Neueste Beiträge von የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ (@communitypvc) auf Telegram

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ Telegram-Beiträge

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
2,020 Abonnenten
1,640 Fotos
34 Videos
Zuletzt aktualisiert 10.03.2025 03:06

Ähnliche Kanäle

Free Airdrop
16,164 Abonnenten
ETV AFAAN OROMOO
2,130 Abonnenten

Der neueste Inhalt, der von የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ auf Telegram geteilt wurde.

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

06 Jan, 17:09

295

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ “ፀሐይ ለማንም ሳታዳላና ሳትዘገይ ለሁሉም እኩል ብርሐኗን እንደምትሰጥ” ሁሉ ክርስቶስም የሰውን ልጆች በዘርና በቀለም ሳይነጣጥል፣ በእኩልነት ወዶና ፈቅዶ፣ ከገባበት ፈተናና መከራ ሊያወጣው የተወለደበት፣ የርህራሄ፣ የፍቅርና የመተሳሰብ በዓል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

የልደት በዓል አምላክ ከዙፋኑ ዝቅ ብሎ በከብቶች በረት ተወልዶ፣ የሰውን ልጅ እንዳገለገለ ሁሉ እኛም ከባለፀግነታችን፣ ከስልጣናችንና ከክብራችን አንድ ደረጃ ዝቅ ብለን በኑሮ ጫና ውስጥ ከሚገኙ ወገኖቻችን ጋር ደስታና ፍቅር የምንጋራበት ፣ የአብሮነት ስጦታ የምናበረክትበት ቀን ነው፡፡ በዚህ ቀን ጎረቤቶቻችን በማጣታቸው ምክንያት አዝነውና ተክዘው እንዳይውሉ የልግስና እጃችንን የምንዘረጋበት፣ በጎነታችን የሚገለጥበት ዕለት መሆን አለበት፡፡

የከተማችን አስተዳደር ነባርና ቀደምት እሴታችን ሆኖ የቆየው ለሰው ልጅ በጎ የማድረግ ባህል ይበልጥ እንዲጎላ በተቋም ደረጃ እንዲመራ በማድረግ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን እያቃለለ ይገኛል፡፡ በሚሰጡ ባለፀጎች አማካኝነት የበርካታ ዜጎቻችን ህይወት ተለውጧል፡፡ ከተጎሳቆለ አኗኗር የተላቀቁ የከተማችን ነዋሪዎች ቁጥር ጨምሯል፡፡ የበጎነት ኢኮኖሚያዊ አበርክቶው ከማደጉ በተጨማሪ በሚሰጡና በሚቀበሉ ሰዎች መካከል የልብ ለልብ ግንኙነትን (ማህበራዊ መስተጋብርን) አንድ ደረጃ ከፍ እንዲል አድርጓል፡፡

ይህ የበጎነት ተግባር በገና በዓልም እንዲጠናከር በጎ ፈቃደኞች የተለመደ የልግስና እጃችሁን እንዳታጥፉ፣ የከተማችን ነዋሪዎች እርስ በርስ የመተሳሰብ ልምዳችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እየጠየኩ መልካም የልደት በዓል እንዲሆን እመኛለሁ።

አቶ ይመር ከበደ - የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

06 Jan, 07:54

279

ከተማ አስተዳደሩ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ400 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የኑሮ ጫና ላለባቸው ነዋሪዎች ማዕድ አጋራ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ400 ሺህ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ አረጋውያን ፣ አቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞች 1.6 ቢሊዮን ብር የሚገመት ማዕድ አጋርቷል።

በማዕከል ደረጃ በተዘጋጀ የማዕድ ማጋራት መድረክ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ማዕድ ስናጋራ የኑሮ ጫና ያለባቸው ዜጎቻችን በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ማድረግ ብቻ ሳይሆን እርስ በርስ መረዳዳት ፣ ያለንን መካፈልና የአብሮነት ባህላችን ከከተማችን ዕድገት ጋር አብሮ እንዲዳብር ለማድረግ ነው ብለዋል።

