ሀዲስ ላይ ደግሞ አሕመድ ኢብኑ ሐፍስ የሚባል ዘጋቢ አለ። ይሄ ዘጋቢ ብዙ ሙንከር(ተቀባይነት የሌላቸው) የሆኑ ዘገባዎች አሉት
📚ሐዲ አልአርዋሕ ኢላ ቢላዲል አፍራሕ ገፅ 501-502

- በቀን መቶ ሴትን ይገናኛሉ የሚለው ሀዲስ ሰነድ ላይ ሑሴን አልጁዕፊይ የሚባል ዘጋቢ አለ። ይህንን ሀዲስ ኡለሞች ኢንካር ያደረጉበት የሆነ ሀዲስ ነው። ኢማም ኸጢብ አልበግዳዲይ ሀዲሱ ዶዒፍ ነው ብሏል
📚 ሐዲ አልአርዋሕ ኢላ ቢላዲል አፍራሕ ገፅ 503
☝️ኢማም ኢብኑል ቀይም እነዚህ ሀዲሶች ዶዒፍ መሆናቸውን ከጠቀሱ በኃላ
"ትክክለኛ ዘገባ የመጣው ሁለት ሚስት እንደሚሰጣቸው ነው ከሁለት ሚስት በላይ ይሰጣቸዋል የሚል ሶሂህ(ትክክለኛ) የሆነ ዘገባ የለም። 
📚 ሐዲ አልአርዋሕ ኢላ ቢላዲል አፍራሕ ገፅ 505

➸ ከዚህ ምንረዳው ካፊሮች እያንዳንዳችሁ 72 ሚስት ታገኛላችሁ እያሉ የሚያመጧቸው ሀዲሶች ዶዒፍ ደካማ መሆናቸውን እንረዳለን። ያመጧቸው ሀዲሶች ለነሱ ማስረጃ ሊሆኑላቸው አይችሉም። ምክንያቱም ሀዲስን ማስረጃ አድርጎ ለማቅረብ ያ ሀዲስ ከነቢዩ ﷺተረጋግጦ የመጣ መሆን አለበት
📚 ሸርህ መንዙመቱል በይቁንያህ ኢብኑ ዑሰይሚን ገፅ 21

ከላይ እንዳየነው ሀዲሶቹ ዶዒፍ(ደካማ) ናቸው።
ባለፈው ርዕሳችን ላይ እንዳየነው ሰለፎች ዘንድ ዶዒፍ የሆነን ሀዲስ ማስረጃ ሊደረግ እንደማይችል አይተናል።
በተጨማሪ👇
📚ሸርህ መንዙመቱል በይቁንያህ ኢብኑ ዑሰይሚን 60
📚 ሙስጠለሁል ሀዲስ ኢብኑ ዑሰይሚን ገፅ 16
ለእያንዳቸው ከ 2 በላይ ሚስቶች ይሰጣቸዋል የሚለው ሀዲስ ዶዒፍ(ደካማ) ከሆነ ስንት ነው የሚሰጡት ከተባለ👇
ኡለሞች ትክክለኛነቱ ላይ የተስማሙበት የሆነ በቡኻሪይ እና ሙስሊም ሌሎች ኪታቦች ላይም በተዘገበ ሀዲስ ላይ
" ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሚስት ይሰጣቸዋል"
📚ሶሂህ አልቡኻሪይ ሀዲስ 3245 እና ሀዲስ 3246
e፣ ሶሂህ ሙስሊም 2834 መፅሐፍ 53, ሀዲስ 20
የሚል ሶሂህ ሀዲስ እናገኛለን።
➸ አንዳንድ 72 ሚስት የሚለው ሀዲስን ሶሂህ ያደረጉ ኡለሞች ሁለት ሚስት የተባለው ከዱንያ(ከዚህ ዓለም) የሆኑ ሴቶች ሲሆኑ ሰባዎቹ ደግሞ ከሁረል ዓይን ናቸው ቢሉም ይሄ አያስኬድም። ምክንያቱም ሶሂህ በሆነ ሀዲስ ላይ
" ለእያንዳንዳቸው ከሁረል ዓይን የሆኑ ሁለት ሚስቶች ይሰጣቸዋል"
📚ሶሂህ አልቡኻሪይ ሀዲስ 3254
የሚል ስላለ ትክክለኛው እና ሶሂህ ማስረጃዎች የሚደግፉት ለእያንዳንድ ሙዕሚን ሁለት ሚስቶች ይኖረዋል የሚል ነው።
ኢብኑ ረጀብ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ
"ለእያንዳንዱ ሰው ሁለት ሚስት ይሰጣቸዋል። በደረጃቸው ልክ ከሁለት በላይ የሚኖሳቸው ቢኖሩም ( 72፣73፣100 እንደሚባለው) የሴቶቹ ብዛት በቁጥር የሚገድብ ሶሂህ የሆነ ማስረጃ የለም
📚 አትተኽዊፍ ሚን አንናር ገፅ 268
አልሃምዱሊላሂ ረቢል ዓለሚን➤
አልሃምዱሊላሂ ረቢል ዓለሚን➤


ከላይ የጠቀሰኳቸውን ማስረጃዎች ከኪታብ በማስረጃ ከፈለጉ ይህንን ይጫኑ👇👇
https://t.me/iwnetlehullu1/460?single
☝️☝️☝️☝️☝️
እውነት ለሁሉ [truth for all]

31 Jan, 10:01

315

👇
እውነት ለሁሉ [truth for all]

31 Jan, 10:01

388

👇
እውነት ለሁሉ [truth for all]

15 Jan, 19:08

277

ምድነው ክርስቲያኖች?

እግዚአብሔር ለራሱ ፈሪ ስለሆነ ነው ልጁን ኢየሱስን ወደ ምድር ልኮ ያስገደለው እያሉን ነው

እግዚአብሔር ግን ራስ ወዳድ ነው የምር ለራሱ ፈርቶ ልጁን የሚያስቀጠቅጥ ተንኮለኛ ነው(:-)

(📗መጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ ምዕራፍ 4 ክፍል 5)

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ
https://t.me/mukamil12
እውነት ለሁሉ [truth for all]

12 Jan, 13:46

468

⓵ ዳንኤል 10
እኔም ዳንኤል ብቻዬን ራእዩን አየሁ፥ ከእኔ ጋር የነበሩ ሰዎች ግን ራእዩን አላዩም፤ ነገር ግን ጽኑ መንቀጥቀጥ ወደቀባቸው፥ ሊሸሸጉም ሸሹ።
⁸ እኔም ብቻዬን ቀረሁ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኃይልም አልቀረልኝም፥ ደም ግባቴም ወደ ማሸብሸብ ተለወጠብኝ፥ ኃይልም አጣሁ።
⁹ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ የቃሉንም ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ።
¹⁰ እነሆም፥ አንዲት እጅ ዳሰሰችኝ፥ በጕልበቴና በእጄም አቆመችኝ።
¹¹ እርሱም፦ እጅግ የተወደድህ ሰው ዳንኤል ሆይ፥ እኔ ዛሬ ወደ አንተ ተልኬአለሁና የምነግርህን ቃል አስተውል፥ ቀጥ ብለህም ቁም አለኝ። ይህንም ቃል ባለኝ ጊዜ እየተንቀጠቀጥሁ ቆምሁ።
¹² እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ዳንኤል ሆይ፥ አትፍራ፤ ልብህ ያስተውል ዘንድ፥ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደረግህበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ቃልህ ተሰምቶአል፤ እኔም ስለ ቃልህ መጥቻለሁ።
… 
ከቁጥር 15-17 ባለው ላይ ደግሞ እስከመታመም ድረስ እንደደረሰ ይገልፃል
☝️ግልፅ ነው። በቁጥር 7 ላይ☝️
"ከእኔ ጋር የነበሩ ሰዎች ግን ራእዩን አላዩም፤
ነገር ግን ጽኑ መንቀጥቀጥ ወደቀባቸው፥"ይላል
➸ከራዕዩ ብርታት የተነሳ ራዕዩን ያላዩ ሰዎች እንዲህ መንቀጥቀጥ ከደረሰባቸው ራዕዩን እያየ የሚቀበል ሰው ሁኔታስ ምን እንደሚሆን አስቡት።

⓶ ራዕይ ወደ አብረሃም ሲመጣ ፈርቶ ነበር👇
ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፦ አብራም ሆይ፥ አትፍራ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።”
  — ዘፍጥረት 15፥1

⓷ ራዕይ ወደ ዘካሪያስ ሲመጣ ፈርቶ ነበር።
“መልአኩም እንዲህ አለው፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።”
  — ሉቃስ 1፥13
⓸ ማርያም መልአክ ወደሷ ሲመጣ ፈርታ ነበር።👇

ሉቃስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁰ መልአኩም እንዲህ አላት፦ ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።
³¹ እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።

➸ በነሱ አረዳድ ነቢዩ ዳንኤል ፣ነቢዩ አብረሃም፣ዘካሪያስ፣ማርያም ራዕይ ሲወርድባቸውና መልአኩን ሲያዩ  እነዚህን ባህሪያት ያሳዩ ነበርና ሀሰተኛ ነቢይ፣ማርያም ደግሞ መጥፎ ናት ማለት ነውን???

አላህ እንዲህ ይላል
وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا
*¶በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»*
{📗 Qur'an17:81}


አልሃምዱሊላሂ ረቢል ዓለሚን
https://t.me/iwnetlehullu1