Последние посты ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር (@ethiopianorthodoxtewahdomezmurs) в Telegram

Посты канала ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን

🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን መዝሙሮች ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።

👥 ✅ @yemezmurgetemoche

📝ለማንኛውንም ሀሳብናአስተያየት
✅ @KIDAN_MEHRET_ENATEbot

ለማስታወቂያ ስራዎች ✅ @gutaitagu16

የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን
34,681 подписчиков
3,183 фото
223 видео
Последнее обновление 06.03.2025 17:05

Похожие каналы

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒
44,186 подписчиков
ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ
21,845 подписчиков

Последний контент, опубликованный в ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር на Telegram

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

19 Feb, 17:46

1,271

"በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ  አሜን"።

#የካቲት_13 ቀን እንኳን #መልካም_ስም_አጠራርና ጣፋጭ ዜና ላለው ለሶርያ መስፍን ልጁ ለሆነ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ #ቅዱስ_ሚካኤልና_ቅዱስ_ገብርኤል ከሞት አስነሥተውት፤ #ቅዱስ_ዑራኤልም ነጥቆ ወደ ሰማይ አሳርጎት በዚያው በሰማይ 14 ዓመት ለኖረ፤ ተመልሶ ወደ ምድር መጥቶ 40 ዓመት ለኖረ በተአምራቱና በትምህርቱ 85ሺህ አረማውያንን አሳምኖ ላጠመቀ #ለተመሰገነ_ለሁለተኛው_ለቅዱስ_አውሳብዮስ ለምስክርነቱና ለዕረፍቱ በዓል፣ ለከበረ #ለቅዱስ_ሰርግዮስ ከአባቱና እናቱ ከወድሞቹም ከሌሎችም ብዙ ሰዎች ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ለኅርማኖስ ልጅ ለታላቁ ሰማዕት #ለቅዱስ_ፊቅጦር ለልደቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበረ አባት ከእስክድርያ አገር ሠላሳ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_ጢሞቴዎስ ዕረፍት፣ #ከቅዱስ_ፋሲለደስ ልጅ #ከቅዱስ_ቴዎድሮስ ከምስክርነቱ መታሰቢያ፣ #ከአባ_ክፍላና_ከአባ_ኅብስት ከመታሰቢያቸው #እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

#ሰማዕቱ_ቅዱስ_ፊቅጦር፦ ለዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ኅርማኖስ ነው እርሱም ለዲዮቅልጥያኖስ የአማካሪዎቹና የሠራዊቱ አለቃ ነው ስለ አምልኮ ጣዖት ሥራ ምክሩና ንግግሩ ሁሉ ከእርሱ ጋራ ነበር የእናቱም ስም ማርታ ይባላል በክርስትናዋ የጸናች ብፅዕት ናት።

ቅዱስ ፊቅጦርም በአደገ ጊዜ አባቱ ወደ ንጉሥ አቀረበው ንጉሡም በመንግሥቱ ውስጥ ሦስተኛ ማዕርግ አድርጎ ሾመው በዚያን ጊዜ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበረ። እርሱም የዚህን ዓለም ክብር ናቀ ሥጋ አይባላም ወይን አይጠጣም ዘወትርም ይጾማል ጸሎትንም ባለማቋረጥ በቀንና በሌሊት ይጸልያል። በክብር ባለቤት #ክርስቶስ ስም የታሠሩትን ይጐበኛቸዋል ለድኆችና ለምስኪኖችም ይመጸውታል።

የቅዱስ ቆዝሞስና ድምያኖስ እናት ቅድስት ቴዎዳዳን በገደሉዋት ጊዜ ንጉሡም ስለ መፍራት ሊቀብራት ማንም አልደፈረም። ይህ ቅዱስ ፊቅጦርም መጥቶ ሥጋዋን ወሰደ ከንጉሥ ስለሚመጣው ቅጣት ሳይፈራ ቀበራት። ጣዖት ስለ ማምለኩ አባቱን ዘወትር የሚገሥጸውና ብዙ ጊዜም የሚመክረው ሆነ አባቱም ወደ ንጉሥ ከሰሰው እንጂ አልሰማውም። ተከሶም ወደ ንጉሥ በአቀረቡት ጊዜ "አማልክት ያልሆኑ ርኲሳን ጣዖታትን ለሚያመልክ ሰነፍ ዝንጉ ልብ የለሽ ለሆነ ንጉሥ አላገለግልም። ከዛሬ ጀምሮ ለሕያው ንጉሥ #ክርስቶስ እገዛለሁ የሰጠኸኝንም ገንዘብህን ንሣ" ብሎ በፊቱ ትጥቁን ፈትቶ ጣለለት።

አባቱ ኅርማኖስም ወደ እስክንድርያ እንዲልከውና በኄርሜኔዎስ መኰንን ዘንድ በዚያ ፊቅጦር እንዲቀጣ ንጉሡን መከረው። በዚያን ጊዜም ከአደባባይ አወጡት እናቱም በብዙ ልቅሶ ልትሸኘው መጣች። እርሱም ሲመግባቸው ስለ ነበረ የታሠሩ ምዕመናን ስለ ድኆችና ምስኪኖች ስለ ሙት ልጆችና ስለ ባልቴቶች የሚሹትን በመስጠት እንድትጐበኛቸው አዘዛት ከዚያም አፉን ለጉመው ወሰዱት።

በእስክንድርያ አገር ወደ መኰንኑ ኄርሜኔዎስ ዘንድ በደረሰ ጊዜ ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት የ #እግዚአብሔርም መልአክ ወደ ሰማያት አውጥቶ ስለ ክብራቸው ለመናገር የሚያስጨንቁ የብርሃን ማደሪያዎችን አሳይቶ ወደ መኖሪያው መለሰው። መኰንኑም በእሳት በአፈሉት በዝፍት፣ በዲን ደግሞ አሠቃየው ከዚያም በብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቹ እሳትን አነደዱ። ደግመው ከውሽባ ማንደጃ ውስጥ ጨመሩት በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም አሠቃዩት የክብር ባለቤት #ጌታችንም ያጸናውና ከሥቃዩ ያስታግሠው መልአኩንም ልኮ ከቊስሉ ይፈውሰው ነበር።

ከዚህም በኋላ ወደ እንዴናው ከተማ ላከው በዚያም ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት ምላሱን ቆረጡ። በእሳት ያጋሉዋቸውን ችንካሮች በጐኖቹ ውስጥ ጨመሩ #እግዚአብሔር ግን አጽንቶ አስታግሦ ያለ ጉዳት በደኅና ያነሣዋል። ከዚህም በኋላ በዚያ በረኃብ እንዲሞት ከዱር ባለ ግምብ ውስጥ አሠሩት። እርሱ ግን መጥረብ የሚያውቅ ስለሆነ ላይዳዎችን በመጥረብና በመሸጥ በየጥቂቱ እየተመገበ የቀረውን ለድኆች እየሰጠ ኖረ። አንድ መኰንንም መጥቶ በዚያ ግምብ አቅራቢያ አደረ ስለ ቅዱስ ፊቅጦርም እርሱ የንጉሥ የሠራዊት አለቃ የሆነ የኅርማኖስ ልጅ እንደሆነ ነገሩት። መኰንኑም ወደርሱ አቅርቦ ብዙ ሸነገለው ባልሰማውም ጊዜ ያሠቃዩት ዘንድ አዘዘ ጅማቶቹን መዘዙ አፋን መቱት ቊልቊል ሰቀሉት በእጆቹ ላይ ከባድ ደንጊያ አንጠልጠሉ። ከዚያም ከሚነድ እሳት ውስጥ ጨመሩት ሙጫ፣ አደሮ፣ ማርና ዘይትን አፍልተው በላዩ ደፉበት በማበራያም አበራዩት አፉንም በአሞትና በእሬት አመረሩት ዐይኖቹንም አወለቁት ደግመውም ዘቅዝቀው ሰቀሉት። የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ተገልጾለት አጸናው አረጋጋው። ሥሮቹንም ሕዋሳቶቹን በቦታቸው መለሰለትና አዳነው።

አንዲት ዓሥራ አምስት ዓመት የሆናት ብላቴና ነበረች ቅዱስ ፊቅጦርን ሲአሠቃዩት በቤቷ መስኮት ታየው ነበር። መላእክትም በእጆቻቸው አክሊሎችን ይዘው እነርሱም በቅዱስ ፊቅጦር ራስ ላይ ሲያኖሩአቸው አይታ እንዴት እንዳየች ለአሕዛብ ነገረቻቸው እጅግም አደነቁ ከእርሳቸውም ብዙዎች በክብር ባለቤት በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ዐረፉ። ያቺም ብላቴና በ #ጌታችን አመነች መኰንኑም ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። የሕይወት አክሊልንም ተቀበለች ሁለተኛም የአመኑትን ሁሉ ራሳቸውን እንዲቆርጡአቸው አዘዘ የሕይወትንም አክሊል ተቀበሉ።

ከዚህም በኋላ የከበረች የቅዱስ ፊቅጦርን ራስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ተጋድሎውንም ሚያዝያ 27 ፈጽሞ የሕይወትና የድል አክሊል ተቀበለ። ምዕመናን ሰዎችም ሥጋውን ወስደው በከበሩ ልብሶች በድርብ በፍታ ገነዙት። እናቱ ማርታም ከአንጾኪያ እስክትመጣ በንጹሕ ቦታ አኖሩት በመጣችም ጊዜ ከዚያ ወሰደችው። ውብ ቤተ ክርስቲያንም ሠርታ ሥጋውን በውስጥዋ አኖረች ከእርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ።

