የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ (@communitypvc)の最新投稿

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ のテレグラム投稿

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
2,020 人の購読者
1,640 枚の写真
34 本の動画
最終更新日 10.03.2025 03:06

類似チャンネル

President Q
7,188 人の購読者
West Hararghe Prosperity Party
4,465 人の購読者
Kello Media
2,096 人の購読者

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ によってTelegramで共有された最新のコンテンツ

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

04 Mar, 15:11

136

‎ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ ልማትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተጠቆመ።

‎የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሞዴል ብሎክ ልማት ተግባራትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

‎በክፍለ ከተማው ወረዳ ሁለት ክላስተር ሦስት ብሎክ 19 ልዩ ስሙ አዲስ ቪሌጅ በተሰኘ መንደር የተጀመሩ የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ መሰረተ ልማቶችን ኃላፊዎቹ ጎብኝተዋል።

‎በብሎኩ የህጻናት ማቆያና መጨዋቻ ስፍራዎች፣ የአረንጓዴ ልማቶች፣ የአረጋውያን ማረፊያ ቦታዎችንና ሌሎች የሞዴል ብሎክ መመዘኛ መስፈርቶችን ያካተቱ ልማቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

‎የብሎኩ አመራሮች አደራ ፋውንዴሽን ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከ200 በላይ ህፃናትን በቀዳማይ ልጅነት መርሃ ግብር የመንከባከብና በአካልና በአዕምሮ የዳበረ ትውልድ ለማፍራት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። ግብረ ሰናይ ድርጅቱ የአካባቢውን ነዋሪዎች ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ ህፃናትን ከልጅነት እስከ 12ኛ ክፍል በነፃ እያስተማረ መሆኑን ገልጿል።

‎የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ አዲስ አበባ ከስሟ ጋር የሚመጣጠን ግብር እንዲኖራት ለማድረግ የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ ልማት ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል።

‎ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚረጋገጠው ከመኖሪያ ብሎክ የሚጀምር ሞዴልና ፅዱ አካባቢ መፍጠር ሲቻል መሆኑን የተናገሩት ኮሚሽነሩ ብልፅግና ፓርቲ ዓላማውን መሰረት ያደረገ ከታች የሚጀምር ብልፅግናን እውን ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

‎የኮሚሽኑ አመራሮች በክፍለ ከተማው ከሞዴል ብሎክ ልማቶች በተጨማሪ በኅብረተሰቡ ተሳትፎ የተሰሩ የኮብልስቶን ፕሮጀክቶችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

‎"ሁሉ አቀፍ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!"
‎የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
‎ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
‎ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
‎ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@aacpvcc
‎ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
‎ዌብሳይት - www.aacpvcc.gov.et
‎Instagram - https://www.instagram.com/aacpvcc/
‎Twitter - https://x.com/aacpvcc

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

03 Mar, 18:39

152

‎ታላቁን የረመዳን ፆም ምክንያት በመድረግ የተለያዩ የበጎነት ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

‎ረመዳን በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ የእዝነትና የርህራሄ ወር ተደርጎ ይወሰዳል። ያለው ለሌለው በማካፈል ከፈጣሪ መንፈሳዊ ፀጋ የሚያስገኝ የበጎነት ስራ ይከናወንበታል።

‎የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በጎ ፈቃደኛ ለጋሾች ይህን የበጎነት ወር ከተቸገሩ ወገኖች ጋር እንዲያሳልፉና ካላቸው እንዲለግሱ በማስተባበር ላይ ይገኛል።

‎የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አብነት አካባቢ የሚገኘው የኡመር ኢብኑል ኸጣብ 26 መስጊድ ወጣት ጀመዓ 1 ሺህ 446ኛው የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ ለ500 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አደርጓል። በዚሁ ክፍለ ከተማ የወረዳ 1 የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ከሰላም መስጊድ እና ከተለያዩ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመተባበር ከ161,000 ብር በላይ ማዕድ አጋርቷል።

