ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር (@ethiopianorthodoxtewahdomezmurs) के नवीनतम पोस्ट टेलीग्राम पर

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር टेलीग्राम पोस्ट

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን

🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን መዝሙሮች ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።

👥 ✅ @yemezmurgetemoche

📝ለማንኛውንም ሀሳብናአስተያየት
✅ @KIDAN_MEHRET_ENATEbot

ለማስታወቂያ ስራዎች ✅ @gutaitagu16

የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን
34,681 सदस्य
3,183 तस्वीरें
223 वीडियो
अंतिम अपडेट 06.03.2025 17:05

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር द्वारा टेलीग्राम पर साझा की गई नवीनतम सामग्री

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

06 Mar, 13:09

1,654

#የካቲት_28

#ቅዱስ_ቴዎድሮስ_ዘሮም
#አንድ_አምላክ_በሆነ_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ_ስም
የካቲት ሃያ ስምንት በዚች ዕለት #ለአርእስተ_አበው_ለቅዱሳን #ለአብርሃም_ለይስሐቅና_ለያዕቆብ የበዓላቸው መታሰቢያና በነገሥታት መክሲሞስና መክስምያኖስ ዘመን ሮማዊ ቅዱስ ቴዎድሮስ በሰማዕትነት አረፈ። እርሱም ከእስያ አውራጃ አስጢር ከሚባል አገር ነው። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ቴዎድሮስ_ማኅበር ከሆኑ #ስድስት_ሺህ_ሦስት_መቶ_አራት ሰዎች በሰማዕትነት ከዐረፉ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።         
ይህንንም ቅዱስ በነገሥታት ዘንድ አማልክትን በማምለክ እርሱ እንደማይስማማ ወነጀሉት በዚያንም ጊዜ አስጠርተው ለአማልክት ለምን አሉት እርሱም እኔ ክርስቲያን ነኝ ከሕያው #እግዚአብሔር ልጅ ከ #ጌታዬ_ከኢየሱስ_ክርስቶስ በቀር ሌላ አላመልክም ብሎ መለሰላቸው።

የበርብዮስጦስ ልጅ ንጉሡም ለአማልክቶቼ ብትገዛ በጭፍራዎቼና በመኳንንቶቼ ሁሉ ላይ አለቃ አድርጌ እሾምሃለሁ ብዙ ወርቅና ብር የከበሩ ልብሶችንም እሰጥሃለሁ አለው ቅዱስ ቴዎድሮስም ወርቅህና ብርህ ለጥፋት ይሁንህ እኔስ በንጉሤ በሕያው #እግዚአብሔር ልጅ በ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ባለጸጋና አለቃ ነኝ አለው።

ንጉሡም ለአምላክህ ልጅ አለውን አለው የከበረ ቴዎድሮስም አዎን ከመለኮቱ ባሕርይ የተገኘ ከእርሱ ጋር ዓለምን የፈጠረ በእውነት ልጅ አለው ብሎ መለሰለት ንጉሡም አምላክህን ብናውቀው ልናገኘው እንችላለን አለው ቅዱስ ቴዎድሮስም ወደርሱ ከተመለስክ እንደ እኔ ጭፍራ ትሆናለህ የተወደደ መሥዋዕትም ያደርግሃል አለው።

ንጉሡም ነገር አታብዛ ብዙ ገንዘብ እሰጥህ ዘንድ ለአማልክቶቼ መሥዋዕትን አቅርብ እንጂ አለው የከበረ ቴዎድሮስም ንጉሡን ረገመው ጣዖታቱንም ሰደበ በዚያንም ጊዜ ንጉሡ ተቆጣ። ልብሱንም እንዲገፉት በትምህርቱም ከአመኑ አሕዛብ ጋር በጨለማ ቤት ያሥሩት ዘንድ አዘዘ። የከበረ ቴዎድሮስም ጸለየ በሌሊትም ወጣ ዕንጨቶችንም ሰብስቦ ጣዖቶችን ሁሉ አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጠላቸው እንዳይሰሙ በአገልጋዮቻቸው ላይ #እግዚአብሔር ከባድ እንቅልፍ አሳድሮባቸዋልና።

ለንጉሡም በነገሩት ጊዜ አጽንቶ አሠረውና ልዩ ልዩ በሆነ በጽኑ ሥቃይ አብዝቶ ያሠቃየው ዘንድ ለመኰንኑ ሰጠው መኰንኑም እንዲህ አለው ለንጉሥ ለምን አትታዘዘም ለአማልክቶችስ ለምን አትሠዋም የከበረ ቴዎድሮስም እኔስ ለረከሱ አማልክት አልሠዋም ለከሀዲ ንጉሥም አልታዘዝም ብሎ መለሰለት።

መኰንኑም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ከወንበሩም ላይ ተነሥቶ እንደ ነብር ተወርውሮ አንገቱን አነቀውና የከበረ ቴዎድሮስን በምድር ላይ ጥሎ ፊቱን ጸፋው በእግሮቹም ረገጠው #እግዚአብሔርም ትዕግስቱን አይቶ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ላከለት መኰንኑንም ገድሎ ከምድር ዐዘቅት አሠጠመው ለከበረ ቴዎድሮስም በእስያ ሀገር ውስጥ እየተዘዋወረ የ #ጌታ_የኢየሱስ_ክርስቶስን ሃይማኖት እንዲአስተምር መንፈሳዊ ፀዓዳ ፈረስን ሰጠው።

ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ የከበረ ቴዎድሮስን ከነፈረሱ እንዲይዙት በትምህርቱም የአመኑትን ሁሉ እንዲገድሉ መቶ ፈረሰኞች ወታደሮቹን ላከ። ከሴቶችና ከልጆች በቀር ስድስት ሺህ አርባ ስምንት ሰውን ገደሉ። ሊይዙትም ወደ ቅዱስ ቴዎድሮስ በደረሱ ጊዜ ፈረሱ በላያቸው ተወረወረ ከአፉም እሳትን አውጥቶ አመድ እስኪሆኑ አቃጠላቸው ነገር ግን ሌሎች አግኝተው ያዙትና ወደ ንጉሥ ወሰዱት እርሱም ወደ እሥር ቤት እንዲአስገቡት እንዳይበላና እንዳይጠጣም ደጃፎችን እንዲዘጉበት አዘዘ።