ለ #እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የቅዱስ ፊቅጦር በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የሚያዝያ 27 ስንክሳር።              

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሰማዕቱ_ቅዱስ_አውሳብዮስ_ዘሀገረ_ሶርያ፦ ይኽም ቅዱስ የሶርያው መስፍን ልጅ ነው፡፡ ለርሱም #መንፈስ_ቅዱስን የተመላች ስሟ አውሎፊያ የምትባ እኅት አለችው ይህንንም በተግሣጽና በጥበብ በማስተማር ካሳደጉት በኋላ የሮሜውን ንጉሥ ልጅ በታላቅ ክብር አጋቡት፡፡ በሠርጉም ዕለት ወደ ቅድስት ወደሆነችው ወደ እኅቱ ዘንድ ገብቶ "እስቲ ምከሪኝ ልቤ ይህን ጋብቻ አይሻውም ዓለምን ንቆ መተውን እንጂ" አላት፡፡እኅቱም "የዚህ የኃላፊው ዓለም ጣዕም ምን ይጠቅምሃል?እንደ ሊቀጳጳሳት ድሜጥሮስ በድንግልና መኖር ይሻልሃል" አለችው፡፡ ምሽትም በሆነ ወደ ሙሽራይቱ ጫጉላ ቤት ገብቶ የእነርሱ ውበትና ደምግባት እንደሚጠፋ ከዚህም ይበልጥ የሚጠቅማቸውን የጽድቅ ሥራ በመሥራት ድንግልናቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ሙሽራይቱን አዋያት፡፡ ሙሽራይቱም በሀሳቡ ተስማምታ ድንግልናቸውን በመጠበቅ በጾም በጸሎት እየዋሉ ሌሊትም ከባሕር ውስጥ፡ገብተው፡ቆመው ሲጸልዩ ያድሩ ጀመር፡፡ አትራ ወደምትባል ቤተ ክርስቲያን ሄደው አራት እልፍ ይሰግዳሉ፡፡
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

19 Feb, 17:46

1,181

በአንዲት ዕለት የሶርያው ንጉሥ ሚስት ቅዱስ አውሳብዮስን አይታው እጅግ ወደደችው፡፡ ከባሮቿም ውስጥ ሁለቱን ልካ ካስመጣችው በኋላ በወርቅ አጊጣ በሐር በተነጠፈ አልጋ ላይ ሆና ጠበቀችው፡፡ ከእርሷም ጋር እንዲተኛ ስትጠይቀው "እኔስ ሚስቴንም እንኳን በግብር ያላወኩ ነኝና ተይኝ ንጉሡ ባልሽ በቤት ባይኖር ሰውም ባያየን #እግዚአብሔር ግን ያየናልና እንዴት በ #እግዚአብሔር ፊት ኃጢአት እሠራለሁ? "በማለት ትቷት ሊወጣ ሲል ልብሱን ያዘችው፡፡ እርሱም ሮጦ በማምለጥ ቤተ ክርስቲያን ሲገባ እርሷ ግን በመጮህ ባሮቿ ሲመጡላት" ክፉ ነገርን አድርጎብኝ ሄደ" ብላ በሐሰት ተናገረች፡፡ ጭፍሮቿም ቅዱስ አውሳብዮስን ከቤተ ክርስቲያን አውጥተው እየደበደቡ ወደ ንግሥቲቱ አመጡት፡፡ እጆቹንና እግሮቹንም አሥረው ከከተማ ውጭ በአራት ዕንጨቶች ላይ አሰቀለችው፡፡ ከባሮቿም ውስጥ አንዲቱ በንግሥቲቱ ተልካ ሄዳ አውሳብዮስን "ከተሰቀልክበት እንዲታወርድህ ለእመቤቴ ያለችህን እሺ በላት" አለችው፡፡ እርሱም "የአመንዝራን ቃል አልሰማም" አላት፡፡ ንግሥቲቱም እሺ እንዳላላት ስታውቅ አንገቱን በገመድ አሳንቃ 160 ፍላጻዎችን በሰውነቱ ውስጥ እንዲጭምሩበት አደረገች፡፡ #ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤልን ልኮለት ፍላጻዎቹን ከሰውነቱ ውስጥ አወጡለትና ፍጹም ጤነኛ ሆነ፡፡ ንጉሡም ከሄደበት ሲመለስ ንግሥት ሚስቱን ቅዱስ አውሳብዮስን ለስቅላትና ለሞት ያበቃችው በምን ምክንያት እንደሆነ ሲጠይቃት አንተ በሌለህበት ወደ መኝታ ቤቴ ገብቶ ሊናገሩት የማይገባ ነገር ጠየቀኝ በከለከልኩትም ጊዜ በሥራዩ አሳመመኝ" አለችው፡፡ ንጉሡም ተቆጥቶ ቅዱስ አውሳብዮስን ከተሰቀለበት አስወርዶ ካስመጣው በኋላ ለምን ይህን እንዳደረገ ጠየቀው፡፡ ቅዱስ አውሳብዮስም እውነቱን በነገረው ጊዜ ጭፍሮቹን ምስክር ይሆኑ ዘንድ ሲጠይቃቸው ንግሥቲቱ ስትጮህ ወደ ውስጥ ሲገቡ ያጋጠማቸውን መሰከሩ፡፡ ንጉሡም የሚስቱን ነገር አምኖ በመቀበል በንዴት የቅዱስ አውሳብዮስን ሰውነቱን በሰይፍ አስቆርጦ ሥጋውን እንደ ላም ሥጋ ቆራርጦ በምንቸት አድርጎ በእሳት እንዲበስል አደረገው፡፡ ነገር ግን አሁንም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ከምቸቱ አውጥተው ከሞትም አድነው በማስነሣት ፍጹም ጤነኛ አደርገው አቆሙት፡፡

ከሞት ከተነሣም በኋላ በአገሩ ውስጥ ሲሄድ ሰዎች አይተውት ለንጉሡ ስለነገሩት ንጉሡ ድጋሚ ካስመጣው በኋላ አራት ዛንጅሮች በአካላቶቹ ውስጥ በማስገባት እጅና እግሩን አሳስሮ በእሳት ውስጥ ጨመረው፡፡ የከበሩ ሁለቱ ቅዱሳን መላእክት አሁንም መጥተው ፈወሱት፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም ነጥቆ ወደ ሰማይ አሳርጎት በዚያው በሰማይ 14ዓመት ኖረ፡፡ ከዚያም ወደ ምድር ተመልሶ መጥቶ ወንጌልን እያስተማረ 40 ዓመት ኖረ፡፡ በእርሱም ትምህርት 85ሺህ አረማውያን አምነው ተጠምቀዋል፡፡ ቅዱስ አውሳብዮስ በመጨረሻ ሰማዕትነቱንና ተጋድሎውን ፈጽሞ የካቲት13 ቀን በክብር ዐርፏል፡፡ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም ስሙ ለሚጠራ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ እስከ ሰባት ትውልድ ሊምርለት ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡

ለ #እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አውሳብዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሰርግዮስ፦ የዚህ ቅዱስ አባቱና እናቱ ደጎች ናቸው። የአባቱ ስም ቴዎድሮስ የእናቱም ስም ማርያም ነው። ዕድሜውም ሃያ ዓመት ሲሆነው በክብር ባለቤት በ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም ይሞት ዘንድ አሰበ ወደ መኰንኑ ቆጵርያኖስም ቀርቦ በክብር ባለቤት በ #ጌታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ ስም ታመነ መኰንኑም ጽኑ ሥቃይን ያሠቃዩት ዘንድ ያሥሩትም ዘንድ አዘዘ #ጌታችንም ነፍሱን ወደ ሰማይ አምጥቀው የቅዱሳን ሰማዕታትን መኖርያ ያሳዩዋት ዘንድ አዘዘ አይታም ተጽናናች ከሥቃይ ከሕማሙም ፈወሰው።

ቀሲስ አባ መጹንና ሁለት ዲያቆናትም ተጋድሎውን ሰሙ ያን ጊዜም ተነሥተው ወደ አትሪብ አገር ገዥ ቀርበው በክብር ባለቤት በ #ጌታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ ታመነ የጸና ግርፈትም ይገርፋቸው ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው። ሕዝቡም ሁሉ በዙርያቸው ሁነው ይመለከቷቸው ነበር ስለ ቄሱና ከእርሱ ጋር ስላሉትም አዘኑ ቄሱ ግን ፊቱን ወደርሳቸው መልሶ ገሠጻቸው አስተማራቸውም "በክብር ባለቤት በ #ጌታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ፡፡ በቀናች ሃይማኖት እንዲህ ጽኑ" አላቸው ከዚህም በኋላ በውኋ ላይ ጸልዮ በላያቸው ረጨ በዚያንም ጊዜ በላያቸው ወርዶአልና የ #መንፈስ_ቅዱስን ጸጋ ተቀበለው በክብር ባለቤት በ #ጌታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ ታመኑ ራሶቻቸውንም በሰይፍ ቆረጧቸው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ከዚያም በኋላ ቄሱን ከውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ይጨምሩት ዘንድ መኰንኑ አዘዘ #እግዚአብሔርም ከእሳት አዳነው። ከ #እግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ተገለጠለትና እርሱ ስለ ክብር ባለቤት #ክርስቶስ ስም ሦስት ጊዜ ምስክር እንደሚሆን አሰረዳው ከእሳት ማንደጃው ውስጥም አወጣው። መኰንኑም ወደ እስክድርያ አገር ላከው ተጋድሎውንና ምስክርነቱን በዚያ ፈጸመ የምስክርኘቱን አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

ከዚያም በኋላ መኰንኑ ቆጵርያኖስ የከበረ ሰርግዮስን ያቀርቡት ዘንድ አዘዘ ታላቅ ሥቃይንም አሠቃየው የነሐስ መንኰራኵሮችንም አምጥተው ከውስጣቸው አስገብተው አበራዩት ሕዋሳቱም አራት ክፍል ሁኖ ሥጋው ሁሉ ተቆራረጠ #ጌታችንም አድኖ ያለ ጉዳት በጤና አስነሣው። ዳግመኛም እንዲሰግድለት ጣዖትን አመጡ ቅዱሱ ግን ሲረግጠው ወድቆ ተቀጥቅጦ ደቀቀ መኰንን ቆጵርያኖስም አይቶ በክብር ባለቤት በ #ጌታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ አመነ "አምላክ ቢሆን ራሱን ማዳን በቻለ ነበር" አለ።

ከዚህም በኋላ የጭፍራ አለቃ ስሙ አውህዮስ የሚባል የከበረ ሰርግዮስን ፈልጎ ያዘው ቆዳውንም ገፈው በተቀላቀለ ኮምጣጤና ጨው ቊስሉን ያሹት ዘንድ አዘዘ #ጌታችን ግን በሥቃዮች ላይ ያጸናውና ያበረታው፡ ነበር። እናቱና እኅቱም ሰምተው ወደርሱ መጡ በአዩትም ጊዜ በላዩ አለቀሱ ከኀዘንም ብዛት እኅቱ ነፍሷን አሳለፈች የከበረ ሰርግዮስም ስለ እኅቱ ወደ #ጌታችን ጸለየ ከሞትም ድና በሕይወት ተነሣች። ያን ጊዜ የሰማዕታትን ገድል የሚጽፍ የአቅፋስ፡አገር ሰው የከበረ ዮልዮስ መጣ ገድሉንም ሁሉ ከእርሱ ተረዳ ለሥጋውም እንደሚያስብ ቃል ገባለት።

ከዚህም በኋላ ደግሞ የከበረ ሰርግዮስን በመንኰራኵር ውስጥ ያሠቃዮት ዘንድ በጆሮዎቹ የእሳት መብራቶችን እንዲጨምሩ የእጆቹንና የእግሮቹን ጥፍሮች እንዲነቅሉ በአንገቱም ከባድ ደንጊያ አንጠልጥለው ከብረት ዐልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቹ እሳትን እንዲያነዱ አውህዮስ አዘዘ እንዳዘዘውም አደረጉበት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም ያጸናውና ያለ ጥፋት በጤና ያስነሣው ነበር። የሠራዊት አለቃ አውህዮስም ማሠቃየቱን በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ፡አዘዘ የከበረ ሰርግዮስ ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ወደ አባቱና ወደ እናቱ ወደ ወንድሞቹም ላከ ዘመዶቹ ሁሉም የእርሱ የሆኑ ሰዎችም መጡ በአፋም ልጓም ለጒመው ቸብቸቦውን ወደሚቆርጡበት ሲስቡት አገኙትና መኰንኑን የረከሱ ጣዖታቱንም ረገሙ መኰንኑም ከከበረ ሰርግዮስ ጋር ሁሉንም ቸብቸቧቸውን እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

19 Feb, 09:24

3,075

#አቡነ_ሠርፀ_ጴጥሮስ ‹ወይኑት› የምትባለውን ቅዱስ ሉቃስ የሣላት የ #እመቤታችን ሥዕል የምትገኝበትን ታላቋን ደብረ ወርቅን እንደ መሶብ አንሥተው እንዳስባረኩ!