‎የሲር ለና በጎ አድራጎት ድርጅት በበኩሉ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ለሚገኙ 900 አቅመ ደካሞች 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት የረመዳን ማዕድ አጋርቷል። በጎ አድራጎት ድርጅቱ የማዕድ ድጋፉን ከሰሎሜ የሴቶች አቅም ግንባታ፣ ከዳሽን ባንክ ሸሪክ፣ ከአምሪን አግሪካልቸራልና ፕሮሰሲግ ድርጅት፣ ከሱመያ ት/ቤት 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች እና በተለያየ ሀገር ከሚኖሩ የግል ባለሀብቶች እንዳሰባሰበው ገልጿል።

‎የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ወረዳ 9 አስተዳደር ከዳሩል ዝክር የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ከ900 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን የረመዳን ማዕድ አጋርቷል።

‎የአራዳ ክፍለ ከተማ በበኩሉ ከ800 በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ ለግሷል።

‎1 ሺህ 446ኛውን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ የተቸገሩ ወገኖችን የመደገፍ፣ የአፍጥር መርሃ ግብር የማዘጋጀትና እርስ በርስ መደጋገፍ እንዲጎለብት የማስተባበር ስራው በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሏል።

‎"በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!"

‎የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
‎ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
‎ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
‎ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@aacpvcc
‎ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
‎ዌብሳይት - www.aacpvcc.gov.et
‎Instagram - https://www.instagram.com/aacpvcc/
‎Twitter - https://x.com/aacpvcc
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

03 Mar, 18:38

122

‎የኅብረተሰቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ ተግባራት በስፋት እየተከናወኑ ነው።

‎የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በመንግስትና በህዝብ አጋርነት ለኅብረተሰቡ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ ተግባራትን በየክፍለ ከተማው በስፋት እያከናወነ ይገኛል።

‎የአካባቢ ልማት ስራዎች በስፋት እየተከናወነባቸው ከሚገኙ ክፍለ ከተሞች መካከል የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ይገኝበታል። ማኅበረሰቡ የሚያነሳቸውን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ነዋሪውን እና በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስተዳደሩ አስታውቋል።

‎ የክፍለ ከተማው ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ባደረሰን መረጃ በወረዳ 12 አስተዳደር ልዩ መጠሪያው ሳሎ ጎራ ማህበር ቤቶች በመንግስትና በማኅበረሰቡ አጋርነት የኮብልስቶን መንገድ ንጣፍ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

‎"ለረጅም ጊዜያት ስንጠይቅ የነበረዉ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ አግኝቷል!" ያሉት የአካባቢው ነዋሪ አቶ ካህሳይ መዝገቡ አካባቢው ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት የዉስጥ ለዉስጥ ኮብልስቶን መሰረተ ልማት ያልነበረውና በክረምት ወቅት በነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ የጎርፍ አደጋ ሲያደርስ የነበረ መሆኑን አንስተው ኅብረተሰቡ ከወረዳ አስተዳደሩ ጋር ደረጃውን የጠበቀ የኮብልስቶን መንገድ መዘርጋቱን ተናግረዋል።

‎የወረዳ 12 የህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ዘውዱ በበኩላቸው አስተዳደሩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የነበረውን የኮብልስቶን መንገድ ንጣፍ ችግር ለመፍታት ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀናጅቶ 2.7 ኪ.ሜትር ደረጃውን የጠበቀ ኮብልስቶን ፕሮጀክት ማጠናቀቁን ጠቅሰዋል።

‎በመዲናዋ በህዝብና መንግስት ትብብር መሰል የአካባቢ መሰረተ ልማት ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል።

‎የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
‎ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
‎ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
‎ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@aacpvcc
‎ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
‎ዌብሳይት - www.aacpvcc.gov.et
‎Instagram - https://www.instagram.com/aacpvcc/
‎Twitter - https://x.com/aacpvcc
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

