Ethiopian Artificial Intelligence Institute Telegram-Beiträge

This is the official Telegram channel of FDRE Artificial Intelligence Institute.
13,583 Abonnenten
2,804 Fotos
242 Videos
Zuletzt aktualisiert 11.03.2025 07:40
Ähnliche Kanäle

9,504 Abonnenten

9,325 Abonnenten

1,878 Abonnenten
Der neueste Inhalt, der von Ethiopian Artificial Intelligence Institute auf Telegram geteilt wurde.
በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ የሚገኘው #ዲጂታልኢትዮጵያ ዐውደ ርዕይ በምስል
በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ሌሎች ተቋማት የተዘጋጀ ዐውደ ርዕይ በሳይንስ ሙዚየም እየቀረበ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምርት እና አገልግሎቶቻቸውን ለአንድ ሳምንት በሳይንስ ሙዚየም ለጎብኚዎች ያቀርባሉ፡፡
ኢንስቲትዩታችንም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረጉ የጤና፣ የቋንቋ፣ ስማርት ሲቲ እና ሌሎች ሲስተሞችን ለጎብኚዎች በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ አፈጻጸምን የሚገመግም የፖናል ውይይት ተካሄደ።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ አፈጻጸምን የሚከታተለው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት አባል ተቋማት የተገኙበት የፖናል ውይይት በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እንዲሁም የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በስራ ኃላፊዎቻቸው አማካኝነት በውይይቱ ተሳትፈዋል። የተቋማቱ አመራሮች በሀገራዊ ስትራቴጂው ጉዞ እና አፈጻጸም ዙሪያ ገለጻ ሰጥተዋል፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በውይይቱ ኢንስቲትዩቱ ከሰው ኃይል አቅም ግንባታ ጋር በተያያዘ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም ዜጎች በ5 ሚሊዮን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ተጠቃሚ በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን እውቀት እየገበዩ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
በስትራቴጂው ትግበራ ወቅት የታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት እና የሀብት ብክነትን ለማስቀረት በቅንጅት እና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግ በመድረኩ ተነስቷል፡፡
በውይይቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ እንደ ሀገር የተያዘውን ራዕይ ለማሳካት የተቋማት መቀናጀት ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራር እና ሰራተኞች ብሔራዊ ቤተመንግሥትን ጎበኙ፡፡
የኢንስቲትዩቱ አመራር እና ሰራተኞች በቅርቡ የታደሰውን ብሔራዊ ቤተመንግሥት እና በውስጡ የሚገኘውን ሙዚየም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ሰራተኞቹ በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ ታሪክ በቤተመንግስቱ ባማረ መልኩ መቀመጡን መመልከታቸውን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም የታሪኩን ጥልቀት እና ስፋት ከኪነ-ሕንጻው አንስቶ በሙዚየሙ እስከሚገኙ ውድ ቅርሶች ድረስ ታሪክን የሚያሳዩ ሕያው ምስክሮች ሆነው እንዳገኟቸው ገልጸዋል፡፡
በብሔራዊ ቤተመንግስት የተደረገው እድሳት ታሪካዊ ቅርሶች ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር ተጣምረው የቀረቡበት መሆኑን ሰራተኞቹ ተመልክተዋል፡፡ ይህም ትናንትን ከዛሬ ያገናኘ የታሪክ ሰንሰነለት በመፍጠር ትውልዱ የራሱን ታሪካዊ ዐሻራ እንዲያኖር ከፍተኛ ተነሳሽነት እንደሚፈጥር ሰራተኞቹ በሰጡት አስተያየት አመላክተዋል፡፡
ጉብኝቱ በኢንስቲትዩቱ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን በውጤታማነት ለማስቀጠል ትልቅ ትርጉም ያለው እና ለሰራተኛውም ተነሳሽነትን የሚፈጥር ስለመሆኑ ተመላክቷል፡፡

“ተቋማትን በማዘመን እና ሀገር አቀፍ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ባለፉት ስድስት ወራት በትኩረት ተሰርቷል፡፡” የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር- ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራር እና ሰራተኞች የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱን ባቀረቡበት ገለፃቸው ባለፉት ስድስት ወራት ቴክኖሎጂውን በተለያዩ ዘርፎች በተግባር በማዋል ረገድ በርካታ ውጤቶች መገኘታቸውን አንስተዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በማብራሪያቸው በፕሮጀክት አፈፃፀም፣ ፖን አፍሪኮን ኤ.አይ 2024 ኮንፍረንስን የመሰሉ ዓለማቀፍ ሁነቶችን በማዘጋጀት፣ በሰው ኃይል አቅም ግምባታ፣ ወረቀት አልባ አሰራርን በመተግበር እና ለሌሎች ተቋማት ድጋፍና ስልጠና በመስጠት ረገድ በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።
የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ውይይት ተደርጓል። በውይይቱም በስራ ክንውን ወቅት ያጋጠሙ ክፍተቶችን ለማረም የተወሰዱ እርምጃዎች በተሳታፊዎች በጥንካሬ ከተነሱት መካከል ተጠቃሽ ነው። በተጨማሪም ተቋሙ እንደ ሀገር የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት እና ከአፍሪካ በዘርፉ ቀዳሚ ተቋም ለመሆን በሪፖርቱ የተጠቀሱ ስራዎች መሠረት ስለመሆናቸው በተወያዮች ተገልጿል፡፡

እ.ኤ.አ በ2025 ለመካሄድ ቀጠሮ ከተያዘላቸዉ በርካታ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሁነቶች መካከል እጅግ ተጠባቂ የሆኑ 4 መርሓ ግብሮችን እንጠቁማችሁ፡፡
ናይጄሪያ በአፍሪካ የመጀመሪያውን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ዩኒቨርሲቲ ልትከፍት ነው፡፡
ዊኒ ኢንስቲትዩት ተብሎ የተሰየመው ዩኒቨርሲቲው በሌጎስ፣ ናይጄሪያ ትምህርት የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ተቋሙ ወጣት ናይጄሪያውያንን በኤ.አይ ቴክኖሎጂ እውቀት እንዲኖራቸው ለማድረግ እና በዘርፉ ሀገሪቱን ዓለማቀፍ ተወዳዳሪ ማድረግን ያለመ ነው።
ዊኒ ዩኒቨርሲቲ በኳታር በተቋቋመው እና በተመሳሳይ ስም በሚታወቀው የኤ.አይ ዩኒቨርሲቲ አነሳሽነት የተመሰረተ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲውን በናይጄሪያ ለማቋቋም ጥረቶች የተጀመሩት እ.ኤ.አ በ2016 ነበር፡፡ ጥረቱ ከናይጄሪያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ኮሚሽን ከፍተኛ ድጋፍ እና ተቀባይነት በማግኘት ወደስራ ሊገባ መሆኑን ኮኔክቲንግ አፍሪካ በድረገጹ አስነብቧል፡፡
ዩንቨርሲቲው በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ብሎክቼይን፣ ክላውድ ኮምፒውቲንግ እና ማሽን ለርኒንግ የትምህርት መስኮች ትምህርት የሚሰጥ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ መከፈት ሥራ አጥነትን ለመቀነስ እና በአፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ እውቀትን የታጠቀ ማህበረሰብን ለማፍራት አስተዋጽኦው ጉልህ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ተቋሙ ሌጎስን የአፍሪካ ሲሊከን ቫሊ ማዕከል በማድረግ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ለኢኮኖሚ እድገት እንዲውል ማድረግን ተልዕኮው አድርጓል፡፡

እንኳን ለከተራ እና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!
መልካም በዓል!