የህዝባችን የኑሮ ጫና ተቃልሎ ማዬት እንፈልጋለን ያሉት ከንቲባ አዳነች ለዚህ የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር ሀብታቸውን በማካፈል ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ በጎ ፈቃደኛ ባለሀብቶች ምስጋና አቅርበው መጭው የገና በበዓል ያማረ፣ የደመቀና ፍቅር የሚዳብርበት እንዲሆን ተመኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ በዘላቂነት ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው
በዛሬው ዕለት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከማዕከል እስከ ብሎክ ድረስ 400 ሺህ ለሚሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች 1.6 ቢሊዮን ብር የሚገመት ማዕድ መጋራቱን ተናግረዋል።

ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እየፈቱ የሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ባለሀብቶች የበጎነት ስራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል።

"በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

24 Dec, 17:54

301

ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ አስጀምረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሁለት የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ የስራና ክህሎት ቢሮ በዚሁ ክፍለ ከተማ በኢንተርፕራይዞች ተሳትፎ የአቅመ ደካሞችን የቤት ግንባታ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀምሯል።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣንም በክፍለ ከተማው በበጋ በጎ ፈቃድ አግልግሎት የሚከናወኑ መኖሪያ ቤቶችን እድሳትና ግንባታ ያስጀመረ ሲሆን አገልግሎቱ ጥራቱን ጠብቆ ባጠረ ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ የተሟላ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ተመላክቷል።

"በጎ ፈቃደኝነት ፤ ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

24 Dec, 16:10

153

ኅብረተሰቡን ያሳተፉ የልማት ፣ የሠላምና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል።

ኮሚሽኑ በተያዘው በጀት ዓመት ኅብረተሰቡ በባለቤትነት የሚሳተፍባቸው የአካባቢ ልማት ፣ የሠላምና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን ቀርፆ ወደ ስራ የገባ ሲሆን የኮሚሽኑ ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች በሁሉም ክፍለ ከተሞች በኅብረተሰብ ተሳትፎ እንዲሁም በበጎ ፈቃድ ስራዎች ዙሪያ ድጋፍና ክትትል እያካሄዱ ነው።

የአካባቢ ልማቶች፣ የአካባቢ ሠላም ተግባራትና መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በርካታ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በኅብረተሰቡና በበጎ ፈቃደኞች ተሳትፎ ተጠናክረው ቀጥለዋል።

ለአካባቢ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የፋይናንስ አሰራሮችን የጠበቀ በቂ ሀብት መሰብሰብ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በልዩ ትኩረት እንዲከናወን አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ተብሏል።

"ሁሉ አቀፍ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!"

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

24 Dec, 14:22

163

በመዲናዋ ባለፉት አምስት ወራት ከ5 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የበጎ ፍቃድ ሥራዎች ተከናውነዋል- ኮሚሽኑ

ባለፉት አምስት ወራት ከ5 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የበጎ ፍቃድ ሥራዎች መከናወናቸውን የአዲስ አበባ የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ገለጸ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ይመር ከበደ እንደተናገሩት በ2017 በጀት ዓመት በከተማዋ ከክረምት በጎ ፍቃድ ባለፈ የበጋ በጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

'በጎነት በሆስፒታል' በሚል ነጻ የህክምና አገልግሎትን ጨምሮ ደም ልገሳ፣ የአቅመ ደካሞች ቤት ዕድሳት፣ ማዕድ ማጋራትና ሌሎችም ከ13 በላይ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

ባለፉት አምስት ወራት ከ5 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የበጎ ፍቃድ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

የቤት ዕድሳትና ግንባታ ስራዎች ትልቁን ድርሻ እንደሚይዙ ገልጸው፤ በበጀት ዓመቱ ከ2 ሺህ 280 በላይ ትላልቅ የቤት ግንባታ ሥራዎች በተለያዩ በጎ ፍቃደኛ ባለሃብቶች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ሁሉም ዜጋ በጉልበቱ፣ በዕውቀቱና በገንዘቡ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በመስጠት ለተሻለ አገርና ትውልድ ግንባታ የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

