አይፈቅደኝም ፣ አይፈቅድሽ ፣ አይቅደንም።
✍️የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ብቻ የሚለው ዘላለማዊ እውነት ነው። እግዚአብሔር ክብሩን ለማንም ለመስጠት ወደፊትም ቢሆን አይስማማም። አባትነቱም ፣ ሁሉን ቻይነቱ ፣ ሁሉን አዋቅነቱ ለዘለዓለም እንደሆነ ሁሉ ፣ ክብሩን መቀበሉ ዘላለማዊ ነው። ክብሩን ለመውሰድ ሊገልም ፣ ሊያድንም ፣ ሊያከብርም ፣ ሊያዋርድም ፣ ሊሾምም ልሽርም ይችላል። ብቻ ክብሩን የሚያገኝበትን መንገድ በራሱ ፍጹም ፈቃድ ይሠራል። ክብሩን የሚወስድበት መንገድም ሥራም ከራሱ ፍጹም ፈቃድ ይመነጫል። የክብሩ መቀበያ መንገድ ከሰው ልጆች እውቀት የላቀ ነው።
“በዚያም ሰዓት የሰው እጅ ጣቶች ወጥተው በንጉሡ ቤት በተለሰነው ግንብ ላይ በመቅረዙ አንጻር ጻፉ፤ ንጉሡም የሚጽፉትን ጣቶች አየ”(ዳን 5፥5)።
✍️የእስራኤል ሕዝብ በባርነት እየማቀቀ ነው። ሕዝበ ባቢሎን ገዢ በመሆን የሰባ ዓመት የበላይነት ድል ተቀናጅተዋል። ናቡከደነፆር በትዕቢቱ ምክንያት ለሰባት ዓመት ሣር እንዲበላ በማድረግ እግዚአብሔር ጉልበቱን አሳይቷል። ናቡከደነፆር እስራኤልን እንጂ የእስራኤልን አምላክ አልገዛም። እግዚአብሔር እሱ ሉዓላዊነቱን ያሳየበት ዘመን ነው። ዳርዮስ አባቱን ተክቶ ንጉሥ ወደ መሆን መጥቶ ሳለ ፣ ናቡከደነፆር ከእስራኤል አገር አባቱ ያጋዛቸውን የወርቅ ፣ የብር ፣ የናስ ፣ እና የተለያዪ የቤተመቅደሱን እቃዎች ለመጠጥ ተጠቀመ። በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ከዙፋኑ ፈጣን እጅ ላከ ፣ በተለሰነው ግርግዳ ፊት ለፊት የሽረት እና የፍርድ ጽሑፍ ለንጉሡ ተጻፈለት። ምንም እስራኤል በባቢሎን ተገዢነት ቢኖርም ፣ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር አብሮ እንዳለ አሳይቷል። እግዚአብሔር በምንም አጋጣሚ ቢሆንም ባቢሎንን አይወግንም።
✍️ቅዱስ ቃሉ ንጉሥ ተዳናገጠ ፣ ተብረከረከ ፣ የወገቡ ጅማት ላላ ፣ ንጉሥ መቆምም መቋቋምም አልቻለም ይላል። ኃይል የእግዚአብሔር ነው። የጽሑፉን ፊቺ ሳይሰማ ንጉሡ መርበድበዱ ከእጁ ጋር አብሮ የተገለጠ ኃይል እንዳለ ማሳያ ነው። እግዚአብሔር የባቢሎንን ንጉሥ ከመንበሩ ላይ የማንሳት ሥልጣን አለው። እግዚአብሔር በጥበቡ ሰለሞን በኩል ለራሱ የቀሳቸውን የወርቅ ዕቃዎችን ካልፈቀደ ፣ ልጁ ኢየሱስ የሞተልንን እኛን እንዴት አብልጦ ይከላከል ይሆን !! ኃይል የእግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር በናቡከደነፆር ፣ በዳርዮስ ፣ በሌሎች ነገሥታት ላይ ደግሞም በሕዝበ እስራኤል ላይም የበላይ ነው። በዋጋ ተገዝታችዋልና አይፈቅዳችሁም። የተቀደሱ ወርቆችን ለባቢሎን ንጉሥ እንዳልፈቀደ ፣ በክርስቶስ በኩል የተቀደሰን እኛን ለጠላት መጠቀሚያ በፍጹም አይፈቅድም። አይፈቅደኝም ፣ አይቅድሽም ፣ አይፈቅድህም ፣ አይፈቅደንም ፣ አይፈቅዳችሁም። የ ጨለማው ዓለም በእኛ ላይ ፈቃድ የለውም። የአምላካችን ፈቃድ ከጠላት ዓላማና እላማ እኛን መጠበቅ ነው።
“በዋጋ ተገዝታችኋል፤ የሰው ባሪያዎች አትሁኑ”1ኛ ቆሮን 7፥23።
✍️አይቅደኝም ፣ አይፈቅድሽ ፣ አይቅደንም።
✍️Abuna
@EsayasAbuna
@Gospelofchristjesus