Neueste Beiträge von የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ (@communitypvc) auf Telegram

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ Telegram-Beiträge

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
2,020 Abonnenten
1,640 Fotos
34 Videos
Zuletzt aktualisiert 10.03.2025 03:06

Ähnliche Kanäle

Booree Gaafa Xiiqii
2,249 Abonnenten

Der neueste Inhalt, der von የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ auf Telegram geteilt wurde.

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

31 Oct, 09:02

129

ስላምና ደህንነትን በተመለከተ

ከማንም በላይ ሰላም እንፈልጋለን፡፡ ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን፤ አንፈልገውም፡፡ ከኃይል አማራጭ ይልቅ የሰላም አማራጭ ውጤቱ ከፍተኛ ነው፡፡ መንግስት ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ ቅድሚያ ሰጥቶ ሰርቷል፡፡ አሁንም ያለን አቋም የትኛውም አይነት አለመግባባት በሰላም እንዲፈታ ነው፡፡ ነገር ግን የትኛውም አካል በኃይል እና ጥላቻ መጠፋፋትን እንጂ ዓላማውን ማሳካት አይችልም፡፡ ሰከን ብሎ ማሳብ ይገባል፡፡ ሃሳብ አልባ ትግል ፍሬ የለውም፡፡

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

31 Oct, 08:36

145

የኑሮ ውድነትንና የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በተመለከተ

የኑሮ ውድነትን በዘላቂነት መቅረፍ የምንችለው ምርታማነትን በመጨመር ነው፡፡ የንግድ ስርዓቱን ማዘምንም ከፍተኛ ፋይዳ አለው፡፡ የኑሮ ውድነቱ እጅ አጠር ዜጎች ላይ ጫና እንዳይፈጥር መንግስት ከ300 እስከ 400 ቢሊዮን ብር የድጎማ በጀት መድቧል፡፡ ማዕድ ማጋራት፣ ትምህርት ቤት ምገባ እና እሁድ ገበያ መንግስት አቅመ ደካሞችን ለማገዝ የሚያደርገው ጥረት አካል ነው፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃም 249 ሺህ አቅመ ደካማ ዜጎች መኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ይህ መንግስት ባለሃብቶችን በማስተባበር ያከናወነው ስራ ነው፡፡ የዋጋ ንረቱ አሁን ላይ ወደ 17 በመቶ ዝቅ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፤ ይህን ወደ ነጠላ አሃዝ ማውረድ የመንግስት ቀዳሚ ትኩረት ነው፡፡

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

31 Oct, 08:06

157

የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በተመለከተ

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ6 ነጥብ 4 በመቶ አድጓል፡፡በተለይ ለኢንቨስትመንት ምቹ ከባቢ በመፍጠር ረገድ የተከናወኑ ስራዎችም ኢንቨስትመንት ለመሳብ ትልቅ አቅም እየፈጠሩ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ያላት መሬትና ታዳሽ ኃይል፣ እንዲሁም የሰው ሃይል ለኢንቨስትመንት ተመራጭ አድርጓታል፡፡

የወጪ ንግድን በተመለከተ

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ባላፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡በዚህ አፈጻጸም ከቀጠልን በበጀት ዓመቱ መጠናቀቂያ ላይ ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ይገኛል፡፡ ይህ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር የ1 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ አለው፡፡ በተለይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በወርቅ ምርት ወጪ ንግድ ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል፡፡ ባለፉት ሶስት ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ 500 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ ይህም የወርቅ ምርት ምን ያህል ለህገ ወጥ ንግድ ተጋልጦ እንደነበር የሚያሳይ ነው፡፡

የመንግስት ገቢን በተመለከተ

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የመንግስት ገቢ በእጅጉን ጨምሯል፡፡ ባላፉት ሶስት ወራት 180 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል፡፡ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር የተሻለ እድገት የተመዘገበበት ነው፡፡ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት የተሰበሰበው ገቢ 109 ቢሊዮን ብር ብቻ ነበር፡፡

የውጭ ሃብት ፍሰትን በተመለከተ
ባላፉት ሶስት ወራት በተለያየ መንገድ ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር መጥቷል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ ተመዝግቦበታል፡፡ ባለፈው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ሃብት 400 ሚሊዮን ዶላር ነበር፡፡
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

31 Oct, 07:40

113

የኢትዮጵያ አየር መንገድን በተመለከተ

በአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ ይህ አዲስ የሚገነባው የአውሮፕላን ማረፊያም በዓመት ከ100 አስከ 130 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተነናግዳል፡፡ አሁን ላይ 124 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለማግዛት አዘናል፡፡ ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ የአውሮፕላን ባለቤት ብቻ ሳይሆን ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ያለው ተቋም ያደርገዋል፡፡ ይህ ለውጥ በተለይ በአገልግሎት ዘርፍ ለማስመዝገብ የተያዘውን ውስጥ ለማሳካት ሚናው የጎላ ነው፡፡ በተያዘው በጀት ዓመትም የአገልግሎት ዘርፉ 7 ነጥብ 1 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብ ይጠበቃል፡፡

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

31 Oct, 07:23

118

ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ

ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማነቃቃት ከፍተኛ ስራ ተከናውኗል፡፡ በተለይ ከኃይል አቅርቦት ጋር ተያይዞ ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ረገድ የተሻል ስራ የተከናወነ ሲሆን፤ አሁን ላይ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም 67 በመቶ ማድረስ ተችሏል፡፡ የኢንዱስትሪ ዘርፉም በተያዘው በጀት ዓመት 12 ነጥብ 8 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል፡፡

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

31 Oct, 07:22

115

ሌማት ትሩፋት

የሌማት ትሩፋት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተስፋ ሰጪ እድገት የተመዘገበበት ዘርፍ ሆኗል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት በሌማት ትሩፋት ምርቶች የ5 ነጥብ 4 በመቶ እድገት የሚያስመዘግቡ ሲሆን፡፡ ለአብነትም በወተት ብቻ በዓመቱ 12 ቢሊዮን ሊትር የወተት ምርት ይጠበቃል፡፡ በዓመቱ 8 ቢሊዮን የዶሮ እንቁላል እንዲሁም 218 ሺህ ቶን ስጋ እና 297 ሺህ ቶን ማር ምርት ለማምረት የሚያስችል አቅም ተፈጥሯል፡፡

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

27 Oct, 12:28

125

#በጎ_ፈቃደኝነት_ለማኅበረሰብ_ለውጥ!

የ2017 ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ ፕሮግራሞች

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

25 Oct, 18:49

122

የ2017 በጀት ዓመት የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት

👉መሪ ቃሉ “በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ!” የሚል ነው፡፡
👉ከጥቅምት 1/2017 እስከ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ድረስ ለ8 ወራት ይቆያል፡፡
👉 በ12 ዋና ዋና ፕግራሞችና 13 መርሀ ግብሮች ይተገበራል፡፡
👉1 ሚሊዮን በጎ ፈቃደኞች ይሳተፉበታል፡፡
👉781,844 የሕብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ይደረጋሉ፡፡
👉6,599,778,376 ብር የመንግስት ወጪን ይታደጋል፡፡

👏ዋና ዋና ተግባራት፣
👉780,824 የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ ይጋራሉ፡፡
👉4,026 የአረጋውያንና አቅመ ደካሞች ቤቶች ይገነባሉ፡፡
👉100,000 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ የችግኝ እንክብካቤ ይደረጋል፡፡
👉12,000 በጎ ፈቃደኞች ከስኬታማ ግለሰቦች የህይወት ልምድና ተሞክሮ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡

👉30,480 የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የህክምና ድጋፍና አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
👉ከደም ለጋሽ ወጣት በጎ ፈቃደኞች 33,352 ዩኒት ደም ይሰበሰባል፡፡
👉2,500 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ በሆስፒታሎች ህሙማንን የመንከባከብ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
👉1965 በጎ ፈቃደኞችን አገልግሎት በሚበዛባቸው የመንግስት ተቋማት ይሰማራሉ፡፡
👉60,000 በጎ ፈቃደኞች በአደባባይ የሚከናወኑ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ ያስተባብራሉ፡፡
👉5000 ወጣቶች በማህበራዊ ሚድያው በጎ ተፅዕኖ እንዲፈጥሩ ይደረጋል፡፡
👉500 የአደጋ ተከላካይ በጎ ፈቃደኞች ወደ አገልግሎት ይገባሉ፡፡
👉1729 በጎ ፈቃደኞችን በተመረጡ ክልሎች የከተማችንን የበጎ ፈቃድ ተሞክሮ እንዲያጋሩ ይደረጋል፡፡

"በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

25 Oct, 16:30

118

በአዲስ አበባ ባለፈው ክረምት 5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የሚገመት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሰጥቷል።

በመዲናችን አዲስ አበባ በ2016 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ 5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት ተሰጥቷል።

የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩ ከግንቦት 1/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ለተከታታይ 5 ወራት “በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!” በሚል መሪ ቃል በ15 ፕሮግራሞች እና በ18 ንዑሳን ተግባራት ሲካሔድ ቆይቷል፡፡

በድግግሞሽ 3 ሚሊዮን በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉ ሲሆን 764 ሺህ 256 ዜጎች በቀጥታ ተጠቃሚ ሆነውበታል፡፡

በዚኽ መርሀ ግብር 2,574 የአቅመ ደካሞች ፣ የሀገር ባለውለታዎች እና አረጋውያን ቤቶች ተገንብተዋል ፤ 12 ሺህ 870 ቤተሰቦች በቀጥታ የቤት ግንባታና እድሳት አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል።

469,176 የኅብረተሰብ ክፍሎች በበዓላትና በተለያዩ ወቅቶች ማዕድ ተጋርተዋል ፤ 89 ሺህ ከፍለው መታከም የማይችሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የህክምና ድጋፍ አግኝተዋል።

በደም እጥረት ምክንያት የሚፈጠርን ሞት ለመቀነስ ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሽ ወጣቶች 32 ሺህ 648 ዩኒት ደም ተሰብስቧል፡፡

94 ሺህ ተማሪዎች የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርትና አጫጭር የክህሎት ስልጠና ያገኙ ሲሆን 6 ሺህ 509 የመንገድ ደህንነት ትራፊኮች የትራፊክ መጨናነቅ በሚበዛባቸው አደባባዮችና መንገዶች ላይ እንቅስቃሴውን በማሳለጥ ፣ በመንገድ አጠቃቀምና በትራፊክ አደጋ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር እንዲኹም በእግረኛ መንገዶች አቅመ ደካሞችን በማሻገር ተሳትፈዋል።

ከ2 ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኞች በአረንጓዴ አሻራ ተግባር እንዲኹም 6 ሺህ 35 በጎ ፈቃደኞች አገልግሎት በሚበዛባቸው የመንግስት ተቋማት የባለጉዳይ እንግልት በመቀነስ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡

የማኅበረሰባችን እርስ በርስ የመረዳዳት እሴት መጠናከር ፤ በጎ ፈቃደኞች ከማኅረሰባቸው መስጠትን ፣ ልግስናን ፣ መደጋገፍን ፣ ፍቅርንና መልካም እሴቶችን መቅሰም ፤ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከፍ ማለት እና ከተማችን ለኑሮ ምቹና ተምሳሌት እንድትሆን ማስቻል በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች ናቸው።

ለተመዘገበው ሁሉ አቀፍ ውጤት የከተማው በየደረጃው ያለ አመራር ፣ የበጎ ፈቃደኞች ፣ የሚዲያ አካላትና የባለድርሻ ተቋማት ትብብር የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። በዚኽም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ልባዊ ምስጋናውን በአክብሮት ይገልፃል።

"በጎ ፈቃደኝነት ፤ ለማኅበረሰብ ለውጥ!"

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

25 Oct, 09:12

129

አንድ ሚሊዮን በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉበትና ከ700 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚሆኑበት የበጋ በጎ ፈቃድ ፕሮግራም ይፋ ተደረገ።

በአዲስ አበባ ከተማ አንድ ሚሊዮን በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉበትና 784 ሺህ 844 የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የበጋ በጎ ፈቃድ ፕሮግራም ዛሬ ይፋ ተደርጓል።

"በጎ ፈቃደኝነት ፤ ለማኅበረሰብ ለውጥ!" በሚል መሪ ቃል ይፋ የሆነው የ2017 ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ ፕሮግራም ከጥቅምት ጀምሮ እስከ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ድረስ የስምንት ወራት የቆይታ ጊዜ ይኖረዋል።

የበጋው የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም 12 ዐበይት መርሃ ግብሮችንና 13 ንዑሳን ተግባራትን አካቷል። በእነዚህ መርሀ ግብሮች 6.5 ቢሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት ለመስጠት እቅድ ተይዟል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው ለበጎ ፈቃደኞች የስራ ስምሪት የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ በጎ ፈቃደኝነት መንግስት ተደራሽ ያላደረጋቸውን ተግባራት በመከወን በርካታ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን እየፈታ መሆኑን ገልፀዋል።

ኮሚሽነር ይመር ከበደ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መዲና በሆነችው ከተማችን በ2016 በጀት ዓመት ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠትና የበርካታ ነዋሪዎችን ተስፋ ያለመለመ ፕሮግራም በመተግበር ለሀገራችን ከተሞች በምሳሌነት የሚጠቀስ ስራ ተስርቷል ብለዋል::

በበጋ የበጎ ፈቃድ ስራዎች የተከልናቸውን ችግኞች መንከባከብ ፣ በሠላም ዕሴት ግንባታ ፣ ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን መደገፍና ማገዝ እንደሚገባ ኮሚሽነሩ አክለው ገልጸዋል።

በጎ ፈቃደኞች ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ኅብረተሰባቸውን በቅንነት እንዲያገለግሉ የስራ አቅጣጫ የሰጡት ኮሚሽነሩ በበጋው የተያዘው ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ደረጄ ካሳ በበኩላቸው ለዘመናት የተከማመሩ ችግሮችን እየቀረፈች ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል መሆን በጀመረችው አዲስ አበባ ከተማ ማኅበራዊ ፍትህን ለማንገስ የተሰሩ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ፍሬ ማፍራታቸውን ገልጸው በበጋ የበጎ ፈቃድ ስራዎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህልን ከፍ የሚያደርጉ ስራዎችን ለመተግበር ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

በ2016 የክረምት በጎ ፈቃድ 5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን ከሦስት ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኞች በድግግሞሽ ተሳትፈውበታል።

"በጎ ፈቃደኝነት ፤ ለማኅበረሰብ ለውጥ!"