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ተገለጸለትና ቃል ኪዳን ሰጠው በዚያንም ጊዜ ከእሥር ቤት አውጥተው ዘቅዝቀው ሰቀሉት ደሙም እንደ ውኃ እስቲፈስ ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ገረፉት ደሙ የነካቸውም ብዙ በሽተኞች ዳኑ ተአምራቱንም ያዩና የሰሙ በ #ጌታችን አመኑ በዚያችም ቀን መቶ አርባ ስምንት ሰዎች ተገደሉ።

እሊህን የተገደሉትንም ሰማዕታት ወደ እሳት ማንደጃ ውስጥ ከእርሱ ጋር ጨመሩአቸው በዚያንም ጊዜ ነፋስ ነፈሰ መብረቅና ነጐድጓድም ሆነ እሳቱንም አቀዝቅዞት የከበረ ቴዎድሮስ ምንም ሳይነካው ከእሳት ውስጥ ወጣ።

ከዚህም በኋላ ንጉሡ የሚያደርግበትን በአጣ ጊዜ ኃምሣ አራት ልጥር የሚመዝን ልጓም አምጥተው አፉን እንዲለጒሙት እግሮቹንና እጆቹንም በችንካር ቸንክረው ለአንበሳ እንዲጥሉት አዘዘ። አንበሳውም ዕንባውን እያንጠባጠበ እንደ ሰው አለቀሰለት እንጂ ምንም አልነካውም። #ጌታችንም ተገለጠለትና ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ዕድል ፈንታውን ከርሱ ጋር በመንግሥተ ሰማያት ያደርግ ዘንድ ቃል ኪዳንን ሰጠው።

ከዚህም በኋላ የሁለት መቶ ሰው ሸክም ዕንጨት መቶ ልጥር ባሩድ መቶ ልጥር የዶሮማር መቶ ልጥር ነሐስ አመጡ ከማንደጃውም ጨምረው እጅግ እስከሚግል አነደዱት ጸሎቱንም ከፈጸመ በኋላ ቅዱስ ቴዎድሮስን ወደ ነደደው እሳት ወረወሩት ምስክርነቱንም ፈጸመ የመላእክት አለቆች ቅዱሳን ሚካኤልና ገብርኤል ነፍሱን ተቀበሉ በሦስት አክሊላትም አቀዳጁት ሥጋውንም አውሳብያ የተባለች የመኰንኑ ሚስት ወሰደች ዋጋው ብዙ በሆነ ሽቱም ገነዘችውና ወደ ገላትያ ወሰደችው በዕብነ በረድ ሣጥንም አድርጋ በዚያ ቀበረችው ቤተ ክርስቲያንም ሠራችለት ከሥጋውም ታላላቆች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጹ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

#ሰላም_ለክሙ_አምዓት_ስሳ። ወበበዐሠርቱ ሠላሳ #ማኅበራነ_ቴዎድሮስ_ማር_መኵሴ_ቴዎድሮስ ዕጓለ አንበሳ። እምኂሩትክሙ ብየ ኃሠሣ። ታናሕስዩ ሊተ ክቡደ አበሳ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_28። 

የካቲት 28 ቀን የሚከበሩ #ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)
2."6,304" ሰማዕታት (በቅ/ቴዎድሮስ አምላክ አምነው ሰማዕትነት የተቀበሉ)

#ወርኀዊ በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን
2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)
3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
4.ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ

=>+"+ እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን:: +"+
(ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ. 73)

በግዕዝ➞ #ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ።
ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን።

ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ #ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ #ኢየሱስ_ክርስቶስ።

በአማርኛ➞ #ጌታ_ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

06 Mar, 13:09

1,896

ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የ #ጌታ እናቱ በ #ማርያም ጸሎት #ኢየሱስ_ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አቡነ ዘበሰማያት(አባታችን ሆይ)...... ይበሉ!!!

††† ወስብሐት #ለእግዚአብሔር †††

#ስንክሳር_ዘወርኃ_የካቲት_28
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

05 Mar, 19:38

3,874

#የየካቲት_27_ግጻዌ

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#የካቲት_27_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሮሜ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤
⁶ ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።
⁷-⁸ ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን፤
⁹ ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና።
¹⁰ መሞትን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለኃጢአት ሞቶአልና፤ በሕይወት መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል።
¹¹ እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ።
¹² እንግዲህ ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።
²² እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤
²³ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
²⁴ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።
²⁵ እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁶ የሁሉ ጌታ በሚሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እየሰበከ ይህን ቃል ወደ እስራኤል ልጆች ላከ።
³⁷ ዮሐንስ ከሰበከው ጥምቀት በኋላ ከገሊላ ጀምሮ በይሁዳ ሁሉ የሆነውን ነገር እናንተ ታውቃላችሁ።
³⁸ እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤
³⁹ እኛም በአይሁድ አገርና በኢየሩሳሌም ባደረገው ነገር ሁሉ ምስክሮች ነን፤ እርሱንም በእንጨት ላይ ሰቅለው ገደሉት።
⁴⁰ እርሱን እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን አስነሣው ይገለጥም ዘንድ ሰጠው፤
⁴¹ ይኸውም ለሕዝብ ሁሉ አይደለም ነገር ግን በእግዚአብሔር አስቀድሞ የተመረጡ ምስክሮች ለሆንን ለእኛ ነው እንጂ፤ ከሙታንም ከተነሣ በኋላ ከእርሱ ጋር የበላን የጠጣንም እኛ ነን።
⁴² ለሕዝብም እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንደ ሆነ እንመሰክር ዘንድ አዘዘን።
⁴³ በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል።
⁴⁴ ጴጥሮስ ይህን ነገር ገና ሲናገር ቃሉን በሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#የካቲት_27_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
" #እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም። ወገብረ መድኃኒት በማእከለ ምድር። አንተ አጽናዕካ ለባሕር በኃይልከ"። መዝ 73፥12-13።
#ትርጉም #"እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥ በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ። አንተ ባሕርን በኃይልህ አጸናሃት፤ አንተ የእባቦችን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበርህ"። መዝሙር 73÷12- 13።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#የካቲት_27_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ዮሐንስ 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ ስለዚህ በዚያን ጊዜ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጣቸው።
¹⁷ ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ።
¹⁸ በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ።
¹⁹ ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም፦ የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሚል ነበረ።
²⁰ ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር።
²¹ ስለዚህ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን፦ እርሱ፦ የአይሁድ ንጉስ ነኝ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ አሉት።
²² ጲላጦስም፦ የጻፍሁትን ጽፌአለሁ ብሎ መለሰ።
²³ ጭፍሮችም ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ሆኖ በአራት ከፋፈሉት፤ እጀጠባቡን ደግሞ ወሰዱ። እጀ ጠባቡም ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ አልነበረም።
²⁴ ስለዚህ እርስ በርሳቸው፦ ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባሉ። ይህም፦ ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#የሚቀደሰው_ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የመድኃኒታችን የስቅለቱ መታሰቢያ፣ እና የጾም ወራት ለሁላችንም ይሁንልን።         
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

