Bole subcity wereda 12 land dvt.&mgt. Office @bw12l Channel on Telegram

Bole subcity wereda 12 land dvt.&mgt. Office

@bw12l


bw12l (English)

Are you interested in staying updated on the latest developments and management projects in Bole Subcity Wereda 12? Look no further than the 'bw12l' Telegram channel! This channel is dedicated to providing information on land development, management activities, and other important updates in Wereda 12. Whether you are a resident, investor, or simply curious about urban development, 'bw12l' has you covered.nnWho is it? 'bw12l' is a Telegram channel created for individuals who want to stay informed about the progress and initiatives taking place in Bole Subcity Wereda 12. It is managed by the local land development and management office, ensuring that the information shared is accurate and reliable.nnWhat is it? 'bw12l' is your go-to source for news, updates, and announcements related to land development and management in Wereda 12. By joining this channel, you will have access to official reports, project updates, and important notices regarding urban planning and infrastructure development.nnStay ahead of the curve and join 'bw12l' today to be a part of the conversation surrounding the future of Bole Subcity Wereda 12!

Bole subcity wereda 12 land dvt.&mgt. Office

04 Apr, 21:38


በአዲስ አበባ ከተማ #ለአፓርትመንት_ቤቶች እና #ለጋራ_መኖሪያ_ቤቶች ወይም ኮንዶሚኒየም ቤቶች አማካኝ የሽያጭ ዋጋ ተመን በ34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ለሁሉም ክ/ከተሞች የአፈፃፀም መመሪያ መጻፉን ቢሮ ይገልፃል

በከተማዋ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተብሎ በገዥ እና ሻጭ መካከል የሚደረግ ውል ላይ የሚቀርበው ዋጋ እጅግ በተጋነነ መልኩ ዝቅተኛ በመሆኑ እና በባለሙያ የሚወሰድ የቤት ግምት ዋጋ ወቅታዊ ባመሆኑ መንግስት ከቤት ሽያጭ ተገቢውን ገቢ እየሰበሰበ እንዳልነበረ ቢሮው ገልጿል።

ይህንን ችግር ለመፍታት እንዲቻል ካለፈው ዓመት ሰኔ 8 ቀን 2015  ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ወቅታዊ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተግባራዊ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

ይሁን እንጂ በከተማ ደረጃ ተጠንቶ ተግባራዊ የተደረገ የቤት ሽያጭ ዋጋ እና አሰራሩ ላይ ከህብረተሰቡ በርካታ ቅሬታዎች እየቀረቡ በመሆኑ በመሬት ልማትና አስተዳደተር ቢሮ እና የመሬት ይዞታ ምዝገበና መረጃ አጄንሲ በጋራ ጥናት በማድረግ የተለዩ ክፍተቶችና እና የቤት ሽያጭ ግምት ላይ ማሻሻያ ተደርጓል ብሏል።

በተደረገው ማሻሻያ ለአፓርትመንት ቤቶች እና ኮንዶሚኒየም ቤቶች የሽያጭ ዋጋ ተመን አምና በሰኔ ወር ከነበረው 34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።

በተሻሻለው  የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሰረት ከኮንደሚንየም እና አፓርትመንት ውጪ ለሆኑ ግንባታዎች፦

➡️ የግንባታ ነጠላ ዋጋ በጭቃ የተሰራ ቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 15,000 ብር፣
➡️ በብሎኬት የተሰራ የቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 20,000 ብር፣
➡️ የህንጻ ወለላቸው ከG+1 እስከ G+5 25,000 ብር እና፣
➡️ G+6 እና በላይ የሆኑ ቤት ወይም ህንጻ ነጠላ ዋጋ በካሬ 30,000 ተደርጓል፡፡

የቦታው መገኛ ዋጋ ('location value') ለከተማው የቦታ ደረጃ የጸደቀው ወቅታዊ አማካይ የሊዝ ጨረታ ዋጋ እንዲሆን መደረጉም ተገልጿል።

የቤት ስም ንብረት ዝውውር ክፍያ ማለትም አሹራ 4 በመቶ እና የቴምብር ቀረጥ 2 በመቶ ከጠቅላላ የቤቱ ሽያጭ ዋጋ ተሰልቶ ከ ከመጋቢት17 ቀን 2016 ዓ/ም  ጀምሮ እንዲከፈልም ቢሮ አዟል።

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር  ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን #መሻሩንም ቢሮ ጠቅሷል።

በፍርድ ቤት እና በባንክ ሃራጅ ሽያጭ የስም ንብረት ዝውውር የሚጠየቅባቸው ይዞታዎችን በተመለከተ ይዞታ አገልግሎትና መብት ፈጠራ ደንብ ላይ በተቀመጠው አግባብ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።

ይህ ማሻሻያ መምሪያ ከመውጣቱ በፊት የስም ንብረት ዝውውር አገልግሎት ጠይቀው በሂደት ላይ ሆኖ ክፍያ የፈጸሙ ተጋልጋዮች በቀድሞ አሰራር በከፈሉት ክፍያ መሰረት ይስተናገዳሉ ተብሏል።

ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንፃዎች የትመና ስራ የሚሰራላቸው ግንባታው በደረሰበት ወይም አሁን ላይ ባለበት ግንባታ ደረጃ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ያሳወቃል

Bole subcity wereda 12 land dvt.&mgt. Office

03 Apr, 21:08


ከአሁን በኋላ በአዲስ አበባ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና መንገድ በ10 ሜትር ርቀት አንዲሆን ተወሰነ
*********
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ለከተማዋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ጉልህ ሚና ባላቸው ጉዳዮች ላይ በዛሬው ዕለት ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የተሽከርካሪ አስተዳደር ህግ እና ሥርዓት ለማስከበር የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ረቂቅ ደንብን ለአሰራር በሚያመች መልኩ ሀሳብ ተሰጥቶበት ደንቡ ፀድቋል።

የከተማዋን ስታንዳርድ እና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም ፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ለማውጣት በቀረበው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በመወያየት ፤ ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤ ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤ ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት በተጨማሪም የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ማቋቋሚያ ደንብ ማዕከሉን በተለይም ለጎዳና ህይወት ፤ ለፆታዊ ጥቃት ሰለባ እና ለወሲብ ንግድ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች ፣ መጠለያ፣ ማገገሚያ እና የተመሰቃቀለ ህይወታቸውን እንደገና ለማደስ የሚያስችል የሙያ እና ክህሎት ሥልጠናዎች የሚያገኙበትን እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ የሚያግዝ አቅም ያለዉ ማዕከል እንዲሆን ለማስቻል በሚያግዘው ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ካቢኔው ተወያይቶ መፅደቁን ከከተማ አስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Bole subcity wereda 12 land dvt.&mgt. Office

03 Apr, 16:07


በአዲስ አበባ ከተማ በመሬት አገልግሎት ላይ ተጥሎ የነበረው  እግድ መነሳቱ ተገለፀ።

ላለፉት 3 ወራት እግድ ተጥሎበት የነበረው የመሬት አገልግሎት ካለፈው ሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱን ይታወቃል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በተጠናው የመዋቅር ጥናት መሠረት የሰራተኞች ድልድል ተካሂዶ ምደባ እስከሚካሄድ ድረስ በሚል ነበር ከጥር  21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 3 ወራት የመሬት አገልግሎት ታግዶ የቆየው።

የከተማ አስተዳደሩ አጠቃላይ የሰራተኛ ድልድሉ በመጠናቀቁ ከመጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የመሬት አገልግሎት የተጀመረ መሆኑን ቢሮ ያሳዉቃል ።

Bole subcity wereda 12 land dvt.&mgt. Office

18 Mar, 13:31


Channel photo updated

Bole subcity wereda 12 land dvt.&mgt. Office

18 Mar, 13:30


ለደንበኛ፣ ለኢንቴኔት ካፌ ወይም ለክፍለ ከተማዎ ኮፒተር ማእከል ፎርም አይሞሉ፣ የኢንተርኔት ድረ-ገጹን ያሳዩዋቸው እና ይህን የቪዲዮ ሊንክ ሼር ያድርጉላቸው።
Addisland.gov.et ላይ ለአገልግሎት እንዴት ማመልከት እንደሚቻል https://youtu.be/HQy29wi36hA

Addisland.gov.et ላይ እንዴት ማስተካከል ወይም መመለስ እንደሚቻል https://youtu.be/C8qeEzibkDY

Addisland.gov.et ላይ ቀጠሮ እንዴት እንደሚኖር ሊንኩን ይመልከቱ https://youtu.be/HQy29wi36hA

በቴሌብር እንዴት መክፈል ይቻላል https://youtube.com/shorts/mc-gzBGPPK4

Bole subcity wereda 12 land dvt.&mgt. Office

18 Mar, 11:28


https://youtu.be/cJ20ScVOEuA?si=-USI7tm7BiQGDg_j

Bole subcity wereda 12 land dvt.&mgt. Office

18 Mar, 11:28


በአገልግሎት አሰጣጡ የነበሩበትን ጉድለቶች በሚያካክስ መልኩ ለአገልግሎት የተዘጋጀው ተቋም!

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የጀመራቸውን አገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ የማዘመን የሪፎርም ስራዎች ጎብኝተዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በጉብኝታቸው ወቅት እንደተናገሩት ቴክኖሎጂን ለማስጀመር ብርቱ ጥረት ቢጠይቅም አንዴ መሰረቱን ካፀናነው ግልፅና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የህዝባችንን እንግልት ስለሚያስቀር የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እያከናወነው እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ብልሹነቶች ላይ ስርነቀል ለውጥ ለማምጣት በመልካም እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን መታዘባቸውን የጠቀሱት አቶ ሞገስ ብዙ የተለፋበት ቴክኖሎጂው ለህዝባችን ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም የድርሻውን እንደሚወጣ አስገንዝበዋል።

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ አቶ ሲሳይ ጌታቸው ቢሮው የሚሰጣቸውን 27 አገልግሎቶች ተገልጋዩ ከቤቱ ሆኖ የሚገለገልበትን የቴክኖሎጂ አማራጭ ለመፍጠር ባለፉት ስድስት ወራት ብርቱ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመው ከላይ እስከ ታች ያሉ የተቋሙ መዋቅሮችን በቴክኖሎጂው የማስተሳሰር እንዲሁም ሙሉ መረጃዎችን በሀርድ ኮፒ እና በሶፍት ኮፒ የመሰነድ ስራ መከናወኑን ገልፀዋል።

ተገልጋዩ በስሙ በሚከፈትለት የመረጃ ፋይል በቴክኖሎጂ የታገዘ ስታንዳርዱን የጠበቀ አገልግሎት እንደሚያገኝ ያስረዱት የቢሮው ሀላፊ ቢሮው ላከናወነው የቴክኖሎጂ ግንባታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ኢትዮ ቴሌኮም የላቀ ድጋፍ ማድረጋቸውን አውስተዋል፡፡

ከታለመላቸው ስራ ውጭ ለሌላ ግልጋሎት የማይውሉ ብዛትና ጥራት ያላቸውን ዘመናዊ ኮምፒውተሮች ያሟላው ቢሮው በየደረጃው የሚገኝ አመራርና ባለሙያ ስራ ላይ መሆኑን የሚከታተል ሲስተምም በቴክኖሎጂ በመታገዝ መዘርጋቱ ተገልጿል።

የመሬት ካርታ ጭምር ዲጂታል መደረጉ የተጠቆመ ሲሆን በየደረጃው የሚገኙት የቢሮው መዋቅሮች በቴክኖሎጂው በመተሳሰራቸው ትክክለኛ ሪፖርቶችን ለመለዋወጥም ያስችላቸዋል ተብሏል።