ረድኤት በረከታቸው ይደርብንና በዛሬዋ ዕለት የካቲት 12 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ታስበው የሚውሉት #አቡነ_ሠርፀ_ጴጥሮስ ያደረጉት ተአምር ይኽ ነው፡- አባታችን ሠርፀ ጴጥሮስ በታላቋ ደብረ ወርቅ በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ላይ በነበሩበት ወቅት ለክብርት #እመቤታችን ታላቅ ፍቅር በነበረው በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ላይ አህመድ በድላይ የተባለ አረማዊ በጠላትነት ተነሣበት፡፡ #ዐፄ_ዘርዐ_ያዕቆብም ደብረ ወርቅ ውስጥ በአቡነ ሠርፀ ጴጥሮስ ለምትጣነውና ‹‹ወይኑት›› ለምትባለው ቅዱስ ሉቃስ ለሣላት ለ #እመቤታችን ሥዕል ሥዕለት ይሳላል፡፡

ዳግመኛም ንጉሡ አቡነ ሠርፀ ጴጥሮስን በጸሎታቸው እንዲያስቡት ለመናቸው፡፡ አባታችንም በወይኑት ሥዕል ፊት እየቆሙ #እመቤታችንን ስለ ንጉሡ ይለምኑለት ነበር፡፡ አቡነ ሠርፀ ጴጥሮስ ምልክት ይሆናቸው ዘንድ በአንደኛው ቀን ፈትል አስፈትለው በሥዕለ ሉቃስ በወይኑት ፊት አስቀምጠው ለዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጸለዩት፡፡ ጻድቁም ጸሎታቸውን እንደጨረሱ ፈትሏ ከራ ተጎንጉና አገኟት፡፡ ወዲያውም ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ድል አድርገው ከአህመድ በድላይ የማረኩትን ጥሩር መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ለደብረ ወርቅ ገዳም አምጥተው ሰጡ፡፡

ርዕሰ ባሕታውያን የተባሉ አባታችን ሠርፀ ጴጥሮስም በጸሎታቸውና በሥዕለ ሉቃስ በወይኑት ረዳትነት ንጉሡ ከአህመድ በድላይ የማረኩትን የብረት ቀሚስና ቆብ በመልበስ ቀን ቀን በረሃ በመውረድ ማታ ማታ ደጋ በመውጣት ሁለት ታላልቅ ሽንቁር ድንጋዮችን በማዘጋጀት አንደኛውን ከፊት አንደኛውን ከኋላ በማሰር እልፍ እልፍ ይሰግዱ ነበር፡፡ ሲሰግዱም ሁለቱ ታላላቅ ድንጋዮች ከፊትና ከኋላ በኃይል ይገጯቸው ነበር፡፡ እርሳቸው ግን የ #ክርስቶስን ጸዋትወ መከራ እያሰቡ ሰውነታቸውን በእጅጉ ያደክሙ ነበር፡፡

#አቡነ_ሠርፀ_ጴጥሮስ ጸበላቸው ጨዋማነት ያለው ሲጠጡትም የሚከብድ ነገር ግን እጅግ ፈዋሽና ኃይለኛ ጸበል ነው፡፡ በሰውነት ውስጥ የሚገኝ ማንኛውንም በሽታንና አጋንንትን የሚያስወጣበት መንገድ ለየት ያለው፡፡ በአንድ ወቅት ይህንን እጅግ ፈዋሽ የሆነውን የአቡነ ሠርፀ ጴጥሮስን ጸበል በተገዳደረ በአንድ ጣሊያናዊ ዶ/ር ላይ ይህ ተአምራት ተፈጸመ፡- ጣሊያናዊው ዶ/ር ማዛሊ ይባላሉ፡፡ በደብረ ማርቆስ ‹ሆስፒታል› የውስጥ ደዌ ‹ስፔሻሊስት› ሆነው በመሥራት ላይ ነበሩ፡፡ ሐኪሙ ብዙ ምእመናን የአቡነ ሠርፀ ጴጥሮስን ጠበል እየጠጡ ፈውስ እንደሚያገኙ ሲሰሙ ሁኔታውን ለመታዘብ ወደ ደብረ ወርቅ መጡ፡፡ እንደተነገራቸውም ቁጥራቸው በጣም ብዙ የሆኑ ምእመናን እጅግ ፈዋሹን የአቡነ ሠርፀ ጴጥሮስን ጠበል ሲጠመቁና ሲጠጡ ያያሉ፡፡ በዚህም ጊዜ ‹‹…አሁን የእውነት ውኃ ሊያድናቸው ነው ወይ!?›› በማለት ማናናቅና መሳለቅ ጀመሩ፡፡ ምግብም ከበሉ በኋላ ‹‹…ደግሞ ከምድር የሚፈልቅ ይህ ውኃ ምን ያደርገኛል?›› በማለት በድፍረት ጸበሉን ጠጡ፡፡ ነገር ግን አፍታም ሳይቆዩ ወዲያው ሆዳቸው በጣም ተነፍቶ መናገርና መተንፈስ አቃታቸው፡፡ አቡነ ሠርፀ ጴጥሮስ በዶክተሩ ላይ ኃይላቸውን ገለጡ፡፡ ከዚህም በኋላ የገዳሙ አባቶች ተጠርተው በጻድቁ ስም ጸሎትና ምሕላ አድርገውላቸው ለጻድቁ ከሰማይ በወረደላቸው በወርቅ #መስቀል ዶክተሩን ቢባርኳቸው ወዲያው በትውኪያ ወጣላቸውና ፈጥነው ዳኑ፡፡ ከዚህም በኋላ ዶ/ር ማዛሊ በአምላከ አቡነ ሠርፀ ጴጥሮስ አምነው ተጠምቀው ሔደዋል፡፡

በዛሬዋ ዕለት የካቲት 12 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ታስበው የሚውሉት አቡነ ሠርፀ ጴጥሮስ ወደ ጎጃም ሲሄዱ አጽፋቸውን አንጥፈው ዓባይን የተሻገሩ፣ ደብረ ወርቅን እንደ መሶብ አንስተው ያስባረኩ፣ የንጉሡ ልጅ ሞቶ ሊቀበር ሲሄድ በጥላቸው ከሞት ያስነሡ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ናቸው፡፡

#በረከታቸው ይደርብን #እግዚአብሔር አምላክም በጸሎታቸው ይማረን🤲

#ከገድላት_አንደበት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

19 Feb, 07:28

2,887

#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሚካኤል ከዋነኞቹም አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ🍀
ያሳባችሁትን ሁሉ ይሙላላችሁ ቅዱስ ሚካኤል
ጤና ፍቅር ሰላም በያላችሁበት የስጣችሁ 🍀
ቅዱስ ሚካኤል ሃገራችንን ሰላም ያድርግልን🙏 🙏አሜን🙏
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

19 Feb, 06:24

2,928

🎵 #መዝሙር
🔴 አዲስ ዝማሬ " ለእኛ በዚህ " ዘማሪት ትንቢት ቦጋለ @EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs

For any suggestion or question 👇 http://t.me/KIDAN_MEHRET_ENATEbot

For more join 👇
@EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs

Bot configuration by:- @gutaitagu16
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

19 Feb, 04:38

3,294

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#የካቲት_12_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ቆሮንቶስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከእናንተ አንዱ ከባልንጀራው ጋር ሙግት ቢኖረው በቅዱሳን ፊት በመፋረድ ፋንታ በዓመፀኞች ፊት ሊፋረድ ይደፍራልን?
² ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? በዓለምስ ላይ ብትፈርዱ ከሁሉ ይልቅ ትንሽ ስለሚሆን ነገር ልትፈርዱ አትበቁምን?
³ የትዳር ጉዳይ ይቅርና በመላእክት እንኳ እንድንፈርድ አታውቁምን?
⁴ እንግዲህ ስለ ትዳር ጉዳይ የፍርድ ቤት ቢያስፈልጋችሁ በቤተ ክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች ፈራጆች አድርጋችሁ ታስቀምጣላችሁን?
⁵ አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ። እንደዚህ ነውን? በወንድሞች መካከል ሽማግሌ ሊሆን የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን?
⁶ ነገር ግን ወንድም ወንድሙን ይከሳል፥ ይህም በማያምኑ ፊት ይደረጋልን?
⁷ እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን?
⁸ ነገር ግን እናንተ ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ፥ ያውም ወንድሞቻችሁን።
⁹ ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ
¹⁰ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
¹¹ ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።
¹² ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ይሁዳ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር፦ ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።
¹⁰ እነዚህ ግን የማያውቁትን ሁሉ ይሳደባሉ፥ አእምሮም እንደሌላቸው እንስሶች በፍጥረታቸው በሚያውቁት ሁሉ በእርሱ ይጠፋሉ።
¹¹ ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።
¹² እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውኃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥
¹³ የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።
¹⁴-¹⁵ ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ፦ እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።
¹⁶ እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፥ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።
¹⁷ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤
¹⁸ እነርሱ፦ በመጨረሻው ዘመን በኃጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ ብለዋችኋልና።
¹⁹ እነዚህ የሚያለያዩ ሥጋውያንም የሆኑ መንፈስም የሌላቸው ሰዎች ናቸው።
ወይም👇
1ኛ ጴጥሮስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶-⁷ በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።
⁸-⁹ እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።
¹⁰ ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤
¹¹ በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።
¹² ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።
¹³ ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
²⁹-³⁰ ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።
³¹ ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ።
³² አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ።
³³ ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤
³⁴ እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#የካቲት_12_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊተ ገዳም። ወከአዉ ደሞሙ ከመ ማይ ዐውዳ ለኢየሩሳሌም። ወኅጥኡ ዘይቀብሮሙ። መዝ.78÷2-3
"የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የጻድቃንህንም ሥራ ለምድር አራዊት፤ ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፥ የሚቀብራቸውም አጡ"። መዝ.78÷2-3
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#የካቲት_12_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ አሥሩም ሰምተው በሁለቱ ወንድማማች ተቈጡ።
²⁵ ኢየሱስ ግን ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ የአሕዛብ አለቆች እንዲገዙአቸው ታላላቆቹም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ።
²⁶ በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