05 Mar, 17:52

3,747

በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በአደባባይ በሚሰብክበት ጊዜ፣ አንድ ሌባ በህዝቡ መሃል እየተንቀሳቀሰ ነበር።

ሌባው ወደዚህ የመጣው ስብከቱን ለመሰማት ሳይሆን ከሰዎች ኪስ ለመስረቅ ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መናገር ሲጀምር ሌባው በስብከቱ ተማርኮ ፈዞ ቆመ፥ የመጣበትንም የመጀመሪያ ዓላማውን ረሳው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ቃላት ማራኪ ከመሆናቸው የተነሳ የሌባወን ሕሊና በጥልቀት ነኩ።

ሌባው ስለ ንስሐ፣ ስለ ይቅርታ እና በጎ ሕይወት ከቅዱስ የሐንስ አፈወርቅ ከሰማ በኋላ የወንጀል ሕይወቱን ለመተው ወሰነ፡፡ ከስብከቱ በኋላ፣ ወደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቀረበ ኃጢአቱንም ተናዘዘ፤ እናም መንገዱን እንዴት መለወጥ እንዳለበት ምክርን ጠየቀ። በርኀራኄው የሚታወቀው ቅዱስ ዮሐንስም ሌባውን ተቀብሎ አዲስ ሕይወት እንዲጀምር ረዳው፡፡

ይህ ታሪክ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስብከቶች ከየትኛውም ሕይወት የመጡ ሰዎችን፣ ከመልካም ምግባር የራቁትን ሳይቀር ወደ እግዚአብሔር መመለስ ለመቻላቸው ምስክር ነው።

ስብከቱ አእምሮአዊ ብቻ ሳይሆን ሕይወትን የሚለውጥ፣ የአድማጮቹን ልብ የሚነካና መልካም ሕይወት እንዲመሩ የሚያደርግም ነው።
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

05 Mar, 16:50

2,648

#የካቲት_27

የካቲት ሃያ ሰባት በዚች ዕለት #የመድኃኒታችን_የስቅለቱ_መታሰቢያ_ነው። ይቅርታውና ቸርነቱ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን። የአንፆኪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አንስጣስዮስ አረፈ፣ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ #አቡነ_ዓምደ_ሥላሴ እረፍታቸው ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አንስጣስዮስ_ሊቅ

የካቲት ሃያ ሰባት በዚች ቀን በታላቁ ንጉስ በቈስጠንጢኖስ ዘመን የከበረ አባት የአንፆኪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ትምህርቱ በአለም የመላ አንስጣስዮስ አረፈ።

የከበሩ አባቶችም በኒቅያ ከተማ የአንድነት ስብሰባ በአደረጉ ጊዜ በዚህ ጉባኤ ከተሰበሰቡት ሊቃውንት አንዱ እርሱ ነው በዚህም ጉባኤ ተስማምተው አርዮስን ከባልንጀሮቹ ጋር አውግዘው ለይተውታል ባልንጀሮቹም የቂሳርያ አውሳቢዮስ የኒቆምድያ አውሳቢዮስና አርናሲስ ናቸው። እነዚህም በ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ታውቀዋል።

እንዚህ የከበሩ አባቶች ስርአትን ሰርተው ወደ የሀገራቸው በተመለሱ ጊዜ እነዚህ ከኤጲስቆጶስነት ሹመት የተሻሩት ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄዱ መስለው ወጡ ወደ አንፆኪያም ከተማ ገብተው ለአንዲት አመንዝራ ሴት ዘንድ ተሰበሰቡ ብዙ ገንዘብም ሊሰጣት ቃል ገቡላት ወደ ቤተክርስቲያን እንድትገባ ይህ አባት ከእርሷ ጋር እንዳመነዘረ የወለደችውም ልጅ የእርሱ እንደሆነ በዚህ ቅዱስ አባት አንስጦስዮስ ላይ ለካህናቱና ለህዝቡ እንድትናገር አስተማሩዋት።

ህዝቡም እንዲህ አሏት አንቺ ሀሰተኛ ነሽ በዚህ ቅዱስ አባትም ላይ ሀሰትን ተናግረሻል በከበረ ወንጌል ካልማልሽ በቀር ቃልሽን አንቀበልም አሏት። እርሷም ስለገንዘብ ፍቅር በሀሰት ማለች። ከዚህም በኃላ ለንጉስ ነግረው ከመንበረ ሲመቱ ወደ አጥራኪያ ደሴት አሳደዱት በስደትም ሳለ በርሷ አረፈ።

ነገር ግን ለእነዚህ ከሀዲያን ወዮላቸው የ #እግዚአብሄርን ልጅ ከመለኮቱ ባህርይ ለይተው ፍጡር ነው ብለውታልና ይህንንም ንፁህ አባት ሰይጣን አባታቸው እንዳስተማራቸው ከአመንዝራ ጋር አንድ ሆነው በተንኮል ከመንበረ ሲመቱ አውጥተውታልና።

