Ethiopian News @ethiopiannewstm Channel on Telegram

Ethiopian News

@ethiopiannewstm


Ethiopian News (English)

Are you interested in staying up-to-date with the latest news and developments in Ethiopia? Look no further than the 'Ethiopian News' Telegram channel! This channel, with the username @ethiopiannewstm, is your go-to source for all things related to Ethiopia. From breaking news to in-depth analysis, this channel covers a wide range of topics, including politics, economy, culture, and more. Whether you are a resident of Ethiopia or simply interested in learning more about this beautiful country, 'Ethiopian News' has got you covered. Join our growing community today and be the first to know about all the important events happening in Ethiopia and beyond.

Ethiopian News

09 May, 17:53


Channel name was changed to «Ethiopian News»

Ethiopian News

29 Dec, 14:22


ለተለያየ አገልግሎት የሚሆን 124 ሺ ተከታይ ያለው ቴሌግራም ግሩፕ መግዛት የምትፈልጉ በ @Business_251 ያዋሩን!

Ethiopian News

06 Jul, 12:24


ለተለያዩ አገልግሎት የሚሆኑ
81k እና 82k ተከታይ ያላቸው የቲክቶክ ገፅ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገዛ በ
@Et_passport ላይ ያዋራን።

⚠️ትክክለኛ ገዢ ብቻ!!

Ethiopian News

29 Jul, 18:06


የአልሻባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ኃላፊን ፏአድ መሐመድ ከሌፍ (ሼንጎሌ) ጨምሮ ሶስት የቡድኑ አመራሮች መገደላቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ አስታወቀ!

የአልሻባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ኃላፊን ፏአድ መሐመድ ከሌፍ (ሼንጎሌ) ጨምሮ ሶስት የቡድኑ አመራሮች መደምሰሳቸውን የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ተናገሩ።

ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ እንደተናገሩት፤ ባለፉት ቀናት ከኢፌዴሪ አየር ኃይል ጋር በመቀናጀት በተወሰደው ርምጃ የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ያዘጋጃቸውን የትጥቅና ስንቅ ዴፖዎች ማውደም ተችሏል፡፡

በተጨማሪም የአሸባሪ ቡድኑ አመራሮችና ታጣቂዎች በተወሰደው ርምጃ ተደምስሰዋል።

ከተደመሰሱት ውስጥ የአልሸባብ ከፍተኛ ኮማንደሮች ውስጥ:-
1. ፏአድ መሐመድ ከለፍ (ሼንጎሌ) የአልሸባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ሃላፊ፣

2.አብዱላዚዝ አቡ ሙሳ የአልሸባብ ቃል አቀባይ፣

3.ኡቤዳ ኑር ኢሴ የአልሸባብ የቦኮል ዞንና የኢትዮጵያ ድንበሮች አዋሳኝ ሃላፊ መደምሰሳቸውን ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Ethiopian News

27 Jul, 19:06


🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ወርቆቻችን
በ18ኛው የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ያስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል።

Ethiopian News

19 Jul, 10:38


በ2014 በጀት ዓመት ከ336 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ !!

የገቢዎች ሚኒስቴር ባሳለፍነው በ2014 በጀት ዓመት ከ336 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ።
ሚኒስቴሩ በዚህ በጀት ዓመት ሊሰበስብ ካቀደው 360 ቢሊዮን ብር ውስጥ 336 ቢሊዮን 710 ሚሊዮን 021 ሺህ 930 ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 93.53 በመቶ ማሳካቱ ነው የተገለፀው።

አፈፃፀሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻፀር የብር 57 ቢሊዮን 494 ሚሊዮን 923 ሺህ 697 ብር ወይም የ20.59 በመቶ እድገት እንዳለው ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው ተናግረዋል።

የተሰበሰበው ገቢ ምንጭም ከአገር ውስጥ ታክስ 196 ቢሊዮን 211 ሚሊዮን 638 ሺህ 548 ብር ሲሆን፤ ከውጭ ንግድ፣ ቀረጥና ታክስ ደግሞ 140 ቢሊዮን 498 ሚሊዮን 338 ሺህ 382 ብር መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ በ2022 ሀገራዊ የታክስ አስተዳደር ተገንብቶ ሀገራዊ ወጪን በራሷ ገቢ ለመሸፈን የምታደርውን ጥረት ለማሳካት ተልእኮ የተሰጠው የገቢዎች ሚኒስቴር በስኬት ገቢን የመሰብሰብ አቅሙ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።

ገቢው በሀገሪቱ በተፈጠረው ጦርነት ብዙ ተቋማት ከስራ ውጭ በሆኑበት፣ በጦርነቱ ምክንያት የንግዱ እንቅስቃሴ በተቀዛቀዘበት፣ በተለያዩ አካባቢዋች በሚፈጠሩ ግጭቶች ተቋሞች በአግባቡ ስራቸውን እንዳይሰሩ በተቸገሩበት እንዲሁም የንግዱ ማህበረሰብ ስራውን ተረጋግቶ ባላከናወነበት ሁኔታ ውስጥ መሰብሰቡ አፈፃፀሙን የተሻለ ሊያስብለው እንደሚችል ተጠቁሟል።

Ethiopian News

19 Jul, 10:38


ህወሃት ከፌዴራል መንግሥት ጋር ለሚደረገው ድርድር ተደራዳሪዎችን መሰየሙን አስታወቀ!