02 Mar, 04:43

209

እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ አደረሰን

የአደዋ ድል የኢትዮጵያዊያን ሕብረ ብሔራዊነት መገለጫ፣ የይቻላል መንፈስ ምንጭ፣ ያለፉ እና የቀጣይ ትውልዶች የወል ትርክት ነው።
የአደዋ ድል በዓልን ስናከብር ድሉ በፈጠረልን የአንድነት እና የይቻላል መንፈስ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ያለንን ቁርጠኝነት በመግለፅ እንዲሆን ጥሪየን አስተላልፋለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

01 Mar, 19:06

173

ከሁሉ በማስቀደም የረዳን እና ያከናወነልን ፈጣሪ ይመስገን!

ዛሬ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ያስመረቅነው የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከል ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን አዳዲስ እድሎችን የሚከፍት፣ የማያቋርጥ የሃብት ምንጭ መፍጠሪያ የሚሆን እንዲሁም ለገጽታ ግንባታ እና ለቱርስት ስበት ትልቅ ሚና የሚጫወት ማዕከል ነው::

ማዕከሉ አለምአቀፋዊ ኮንፍራንሶችን፣ የንግድ ውይይቶችንና ስምምነቶችን፣ ባህላዊ መድረኮችንና ልዩ ልዩ ኤግዚቢሽኖችን ለማስተናገድ እንዲሁም አዳዲስ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩበት የንግድና የኢኮኖሚ ስምምነቶች የሚጎለብቱበት ነው::

15ሺ ካሬ የውጪ ሁነት ማስተናገጃ ቦታ ያለው የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከል ባለ 5 ኮከብ ዘመናዊ ሆቴል፣ ሪስቶራንቶች፣ የስፖርት፣ የጤና፣ የመዝናኛ እና የልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫን ያከተተ ግዙፍ ማዕከል ነዉ።

ከዚህም ባሻገር፣ በአንድ ጊዜ እስከ 2000 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችል ፓርኪንግ ያለዉ ሲሆን የለሚ ፓርክ እና በቀጥታ ከአየር መንገድ ጋር የሚያገናኝ ሰፊ የመንገድ መሰረተ ልማትም ከማዕከሉ ጋር ተያይዞ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ፤ይህም ኢኮኖሚያችንን የሚያነቃቃ፣ ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር ከመሆኑ በላይ እንግዶች ሲመጡ ያለምንም እንግልት ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ስፍራ እንዲያገኝ ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡

ይህ ስራ ከዳር እንዲደርስ የቅርብ ድጋፍና ክትትል ላደረጉልን ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ከፍ ያለ ምስጋናና አክብሮቴን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላቀርብ እወዳለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

01 Mar, 18:59

146

"አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ኢትዮጵያ ሰርታ የምታሳይ ሀገር መሆኗን የሚያሳይ ነው።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

“በዚህ ዓለም ዐቀፍ ማዕከል ንግድ እንነግድበታለን፣ እውቀት እንለዋወጥበታለን፣ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን እንቀምርበታለን” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ማዕከሉ በኢትዮጵያ ሀሳብን አልቆ መፈፀም ልምድ እየሆነ መምጣቱን ማሳያ ነውም ብለዋል።

በሀሳብ ደረጃ የነበረውን ጅምር ከዕቅዱ በላይ ዓለም አቀፍ ደረጃውን ያሟላ አድርገን አልቀን መስራታችንም ለዚህ ዋቢ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

“መፍጠን፣ መፍጠር፣ መስራት ይጠበቅብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመሩት ስራዎች ውጤት እያሳዩ ነው ብለዋል።

“ነገር ግን ስራዎች በችግር ውስጥ እንደሚሰራ መረዳት ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የምንፈልገውን ለውጥ እስክናመጣ አበክረን መስራት ይገባናል ሲሉ ነው ያሳሰቡት።

