Ministry Of Education @ethiopianexaminations Channel on Telegram

Ministry Of Education

@ethiopianexaminations


This is the Ministry of Education channel.

Ministry Of Education Promotional Article (English)

Welcome to the Ministry of Education channel on Telegram, also known as @ethiopianexaminations. This channel is your go-to source for all the latest updates, news, and information related to the education sector in Ethiopia. Whether you are a student, parent, teacher, or education enthusiast, this channel has something for everyone

The Ministry of Education channel provides valuable insights into the education system in Ethiopia, including information on upcoming examinations, curriculum changes, scholarship opportunities, and educational policies. Stay informed about important dates, exam results, and educational reforms by following this channel closely

Who is it? The Ministry of Education channel is managed by the Ethiopian government's Ministry of Education, ensuring that all information shared is accurate, reliable, and up to date. What is it? It is a platform designed to keep students, parents, and educators informed about everything related to education in Ethiopia

Join thousands of other subscribers on the Ministry of Education channel to stay ahead of the curve and make informed decisions about your educational journey. Whether you are preparing for exams, looking for study tips, or seeking guidance on educational opportunities, this channel has got you covered. Don't miss out on the chance to be part of this vibrant educational community. Subscribe today and embark on a journey towards academic success and personal growth.

Ministry Of Education

29 May, 11:11


"አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከሰኔ 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ" - የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከመጪው ምርጫ በኋላ ሰኔ 21/2013 ዓ.ም ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ የየሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ከምርጫው በኋላ ሰኔ 21 ሁሉም የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል ነባር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመጪው ምርጫ ወደደቤተሰቦቻቸው በመሄድ በምርጫው ይሳተፋሉ ብለዋል።

"የተማሪዎቹ መሄድ ግዴታ አይደለም" ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው ፤ መምረጥ ለሚፈልጉ ነባር ተማሪዎች እንዲመች ከምርጫው በፊትና በኋላ ያሉ ቀናት የዕረፍት ጊዜ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።

"ምርጫ ማድረግ መብት እንደመሆኑ፤ መምረጥ የማይፈልጉ ነባር ተማሪዎች በያሉበት ዩኒቨርሲቲ መቆየት ይችላሉ" ብለዋል።

ነባር ተማሪዎቹ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ባዘጋጀው የበይነ መረብ የመራጭነት መመዝገቢያ አማካኝነት በምርጫው ለመሳተፍ የመራጭነት ምዝገባ አድርገዋል።

ተማሪዎቹ ወደየመጡበት አካባቢ በመሄድ በምርጫው እንዲሳተፉ ምርጫ ቦርዱ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል።

@ethiopianexaminations
@ethiopianexaminations

Ministry Of Education

24 Sep, 17:52


የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሕዳር 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ/ም የሚሰጥ ሲሆን ፈተና ላይ መቀመጥ የሚችሉት 7ኛ ክፍልን ተምረው ያጠናቀቁና የ8ኛ ክፍልን የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው።

በተመሳሳይ ደግሞ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መውሰድ የሚችሉት የ11ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀቁ እና የ12ኛ ክፍልን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው ተብሏል።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሕዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ/ም እንደሚሰጥ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል።

@ethiopianexaminations
@ethiopianexaminations

Ministry Of Education

11 Jun, 17:56


ከትምህርት ሚኒስቴር ለሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች የተሰጠ ማሳሰቢያ!

(የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር)

የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በመቋረጡ ሀገር አቀፍ የብሔራዊ ፈተና /ምዘና/ የሚሰጥበት ጊዜ በትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም በኤጀንሲው አለመገለፁ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የተለያዩ አካላት ሀሰተኛ ማህበራዊ ድረገፆች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ስምና ሎጎ ተጠቅመው ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን እያሰራጩ እንደሚገኙ ተደርሶበታል።

ስለዚህ ውድ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትምህርት የሚጀመርበትን እና ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና /ምዘና/ የሚሰጥበትን ጊዜ ወደፊት የሚገልፅ መሆኑን እያሳወቀ ተማሪዎች ከወቅታዊው በሽታ ለራሳችሁ እና ለቤተሰባችሁ ጥንቃቄ በማድረግ የመማሪያ መፅሀፍትንና ደብተሮቻችሁን እያነበባችሁ እንድትቆዩ እናሳስባለን።

@ethiopianexaminations
@ethiopianexaminations

Ministry Of Education

13 Mar, 13:24


ስለኮሮና ቫይረስ ወሳኝ መረጃ❗️

ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ ያቆመዋል!

በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ!

➣ ከሮና ቫይረስ የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡

➣ ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ ...ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡

➣ በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/Snow አትመገቡ!

➣ የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡ ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም፡፡ ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡

➣ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው፡፡

➣ አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ ተጠቂ አትሆኑም፡፡

❶ ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡

➋ ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡ በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጡዓቸው ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡

በቫይረሱ የመጠቃት ምልክቶች ምን ምንድን ናቸው?

❶ ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጎሮሮላይ በማድረግ የጉሮሮ ብግነት እና የጎሮሮ ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል::

➋ ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደ ትራኪያ ከወረደ በኋሊ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡ ሳምባን በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ብግነት ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት የሚታይባችሁ ሉ በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!!
በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል?

❶ የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ
መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላ በተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡

➣ ቫይረሱ በሰው እጅላይ በሕይወት መቆየት የሚችለው 10 ደቂቃ ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ ወይም [እንደ ቀመኛ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ ወይም [እንደ ቀመኛ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ ጉሮሮ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡

➣ ስለዚህ ለራሳችሁና ለባልንጀራችሁ (ለሌላው ሰው) ደህንነት ስትሉ በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡

➋ አፍ እና ጉሮሮን ጸረ-ተሕዋስ መድሀኒቶችን በመጠቀም መጉመጥመጥ ቫይረሱን ሊያስወግድ ወይም ወደ ጉሮሮ የሚሄዱትን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ አፍን መጉመጥመጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ትራኪያ አልፎም ወደ ሳምባ ቫይረሱ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያግደው ወይም ሊቀንሰው ይችላል፡፡

➌ የኮምፒውተራችሁን ኪ-ቦርድ እና ማውዝ በጸረ- ተህዋስ በሚገባ አጽዱ፡፡

➣ ሁላችንም ራሳችንን በሚገባ ብንንከባከብ ለእኛና ለሌሎች መልካም ይሆንልናል!!!

Ministry Of Education

13 Mar, 12:53


Unicef
Corona virus is large in size where the cell diameter is 400-500 micro and for this reason *any mask prevents its entry*

The virus does not settle in the air but is grounded, so it is *not transmitted by air*.

Coronavirus when it falls on a metal surface, it will live 12 hours, so *washing hands with soap* and water well enough.

Corona virus when it falls on the fabric remains 9 hours, so *washing clothes* or *being exposed to the sun for two hours* meets the purpose of killing it.

The virus lives on the hands for 10 minutes, so putting an *alcohol sterilizer* in the pocket meets the purpose of prevention.

If the virus is exposed to a temperature of 26-27 ° C. it will be killed, as it does not live in hot regions. Also *drinking hot water and sun exposure* will do the trick
And *stay away from ice cream and eating cold* is important.

*Gargle with warm and salt water* kills the tonsils' germs and prevents them from leaking into the lungs.

Adherence to these instructions fulfills the purpose of preventing viruses.
UNICEF

Ministry Of Education

10 Feb, 11:55


የ2012 ዓ/ም ሀገር አቀፍ ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ፦

1. የ12ኛ ክፍል ፈተና ከግንቦት 24 እስከ 27 ቀን 2012 ዓ/ም እና
2. የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 01 እስከ 03 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ

@ethiopianexaminations
@ethiopianexaminations

Ministry Of Education

06 Oct, 05:21


ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መረጃ በቀላሉ ለመለዋወጥ እንዲያመቻችሁ በማሰብ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችን ግሩፕ ሊንክ አቅርበንላችኋል። በየምርጫችሁ ተቀላቀሉ። መልካም ቆይታ።

1 Hawassa university

2 Haremaya university

3 Bahrdar university

4 Debretabor university

5 Debremarkos university

6 DireDawa university

7 Jimma university

8 Arbaminch University

9 Adigrat university

10 Adama scince and technology university

11 Axum university

12 Mekelle university

13 Gondar university

14 Addis ababa university

15 Semera university

16 Wellega university

17 Mettu university

18 Debrebirhan university

19 wachemo university

20 woldiya university

21 wollo university

22 wolayta soddo university

23 Kebri Dhar university


24 Werabe university

25 debark university

26 Dembi dollo

27 Ambo university

29 Bonga university

30 Arsi university

31 Injibara University

32 Mizan tepi university

33 Jimma university

34 Bule Horra university

@ethiopianexaminations
@ethiopianexaminations

Ministry Of Education

06 Oct, 04:31


#Wachemo University

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አዲስ የአንደኛ አመት መደበኛ ፕሮግራም የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በሙሉ
ከዚህ በፊት እንደተገለፀው የመግቢያ ቀን ከመስከረም 28 - 29 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
Wachemo University Students' Union

@ethiopianexaminations
@ethiopianexaminations

Ministry Of Education

05 Oct, 18:20


#HawassaUniversity

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አዲስ የአንደኛ አመት መደበኛ ፕሮግራም የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በሙሉ
ከዚህ በፊት በተገለፀው የመግቢያ ቀን ከመስከረም 25 - 27 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የተማሪዎች ምደባ ዘግይቶ በመገለፁ ምክንያት የመግቢያውን ቀን ማራዘም አስፈልጓል። በዚሁ መሠረት የምዝገባው ቀን ከጥቅምት 3 - 5 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

@ethiopianexaminations
@ethiopianexaminations

Ministry Of Education

05 Oct, 16:06


ማስታወቂያ!

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ትምህርት ዘመን ለመደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ፦
የምዝገባ ጊዜ ለውጥ ተደርጓል፥ ለበለጠ መረጃ ከላይ የተለጠፈውን ያንብቡት። አንብበውም ለሌሎች ያጋሩት!!

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
የሠላም አምባሳደር፥የዕውቀት ምንጭ!!

@ethiopianexaminations
@ethiopianexaminations

Ministry Of Education

05 Oct, 10:40


የመግቢያ ቀን መራዘሙን ስለማሳወቅ

የደብረታቦር ዩኒቨርስቲ አዲስ መደበኛና ኤክስቴንሽን ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ መስከረም 24-28 ተብሎ የነበረ ቢሆንም ከምደባ መዘግየት ጋር ወደ ጥቅምት 3 - 5 ድረስ ተራዝሟል ጊዜ ተራዝሟል፡፡

@ethiopianexaminations
@ethiopianexaminations

Ministry Of Education

05 Oct, 09:23


በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ባሕር ዳር ዩንቨርስቲ ለተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ

የትምህርት ሚንስቴር የ2012 አዲስ ተማሪዎች ዩንቨርስቲ ምደባ በመዘግየቱ ምክንያት መስከረም 26 እና 27 ቀን 2012 ዓ.ም የነበረው ምዝገባ ከመስከረም 26 እስከ መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እያስታወቅን ለምዝገባ ስትቀርቡ ከ12ኛ ክፍል ትራንስክርቢት እና የብሔራዊ ፈተና ውጤት ካርድ ያልደረሰ በመሆኑ ከአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ድረገፅ ላይ ውጤታችሁን ፕሪንት አድርጋችሁ እንድታቀርቡ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ
የተጠቀሱትን የምዝገባ ቀናት አሳልፎ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናስታውቃለን፡፡

@ethiopianexaminations
@ethiopianexaminations

Ministry Of Education

05 Oct, 08:16


ማስታወቂያ ለመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች በመሉ

ከዚህ በፊት የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የመግቢያና የመመዝገቢያ ቀናት መስከረም 26 እና 27 እንዲሁም በቅጣት መስከረም 28 መሆኑን ማስታወቃችን ይታወሳል፤ ነገር ግን የምደባ ጊዜው በመዘግየቱ ምክንያት የመግቢያ ጊዜው የተራዘመ ሲሆን በጥቂት ቀናት ውሰጥ የመግቢያ ቀናትን እናስታውቃለን።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

@ethiopianexaminations
@ethiopianexaminations

Ministry Of Education

05 Oct, 01:06


የመግቢያ ቀን መራዘሙን ስለማሳወቅ

የደብረታቦር ዩኒቨርስቲ አዲስ መደበኛና ኤክስቴንሽን ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ መስከረም 24-28 ተብሎ የነበረ ቢሆንም ከምደባ መዘግየት ጋር ተያይዞ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

@ethiopianexaminations
@ethiopianexaminations

Ministry Of Education

04 Oct, 16:15


👍የዩኒቨርሲቲ ምደባችሁን መመልከት ትችላላችሁ!

http://twelve.neaea.gov.et/Home/Placement

መልካም የትምህርት ዘመን!

@ethiopianexaminations
@ethiopianexaminations

Ministry Of Education

04 Oct, 14:35


ምደባችሁን ከ11:30 ጀምሮ ተመልከቱ!

ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ!

ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ምደባ ስለትከናወነ የተመደባችሁበትን ከፍተኛ ት/ት ተቋም ከዛሬ ማለትም 23/01/2012 አ.ም. ከ11: 30 ሰኣት ጀምሮ በአገር አቀፍ የት/ት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዌብ ሳይት http://www.neaea.gov.et
ማየት የምትችሉ መሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ያስታውቃል።

@ethiopianexaminations
@ethiopianexaminations