#እግዚአብሔር ግን ቸል አላለም ይህን አባት ከአሳደዱት በኃላ ያቺ አመንዝራ ሴት ጭንቅ በሆነ ደዌ ተይዛ ብዙ ተሰቃየች ለሞትም ተቃረበች ያን ጊዜም ይህ ሁሉ የደረሰባት በከበረ ወንጌል በሀሰት ስለማለች እንድሆነ ተገነዘበች። በአንፆኪያም ሰዎች ሁሉ ፊት በደሏን አመነች እንዲህም አለቻቸው፦ ይህ ቅዱስ አንስጣስዮስ ከዝሙት ንፁህ ነው እነዚያ ከሀዲያን ብዙ ገንዘብ ሰጥተውኝ በእርሱ ላይ ሀሰትን እንድናገር በከበረ ወንጌልም በሀሰት እንድምል አደረጉኝ እንጂ።

የአንፆኪያ አገር ሰዎችም ኃጢአቷን ማመኗን በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ ካህናቱም በፀሎትና በቅዳሴ ጊዜ ስሙን የሚያነሱ ሆኑ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም አመሰገነው በመታሰቢያውም ቀን ስለ ውለታው የውዳሴ ድርሳን ጽፎለታል::

#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አንስጣስዮስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ጻድቁ_አቡነ_ዓምደ_ሥላሴ

የካቲት 27 ዳግመኛም በዚህች ቀን አቡነ ዓምደ #ሥላሴ እረፍታቸው ነው፡፡ አቡነ ዓምደ ሥላሴ የትውልድ ሀገራቸው ጎጃም ሲሆን በዐፄ ሱስንዮስ ዘመን የነበሩ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደርጉ የነበሩ ገዳማዊ መነኩሴ ናቸው፡፡ ጻድቁ ማኅበረ #ሥላሴን ያቀኑ ታላቅ አባት ሲሆኑ በተለይም አንድ የሚታወቁበት ትልቅ ታሪክ አላቸው፡፡ እርሱም ዐፄ ሱስንዮስ ካቶሊካውያን ደግፈው 8ሺህ የሀገራችንን ሊቃውንት በአንድ ቀን ባሳረዱ ጊዜ ንጉሡ ወዲያው ‹‹ኦርቶዶክስ ይርከስ ካቶሊክ ይንገስ›› ብሎ ያወጀበት ምላሱ ተጎልጉሎ ወጣ፡፡ እንደ አርዮስም ሆዱ አብጦ አንጀቱ ተልቶ ሊሞት ባለ ሰዓት አቡነ ዓምደ #ሥላሴ አዘዞ ድረስ ሄደው ‹‹ፋሲል ይንገሥ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ትመለስ የሱስንዮስም ምላስ ይመለስ›› በማለት ተጎልጉሎ የወጣውን ምላሱን በመስቀላቸው ቢባርኩት ምላሱ ተመልሶለታል፡፡

ዐፄ ሱስንዮስ ግን ለካደበት ክህደት ቅጣቱ ነውና በመቅሰፍቱ ሳይድን በዚያው ታሞ ማቆ ማቆ ክፉ አሟሟት ሞቷል፡፡ ከዚህ በኋላ አቡነ ዓምደ #ሥላሴ የዐፄ ፋሲልን ሹመትና ሃይማኖትን በአዋጅ አጽንተው ተመልሰው ወደ ገዳማቸው ማኅበረ #ሥላሴ ገዳም ገብተዋል፡፡ ዐፄ ፋሲልንም የማኅበረ #ሥላሴን ገዳም ግዛቱን ከሱዳን እስከ ጣቁሳ ድረስ እንዲሆን በአዋጅ ወስነው ሰጥተውት ነበር ነገር ግን ላይጠቀምበትና ላይጸና ነገር የደርግ መንግሥት የገዳሙን ሥርዓት ከማፍረሱም በላይ ርስት ጉልቱን ነጥቆ ወሰደበት፡፡

በደርቡሾች ወረራ ጊዜ እንግሊዞች አጋጣሚውን ተጠቅመው የአቡነ ዓምደ #ሥላሴን ቅዱስ ገድል ዘርፈው ወስደውታል፡፡ ዛሬ በእንግሊዝ ሀገር ገድለ አቡነ ዓምደ #ሥላሴ ይገኛል፡፡ ጻድቁ የካቲት 27 ቀን ያረፉ ሲሆን ዐፅማቸው በዚያው በመሠረቱት በማኅበረ #ሥላሴ ገዳም በክብር ተቀምጧል፡፡

#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋር ትሁን አሜን፡፡

††† የካቲት 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ አንስጣስዮስ ርቱዓ ሃይማኖት (ዘአንጾኪያ)
2.አቡነ ዓምደ ሥላሴ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
2.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
4.ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
5.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
6.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
7.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት

††† "የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::" †††
(1ዼጥ. 2:21-25)

በግዕዝ➞ #ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ።
ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን።

ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ #ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ #ኢየሱስ_ክርስቶስ።

በአማርኛ➞ #ጌታ_ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።

ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የ #ጌታ እናቱ በ #ማርያም ጸሎት #ኢየሱስ_ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አቡነ ዘበሰማያት(አባታችን ሆይ)...... ይበሉ!!!

††† ወስብሐት #ለእግዚአብሔር †††

#ስንክሳር_ዘወርኃ_የካቲት_27
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

05 Mar, 05:48

4,615

🎵 #መዝሙር
🔴 አዲስ ዝማሬ " ከበጎችህ መሀል " ዘማሪ ቀሲስ ብርሃን እሸቱ @EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs

For any suggestion or question 👇 http://t.me/KIDAN_MEHRET_ENATEbot

For more join 👇
@EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs

Bot configuration by:- @gutaitagu16
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

05 Mar, 04:15

4,518

እስራኤል ለ #እግዚአብሔር የተለየች ነበረች፡፡ የተቀደሰች ነበረች፡፡ እርሷ ግን አምላኳን ትታ ፊቷን ወደ በአል አዙራለች፡፡ ለጣዖት የተሠዋውን መሥዋዕት መመገብ ዠምራለች፡፡ ደግነትን ጥላለች፡፡ ከ #እግዚአብሔር ውጪ ለራሷ ነገሥታትን ሾማለች፡፡ ነፋስን ዘርታ ዐውሎ ነፋስን አጭዳለች፡፡ በአሕዛብ መካከል እንደ ረከሰ ዕቃ ኾናለች፡፡ ፈጣሪዋን ረስታለች፡፡ የ #እግዚአብሔር ጉባዔ መኾኗ ቀርቶ የዲያብሎስ መፈንጫ ኾናለች፡፡ በ #እግዚአብሔር ክንድ መደገፍን ትታ በአሦርና በግብጽ ትተማመን ዠምራለች /ሆሴ.፰/፡፡ ከዚኽ ኹሉ እንድትወጣና ወደ ፈጣሪዋ እንድትመለስም #እግዚአብሔር ይጠራታል፡፡

የትንቢተ ሆሴዕ ሌላውና ዋናው ዓላማም እስራኤል ከዚኽ ድርጊቷ ተመልሳ በንጽሕናና በቅድስና ከሙሽራዋ ከ #እግዚአብሔር ጋር በፍቅር እንድትኖር መጋበዝ ነው /ሆሴ.፲፬/፡፡ ነቢዩ ሆሴዕ ሕዝቡ ምን ያኽል ኃጢአታቸው በዝቶ ከሞት አፋፍ ላይ እንዳደረሳቸው ይናገርና፥ ቢመለሱ ግን ይኽ ሞት እንደሚዋጥ ተስፋን ይሰጣቿል /ሆሴ.፲፫፡፲፬/፡፡ ተወዳጆች ሆይ! እንዲኽ ኃጢአተኞች ለምንኾን ለእኛም የተከፈተልንን የድኅነት ተስፋ ልንጠቀምበት ያስፈልጋል፡፡ ምንም ያኽል አመንዝሮች ብንኾንም #እግዚአብሔር #እግዚአብሔር ነው፡፡ እስከተመለስን ድረስ እንደ ደናግላን አድርጐ ይቀበለን ዘንድ የታመነ ወዳጅ ነው፡፡ የፍቅሩ ልኬት እንዲኽ ነው ተብሎ የሚመጠን አይደለምና በ #እግዚአብሔር ፊት የሚዘጋ የንስሐ በር የለም፡፡ አኹን ያለንበት ዘመን #እግዚአብሔር መጥቶ ጽድቅን እስኪያዘንብልን ድረስ እርሱን የምንሻበት ዘመን ነው፡፡ እንኪያስ በጽድቅ እንዝራ፤ እንደ ምሕረቱ መጥንም እንጨድ፤ ጥጋታችንም እንረስ፡፡ ክፋትን አርሰን ኃጢአትን ማጨድ ይብቃን፡፡ የሐሰትንም ፍሬ መብላት ይብቃን /ሆሴ.፲፡፲፪-፲፫/፡፡

#በአጠቃላይ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስተምሩት የትንቢተ ሆሴዕ ዋና መልእክት ፍቅረ #እግዚአብሔርን መግለጥ ስለኾነ “የብሉይ ኪዳን ዮሐንስ” ይሉታል /ሆሴ.፪፡፳፩-ፍጻሜ/፡፡ መጽሐፈ ሆሴዕ ክብር ይግባውና ስለ #ጌታችንና_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደዚኽ ዓለም መምጣት /ሆሴ.፮፡፩-፫/፣ ወደ ግብጽ መሰደድና መመለሱ /ሆሴ.፲፩፡፩/፣ ስለ ሞቱና ትንሣኤው በኅብረ አምሳል ያስተምራል /ሆሴ.፲፫፡፲፬/፡፡ በሐዲስ ኪዳንም በብዛት ተጠቅሶ ይገኛል /ሮሜ.፱፡፳፭-፳፮/፡፡

የትንቢተ ሆሴዕን መጽሐፍ እንደሚከተለው መክፈል እንችላለን፡፡
1. የእስራኤል ነባራዊ ኹኔታ ምን እንደሚመስል /ምዕ.፩-፫/፤
2. #እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለው ተግሳጽ /ምዕ.፬-፲/፤
3. የድኅነት ተስፋ /ምዕ.፲፩-፲፫/፤
4. የንስሐ ፍሬ ምን እንደኾነ /ምዕ.፲፬/፡፡

የነቢዩ ሆሴዕ የመጨረሻ ዕረፍት
ነቢዩ ሆሴዕ እንዲኽ እስራኤልን እያገለገለ ከኖረ በኋላ በመልካም ሽምግልና በሰላም በፍቅር ዐረፈ፡፡ መታሰቢያውም የካቲት ፳፮ ላይ ነው፡፡
ምስጋና #ለእግዚአብሔር ይኹን፤ የነቢዩ ሆሴዕ በረከትና ረድኤትም ከኹላችን ጋር ትደር ለዘለዓለሙ አሜን!!!

Ø የትንቢተ ሆሴዕ አንድምታ መቅድም፤
Ø የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤
Ø ስንክሳር፤
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

05 Mar, 04:15

4,296

#ነቢዩ_ሆሴዕ

በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

“ሆሴዕ” ማለት ከ፲፪ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ሲኾን የስሙም ትርጓሜ “መድኃኒት” ማለት ነው፡፡ መድኃኒት መባሉም እንደ ኢያሱ ወልደ ነዌ ባጭር ታጥቆ፥ ጋሻ ነጥቆ፥ ዘገር ነቅንቆ አማሌቃውያንን አጥፍቶ እስራኤልን አድኖ፥ እንደ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋዉን ቆርሶ፥ ደሙን አፍስሶ፥ ፲፫ቱን ሕማማተ #መስቀል ታግሦ፥ አጋንንትን ድል ነስቶ ነፍሳትን አድኖ አይደለም፤ አባት እናቱ በትንቢቱ በትምህርቱ እንዲያድን አውቀው “ሆሴዕ - መድኃኒት” ብለዉታል እንጂ፡፡ ስለዚኽ የስሙ ትርጓሜ ተልእኮውን የሚያስረዳ ነው ማለት ነው፡፡

#ነቢዩ_ሆሴዕ እስራኤላውያን (ሰማርያ - ሰሜናዊው ክፍል) በ፯፻፳፪ ቅ.ል.ክ. በአሦራውያን ወደ ምርኮ ከመኼዳቸው በፊት፥ ዳግማዊ ኢዮርብዓም በሰማርያ ነግሦ በነበረበት ዘመን በእስራኤል (በሰሜናዊው) መንግሥት ተነሥቶ የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ከመጽሐፉ መረዳት እንደምንችለውም ነቢዩ ሆሴዕ በሚያገለግልበት ወራት ነቢዩ ኢሳይያስ፣ ነቢዩ ሚክያስና ነቢዩ አሞጽም ያገለግሉ ነበር /ሆሴ.፩፡፩/፡፡

#ነቢዩ_ሆሴዕ ባለትዳር ነው፡፡ ሚስቱም “ጎሜር” እንደምትባል ተጠቅሷል /ሆሴ.፩፡፫/፡፡ ከመጽሐፉ ማንበብ እንደምንችል “ጎሜር” ጋለሞታ ነበረች፡፡ መተርጕማን እንደሚያስተምሩት ግን፡- “የጎሜር ጋለሞታ ተብላ መጠራት በኹላችንም ልቡና እንደሚመጣ የወንድና የሴት ዓይነት ግልሙትና አይደለም፡፡ #እግዚአብሔር ያላዘዘውን ሥራ መሥራትም ዝሙት ነውና ጎሜር ጣዖትን ታመልክ ስለነበረ ነው” ይላሉ፡፡ #እግዚአብሔር ነቢዩን ይኽቺ ሴት እንዲያገባ ያደረገውም ሕዝቡ ምን ያኽል ከ #እግዚአብሔር ርቆ እንደነበርና ከጣዖታት ጋር እንደምን ያለ አንድነት ፈጥረው እንደነበሩ በምሳሌ ሲናገራቸው ነው፡፡

በደንብ ካስተዋልነው ሆሴዕ ማለት መድኃኒት ነው፡፡ ጎሜር ደግሞ ጋለሞታ ናት፡፡ ይኽ መድኃኒት የተባለ ሆሴዕ ይኽቺን ሴት አግብቷታል፡፡ በጣም ይወዳት እንደነበረም ተገልጧል፡፡ በዚኽም እውነተኛው መድኅን ( #ኢየሱስ) የገዛ መንገዳችንን ተከትለን በጠፋንበት ወራት እኛን ከመውደዱ የተነሣ እንደፈለገንና ከእኛ ጋርም እንደተዋሐደ ምስጢርን የሚያስረዳ ነው /ሆሴ.፫፡፩/፡፡ በአጭሩ ይኽቺ ሴት (ጎሜር) የምእመናን ምሳሌ ናት፡፡

#ነቢዩ_ሆሴዕ ከባለቤቱ ከጎሜር ሦስት ልጆችን ወልዷል፡፡ #የመዠመሪያው ልጅ ወንድ ሲኾን “አይዝራኤል” ይባላል፤ ይኸውም “የናቡቴን ደም ተበቅዬ ኢይስራኤል በተባሉበት ቦታ አጠፋቸዋለኹ” ለማለት ነው፡፡ #ኹለተኛይቱ ሴት ስትኾን “ሎሩሃማ - ምሕረት ዘአልባ - ምሕረት የሌላት” ትባላለች፤ ይኸውም “የእስራኤልን ወገኖች ዳግመኛ ይቅር አልላቸውምና” ለማለት ነው፡፡ #ሦስተኛው ልጅ ወንድ ሲኾን “ሎዓሚ - ኢሕዝብ - ሕዝቤ ያልኾነ” ይባላል፤ ይኸውም “እናንተ ወገኖቼ አይደላችሁምና እኔም አምላካችሁ አይደለኹም” ለማለት ነው፡፡ ይኼ ኹሉ መባሉ ምንም እንኳን አባታቸው “ሆሴዕ - መድኃኒት” ቢኾንም ሕዝቡ እስካልተመለሱ ድረስ እንደሚጠፉ፣ ምሕረት እንደማያገኙ፣ ሕዝቡ እንደማይባሉ እርሱም አምላካቸው እንደማይባል ሲገልጽ ነው፡፡ ነፍሳችን እንዲኽ ወደ መድኃኒቷ ካልተመለሰች እንዲኽ መባሏ የማይቀር ነው፡፡ እንዲኽ ከመባልስ #እግዚአብሔር ይሰውረን፡፡

#ነቢዩ_ሆሴዕ በራሱ መጽሐፍ እንደነገረን በዘመኑ የነበሩት ነገሥታት ስድስት ናቸው፡፡ በይሁዳ በኵል የነበሩት ዖዝያን፣ ኢዮአታም፣ አካዝና ሕዝቅያስ ሲኾኑ፤ በእስራኤል በኵል የነበሩት ደግሞ ዮአስና ኢዮርብዓም ናቸው /ሆሴ.፩፡፩/፡፡ ስለዚኽ የነቢዩ የአገልግሎት ዘመን ከ፯፻፹፯ አንሥቶ እስከ ፮፻፺፯ ቅ.ል.ክ. ድረስ ገደማ ነው ማለት ነው፡፡

በዚኽ ስም የሚጠሩ ሌሎች ሦስት ሰዎች አሉ፡፡ ከእነርሱ አንዱ ከሰሜናዊው የእስራኤል መንግሥት ነገሥታት የመጨረሻውና በእርሱ ዘመነ መንግሥት ሰማርያ የወደቀችው ንጉሥ ነው፡፡

#ነቢዩ_ሆሴዕ የነበረበት ነባራዊ ኹኔታ

ነቢዩ ሆሴዕ በነበረበት ወራት ሕዝቡ በምን ዓይነት ግብረ ገብነታዊና ሃይማኖታዊ ውድቀት እንደነበሩ ከመጽሐፉ በግልጽ ማንበብ እንችላለን፡፡ ትንቢተ ሆሴዕን ስናነብ በሕዝቡ ዘንድ መገዳደል፣ ዝሙት፣ ጣዖትን ማምለክ፣ ትዕቢት፣ … ተንሰራፍቶ እንደነበር እንገነዘባለን፡፡ በየትኛውም ዓይነት ደረጃ ያለ ሰው #እግዚአብሔርን የረሳበት ዘመን ነበር /ሆሴ.፲፫፡፮/፡፡ ለዚኽም ነው ነቢዩ ሆሴዕ፡- “ምድሪቱ ከ #እግዚአብሔር ርቃ ታላቅ ግልሙትና ታደርጋለች” /ሆሴ.፩፡፪/፤ “እውነትና ምሕረት #እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም” /ሆሴ.፬፡፩/፤ “ስለዚኽ ምድሪቱ ታለቅሳለች” /ሆሴ.፬፡፫/ እያለ የተናገረው፡፡ ሕዝቡ እውቀትን ከማጣት የተነሣ ጠፍቷል /ሆሴ.፬፡፩፣፮/፡፡

ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ነቢዩ ሆሴዕ በሚያገለግልበት ዘመን የነበሩት ነገሥታት ፮ ናቸው፡፡ ከዚኽም በተጨማሪ፡- “ንጉሥ የለንም” ብሎ እንደተናገረው ዙፋኑ ለ፲፩ ዓመታት ያኽል ባዶ ነበር /ሆሴ.፲፡፫/፡፡ በዙርያም የአሦር መንግሥት ተደጋጋሚ ጥቃትን ሲያደርስ ነበር፡፡ ነቢዩ ተግሳጹን ጠንከር ያደረገውም ከዚኽ ነባራዊ ኹኔታ የተነሣ ነው፡፡

#ትንቢተ_ሆሴዕ

ትንቢተ ሆሴዕ ፲፬ ምዕራፍን የያዘ መጽሐፍ ሲኾን እጅግ ግሩምና አኹን ካለንበት ነባራዊ ኹኔታ ጋር በጣም የሚመሳሰል ነው፡፡ ይኸውም እንደሚከተለው በአጭር በአጭሩ ማየት እንችላለን፡-

የዚኽ መጽሐፍ የመዠመሪያው ዓላማ #እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያለውን አንድነት የሚገልጥ ነው፡፡ ምንም እንኳን እስራኤል (የሰው ልጅ) ጋለሞታ ብትኾንም #እግዚአብሔር ይወዳታል፡፡ እጮኛው እንትኾን፣ ለዘለዓለም በሰማያዊው ጫጉላ ከእርሱ ጋር ተዋሕዳ እንድትኖር፣ ጽድቅና እውነት የሚባሉ ልጆችም እንድትወልድለት ይፈልጋል /ሆሴ.፪፡፳፩/፡፡ ለብቻው እንደሚቀመጥ የምድረ በዳ አህያ ወደ አሦር መውጣቷን እንድትተው፣ ለአሕዛብ የምትሰጠውን እጅ መንሻ ትታ እንድትመለስ ይሻል /ሆሴ.፰፡፱/፡፡ ወዳጄ ሆይ! እኔና አንተም ወደዚኽ አንድነት እየተጠራን ነውና ከጋለሞታነታችን ተመልሰን እጮኛችንን ለመቀበል የሰርግ ልብሳችንን እናዘጋጅ /ማቴ.፳፭/፡፡

የዚኽ መጽሐፍ ሌላው ዓላማ እስራኤል ምን ያኽል በደዌ እንደተያዘች መግለጥና /ሆሴ.፭፡፲፫/ ብቸኛው መድኃኒቷ #እግዚአብሔር መኾኑን መግለጥ ነው /ሆሴ.፲፬፡፬/፡፡ በሌላ አገላለጽ የያዛት ደዌ ምን ያኽል አደገኛ እንደኾነ አውቃ ዘይትን አፍስሶ ወደሚያድናት ሐኪሟ እንድትመለስ ማድረግ ነው፡፡ በመጽሐፉ እንደተገለጸ ለያዛት ደዌ ምንጩ ብዙ ነው፡፡ ጥቂቶቹን ለመግለጽ ያኽልም፡- ከ #እግዚአብሔር ርቃ ምድራዊ ነገር ላይ ብቻ መባከኗ /ሆሴ.፩፡፪/፤ እውቀትን ከማጣቷ የተነሣ /ሆሴ.፬፡፮/፤ ትዕቢቷ /ሆሴ.፭፡፭/፤ በ #እግዚአብሔርና በዲያብሎስ፣ በአምልኮተ #እግዚአብሔርና በአምልኮተ ጣዖት፣ በመልካምና በክፉ ነገር መካከል ያለውን ድምበር ማፍረሷ /ሆሴ.፭፡፲/፤ #እግዚአብሔር ክፋቷን እንደሚያስበው እርሷ አለማሰቧ /ሆሴ.፯፡፪/፤ ከ #እግዚአብሔር ዘንድ ምሕረትን እየፈለገች ግን ደግሞ ከእርሱ ጋር አንድነትን መፍጠር መጥላቷ /ሆሴ.፯፡፲፬/፤ ከምድር ፍሬ ብቻ ደስታን አገኛለኹ ስትል እውነተኛውን ደስታ ማጣቷ /ሆሴ.፱፡፲፮/፤ ወእለ ዘተርፈ መግለጽ እንችላለን፡፡ ተወዳጆች ሆይ! እኛስ በዚኽ ቃል ስንመዘን ምን ያኽል በደዌ ተይዘን ይኾን? ታድያ መቼ ነው የምንታከመው?
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

19 Feb, 19:14

1,264

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#የካቲት_13_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ቆሮ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ትምክህት የሚያስፈልግ ነው፤ አይጠቅምም ነገር ግን ከጌታ ወዳለው ራእይና መገለጥ እመጣለሁ።
² ሰውን በክርስቶስ አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም ወይም ከሥጋ ውጭ እንደ ሆነ አላውቅም፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤ እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ።
³ እንዲህ ያለውንም ሰው አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ ወይም ያለ ሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤
⁴ ወደ ገነት ተነጠቀ፥ ሰውም ሊናገር የማይገባውን የማይነገረውን ቃል ሰማ።
⁵ እንደዚህ ስላለው እመካለሁ፥ ስለ ራሴ ግን ከድካሜ በቀር አልመካም።
⁶ ልመካ ብወድስ ሞኝ አልሆንም፥ እውነትን እላለሁና፤ ነገር ግን ማንም ከሚያይ ከእኔም ከሚሰማ የምበልጥ አድርጎ እንዳይቆጥረኝ ትቼአለሁ።
⁷ ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።
⁸ ስለዚህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።
⁹ እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።
¹⁰ ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።
¹¹ በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ፤ እናንተ ግድ አላችሁኝ፤ እናንተ እኔን ልታመሰግኑ ይገባ ነበርና። እኔ ምንም ባልሆን እንኳ፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አልጎድልምና።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶-⁷ በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።
⁸-⁹ እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።
¹⁰ ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² ያን ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ።
²³ እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ።
²⁴ ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥
²⁵-²⁶ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳቸውን ከሰጡት ከምንወዳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር የተመረጡትን ሰዎች ወደ እናንተ እንልክ ዘንድ በአንድ ልብ ሆነን ፈቀድን።
²⁷ ራሳቸውም ደግሞ በቃላቸው ያንኑ ይነግሩአችሁ ዘንድ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል።
²⁸-²⁹ ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።
³⁰ እነርሱም ተሰናብተው ወደ አንጾኪያ ወረዱ፥ ሕዝቡንም ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጡአቸው።
³¹ ባነበቡትም ጊዜ ከምክሩ የተነሣ ደስ አላቸው።
³² ይሁዳና ሲላስም ደግሞ ነቢያት ነበሩና ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው አጸኑአቸው።
³³ አያሌ ቀንም ከተቀመጡ በኋላ ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ሐዋርያት ሄዱ።
³⁴ ሲላስ ግን በዚያ ይኖር ዘንድ ፈቀደ።
³⁵ ጳውሎስና በርናባስም ከሌሎች ከብዙ ሰዎች ጋር ደግሞ የጌታን ቃል እያስተማሩና ወንጌልን እየሰበኩ በአንጾኪያ ይቀመጡ ነበር።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#የካቲት_13_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"አይቴኑ አሐውር እመንፈስከ። ወአይቴ እጎይይ እምቅድመ ገጽከ። እመኒ ዐረጉ ውስተ ሰማይ ሀየኒ አንተ። መዝ.138÷7-8
"ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ"። መዝ.138÷7-8
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#የካቲት_13_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁷ አታመንዝር እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
²⁸ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።
²⁹ ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻልሃልና።
³⁰ ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻላልና።
³¹ ሚስቱን የሚፈታት ሁሉ የፍችዋን ጽሕፈት ይስጣት ተባለ።
³² እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ሠለስቱ_ምዕት_ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ አውሳብዮስ ጻድቅ፣ የቅዱስ ሰርግዮስ ሰማዕት፣ የቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት፣ የአባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ የዕረፍት በዓልና የቅዱስ ፊቅጦር የልደት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

19 Feb, 17:46

1,667

እንዲህም ሆነ ከሕዝቡ ውስጥ አንድ ታናሽ ሕፃን #እግዚአብሔር ዐይኖቹን ገልጦለት የቅዱሳን ሰማዕታትን ነፍሶቻቸውን መላእክት ወደ ሰማያት ሲያወጧቸው አይቶ " #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ ይቅር በለኝ" እያለ በከፍተኛ ቃል ጮኸ እናትና አባቱም መኰንኑ ሰምቶ ስርሱ እንዳያጠፋቸው አፋን የሚዘጉ ሆኑ እርሱ ግን እንዲህ እያለ መጮኹን አልተወም በላዩ እስከ ተኙበትና ነፍሱን እስከ አሳለፈ ድረስ ከሰማዕታትም ጋር የምስክርነት አክሊልን ተቀበለ።

ለ #እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታት በጸሎቱ ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት13 ስንክሳር።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#የእስክንድርያ_አገር_ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_ጢሞቴዎስ፦ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሁለተኛ ነው። ይህንንም አባት ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራና ችግር ደርሶበታል ። እንዲህም ሆነ በዚያ ወራት የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሳዊሮስ ወደ ግብጽ አገር መጣ እርሱም ከዚህ አባት ጢሞቴዎስ ጋር ምእመናንን እያጽናና ከሀገር ወደ ሀገር ከገዳም ወደ ገዳም ከቦታ ወደ ቦታ የሚዘዋወር ሆነ።

በዚህም አባት ጢሞቴዎስ ዘመን ከቊስጥንጥንያ የመጡ ክፉዎች ሰዎች በግብጽ አገር ተገለጡ እነርሱም የ #ክርስቶስን ተዋሕዶ ምትሐት በሚያደርግ መከራውንና ትንሣኤውንም በሚክድ በረከሰ በአውጣኪ ትምህርት የሚያምኑ ናቸው ይህም አባት አውግዞ ከግብጽ አገር አሳደዳቸው።

ዳግመኛም በዘመኑ ምእመን ንጉሥ አንስጣስዮስ አረፈና በርሱ ፈንታ ኬልቄዶናዊ መናፍቅ ዮስጣትያኖስ ነገሠ እርሱም በአባ ጢሞቴዎስ ፈንታ ሊናርዮስን ሊቀ ጵጵስና ሾመው ሃይማኖታቸው የቀና ምእመናንን ሁሉ በኬልቄዶን ጉባኤ ወደተወሰነ ሃይማኖት ሊመልሳቸው ወዶ በቅስጥንጥኒያ ጉባኤ ሰብስቦ የአንጾኪያውን ሊቀ ጳጳሳት አባ ሳዊሮስን ከኤጲስቆጶሳቶቹ ጋር አስመጣው።

በኬልቄዶን ጉባኤ በተወሰነች በተበላሸች ሃይማኖቱ ያምኑ ዘንድ አስገደዳቸው እነርሱ ግን አልተቀበሉትም ትእዛዙንም አልሰሙም ስለዚህም ሃይማኖታቸው በቀና ምእመናን ሁሉ ታላቅ መከራ አደረሰባቸው።

ይህም አባት ጢሞቴዎስ በመንበረ ሢመቱ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኑሮ በሰላም ዐረፈ።

ለ #እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ  ጢሞቴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።

በግዕዝ➞ #ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ።
ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን።

ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ #ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ #ኢየሱስ_ክርስቶስ።

በአማርኛ➞ #ጌታ_ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።

ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የ #ጌታ እናቱ በ #ማርያም ጸሎት #ኢየሱስ_ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አቡነ ዘበሰማያት(አባታችን ሆይ)...... ይበሉ!!!

<<< ወስብሐት ለ #እግዚአብሔር >>

#ስንክሳር_ዘወርኃ_የካቲት_13