#Ethiopia
#voluntarism
#Humanityfirst

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

08 Dec, 12:13

348

በጎ ፈቃደኝነት ማኅበረሰቦች በሚፈልጉት ዕድገትና ለውጥ ውስጥ እንዲሳተፉ የሚያስችል ፣ ለጋራ ዕድገት በትብብር የመሰለፍ የስልጡን ዜጎች መገለጫ መሆኑ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ዓለም አቀፍ የበጎ ፈቃደኞችን ቀን በፓናል ውይይት አክብሯል።

በፓናል ውይይቱ ላይ የሜሪጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ፣ የጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃና ማገገሚያ ማዕከል መስራችና ስራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን መለስ አየለ ፣ የጉዞ አድዋ መስራችና የሕይወት ዘመን በጎ ፈቃደኛ መሀመድ ካሳ እንዲሁም የሰርቭ ግሎባል በጎ አድራጎት ድርጅት ካንትሪ ዳይሬክተር ታሪኩ ነጋሽ ለተሳታፊዎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልምዳቸውን አካፍለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ በጎ ፈቃደኞች በቁርጠኝነት በሰጧቸው ነፃ አገልግሎቶች መንግስት ተደራሽ ባላደረጋቸው መስኮች በመሳተፍ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን የተናገሩት የበጎ ፈቃድ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ደረጀ ካሳ ለዚህ ስኬት አስተዋፅዖ ያበረከቱ በጎ ፈቃደኞችን አመስግነዋል፡፡

ባለፉት የለውጥ አመታት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ያቃለሉ ሰው ተኮር ስራዎች መከናወናቸውን ምክትል ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

ኮሚሽኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተቋማዊ ሆኖ እንዲቀጥልና የኅብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲጎለብት የተለያዩ የአሰራር ስልቶችን ቀይሶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ ገልጸዋል።

በጎ ፈቃደኞች በከተማዋ ዘርፈ ብዙ ለውጦች ውስጥ እያደረጉ ያለውን ጉልህ አስተዋፅዖና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ያቀረቡት ኮሚሽነሩ ከተቋማትና በጎ ፈቃደኞች ጋር በትብብር የበጎነት ባህል ይበልጥ እንዲዳብር እንሰራለን ብለዋል።

በጎ ፈቃደኝነት ማኅበረሰቦች በሚፈልጉት ዕድገት ውስጥ እንዲሳተፉ የሚያስችል ፣ ለጋራ ለውጥ በራስ ተነሳሽነትና በነፃ የመተባበር አገልግሎት በመሆኑ ሁሉም በያለበት መልካም በማድረግ እንዲሳተፍ የመድረኩ ታዳሚዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዓለም አቀፍ የበጎ ፈቃደኞች ቀን የበጎ ፈቃደኞችን አስደናቂ ስኬቶች እውቅና መስጠት ፣ ማክበርና በጎ ፈቃደኝነት በማኅብረሰብ ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ የሚያሳድረውን አዎንታዊ ተፅእኖ ማንፀባረቅ ዓላማ ያደረገና በየዓመቱ የሚከበር በዓል ነው።

#በበጎነት_ስላገለገሉን_እናመሰግናለን፡፡
#InternationalVolunteersDay
#VolunteerRecognition
#VolunteerImpact
#CommunityService
#MakingADifference
#ThankYouVolunteers
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

06 Dec, 16:04

258

አለም አቀፍ የበጎ ፈቃደኞች ቀን

ዓለም አቀፍ የበጎ ፈቃደኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ በፈረንጆች አቆጣጠር ታህሳስ 5 ቀን ማለትም በነገው ዕለት ይከበራል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በ1985 እንዲከበር የተወሰነው ይህ ቀን በዓለም ዙሪያ የበጎ ፈቃደኞች አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው እ.ኤ.አ. በ1986 ሲሆን ቀኑ በጎ ፈቃደኝነት ዘላቂ የልማት ግቦችን ከማሳካት አንፃር ያለውን ጠቀሜታ ለማሳየትም እንደ አጋጣሚ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

ዓለም አቀፍ የበጎ ፈቃደኞች ቀን የበጎ ፈቃደኞችን አስተዋፅዖ የሚያከብርና እውቅና የሚሰጥ ዓለም አቀፍ በዓል እንደመሆኑ የበጎ ፈቃደኞችን በዋጋ የማይተመን አገልግሎት የሚያከብር ዓመታዊ ዝግጅት ነው። ብዙ ሰዎች በበጎ ፈቃደኝነት ተግባራት እንዲሳተፉ ለማነሳሳትና ለማስተዋወቅ ያለመ የበጎ ፈቃደኞች ልዩ ቀን ተደርጎም ይወሰዳል።

ጊዜያቸውን ፣ ጉልበታቸውን ፣ ገንዘባቸውንና ክህሎታቸውን የሰጡ ግለሰቦች ለማኅበረሰባቸው ፣ ለሀገራቸውና ለዓለም አዎንታዊ ለውጦችን ለማምጣት የሚያደርጉትን ነፃ የሆነ ጥረት ለማድነቅ እንደ ዕድል ሆኖ ያገለግላል። ይህ ቀን የበጎ ፈቃደኞችን አስደናቂ ስኬቶች እውቅና ለመስጠት ፣ ለማክበርና በጎ ፈቃደኝነት በማኅብረሰብ ላይ የሚያሳድረውን አዎንታዊ ተፅእኖ ለማንፀባረቅ ዕድል ይሰጣል።

በዓለም ዙሪያ ያሉ በጎ ፈቃደኞች በቁርጠኝነት በሰጧቸው ግልጋሎቶች ዘላቂ የልማት ግቦችን በማሳካት ለውጦችን አምጥተዋል፡፡ የሚያጋጥሙ ፈታኝ ሁኔታዎች በተለይም የአየር ንብረት ለውጥ ፣ ግጭቶች እና ማኅበራዊ ኢ-ፍትሐዊነት ከአቅም በላይ በሚሆኑበት ወቅት በጎ ፈቃደኝነት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አስፈላጊ ነው። በእነዚህ የፈተና ጊዜያት በየትኛውም የዓለም ክፍል ያሉ በጎ ፈቃደኞች ምላሽ ለመስጠት ግንባር ቀደም ወታደሮች ናቸው። በድፍረት፣ በትጋትና በፈቃደኝነት ተግዳሮቶችን ይጋፈጣሉ።

በጎ ፈቃደኞች በማኅበረሰባቸው ውስጥ የአገልጋነት ባህልን ይፈጥራሉ። በትውልዶች መካከል ያለውን ልዩነት በማጥበብ ዘላቂ ልማትና ሠላም እንዲሰፍን ይሰራሉ።
በጎ ፈቃደኝነት በትውልዶች መካከል የሚወራረስ ዑደት ነው። ሰዎችን የችግሮቻቸው የመፍትሔ አካል የማድረግ ቁርጠኝነትም ነው። በጎ ፈቃደኝነት ማኅበረሰቦች በሚፈልጉት ዕድገትና ለውጥ ውስጥ እንዲሳተፉ የሚያስችል ፣ ለጋራ ዕድገት በትብብር የመሰለፍ የስልጡን ዜጎች መገለጫ ነው።

በበጎ ፈቃደኝነት መሳተፍ በማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍና የራስን ጥረት ለመገንዘብ እንዲሁም ለመደገፍ ዓይነተኛ መንገድ ነው። በበጎነት ለመሳተፍ ወይም በጎነት ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ የሚከተሉትን እናድርግ፡-

• ጊዜዎን በፈቃደኝነት ይስጡ፡- ከፍላጎቶችዎ እና ችሎታዎችዎ ጋር ለሚስማማ ዓላማ ወይም ድርጅት በፈቃደኝነት መስራት ያስቡበት። የእርስዎ አስተዋፅዖ ምንም ያህል ትንሽ ቢሆን ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል።

• በጎ ፈቃደኞችን ያመስግኑ፡- በግልም ሆነ በማህበረሰብ ውስጥ ለምናውቃቸው በጎ ፈቃደኞች ምስጋናችን ለመግለጽ ጊዜ አንውሰድ። በቀላል "አመሰግናለሁ" ማለት ለጥረታቸው እውቅና በመስጠት የበለጠ እንዲያገለግሉ ተነሳሽነት ይፈጥርላቸዋል፡፡

• በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዝግጅቶች ላይ ይገኙ፡- ብዙ የህብረተሰብ ክፍሎች በአለም አቀፍ የበጎ ፈቃደኞች ቀን የበጎ ፍቃድ ስራዎቻቸውን ለማሳየት የተለያዩ መርሀ ግብሮችን ያዘጋጃሉ። ድጋፍዎን ለማሳየት በእነዚህ ዝግጅቶች ላይ ይሳተፉ።

• ለበጎ ፈቃደኛ ድርጅቶች ይለግሱ፡- ለበጎ ፈቃደኛ ድርጅቶች የሚደረጉ ማንኛውም ዓይነት ድጋፎች ፕሮግራሞቻቸውን እና ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ ያግዛሉ። መጠነኛ ልገሳ እንኳን አዎንታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል።

• የበጎ ፈቃደኛ ታሪኮችን ያካፍሉ፡- ሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን እንዲቀላቀሉ ስለሚያበረታታ በማህበረሰብዎ ውስጥ ለውጥ የሚያደርጉ የበጎ ፈቃደኞች አነቃቂ ታሪኮችን ለማጋራት ማህበራዊ ሚዲያ እና ሌሎች መድረኮችን ይጠቀሙ።

#በበጎነት_ስላገለገሉን_እናመሰግናለን፡፡

#InternationalVolunteersDay
#VolunteerRecognition
#VolunteerImpact
#CommunityService
#MakingADifference
#ThankYouVolunteers
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

01 Nov, 15:17

526

ህዝብ ያመነበትና ተሳትፎውን ያረጋገጠ የአካባቢ ልማት ዘላቂነት እንደሚኖረው ተገለፀ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የሚያከናውናቸው የአካባቢ ልማት ስራዎች በሕዝብ ተሳትፎና እምነት የሚተገበሩ መሆናቸውን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወይዘሮ ፀሐይ ኪባሞ ገልፀዋል::

ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት በኅብረተሰብ ተሳትፎና ሀብት አሰባሰብ ዙሪያ ያተኮረ የፓናል ውይይት መድረክ አካሂዷል። በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ የብሎክ ካውንስል መሪዎች ፣ የወረዳና የክፍለ ከተማ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ሕዝብ የለያቸው የልማት ፍላጎቶች በነዋሪው የገንዘብ ፣ የዓይነትና የእውቀት አስተዋፅዖ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ በሚመድበው የድጎማ በጀት ይከናወናሉ።

ከህዝቡ የሚሰበሰብ ማንኛውም ሀብት በህጋዊ ደረሰኝ ብቻ እንዲሆን ማድረግ የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነትን ለማረጋገጥና የብልሹ አሰራር ተጋላጭነትን ለመቀነስ እንደሚያግዝ ምክትል ኮሚሽነሯ አብራርተዋል። ወቅቱን የጠበቀ ኦዲት በማድረግ ግልፅነትን መፍጠር የኅብረተሰቡን ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ ለማሳደግ ጥቅም እንዳለው ነው ወ/ሮ ፀሐይ የተናገሩት።

በበጀት ዓመቱ የተያዙ የልማት ስራዎችን በወቅቱ ለማጠናቀቅ ከወዲሁ ሀብት በበቂ ሁኔታ ማሰባሰብ እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ በቂ የሀብት መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማሰራጨትና ክትትሉን በማጠናከር ድጋፍ እያደረገ መሆኑን በመጠቆም ለልማት ስራው ውጤታማነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

"ሁሉ አቀፍ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!"
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

31 Oct, 17:15

253

በስኬታማ የሀብት አጠቃቀም ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመያዝ ለተቋማዊ ውጤት መረባረብ ይገባል።

ኮሚሽኑ በሀብት አጠቃቀምና በኦዲት ዙሪያ ለተቋሙ ባለሙያዎችና አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት ኮሚሽነር ይመር ከበደ አንድ ተቋም ለተደራጀበት ዓላማ አሰራሮችንና መመሪያዎችን ለማስጠበቅ የኦዲት ስራ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው የኮሚሽኑ አሰራሮች እንዲጠበቁ በቂ ግንዛቤ በመያዝ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ሀብት ከብክነት በፀዳ መልኩ በትክክል ስራ ላይ መዋሉን ማረጋገጥ ለተቋማዊ ለውጥ ወሳኝ እንደሆነ ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት።
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

31 Oct, 10:55

202

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ

- ስለሰላምና ደህንነት:- ከማንም በላይ ሰላም እንፈልጋለን፡፡ ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን፤ አንፈልገውም፡፡ ከኃይል አማራጭ ይልቅ የሰላም አማራጭ ውጤቱ ከፍተኛ ነው፡፡ መንግስት ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ ቅድሚያ ሰጥቶ ሰርቷል፡፡ አሁንም ያለን አቋም የትኛውም አይነት አለመግባባት በሰላም እንዲፈታ ነው፡፡ ነገር ግን የትኛውም አካል በኃይል እና ጥላቻ መጠፋፋትን እንጂ ዓላማውን ማሳካት አይችልም፡፡ ሰከን ብሎ ማሳብ ይገባል፡፡ ሃሳብ አልባ ትግል ፍሬ የለውም፡፡

- ስለአማራ ክልል አሁናዊ ሁኔታ:- በአማራ ክልል ላይ ከየትኛውም መንግስት በላይ አሁን ያለው መንግስት በርካታ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ነው፡፡ በክልሉ ታላላቅ የመንገድ፣ የኢንዱስትሪ የቱሪዝም ልማቶች እየተከናወኑ ነው፡፡ በዚህም ክልሉን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡ የፋሲል ቤተ-መንግስት እየታደሰ ነው፤ በዋና ዋና ከተሞች የኮሪደር ልማት እየተከናወነ ነው፡፡ የመገጭ ግድብን 7 ቢሊዩን ብር መድበን ከበርካታ ዓመታት የግንባታ መቋረጥ በኋላ ቀን ከሌት እየገነባን ነው፡፡ ነገር ግን በክልሉ ልማት እንዳይከናወን ለማደናቀፍ የሚጥሩ ኃይሎች አሉ፡፡ ይህን ተባብረን ማስቆም አለብን፡፡ የአማራ ህዝብ ማን እንደሚሰራለትና ማን እንደሚያወራለት ጠንቅቆ የሚያውቅ ጨዋ ህዝብ ነው፡፡ መንግስት ክልሉን የማልማት ስራውን አሁንም አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

- ስለገዥ ትርክት:- ህገመንግስታዊነት-የህግ መንግስት መርሆችና ዴሞክራሲን ያከበረ የጋራ ትርክት መገንባት ፣ ህብረብሔራዊነት - ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔር፣ ብሔረሰብና ህዘቦች ሀገር መሆኗን መቀበል ያስፈልጋል ፣ ብልጽግናን በየደረጃው ማረጋገጥ - በሁለም አግባብ በየደረጃው ልማትና ብልጽግናን በማረጋገጥ ድህነትን ለመድፈቅ በጋራ መስራት ይገባል ፣ ማረምና ማስቀጠል-
ትናንት የነበሩ ድክመቶችን ማረም፤ ያሉ ጥንካሬና ወረቶችን ደግሞ ማስቀጠል ይገባል ፣ ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር -የጋራ ህልም በመፈጠር የበለጸገችና ያደገች ኢትዮጵያን ለማየት በጋራ መሰለፍ ይገባል፡፡ ከፓርቲ ባለፈ ትውልድን የሚሻገር እሳቤ መፍጠር ይገባል፡፡

- ስለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን:- ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የተሻለ ስኬት እንዲያስመዘግበ የምክር ቤቱ አባላት ጠንካራ ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ ለታሃድሶ ኮሚሽንን እና ለሽግግር ፍትህም መሰል ድጋፍ መደረግ አለበት፡፡ ከዚህ ቀደም ከነበሩ ኮሚሽኖች ትምህርት በመውሰድ አሁን ያሉ እድሎችን መጠቀም ይገባል፡፡ ከዚህ አኳያ መንግስት እንደ አስፈጻሚ አካል የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

-ስለኮሪደር ልማት :- ኮሪደር ልማት ማለት ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት ማለት ነው፡፡ ከከተሜነት እድገት ጋር የተሳሳረ ልማት ነው፡፡ በኮሪደር ልማት ሰፋፊ መንገድ ከመስራት ባለፈ ታዳጊዎች እግር ኳስ የሚጫወቱባቸውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የእግረኛ መንገዶች ተሰርተዋል፡፡ ይህም ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሃዊ ልማት ለዜጎቻችን ያቀረብንበት ነው፡፡ አሁን ላይ በተለያዩ ከተሞች ከምንሰራው የኮሪደር ልማት ባሻገር፤ የገጠር ኮሪደር ልማት ጀምረናል፡፡ ይህም ኢትዮጵያዊያን የተሻለ ኑሮ ይገባቸዋል በሚል የተጀመረ ነው፡፡ የተሟላ ብልጽግናን የምናረጋግጠውም በዚሁ መንገድ ነው፡፡

- ስለዲፕሎማሲ:- የኢትዮጵያ አቋም ከሁሉም ጋር በትብብርና ሰጥቶ በመቀበል መርህ መኖር ነው፡፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የኃይል ማዕከል ናት፤ ከራሷ ባለፈ ለአፍሪካ ልማት ቁርጠኛ ናት፡፡ ከየትኛውም ጎራ ጋር ሳንሰለፍ ከሁሉም ጋር በሰጥቶ መቀበል መርህ ለብሔራዊ ጥቅማችን እንሰራለን፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህን በመገንዘብ ሀገርን አስቀድሞ መስራት አለበት፡፡ በውስጥ የሚኖረን አንድነትና ሰላም ለዲፕሎማሲያዊ ጥንካሬያችን ከፍተኛ ሚና አለው፡፡

- ስለባህር በር ጥያቄ: - ኢትዮጵያ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በቀይ ባህር ላይ የባህር በር ያስፈልጋታል፡፡ በዚህ ጉዳይ ወደ ኋላ የማይል ይፋዊ አቋም አለን፡፡ ነገር ግን ይህን ለማሳካት ጦርነትም ሆነ የኃይል አማራጭ አንፈልግም፡፡ ፍላጎታችንን ማሳካት የምንሻው በሰላማዊ አማራጭ ነው፡፡ ይህ ምክንያታዊና ፍትሃዊ ጥያቄ ነው፤ እኛ ባናሳካው ልጆቻችን ያሳኩታል፡፡ ኢትዮጵያ የትኛውንም ሀገር ላይ ወረራም ሆነ ጥቃት አትፈጽምም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያን ለመንካት የሚሞክሩ ካሉ አሳፍረን እንመልሳለን፡፡ ይህን ማድረግ የሚያስችል በቂ አቅም አለን፡፡

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia