የስራ ኃላፊዎቹ ከኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዩች ዙሪያም ውይይት አድርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) የስራ ኃላፊዎቹን ተቀብለው ስለኢንስቲትዩቱ ስራዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
የጆን ስኖው ኢንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ቢንያም ፍቃዱ (ዶ/ር) የተመራው የስራ ኃላፊዎች ልዑክ ኢንስቲትዩቱ የሰራቸው ስራዎች የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ኃላፊዎቹ በጉብኝታቸው ወቅት የኢንስቲትዩቱ ስራዎች የማህበረሰቡን ችግሮች የመፍታት አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑን እንደተገነዘቡ አንስተዋል። በተጨማሪም ተቋሙ ለአፍሪካ ሃገራት ተምሳሌት መሆን እንደሚችል አመላክተዋል።
በተለይም ኤ.አይ በጤናው ዘርፍ ያለውን አበርክቶ በተግባር እንደተመለከቱ እና ለወደፊቱ ቴክኖሎጂውን በስፋት ተግባራዊ ለማድረግ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ጆን ስኖው ኢንክ ላለፉት 30 ዓመታት በኢትዮጵያ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ዲጂታል የጤና ሥርዓቶች ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰራ የሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም ነው።
ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም