Neueste Beiträge von Ethiopian Artificial Intelligence Institute (@ethiopianaii) auf Telegram

Ethiopian Artificial Intelligence Institute Telegram-Beiträge  

Ethiopian Artificial Intelligence Institute
This is the official Telegram channel of FDRE Artificial Intelligence Institute.
13,583 Abonnenten
2,804 Fotos
242 Videos
Zuletzt aktualisiert 11.03.2025 07:40

Ähnliche Kanäle

telebirr
328,034 Abonnenten

Der neueste Inhalt, der von Ethiopian Artificial Intelligence Institute auf Telegram geteilt wurde.

Ethiopian Artificial Intelligence Institute

07 Feb, 10:48

1,482

ዘጋቢ ፊልሞችን ያዘወትራሉ?

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዙሪያ የተሰሩ እና የቴክኖሎጂውን እድገት ከዘርፉ መሪ ተዋንያን አንደበት የሚያስቃኙ ጥቂት ዘጋቢ ፊልሞችን እንጠቁማችሁ።

በፊልሞቹ ቴክኖሎጂው ያስገኛቸው እድሎች፣ ፈተናዎች እና መጻኢ ተስፋዎች ከተለያዩ የታሪክ ሁነቶች አንፃር ተዳሰዋል።

በጥቆማው የቀረቡትን ሁሉንም ዘጋቢ ፊልሞች በዩትዩብ ማግኘት ይችላሉ።

#AIDocumentary #Documentary #MachineLearning #ArtificialIntelligence #FutureOfAI

ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

07 Feb, 05:15

1,541

ኦፕን ኤ.አይ ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ ሁለት አዳዲስ የኤ.አይ ሥርዓቶችን (ኤጀንቶች) አስተዋወቀ፡፡

የመጀመሪያው ኤ.አይ ኤጀንት ለጥናትና ምርምር ስራ አጋዥ እንዲሆን የተሰራ ነዉ፡፡ ዲፕ ሪሰርች የተሰኘው ኤጀንቱ የኦፕን ኤ.አይ ኦ ስሪ ሚኒ (o3-mini) ሞዴልን በመጠቀም በልጽጓል፡፡

በጥናትና ምርምር ስራ ዉስጥ ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጀዉ የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን አስሶ የተጠናከረ ጽሁፍ ማዘጋጀት ነዉ፡፡ ኤጀንቱ በበይነ መረብ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ጽሁፎችን፣ ምስሎችን እና ሰነዶችን አሰሳ በማድረግ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ትንተና ያዘጋጃል፡፡

ዲፕ ሪሰርች በቻት ጂፒቲ ላይ የሚገኝ ሲሆን የካቲት ወር መጨረሻ ላይ አዳዲስ ማሻሻያዎችን በማካተት በመተግበሪያ መልኩ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ተነግሯል፡፡

ሌላኛዉ ኤ.አይ ኤጀንት ደግሞ ‎ኦፕን ኤ.አይ ኦፕሬተር ይሰኛል፡፡ ኮምፒዩተር ዩዚንግ ኤጀንት (CUA) የተሰኘ አዲስ ሞዴልን በመጠቀም የበለፀገ ነዉ፡፡ ይህ ኤጀንት በበይነ መረብ አሳሾች (ብራውዘር) ላይ በተጠቃሚዎች ፍላጎት መሠረት የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የሚችል ነው፡፡ በዚህም ቅጾችን መሙላት፣ ሸቀጦችን ማዘዝ፣ የሆቴሎች ዋጋ ዝርዝርን ማጥናት እና የተሻለ ዋጋ ያለውን ማሳወቅ የመሳሰሉ ስራዎችን በመከወን የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ያሟላል፡፡

ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

06 Feb, 14:43

1,601

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት መርሓ ግብርን ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለማስተማር የሚያስችል የትግበራ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ያለመ ነው፡፡

በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ ለመርሓ ግብሩ ዉጤታማነት በትጋት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡ እንደ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ እንደሀገር በመስኩ ያለውን የተማረ የሰው ኃይል እጥረት በመፍታት ሀገሪቷን ከዘርፉ ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር በዓለማቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የሰው ኃይል ለመፍጠር የስምምነቱ አስተዋጽኦ የላቀ ነው፡፡

በስምምነቱ ላይ የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ከማል ኢብራሂም (ዶ/ር) መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የትምህርት መርሓ ግብሩ በከፍተኛ ተፈጻሚነት እንዲተገበር የተቋማቱ በትብብር መስራት የማይተካ ሚና እንዳለው ም/ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡ ስምምነቱ የተማሪዎችን የዳታ እጥረት ችግር በመፍታት ምርምሮቻቸዉን መስራት የሚችሉበት እድል በመፍጠሩ ተፈጻሚነቱን ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆናቸዉንም አስታዉቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩቱ ቀደም ሲል ከአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በሀገራችን የመጀመሪያውን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሦስተኛ ዲግሪ መርሓ ግብር በማስተማር ላይ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

06 Feb, 09:35

1,572

ግዙፍ ሀብት የሚንቀሳቀስበት የግንባታውን ዘርፍ ለማቀላጠፍ ለባለሙያዎች እገዛ የሚያደርጉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ መተግበሪያዎችን እናስተዋውቃችሁ!

መተግበሪያዎቹ ለተወሰነ ጊዜ ከፊል አገልግሎት በነጻ የሚሰጡ ሲሆን ለሙሉ አግልግሎት ክፍያ የሚጠይቁም ይገኙበታል፡፡
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

06 Feb, 06:26

1,553

https://youtu.be/f3sZuGulfII
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

05 Feb, 17:45

1,758

ሥነ-ምግባራዊ አመራር እና ፀረ-ሙስና ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

‎ለኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና ለፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አመራሮች “ሥነ-ምግባራዊ አመራር ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት” በሚል መሪ ቃል ከፌደራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው።

‎ስልጠናው የሙስና ወንጀል አይነቶች፣ ምንነቶች፣ ልዩ ባሕርያት እና የሙስና ወንጀሎች የሚያስከትሉት ጉዳት እና የመከላከያ ስልቶች ላይ ያተኮረ ነው።

በስልጠናው ተሳታፊ አመራሮች ውስብስብ የሆነውን የሙስና ወንጀል በመከላከል ረገድ ጊዜውን የሚመጥን ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያስችል ነው፡፡

ሦስቱ ተቋማት በቴክኖሎጂ የታገዘ የሙስና መከላከያ ሥርዓት በማልማት እያደረጉ ያለውን ተግባር ከማጠናከር በተጨማሪ አመራሮቹ ተቋማዊ እና ሀገራዊ የፀረ-ሙስና ትግሉን በሚገባ ተገንዝበው ለተግባራዊነቱ እንዲረባረቡ በመድረኩ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

05 Feb, 09:34

1,573

Officials from Zeel AI visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute.

The delegation received a comprehensive tour of the institute's facilities and was welcomed by the institute’s Deputy Director General, Mr. Yitagesu Desalegn. The Deputy Director General provided a comprehensive overview of the institute's multifaceted, AI focused operations, research, and initiatives.

During the visit, the Deputy Director General highlighted the institute’s engagement in integrating AI technology into various sectors, showcasing its commitment to leveraging AI for national development. Furthermore, the Deputy Director General emphasized the institute's focus on addressing pressing societal challenges through AI-driven solutions.

The visit culminated in a detailed discussion between the delegation and the institute’s high-level officials to explore potential collaboration initiatives.

Zeel AI is a privately-funded defense technology company that focuses on developing scalable defense platforms.
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

31 Jan, 13:51

991

በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ በሚገኘው #ዲጂታል_ኢትዮጵያ ዐውደ ርዕይ ላይ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከቀረቡ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል AI-Based Smart Court System አንዱ ነው፡፡ ለመሆኑ ይህ ሲስተም ምን አይነት ገጽታዎች አሉት?

AI-Based Smart Court System በውስጡ አምስት የተለያዩ ነገር ግን በአንድነት የሚሰሩ ሲስተሞችን ያካተተ ነው፡፡ እነዚህም፡-

1️⃣ ቪዲዮ ኮንፍረንስ
2️⃣ ትራንስክሪፕሽን (የአማርኛ ድምጽን ወደ ጽሁፍ የሚቀይር)
3️⃣ ቻትቦት
4️⃣ ሞባይል መተግበሪያ እና
5️⃣ ቅሬታ ማስተናገጃ ናቸው፡፡


ይህን የተቀላጠፈ የፍትሕ ሥርዓት መስጠት የሚያስችል ሲስተም ተግባራዊ ለማድረግ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የስማርት ኮርት ሩም ግንባታ ተከናውኗል፡፡ ስማርት ኮርት ሩም ሙሉ የችሎት ሂደትን በቪዲዮ እና በድምጽ ለመሰነድ ከማስቻሉም ባሻገር የችሎት ሂደቱን በአካል ቦታው ላይ መገኘት ሳያስፈልግ በቪዲዮ ኮንፍረንስ አማካኝነት ማካሄድ የሚያስችል እድል ይሰጣል፡፡

የዚህ ሥርዓት ቁልፍ አካል የሆነው የትራንስክሪፕሽን (የአማርኛ ድምጽን ወደ ጽሁፍ የሚቀይር) ትግበራ ምን ይመስላል?

🟠 በችሎት ሂደት የሚደረጉ ንግግሮችን ወደ ጽሁፍ ይቀይራል፣
🟠 ተግባራዊ ከተደረገ ጀምሮ 11,677 የችሎት ውሎዎችን ወይም በሰዓት ሲተመን 2917 ሰዓት የሚጠጋ ድምጽን ወደ ጽሁፍ በመቀየር ደንበኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ አስችሏል፡፡


በተጨማሪም ከላይ በተጠቀሱት አምስት የሲስተሙ አካላት አማካኝነት ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች በመስጠት የፍትሕ ስርዓቱን ለማቀላጠፍ እየዋለ ይገኛል፡፡
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

30 Jan, 12:00

1,494

https://youtu.be/Bn7wrvtqARc
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

30 Jan, 10:37

1,403

በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ የሚገኘው #ዲጂታልኢትዮጵያ ዐውደ ርዕይ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) አገልግሎቶቻቸውን ለጎብኚዎች እያቀረቡ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ይዟቸው ከቀረቡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴከኖሎጂን መሠረት ካደረጉ ሥርዓቶች መካከል ጥቂቶቹን እናስተዋውቃችሁ፡፡

🟠 Ethiopian Federal Police App (EFP App)
🟠 AI-Based Smart Court System
🟠 Smart City & Tier-3 Cloud Modular Datacenter
🟠 Learn and Transcribe ET Language
🟠 AI-Based Breast Cancer Screening System
🟠 ECG Based Interpretable Heart Disease Detection System