19 Feb, 04:38

2,794

²⁷ ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የእናንተ ባሪያ ይሁን፤
²⁸ እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ ወይም የ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ_ቅዳሴ ነው። መልካም የ #ቅዱስ_ሚካኤል መታሰቢያ፣ የአባ ገላስዮስ የዕረፍት_ የአቡነ ሠርጸ ጴጥሮስ ዕረፍትና ሮማዊው ፋሽስት የገደላቸው የ 30,000 ሺ ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት መታሰቢያ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

18 Feb, 18:07

3,714

#ንስሐ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤” — ራእይ 2፥22

...... #ንስሐ እንግባ ሲኦል እንዳንገባ.....
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

16 Feb, 06:24

151

"በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ  አሜን"።

እንኳን #ለዘመ_አስተርዮ_የመጨረሻ_ሳምንት ለቅበላ #ለዕለተ_እሑድ_ሰንበት እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

#የዚህ_ሳምንት_መዝሙር_ዘቅበላ፦ ሃሌ ሉያ በ፭ "#ወብዙኃን_ኖሎት_መጽኡ ወስዕኑ ከሢቶታ ለዕብን እምአፈ ዐዘቅት እስከ ይመጽእ #ያዕቆብ ዘክቡት ውስተ ሐቋሁ ዘሀሎ ይሠጐ እምሰብእ ከሠተ ወአስተየ መርዔቶ ወከማሁመ #መጽኡ_ብዙኃን_ነቢያት ወሰስዕኑ ከሢቶታ ለጠጥምቀት እስከ ይመጽእ #ዐቢይ_ኖላዊ እምሰማይ ከሠተ ወአጥመቀ ብዙኃነ አሕዛበ በውስቴታ መንክር ተአምሪሁ ለመድኀኒነ በከመ ወፅአት #በትር_እምሥርወ_ዕሤይ በአምሳለ #በትረ_ያዕቆብ በዘይርዒ አባግዒሁ #ይእቲኬ_ማርያም_ይእቲ ወበእንተ ዘይቤ ትወፅእ በትር ወየዐርግ ጽጌ ውእቱኬ ዋሕድ ውእቱ ውእቱኬ #ወልደ_አምላክ_ውእቱ። ትርጉም፦ #ብዙ_እረኞች መጡ ከጉድጓድ ውኃ ላይ የተገጠመው ድንጋይ ማንከባለልና በጎቻቸውን ውኃ ማጠጣት አልቻሉም #ያዕቆብ_ሲመጣ ግን ድንጋዩን ከጉድጓዱ ላይ አንሥቶ መንጋዎቹን አጠጣቸው፣ እንዲሁም #ብዙ_ነቢያት_ቢመጡም ከሰማይ የሚመጣው #ታላቅ_እረኛ_ክርስቶስ_እስኪመጣና_የጥምቀት ምሥጢር ከፍቶ ብዙ አሕዛብን በውኃ እስከያጠምቅ ድረስ የጥምቀትን ምሥጢር ሊገልጧት አልተቻላቸውም። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

15 Feb, 18:31

2,256

¹¹ ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ መቅጃ የለህም ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ?
¹² በእውኑ አንተ ይህን ጕድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? ራሱም ልጆቹም ከብቶቹም ከዚህ ጠጥተዋል አለችው።
¹³ ኢየሱስም መልሶ፦ ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤
¹⁴ እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት።
¹⁵ ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ አለችው።
¹⁶ ኢየሱስም፦ ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ወደዚህ ነዪ አላት።
¹⁷ ሴቲቱ መልሳ፦ ባል የለኝም አለችው። ኢየሱስ፦ ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፤
¹⁸ አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነት ተናገርሽ አላት።
¹⁹ ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ።
²⁰ አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተም፦ ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ አለችው።
²¹ ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል።
²² እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን።
²³ ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤
²⁴ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።
²⁵ ሴቲቱ፦ ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው።
²⁶ ኢየሱስ፦ የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ አላት።
²⁷ በዚያም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡና ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተደነቁ፤ ነገር ግን፦ ምን ትፈልጊያለሽ? ወይም፦ ስለ ምን ትናገራታለህ? ያለ ማንም አልነበረም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ #ቅዳሴ_እግዚእነ ነው። መልካም በዓልና መልካም ዕለተ ሰንበት ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️