የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሞዴል ብሎክ ልማት ተግባራትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በክፍለ ከተማው ወረዳ ሁለት ክላስተር ሦስት ብሎክ 19 ልዩ ስሙ አዲስ ቪሌጅ በተሰኘ መንደር የተጀመሩ የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ መሰረተ ልማቶችን ኃላፊዎቹ ጎብኝተዋል።
በብሎኩ የህጻናት ማቆያና መጨዋቻ ስፍራዎች፣ የአረንጓዴ ልማቶች፣ የአረጋውያን ማረፊያ ቦታዎችንና ሌሎች የሞዴል ብሎክ መመዘኛ መስፈርቶችን ያካተቱ ልማቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
የብሎኩ አመራሮች አደራ ፋውንዴሽን ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከ200 በላይ ህፃናትን በቀዳማይ ልጅነት መርሃ ግብር የመንከባከብና በአካልና በአዕምሮ የዳበረ ትውልድ ለማፍራት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። ግብረ ሰናይ ድርጅቱ የአካባቢውን ነዋሪዎች ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ ህፃናትን ከልጅነት እስከ 12ኛ ክፍል በነፃ እያስተማረ መሆኑን ገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ አዲስ አበባ ከስሟ ጋር የሚመጣጠን ግብር እንዲኖራት ለማድረግ የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ ልማት ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል።
ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚረጋገጠው ከመኖሪያ ብሎክ የሚጀምር ሞዴልና ፅዱ አካባቢ መፍጠር ሲቻል መሆኑን የተናገሩት ኮሚሽነሩ ብልፅግና ፓርቲ ዓላማውን መሰረት ያደረገ ከታች የሚጀምር ብልፅግናን እውን ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
የኮሚሽኑ አመራሮች በክፍለ ከተማው ከሞዴል ብሎክ ልማቶች በተጨማሪ በኅብረተሰቡ ተሳትፎ የተሰሩ የኮብልስቶን ፕሮጀክቶችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
"ሁሉ አቀፍ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!"
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@aacpvcc
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.aacpvcc.gov.et
Instagram - https://www.instagram.com/aacpvcc/
Twitter - https://x.com/aacpvcc