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተከሰተውን የእርስ በርስ ጦርነት በሰላም ለመፍታት ለሚደረገው ድርድር የሰላም ቡድን መቋቋሙን የህወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።

የፌዴራል መንግሥት ለዚሁ ይደረጋል ለባለው ድርድር ተደራዳሪ ኮሚቴ በማቋቋም ሥራ መጀመሩን መግለፁ ይታወሳል።

ይህንም ተከትሎ የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ”ለድርድር የሚሆን ልዑክ ወደ ናይሮቢ ለመላክ ዝግጁ እንሆናለን” ሲሉ መናገራቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ቃላ አቀባዩ ተደራዳሪ ቡድኑ ውስጥ እነማን እንደተካተቱና ቁጥራቸውን በተመለከተ ያሉት ነገር ባይኖርም፤ በከፍተኛ ሥልጣን ደረጃ የሚገኙ አባላት ያሉት ኮሚቴም መቀቋቋሙን ግን ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሃት ጋር የሚደረገው ምንም አይነት ድርድር ሊመራ የሚችለው በአፍሪካ ህብረት ብቻ መሆኑን አቋሙን ያስታወቀ አስታውቋል። ይህንንም ተከትሎ የህወሃት አመራሮች በህብረቱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ በማንሳት ድርድሩ በህብረቱ ጥላ ሥር ብቻ እንዲሆን እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።

“ኹሉንም የድርድር ሂደቶች ለአፍሪካ ኅብረት መስጠቱ ለእኛ በጣም ሀላፊነት የጎደለው ተግባር ነው” ያሉት ጌታቸው፣ ማንኛውም ድርድር በሰላም ጥረት ውስጥ ንቁ ሚና የተጫወቱትን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ማካተት አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

ቃል አቀባዩ በተጨማሪም በአማራ ክልል ዘንድ የይገባኛል ጥያቄ ያለበትና፤ በአሁኑ ወቅት በአማራ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ያለው ምዕራብ ትግራይ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም በማለት መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘገባው አስነብቧል።

ከህወሃት ከምዕራብ ትግራይ በተጨማሪ የመሰረተ ልማት ጥያቄ ለድርድር አይቀርብም በሚል በተደጋጋሚ መናገሩ የሚታወስ ሲሆን፤ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ግን እስካሁን የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ የለም።

የፌዴራል መንግሥት ከህወሃት አመራሮች ጋር የሚያደርገው ውይይት መቼ እንደሚጀመርም ሆነ፣ የት እንደሚደረግ ከኹለቱም ተደራዳሪ ወገኖች በኩል እስካሁን የተገለጸ መረጃ ባይኖርም፤ በህወሃት በኩል የኬንያ መዲና ናይሮቢ ትሁን የሚል ሃሳብ ቀርቧል።

Addis Maleda

Ethiopian News

19 Jul, 10:38


በየቦታው እና በየትቦው የምንጥለው የውሃ መያዣ ፕላስቲክ .....የፍሳሽ መስመሮችን ይዘጋል ..... አካባቢን በመበከል የጤና እክል ያስከትላል !!
@ መገናኛ

Ethiopian News

19 Jul, 10:38


በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግስት ጉዳይ ፈፃሚ ጎንደር ገቡ!

በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግስት ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ለጉብኝት ጎንደር ከተማ ገቡ፡፡ አምባሳደሯ አጼ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። አምባሳደሯ በቆይታቸው በወቅታዊና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

[FBC]

Ethiopian News

19 Jul, 06:43


ሱዳን፤ በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር መካከል የትኛውም ታጠቂ ሃይል እንዳይንቀሳቀስ መወሰኑን አስታወቀች!

በጄነራል አብዱል ፋታህ አል-ቡርሃን የሚመራው የሱዳን የጸጥታ እና መከላከያ ምክር ቤት ሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በመተማ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኛትን መንገድ እንዲከፈት ተወስኗል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ጥብቅ ቅንጅት በማድረግ የዓለም አቀፍ የድንበር ቁጥጥር እንዲጠናከር እና የትኛውም የታጠቁ ሃይሎች በሁለቱ ሀገራት መካከል እንዳይንቀሳቀሱ ምክር ቤቱ ወስኗል።

ውሳኔው የሁለቱ ሀገራት አመራሮች በድንበር አካባቢ ለተቀሰቀሰው ውጥረት “አፋጣኝ እና ዘላቂ” መፍትሔ ለማበጀት የጀመሩትን ውይይት መነሻ በማድረግ እንዲሁም “የታጠቁ ኃይሎች ወደ ሱዳን ግዛት ሰርገው እንዳይገቡ ለመከላከል ከኢትዮጵያ በኩል ለታየው መልካም ፈቃድ” የተላለፈ ምላሽ መሆኑን ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

Via Alain

Ethiopian News

09 Jun, 13:25


የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለዕስረኛ የተቀመጠ 14 እሽግ ብርድልስ በመስረቅ ወንጀል የተጠረጠረውን ዋና ሳጅን አለማየው አባተን ፍርድ ቤት አቀረበ።

የእስረኛ ንብረት ክፍልን በተመሳሳይ ቁልፍ በመክፈት ለዕስረኛ የተቀመጠ አስራ አራት እሽግ ብርድ ልብስ በመስረቅ ወንጀል የተጠረጠው ዋና ሳጅን አለማየሁ አባተን ፍርድ ቤት ያቀረበው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መርማሪ የተሰረቀውን ብርድ ልብስ ዋጋ ግምት እንዲቀርብ መጠየቁንና የተሰረቀውን ንብረት ተከታትሎ ለመያዝ እየሰራ መሆኑን ለችሎቱ አስረድቷል።

ተጨማሪ ማጣሪያ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪው ዋና ሳጅን አለማየው አባተ በበኩሉ ከዚህ በፊት 10 የምርመራ ቀናት የተሰጠው በቂ መሆኑን ገልጾ በድጋሚ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ሊሰጥ እንደማይገባ ተከራክሯል።

ተጠርጣሪው የዕስረኞች ንብረት ክፍል ቁልፍ የሚይዝ ሌላ ሰው መሆኑን ጠቅሶ ከጉዳዩ ጋር ምንም የሚያገናኘኝ ነገር የለም ብሏል ለቾሎቱ።

በተጨማሪም በአሁን ወቅት ደሞዙ እንዳልገባለት የገለጸው ተጠርጣሪ ዋና ሳጅን አለማየው አባተ ባለቤቱ ስራ እንደሌላት ጠቅሶ የዋስ መብቱ እንዲከበር ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ጉዳዩን የተከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጂ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ምርመራውን ተጠናቆ እንዲቀርብ 7 ተጨማሪ ቀናትን ለመርማሪ ፖሊስ ፈቅዷል።

ይህ በእንዲህ እያለ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአባላት የሚፈጸሙ ማንኛውንም የስነምግባርም ሆነ የወንጀል ድርጊትን በመከታተል የማጥራት ስራ መጀመሩ ከተቋሙ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

Ethiopian News

09 Jun, 13:25


የፓስፖርት አገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌብር ለመፈጸም የሚያስችል ስምምነት ተደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ ፓስፖርት የሚያወጡ፣ የሚያሳድሱና ምትክ የሚፈልጉ ደንበኞች ቴሌብርን ተጠቅመው በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ሆነው የአገልግሎት ክፍያቸውን መፈጸም ይችሉ ዘንድ ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ፈጸመ፡፡

ይህ በዛሬው ዕለት የተደረገው የአጋርነት ስምምነት በዋናነት የኢትዮ ቴሌኮም የቴሌብር አገልግሎትን ከፓስፖርት አገልግሎት ክፍያ አሰራር ጋር በማስተሳሰር በየጊዜው እያደገ የመጣውን የደንበኞች የክፍያ አማራጭ የአገልግሎት ፍላጎት ቀላል እና አስተማማኝ በማድረግ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት፣ ለማሳደስ፣ ለጠፋ ምትክ ለማውጣት እና የተበላሸ እንዲስተካከልላቸው የሚፈልጉ ደንበኞች የአገልግሎት ክፍያቸውን ባሉበት ቦታ በቀላሉ መክፈል ያስችላቸዋል፡፡

በተጨማሪም ደንበኞች ለከፈሉት የአገልግሎት ክፍያ ማስረጃው በቅርብ እንዲኖራቸው፣ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣትም ሆነ ለማሳደስ ወደ ኤጀንሲው ሲሄዱ የሚደርሰውን የገንዘብና የጊዜ ብክነት፣ የጉልበት ድካም እና የደላሎች ወከባ በመቀነስ ለደንበኞች ምቹና ቀልጣፋ የአገልግሎት ክፍያ አማራጭ ለማቅረብ ያለመ ነው፡፡

የቴሌብር የዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ተግባራዊ ከተደረገ ጀምሮ ለዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት መስፋፋት ጉልህ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ሲሆን አገልግሎቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ 19.95 ሚሊዮን ደንበኞች፣ 82 በላይ ዋና ወኪሎች፣ 69.8 ሺህ ወኪሎች እና 18.8 ሺህ ነጋዴዎች ማፍራት ችሏል፡፡

በተጨማሪም በቴሌብር 20.63 ቢሊዮን ብር የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ዝውውር የተደረገ ሲሆን ከ12 ባንኮች ጋር ከባንክ ወደ ቴሌብር እና ከ10 ባንኮች ጋር ደግሞ ከቴሌብር ወደ ባንክ ገንዘብ ለማስተላለፍ ትስስር መፍጠሩ ለዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ያለውን ከፍተኛ ተመራጭነት ያሳያል፡፡

ኩባንያችን የህብረተሰቡን የተለያዩ የቴሌኮም ፍላጎቶችን ለማሟላት እና ዘመኑ ያፈራቸውን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር በአጋርነት ከሚሰሩ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመተባበር የማህበረሰባችንን የኑሮ ዘይቤ ለማሻሻል፣ ለማቅለል ብሎም የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ እውን ለማድረግ እንዲሁም በማህበረሰባችን ላይ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ኩባንያው በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ትኬትን፣ የመብራት አገልግሎት፣ የትራፊክ ደንብ መተላለፍ ቅጣትን፣ የውሃና ፍሳሽ መሥሪያ ቤቶች የወርሃዊ አገልግሎት ክፍያን እንዲሁም የሃይብሪድ ዲዛይንስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር /ራይድ/ አገልግሎት ክፍያን በቴሌብር ለማከናወን የሚያስችል የጋራ ስምምነትን ጨምሮ በርካታ ድርጅቶች የአገልግሎት ክፍያዎቻቸውን በቴሌብር እንዲፈጽሙ የሚያስችል ስምምነት አድርጓል፡፡

Ethiopian News

09 Jun, 13:25


ለተመስገን ደሳለኝ፣ ሰለሞን ሹምዬ እና መዓዛ መሐመድ የተፈቀደው የ10 ሺህ ብር ዋስትና ተሻረ።
*********

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ሰለሞን ሹምዬ እና መዓዛ መሐመድ በስር ፍርድ ቤት የተፈቀደላቸውን የ10 ሺህ ብር ዋስትና ሻረ። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን የሻረው፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዋስትና ትዕዛዙ ላይ ይግባኝ ካቀረበ በኋላ ነው።

የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 2፤ 2014 ከሰዓት በጽህፈት ቤት በኩል በሰጠው ትዕዛዝ ለመርማሪ ፖሊስ የ8 ቀናት የምርመራ ጊዜን ፈቅዷል።

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

Ethiopian News

09 Jun, 13:25


ለባለሥልጣኑ አዲስ የስራ አመራር የቦርድ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመደቡለት

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አዲስ የስራ አመራር የቦርድ አባላት በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደተመደቡለት አስታወቀ፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ለባለሥልጣን መ/ቤቱ በላከው ደብዳቤ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አዲስ የስራ አመራር የቦርድ አባላትን አሳውቀዋል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አደረጃጀት፣ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ ደንብ ቁጥር 512/2014 አንቀጽ 8 (1) የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ለመወጣት ያስችለው ዘንድ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ አዲስ የስራ አመራር የቦርድ አባላትን ዝርዝር አሳውቋል፡፡

በዚሁም መሰረት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አዲስ የተመደቡት የስራ አመራር የቦርድ አባላት ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1. ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ……………………ሰብሳቢ
2. ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር …….…… …አባል
3. ዶ/ር በለጠ ሞላ የኢኖቪሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ………………..አባል
4. አቶ ተስፋዬ ዳባ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ …....……. አባል
5. ዶ/ር ሹመቴ ግዛው የኢንፎርሜሽ መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ………………አባል
6. ወ/ሮ ሳሀረላ አብዱላሂ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር…………………..አባል
7. ዶ/ር አንዱዓለም አድማሴ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ………….......አባልና ጸሀፊ ናቸው።

Ethiopian News

09 Jun, 13:25


ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሶማሊያ ፕሬዝዳንት በዓለ ሲመት ላይ ለመታደም ሞቃዲሹ ገቡ

በአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ በዓለ ሲመት በዛሬው እለት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በፕሬዚደንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት የሶማሊያዋ መዲና ሞቃዲሹ ገብተዋል።

ከኢትዮጵያ በተጨማሪም የጅቡቲ፣ የኬንያ፣ የቱርክ፣ የባህሬን፣ የዐረብ ሊግ፣ የሕንድ፣ የኢንዶኔዥያ እና የኦማን ተወካዮች ሞቃዲሾ መግባታቸውን የሶማሊያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

በዓለ ሲመቱ ዛሬ በሞቃዲሾ የሚካሄድ ሲሆን፤ በዓሉ ከአልሸባብ ጥቃት በጸዳ መልኩ እንዲከበር ሰፊ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።

Ethiopian News

09 Jun, 13:25


ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው በተጠረጠረበት ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት ወንጀል ጉዳይ መታየት ያለበት በብሮድካስት አዋጅን ነው ወይስ በፍርድ ቤቱት ጊዜ ቀጠሮ ነው የሚለውን መርምሮ ብይን ለመስጠት በይደር ተቀጠረ።

በዩቱዩብ ማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፈው የአልፋ ቴሌቢዥን መስራች ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ከጠበቃው ታደለ ገ/መድህን ጋር በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቦ ጉዳዩን ተከታትሏል።

የምርመራ መዝገቡን የያዙት ሁለት መርማሪ ፖሊሶች ከዚህ በፊት በተሰጣቸው የምርመራ ጊዜ ውስጥ የሰሩትን የምርመራ ሪፖርት ለችሎቱ አቅርበዋል።

በዚህም በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በሚሰሩ አካላት የተደረገ የገንዘብ ስለመኖሩ ማስረጃ መሰብሰባቸውን ለችሎቱ ገልጸዋል።

ከቀሪ ባንኮች የተደረገ የገንዘብ ድጋፍ ውጤት እና በጋዜጠኛው እጅ ላይ የተገኘ ኤሌክትሮኒክስ ምርመራ ውጤት እየጠበቁ መሆናቸውን እንዲሁም ተጨማሪ ማስረጃ ከመንግስት ተቋማት ማምጣት እንደሚቀራቸው ለችሎቱ አስረድተዋል።

ከወንጀሉ ውስብስብነት አንጻር ድርጊቱ በሀገር ውስጥ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ አባሪ ለመያዝ እና ቀሪ ማስረጃ ለመሰብሰብ ለተጨማሪ ማጣሪያ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው በመግለጽ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድላቸው ችሎቱን ጠይቀዋል።

የጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ጠበቃ ታደለ ገ/መድህን በበኩላቸው ደንበኛዬ የተጠረጠረው በሚዲያ በሰራው ስራ በመሆኑ ጉዳዩ ሊታይ የሚገባው በመገናኛ ብዙሀን አዋጅ1238/2013 መሰረት ነው ሲሉ ተከራክረዋል።

በዚህ አዋጅ አንቀጽ 86 ድንጋጌ የብሮድ ካስት የወንጀል ድርጊት በጊዜ ቀጠሮ የሚያሰጥ እንዳልሆነ የገለጹት ጠበቃ ታደለ በዘፈቀደ እስር መታሰሩ አግባብ አደለም በማለት ተከራክረዋል።

ከዚህ በፊት ለፖሊስ በተሰጠው በቂ ጊዜ የምርመራ ስራቸውን በትጋት ባልሰሩበት ሁኔታ ተመሳሳይ ይዘትና ጥያቄ አሁንም ማቅረባቸው በደንበኛዬ ላይ የሰባዊ መብት ጥሰት የሚያስከትል ነው ብለዋል ጠበቃ ታደለ።

ይህም በፖሊስ የቀረበው የተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጥያቄ ሀገራችን በአለም አቀፍ ደረጃ የተስማማችበት የሰባዊ መብት ህግጋትን የሚጥስ ነው ሲሉ ተቃውመዋል።

በተጨማሪም ጠበቃው ቀሪ ማስረጃዎች ከመንግስት መስሪያ ቤት የሚመጣ በመሆኑ ደንበኛዬ ደግሞ ሰነዶችን ሊያጠፋ ወይም ሊደልዝ በማይችልበት ሁኔታ ላይ ታስሮ የሚቆይበት የህግ አግባብ የለም ብለዋል።

ደንበኛዬ ፖሊስ የሚያዙ ቀሪ አባዎች አሉ ብሎ የገለጻቸውን አያውቅም ስለዚህ እንደመያዣ ሆኖ በስር የሚቆይበት አግባብ ስለሌለ የፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ ጥያቄ ውድቅ ይደረግልን እና ዋስትና ይፈቀድል ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

መርማሪ ፖሊሶች የዋስትና ጥያቄውን ተቃውመዋል።

እኛ የያዝነው በመገናኛ ብዙሀን ስራው ሳይሆን ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት ወንጀል ተጠርጥሮ ነው ሲሉ ማብራሪያ ሰተዋል።

በዚህ በተሰጠን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ በርካታ ስራ ሰርተናል ያሉት መርማሪ ፖሊሶች በሰራነው ዝርዝር ስራ ደግሞ በሀገር ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ ድጋፍ ከሚያደርጉ አካላት በባንክ በዶላርና በኢትዮጲያ ገንዘብ ያስገቡት ገቢን የሚመለከት ማስረጃ እየመጣ ነው ተጨማሪ የሚመጣም አለ ሲል ፖሊስ ለችሎቱ አብራርቷል።

የችሎቱ ዳኛ በግንቦት 29 ቀን በነበረ የችሎት ቀጠሮ ጋዜጠኛው የተጠረጠረበት ወንጀል የሚሸፈነው በብሮድካስት ህግ ነው ወይስ በፍርድ ቤት ጊዜ ቀጠሮ ነው በሚለው ጉዳይ ላይ ፖሊስ አጣርቶ እንዲቀርብ መታዘዙን አስታውሰዋል።

በዚህ ትዛዝ መሰረት መርማሪ ፖሊሶቹ ማጣራትና አላማጣራታቸውን የማረጋገጫ ጥያቄ ዳኛው ያቀረቡ ቢሆንም ፖሊስ አለማጣራቱን መልስ ሰቷል።

በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ የብሮድካስት አዋጅ ለመመልከት በጠባቃ በኩል እንዲቀርብ ታዟል።

ጋዜጠኛ በቃሉ የተጠረጠረበት ወንጀል የሚታየው በብሮድካስት አዋጅ ነው ወይስ በፍርድ ቤት ጊዜ ቀጠሮ የሚለውን አጣርቶ ብይን ለመስጠት በይደር ቀጥሯል።

Via Tarik Adugna

Ethiopian News

09 Jun, 13:25


አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ተሾሙ!

አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ።

አምባሳደር ተስፋዬ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዘርፍ ሚኒስትር ዴአታ ሆነው ተሹመዋል።

አምባሳደር ተስፋዬ ሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ/ ም ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እስከተሾሙ ድረስ በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ ሆነው በማገልገል ላይ እንደነበሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት መረጃ ያሳያል።

Ethiopian News

08 Jun, 16:58


ከላይ የተገለጡት ሰላምንና ጸጥታን የማስከበር ሥራዎች በቁርጠኝነትና በመሥዋዕትነት የተከናወኑ ናቸው። ለዚህም በሥራ የተሳተፉትን ሁሉ ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ያመሰግናል። የፖለቲካ መዋቅሩ ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የፈጸሙት የሀገርን አንድነት፣ ሰላምና ብልጽግና የማረጋገጥ ሥራ ውጤታማ የሆነው መላው ሕዝብ በዓላማው አምኖ፣ በሥራው አብሮ በመሰለፉ መሆኑ ይታመናል። ኢትዮጵያ ሕዝቦቿ በነጻነትና በሰላም የሚሠሩባት፣ የሚንቀሳቀሱባትና የሚያመርቱባት ሀገር እንድትሆን ሕገ ወጥነት በምንም መልኩ ዕድል ሊያገኝ አይገባም። ሕገ ወጥነት - የብሔርን፣ የሃይማኖትን፣ የፖለቲካ ቡድንን ወይም የሚዲያና የአክቲቪስትነትን ካባ ቢደርብም፣ ሕገ ወጥነት መሆኑ አይቀርም። አይጥ ምንም ዓይነት ቀለም ብትቀባ አይጥ መሆኗና ንብረት ማበላሸቷ አይቀርም።

ውድ ኢትዮጵያውያን፣

ስለ ጸጥታና ደኅንነት እየተናገርን በሕግ ከተቋቋሙ የጸጥታ መዋቅሮች ውጭ የታጠቁ የጸጥታ አደረጃጀቶች እንዳሻቸው እንዲሆኑ መፍቀድ ተገቢ አይደለም። በሀገር ውስጥ ኃይልን በብቸኝነት የመጠቀም መብት ለመንግሥት የተሰጠ መብት ነው። ዜጎች በሰላም ጊዜ አልሚ፣ በጦርነት ጊዜ ተፋላሚ መሆናቸው ከጥንትም የነበረ ነው። ያ ማለት ሀገር ስትወረር ሁሉም ለሀገሩ ተፋላሚ ይሆናል፤ ሀገር ሰላም ስትሆን ደግሞ ሁሉም ወደ ሕጋዊ ማሕቀፍ ይገባል ማለት ነው።


ከዚህም በተጨማሪ በሚዲያ፣ በአክቲቪስትነት፣ በፖለቲካ ቡድን እና በብሔር ስም የሚደረግ ሀገር የማፍረስ ሤራን መንግሥት በምንም መልኩ እንደማይታገሥ መታወቅ አለበት። የሃይማኖት ተቋማት የሰላምና የጤናማ ማኅበረሰብ መገንቢያ ማዕከላት እንጂ የአክራሪዎችና የሀገር አፍራሾች መናኸሪያ እንዲሆኑ ሊፈቀድ አይገባም። ሃይማኖቶች በስማቸው ጥፋት የሚፈጽሙ ነውረኞችን መቆንጠጥ ሲገባቸው ችላ በማለታቸው ጥፋት ፈጻሚዎቹ የልብ ልብ እየተሰማቸውና ተቋማቱን እንደከለላ በመቁጠር በድርጊታቸው ቀጥለውበታል።

በሀገራችን ሃይማኖት ተኮር ጥፋቶች በዘላቂነት ሊቀንሱ የሚችሉት አንዱ ወደሌላው ጣት በመቀሰር ሳይሆን ሁሉም በቅድሚያ በራሱ ተቋም ውስጥ የሚሸሸጉ ጥፋት ፈጻሚዎችን ምሽግ ለማሳጣት ሲችል ነው። ለዚህ ደግሞ ምእመናንና የሃይማኖት አባቶች የሚገባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል።

በአጠቃላይ የተጀመረው ሰላምና ጸጥታን የማስፈን፣ ሕግና ሥርዓትን የማስከበር፣ ብሎም የኢትዮጵያን ብልጽግና በጽኑ መሠረት ላይ የመገንባት ተግባር ከግብ እንዲደርስ፤ የተጀመረው ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ ብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤቱ ጥሪ ያቀርባል።


የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት
ሰኔ 1፣ 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Ethiopian News

08 Jun, 16:58


በወቅታዊ ሀገራዊ የደኅንነትና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ ከብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ


የተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች፣

ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት፣ ከአንድ ወር በፊት፣ ሚያዝያ 14 ቀን 2014 ዓ.ም.፣ ሀገራዊ የጸጥታ ሁኔታን በጥልቀት መገምገሙ ይታወሳል። በዚያ ግምገማውም እንደ አልሸባብ፣ ሸኔና ጁንታ ያሉ የሽብር ኃይሎችን ሁኔታ ተመልክቷል። ከኮንትሮባንድ፣ ከሕገ ወጥ ታጣቂዎች፣ ከጽንፈኛ የሚዲያና የፖለቲካ ቡድኖች፣ ከአክራሪ ሃይማኖተኞችና ከሙሰኞች የሚመጡ ፈተናዎች በሀገር ላይ ያስከተሉትን ሥጋት ተመልክቷል። የመንግሥት መዋቅር የጥራትና የቁርጠኝነት ችግሮች እንደታዩበትም ገምግሟል። እንዲሁም የውጭ ጠላቶቻችንን ሤራና የውክልና ጦርነቱን ሁኔታ በጥልቀት መርምሯል።

ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ በሚያዝያ ወር ባደረገው ስብሰባው እነዚህ ፈተናዎች በሀገርና በሕዝብ ላይ ያሳደሩትን ሥጋትና ፈተና በሚገባ ተንትኖ አስቀምጦ ነበር። የሕዝቡ የደኅንነት ሥጋትና ሀገራዊ አለመረጋጋት መባባሱን፤ ሕዝብ በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ እየተደረገ መሆኑን፤ በሃይማኖትና በብሔር አክራሪነት የተነሣ የሀገርን አንድነት ለመሸርሸር እየተሠራ መሆኑን፤ የሕገ ወጥ ታጣቂዎች ዐቅም እየጨመረ የሕጋዊ መዋቅሮች ዐቅም እየደከመ መምጣቱን፤ የሕገ ወጥ ታጣቂዎች መበራከትና መጠናከር ለኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ፈተና መሆኑን፤ ሕገ ወጥ ቡድኖቹ የሕዝቡን ሰብአዊና ማኅበራዊ መብቶች እየጣሱ ሕዝብ መሰቃየቱን፤ በጠቅላላ ሥርዓት አልበኝነት እንዲስፋፋ ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረለት መሆኑን፤ ይህም ለውጭ ጠላቶቻችን ዕድል እንደፈጠረላቸው፤ ነገሩ በአስቸኳይ ካልተስተካከለ ሀገርን ወደ ከፋ አደጋ እንደሚያስገባ በሚያዝያ ስብሰባው መገምገሙ ይታወቃል።

እነዚህን ችግር ፈጣሪዎችና በሕዝቡ ላይ ያንዣበቡ ፈተናዎች በዝምታና በትዕግሥት ማየቱ አደገኛውን ቀይ መሥመር እንዲታለፍ እንደሚያደርግ ታምኖበት ነበር። መንግሥት ችግሮችን በሆደ ሰፊነት እያለፈ፣ በጊዜ ብዛት ቀስ በቀስ ለማረም የተከተለው ስልት እንደ ድክመትና ዐቅመ ቢስነት መታየቱን የደኅንነት ምክር ቤቱ አረጋግጧል። ሕዝቡ በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ ውይይቶችና በተወካዮቹ አማካኝነት መንግሥት ጠበቅ ያለ የሕግ ማስከበር ሥራ እንዲሠራ እየወተወተ መሆኑን ምክር ቤቱ ተመልክቷል። ችግሮችን በውይይት፣ በሀገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች በኩል ለማረም የተደረጉ ጥረቶች መጠነኛ ውጤት ማምጣታቸውን ተረድቷል።

የተወሰኑ አካላት በሕጋዊ መሥመር ለመሥራት መወሰናቸውን፤ ወደ መደበኛ የጸጥታ ተቋማት ገብተው ለመሠማራት መወሰናቸውን ተገንዝቧል። አንዳንድ አካላትም ወደ ሰላማዊ ኑሮ ለመመለስ ያደረጉትን ውሳኔ በሚያዝያው ስብሰባው በክብር ተቀብሎት እንደነበር ይታወሳል።
መንግሥት የሰጠውን የሰላም ዕድል ያልተጠቀሙና በሕገ ወጥ ተግባራት ከመሠማራት ያልተቆጠቡ አካላትን በተመለከተ የደኅንነት ምክር ቤቱ በሚያዝያ ወር ባደረገው ውይይት የሚከተሉትን አቅጣጫዎች አስቀምጦ ነበር፡-

• በተደራጁና ያለፈቃድ በታጠቁ ቡድኖች ላይ ሕግን የማስከበር ሥራ መሠራት እንዳለበት፣
• በሁሉም አካባቢዎች የሚታዩ ሕገ ወጥ ተግባራት በፍጥነት መስተካከል እንዳለባቸው፣
• በየአካባቢው የሕዝብ ቅሬታ ምንጮች የሆኑ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በፍጥነት ማስተካከል እንደሚገባ፣
• ግጭት ቀስቃሽና ጽንፈኛ የሚዲያ አካላት፣ የፖለቲካ ቡድኖችና አክቲቪስቶች ሕጋዊውን ሥርዓት ብቻ እንዲከተሉ የሚያደርግ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ፣
• የመንግሥትን መዋቅር በማጥራት፣ ሚናውን ለይቶ በቁርጠኝነት እንዲሠራና ሕዝብና መንግሥት የጣሉበትን ኃላፊነት እንዲወጣ የሚያደርግ ተግባር እንዲከናወን አቅጣጫዎች ተቀምጠው ነበር።

በዚህ መሠረት የተከናወኑትን ተግባራት ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ረቡዕ ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓም ባደረገው ስብሰባ በጥልቀት ገምግሟል። በግምገማውም መሠረት የመንግሥትን ኃይልን በብቸኝነት የመጠቀም ሕጋዊ ሥልጣን የሚገዳደሩ ኃይሎችንና የሕገ ወጥነት ተግባራትን ወደ ተገቢው ሥርዓት የማስገባቱ ሥራ በታቀደለት መንገድና በተሻለ ጥራት እየተከናወነ መሆኑን፤ ሥራውም የታለመለትን ግብ እያሳካ እንደሆነ አረጋግጧል።

በኦሮሚያ ክልል በተከናወነው አኩሪ ሥራ የሸኔን ልዩ ልዩ ቡድኖች በመደምሰስ፣ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን በማምከን፣ በጠላት እጅ የነበሩ አካባቢዎችን መልሶ በመቆጣጠር፣ መዋቅሩን በማጥራት፣ ሕዝብን በማወያየትና በማሰለፍ ውጤታማ ሥራ መከናወኑን ለማወቅ ተችሏል። በሺዎች የሚቆጠሩ የሸኔ አባላት መገደላቸውን፣ መማረካቸውንና በፈቃዳቸው እጅ መስጠታቸውን ከሪፖርቶቹ ተረጋግጧል። አያሌ የጦር መሣሪያዎችና ቁሳቁሶች ከሸኔ አባላት ተማርከዋል። መንግሥታዊ መዋቅሩን በሚገባ በማጥራት፣ ለአመራር ብቁ የማድረግ ተግባር በመልካም ሁኔታ ተከናውኗል።

በአማራ ክልል በተሠሩ ሥራዎች ሕዝቡን ለእፎይታ ያበቁ ተግባራት መከናወናቸውን የደኅንነት ምክር ቤቱ ገምግሟል። በዚህም መሠረት ከጸጥታ ተቋማት የከዱ አባላትን በመያዝ፣ በተለያዩ ወንጀሎች የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ሥር በማዋል፤ ተበትነው ለጸጥታ ሥጋት ሲሆኑ የቆዩ የጦር መሣሪያዎችን በማሰባሰብ፣ በሕገ ወጥ ተግባር ተሠማርተው የነበሩ አክቲቪስቶችን ሥርዓት በማስያዝ፣ ሕዝቡ የሰላምና የጸጥታው አካል እንዲሆን አወያይቶ በማሰለፍ፣ የተሻለ ሥራ መሠራቱን ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ተመልክቷል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተደረገውን ሰላምና ጸጥታ የማስፈን እንቅስቃሴ ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ በገመገመበት ወቅት አበረታች ሥራዎች መከናወናቸውን ተገንዝቧል። የታጠቁ ሽፍቶችን ሥርዓት ከማስያዝና ከመደምሰስ አንጻር፣ ሕገ ወጥ ተግባትራን ከመቆጣጠር፣ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎችን ከመሰብሰብ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቦታቸው ከመመለስ አንጻር የተከናወኑ ተግባራት ለውጥ ያመጡ መሆኑን ለመመልከት ተችሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደቡብና በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታትም የታጠቁና የተደራጁ ሽፍቶችን መልክ ከማስያዝ፣ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ከመግታት፣ በተለያዩ ማኅበረሰቦች መካከል የሚከሠቱ ግጭቶችን ከማስቀረትና ከመፍታት፣ ሕገ ወጥ ተግባራትን ከመቆጣጠር፣ የመንግሥት መዋቅርን ከማጥራት አንጻር ሥራዎቹ በታቀዱት መሠረት መከናወናቸውን አረጋግጧል። በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና በኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ሊደረግ ታስቦ የነበረው የአልሸባብ እንቅስቃሴ በጸጥታ አካላት ቅንጅት መክሸፉን ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ተመልክቷል። አልሸባብ ከጁንታውና ከሸኔ ጋር በተደጋጋሚ ሊያደርጋቸው የሞከራቸው ትሥሥሮች በተጠና የጸጥታ አካላት ኦፕሬሽን እንዲመክኑ መደረጋቸውን አረጋግጧል።

ዓለም አቀፍ የሚዲያ ትኩረትን ለመሳብ የሚሞክሩ የጥፋት ኃይሎች በመዲናችን አዲስ አበባ ላይ የተለያዩ የጥፋትና ጸጥታ የማደፍረስ እንቅስቃሴዎችን በተደጋጋሚ ሲሞከሩ የጸጥታና የደኅንነት ተቋማቱ የተናበበ አካሄድ እንዳከሸፈው ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ገምግሟል። በዝርፊያና በከተማ ወንጀሎች ላይ ተሠማርተው የከተማውን ነዋሪዎች ሲያማርሩ የቆዩ አካላትን ተከታትሎ በሕግ ጥላ ሥር ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራትም ውጤታማ ለውጥ ማምጣታቸውን የደኅንነት ምክር ቤቱ ተመልክቷል።

Ethiopian News

08 Jun, 16:58


ጀ/ል ባጫ ደበሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ አቀረቡ።
*******
በቅርቡ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ጀ/ል ባጫ ደበሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ለኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ሹም አምባሳደር ቤቲ ቼቤት አቀረቡ፡፡

የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ባቀረቡበት ወቅት የኢትዮጵያን እና የኬንያን የቆየ ወዳጅነት ያስታወሱት አምባሳደር ባጫ የሃገራቱን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልፀዋል፡፡

አምባሳደሩ ይፋዊ የሹመት ደብዳቤያቸውን ከሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር ጋር በመገናኘት በቀጣዮቹ ቀናት የሚያቀርቡ ይሆናል።

7,175

subscribers

677

photos

34

videos