“ኢትዮጵያን የሚያህል አዲስ አበባን የሚመጥን ለውጥ ማምጣት አላማችን ነው። ለልጆቻችን በረከት ለማውረስ የምታኮራ ሀገር ለማስረከብ እንሰራለን። ኢትዮጵያም ይህንን ማድረግ ትችላለች” ብለዋል።

አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ለቀጣዮቹ 10 ቀናት ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ህዝቡ መጥቶ እንዲጎበኝም ጋብዘዋል።
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

21 Jan, 19:07

260

ባለፉት ስድስት ወራት በኅብረተሰቡ ተሳትፎ 62.9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአካባቢ ልማት ማከናወኑን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው ለኮሚሽኑ ኮሙኒኬሽን እንዳስታወቁት በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት የክፍለ ከተማውን ኅብረተሰብ በማሳተፍ 31 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ፣ በዓይነትና በጉልበት ለመሰብሰብ ታቅዶ 62.9 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል። ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውና ለመሰረተ ልማት ተግባር ማዋጣት ለማይችሉ ነዋሪዎችም ፕሮጀክት በመቅረፅና 1.1 ሚሊዮን ብር በመሰብሰብ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች መከናወናቸውን ነው ኃላፊዋ የተናገሩት።

ኅብረተሰቡን በአካባቢ ልማት በስፋት በማሳተፍም 19.6 ኪ.ሜ ሰቤዝና 16.1 ኪ.ሜ ኮብል ጥገና ተከናውኗል ብለዋል። የኅብረተሰቡን የልማት ፍላጎት መሰረት በማድረግ 4 አነስተኛ ድልድዮች፣ 10.7 ኪ.ሜ ቱቦ ቀበራ፣ 10 ኪ.ሜ ቱቦ ጥገና፣ 3 የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ማዕከላት እንዲሁም 5 የጋራ መፀዳጃ ቤቶች ተገንብተዋል።

የተሰሩ ልማቶች ለኅብረተሰቡ የረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ መሆናቸውን የተናገሩት ወ/ሮ እቴማር 9.4 ኪ.ሜ የዲች ስራ፣ 4 ኪ.ሜ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መብራት ዝርጋታ እና 2.8 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ መሰራቱን ገልፀዋል። 5 ኪ.ሜ ቴራዞ ንጣፍ እና 2 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ መከናወኑን ኃላፊዋ አክለዋል።

በክፍለ ከተማው በተከናወኑ መሰረተ ልማቶች ለ628 ወጣቶች ጊዜያዊ የስራ እድል እንዲሁም 62.9 ሚሊዮን ብር የገቢያ ትስስር ተፈጥሯል።

ማኅበረሰቡን በአካባቢ ሰላም፣ በፅዳት፣ በልማት፣ በመልካም አስተዳደር እና በሌሎች ተግባራት በማስተባበርም 64 ብሎኮችን ሞዴል ማድረግ መቻሉን ያብራሩት ኃላፊዋ ኅብረተሰቡ በአካባቢ ልማትና ሰላም እያሳየ ያለውን የነቃ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

17 Jan, 17:32

297

ከ11 ሺህ በላይ የአካባቢ ቅጥር ጥበቃዎች ስምሪት መሠጠቱ ተገለጸ።

ኮሚሽኑ ለጥምቀት በዓል በህብረተሰብ ተሳትፎ ለተቀጠሩ ቅጥር የአካባቢ ጥበቃዎችና ለብሎክ ካውንስል አባላት ስምሪት መስጠቱን አስታውቋል ።

በዓሉ ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በሠላም እንዲከበር ለብሎክ ካውንስል አባላትና ለአካባቢ ቅጥር ጥበቃዎች ስልጠና በመስጠት ስምሪት መስጠቱን የህብረተሰብ ተሳትፎ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ፀሐይ ኪባሞ ገልፀዋል ።

የብሎክ ካወንስል አባላትና አመራሮች ነዋሪውን በማስተባበር የበዓል ማከበሪያ ቦታዎችንና መኖሪያ አካባቢያችን በንቃት መጠበቅ አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ደግሞ ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት የሚያስችል ስልጠና መሰጠቱንና አደረጃጀት መፈጠሩን ምክትል ኮሚሽነር ፀሐይ ኪባሞ አክለው ገልጸዋል ።

በመድረኩ የተገኙት አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ በየደረጃው ያለዉ የፀጥታ ኃይል በዓሉን በሠላም ማክበር የሚያስቸል በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልፀው የቅጥር ጥበቃ አባላትም የኋላ ደጀን በመሆን የመኖሪያ ቤቶችንና ድርጅቶችን በንቃት መጠበቅ የሚያስችል ስምሪት መውሰዳቸው የተቀናጀ ውጤት ማምጣት የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል ።

በስልጠና ማጠቃለያ መድረኩ የተሳተፉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከፀጥታ ኃይሉና ከወጣቱ ጋር በመቀናጀት በዓሉ ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር ለመኖሪያ አካባቢዎች ትኩረት ሰጥተው በንቃት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል ።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

17 Jan, 17:31

209

ተገልጋይ በሚበዛባቸው የመንግስት ተቋማት የሚያገለግሉ 1 ሺህ 200 በጎ ፈቃደኞች የስራ ስምሪት ወሰዱ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ተገልጋይ በሚበዛባቸው የመንግስት ተቋማት በሙያቸው አገልግሎት ለመስጠት ለተዘጋጁ በጎ ፈቃደኞች የስነ-ምግባር ስልጠናና የስራ ስምሪት መርሀ ግብር አካሂዷል።

የሙያ በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተቋማት ውስጥ የአገልግሎት እንግልት ችግሮችን በማቃለልና የመንግስት ወጪ በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያበረከተ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን በጎ ፈቃደኞች አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት የበጎ ፈቃድ መርሆዎችንና የስነ ምግባር ደንቦችን አክብረው ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው በመድረኩ ተመላክቷል።

በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ህዝብን ለማገልገል ዛሬ የስራ ስምሪትና የስነ ምግባር ስልጠና የወሰዱት 1 ሺህ 200 በጎ ፈቃደኞች ሲሆኑ በገቢ አሰባሰብ ግንዛቤ ማስጨበጥና መረጃ የማደራጀት ስራ ላይ ይሰማራሉ።

በሚሰማሩበት የሙያ ዘርፍ ህዝባቸውን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን በመድረኩ የተገኙ በጎ ፈቃደኞች ተናግረዋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

16 Jan, 16:27

214

ከ12 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች መጪው የከተራና የጥምቅት በዓል በሠላም እንዲጠናቀቅ የማስተባበር አገልግሎት ይሰጣሉ።

በመዲናዋ መጪው የከተራና የጥምቀት በዓል በሠላም እንዲጠናቀቅ ከ12 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች የማስተባበር አገልግሎት ይሰጣሉ።

በወረዳና በክፍለ ከተማ በተካሄዱ መድረኮች በዓሉ ኃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር በጎ ፈቃደኞች የማስተባበር ሚናቸውን መወጣት እንዲችሉ የአገልግሎት ስምሪትና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን በዛሬው ዕለት በከተማ ደረጃ የማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል።

በሁሉም የጥምቀት ማክበሪያ ቦታዎች በጎ ፈቃደኞች ሚናቸውን ለይተው ከበዓሉ ባለድርሻዎች ጋር በመቀናጀት ለበዓሉ በድምቀት መከበር ኅብረተሰባቸውን በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

በጎ ፈቃደኞች በበኩላቸው በዓሉ ከተማዋ የምትደምቅበትና በርካታ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች የሚታደሙበት በመሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በትጋት እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል።

ኃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት ማህበራዊ መስተጋብሮችን በመፍጠር የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህል ይበልጥ የሚገለጡባቸው እሴቶቻችን ናቸው።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis